የአፍሪካ አካዳሚ أكاديمية أفريقيا
6.19K subscribers
196 photos
40 videos
9 files
114 links
አፍሪካ ኦንላይን መድረክ ነፃ የሸሪዓ ትምህርት ማስተማሪያ

ለበለጠ መረጃ የአካዳሚውን ተቆጣጣሪ ያነጋግሩ: @ethio_africaacademy
Download Telegram
የሐዲሱ አስተምህሮቶች
1. የሰው ልጅ የስራ መዝገቡ በሞት እንደሚቋጭ።
2. ጠቃሚ እውቀትን ተምሮ ያስተማረ ሰው ከዚች አለም በሞት ቢለይም ስራው በቋሚነት ይመዘገባል።
3. ጠቃሚ እውቀት የሚባለው የሰውን ልጅ በዱንያው በአኽራውም የሚጠቅም እውቀት ማለት ነው።
4. የሸሪዓ ትምህርት በጠቃሚ እውቀት ውስጥ እንደ ቀዳሚነት ይጠቀሳል።

ከሁለተኛ ዙር ተማሪዎች ተርታ ለመሰለፍ አሁንም እድሉ አላለፈም።
ለሁለተኛ ዙር ምዝገባው አሁንም ክፍት ነው።
የምዝገባ ድህረገጽ፡https://bit.ly/3Ct4pW1

#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት
#ሁለተኛ_ዙር
▶️በዲፕሎማ የሸሪዓ ትምህርት ፕሮግራም ውስጥ የትምህርት እይታ ገፅ ማስተዋወቂያ:-
1️⃣ኤሌክትሮኒክ መድረክ፦ እሱም ዋና እይታ ገፅ ሲሆን በሱ አማካይነት ተማሪው የሚከተሉትን መጎብኘት ይችላል።
▪️ትምህርቶችን መመልከት ( በምስል፣ በድምፅ እና በpdf)
▪️ፈተናዎችን ማከናወን
▪️ማስታወቂያዎች እና ማስታወሻዎች
▪️የደረጃዎች መዝገብ እና ውጤት
▪️የዲፕሎማ ማጠናቀቂያ ምስክር ወረቀት

➡️የዲፕሎማ ፕሮግራሙን በትክክል ለማጠናቀቅ እና እነዚህ ከላይ የተወሱት ነጥቦች ለማግኘት፤ ግዴት ማንኛውም ተማሪ በመድረኩ ላይ አካውንት ሊኖረው ይገባል። በመድረኩ ላይ አካውንት ካልከፈቱ በስተቀር ተማሪው በዲፕሎማ ፕሮግራሙ ላይ እውቅና የለውም።

➡️ለምዝገባ፣ ወደ አካወንቷ ለመግባት እና አዲስ ሒሳብ ለመክፈት ይህን ድረ ገፅ ይጫኑ http://am.africaacademy.com

2️⃣የቴሌግራም ቻናል፦ እሱም ሁለተኛው የትምህርት እይታ ገፅ ሲሆን ተማሪው የሚከተሉትን መጎብኘት ይችላል።
▪️ቀናው ትምህርቶችን መከታተል
▪️ማስታወቂያዎች እና ማስታወሻዎች

➡️ተማሪው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ፈተናዎችን ማከናወን አይችልም።

3️⃣የሳተላይት ቻናል፦ እሱም ሶስተኛው የትምህርት እይታ ገፅ ሲሆን ተማሪው የሚከተሉትን አገልግሎት ያገኛል፦
▪️በአፍሪካ ቲቪ ላይ በተዘጋጀው የስርጭት መርሃ-ግበር መሰረት ዕለታዊ ትምህርቶችን መከታተል ይችላል።

☑️ከሁለተኛ ዙር ተማሪዎች ተርታ ለመሰለፍ አሁንም እድሉ አላለፈም።
ለሁለተኛ ዙር ምዝገባው አሁንም ክፍት ነው።
▪️የምዝገባ ድህረ ገጽ፡https://bit.ly/3Ct4pW1
▪️የቴክኒክ ድጋፍ ሊንክ፡ https://bit.ly/3p83jLl

#አፍሪካ_አካዳሚ
#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት
#ሁለተኛ_ዙር
🛎ከሁለተኛ ዙር ተማሪዎች ጋር ሁን።
ለሁለተኛ ዙር ምዝገባው አሁንም ክፍት ነው።
የምዝገባ ድህረገጽ፡https://bit.ly/3Ct4pW1
በመግቢያ ምዝገባ (login) ማንኛውም ችግር ካጋጠማችሁ ወይም ትብብር ካስፈለጋችሁ ከታች ባለው ድረገጽ ከቴክኒክ ድጋፍ ጋር ለመገናኘት አትወላወሉ።
የቴክኒክ ድጋፍ ሊንክ፡ https://bit.ly/3p83jLl

#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት
#ሁለተኛ_ዙር
የመጀመሪያ ዙር የዲፕሎማ ፕሮግራም ላይ ወይም በአጫጭር ኮርሶች ከተመዘገብክ፤ በአሁኑ አካውንት ወደ ሁለተኛ ዙር የዲፕሎማ ፕሮግራም መሳተፍ ይችላሉ።
ብቻ በድረገጹ ላይ ተጫነው፡ https://am.africaacademy.com/course/view.php?id=228
ከዛም ተሳተፍ የሚለውን ተጫነው።

የቴክኒክ ድጋፍ ሊንክ፡ https://bit.ly/3p83jLl

#አፍሪካ_አካዳሚ
#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት
#ሁለተኛ_ዙር
ነገ ሀሙስ ከተከበሩት ሼይኽ ኑረላህ ሃሚዲን ጋር በሚኖረን ልዩ መድረክ ተጠባብቁን።
እሱም በአፍሪካ አካዳሚ የፌስቡክ ገፅ ላይ ከቀኑ 7፡30 እንደ ኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በቀጥታ ስርጭት ይለቀቃል።
ለተሳታፊዎች ልዩ ሽልማቶች ተዘጋጅቷል።
http://m.facebook.com/africaacad

ከሁለተኛ ዙር ተማሪዎች ተርታ ለመሰለፍ አሁንም እድሉ አላለፈም።
ለሁለተኛ ዙር ምዝገባው አሁንም ክፍት ነው።
የምዝገባ ድህረገጽ፡https://bit.ly/3Ct4pW1

#አፍሪካ_አካዳሚ
#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት
#ሁለተኛ_ዙር
📩የተከበራችሁ እና የተወደዳችሁ ውድ የአፍሪካ አካዳሚ የሁለተኛ ዙር ተማሪዎች፤ ለረጅም ጊዜ ስትጠብቁት የነበረ እድል ደርሷል።
ዲፕሎማ የሸሪዓ ትምህርት ፕሮግራም የሚጀመረው እሁድ ቀን 17/09/2023 (እ.እ.አ) ነው።🎉🎉

ለትዕግስታችሁ እና ለትብብራችሁ የላቀ ምስጋና እናቀርባለን።

ትምህርቱን ለመጀመር ዝግጁ ናቹ ወይ🤩🎉?

#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት
#ሁለተኛ_ዙር
📬የአፍሪካ አካዳሚ ዲፕሎማ የሸሪዓ ትምህርት አንኳር አንኳር ነጥቦች፡:

1️⃣የመጀመሪያ ነጥብ፡ ኢኽላስ
እሱም እውቀትን በመፈለግ ውሰጥ ልባችንን ለአንድ አላህ ብቻ ማጥራት። ከኢኽላስ ትሩፋቶች መካከል፦ ከስራዎች ሁሉ የበላይ ስራ መሆኑ።

📒ኢማም አህመድ (ረ.ዐ) እንድህ ይላሉ፦ ኒያ የተስተካከለለት እንደሆነ እውቀት ተተኪ የለውም። ምክንያቱም እውቀት ወደ ተግባር ሰለ ሚመራ። እውቀት በምንማርበት ጊዜ ከራሳችን እና ከሰው ልጅ መሃይምነትን ማስወገድ እና ሸሪዓውን ለመጠበቅና እሷን ለመመከት መነየት አለብን።

ሸሪዓን መጠበቅ ስንል፦ አብዛኛው ሰው የሚዘነጋውን የሸሪዓ ክፍል መቀለብ ሲሆን ሸሪዓን መመከት ስንል ደግሞ ለጠላቶቹ ወረራ ምላሽ መስጠት ነው።

የኒያችን መስተካከል የእውቀት ጎዳናን ያገራልናል። 📒ኢብኑ አባስ ረ.ዐ እንዲህ ይላሉ፦ የሰው ልጅ የሚጠበቀው እንደ ኒያው ነው።

የኒያ መስተካከል ከእሳት ያድናል።
📒የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንድህ ይላል፦ እውቀትን ፍለጋ የተጓዘ ሰው አላህ የጀነት ጎዳናን ያገራለታል። እንዲም ብሏል፦ እወቀትን ምሁራንን ለማሳየት፣ አላዋቂዎችን ለመከራከር እና መቀመጫን ለማመራረጥ አትማሩ። እንዲህ ላደረገ ሰው ለሱ እሳት አለ።

2️⃣ሁለተኛ ነጥብ፡ መከተብ (መፃፍ)
እሱም የሚነገርህን እውቀት መፃፍ። ምክንያቱም መከተብ የእውቀት ጎዳን ሲሆን እውቀትንም ይጠብቃል። ከመከተብ እንዳትርቅ። ምክንያቱም እጅን ማንቀሳቀስ የአዕምሮ ማንቀሳቀስ አጭሩ መንገድ ነው።

3️⃣ሶሰተኛ ነጥብ፦ መሸምደድ
እሱም የተማርከውና የከተብከውን እውቀት መሸምደድ።📒የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብሏል፦ ቃለን ሰምቶ የሸመደደና የቀለበና ላደረሰ አላህ ፊቱን ያብራለት።

4️⃣አራተኛ ነጥብ፦ እውቀትን ማረጋገጥ።
በተማርከው መስራት። ምክንያቱም የምንማረው ልንሰራበት ስለሆነ። እውቀት ስራን ይጣራል እሺ ከአለ ደግ አለበለዚያ ይሄዳል። አላህ የእውቀት በር የሚከፍትልህና የሚጨምርልህ በእውቀቱ በምትሰራ መልክ ነው። በእውቀት መስራት የአውቀት መፈለጋ ላይ ያግዛል። በዚህ መልክ እውቀት ለአንተ ተከራካሪ እንጂ በአንተ አይከራከርም።

አላህ ወይ የሚጠቅመንን እውቀት አስተምረን። በአስተማርከን የሚጠቀሙ አድርገን። እውቀትንም ጨምረን።

#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት
#ሁለተኛ_ዙር
በፍለስጢን ላሉ ወንድሞቻችን ለደረሰባቸው ታላቅ መከራ መፅናናትን እየገለፅን፤ አላህ ሙታኖቻቸውን ተቀብሎ ሰማዕታት እንዲያደርጋቸው፣ የቆሰሉትን እንዲፈውሳቸውና እንዲያጸናቸውም እንማፀናለን።

ሙስሊም የአንድ ሙስሊም ወንድም ነውና ለፍለስጢማውያን ወንድሞቻችሁ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉላቸው። እንዲሁም አብዝታችሁ ዱዓ አድርጉላቸው።

#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት
#ሁለተኛ_ዙር
🔰በአላህ ፍቃድ ዲፕሎማ የሸሪዓ ትምህርት የሁለተኛ ዙር ተማሪዎች የመጀመሪያዎቹ ሁለት ኮርስ ትምህርት(የተፍሲር ኮርስ እና የሐዲስ ኮርስ ትምህርት) በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል።

በዚህ ሴሚስተር ውስጥ ሌላ አራት የትምህርት አይነቶችን ይማራሉ። እነሱም፦ የፊቅህ ትምህርት፣ የአቂዳ ትምህርት፣ የነቢዩ ሲራ ትምህርት እና የተርቢያ ትምህርት ናቸው። ስለ ሀይማኖታቸው በመማራቸው እንኳን ደስ አላቸው። አላህ (ሱ.ወ) ለኛም ለነሱም ጠቃሚ እውቀትንና መልካም ስራ እንዲሰጠን እንለምናለን።

#አፍሪካ_አካዳሚ
#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት
🔰በአላህ ፊቃድ የአፍሪካ አካዳሚ ተማሪዎቻችን የዲፕሎማ የሸሪዓ ትምህርት ፕሮግራም የሴሚስተሩ ሶስተኛ ኮርስ የአቂዳ ትምህርት ጀምሯል።

በዚህ ሴሚስተር የአቂዳ ኮርስ ትምህርት ከሚዳስሳቸው ነጥቦች መካከል የሚከተሉት ናቸው፦
- የአቂዳ ምንነት
- የእስላማዊ አቂዳ ምንጮች
- የእስላማዊ አቂዳ መለያዎች
- የአህሉ ሱና ወል ጀማዓ የአቂዳ አቋም
- ከትክክለኛ አቂዳ የማፈንገጥ ምክንያት
- ሶስቱ የአቂዳ አይነቶች( ተውሂድ አል- ሩቡቢያ፣ አል-ኡሉሂያ እና አል-አስማዕ እና አል-ስፋት)።

#አፍሪካ_አካዳሚ
#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት
አለም እያስተናገደች ያለችው ክስተት እና መከራ ቆም ብለን ልናሰላስል እና ትምህርቶችን እንድንጎናፀፍ ይጠራናል። በተለይ እስላማዊ አለም እያጋጠመ ከለው መከራ ውሰጥ የዛሬ የፍልስጥናውያን ክስተት መጥቀስ ይቻላል።

በፍልስጥን ውሰጥ እየተከሰተ ላለው መከራ ምን ትምህርት እንደቀሰማችሁ በታች ባለው ሊንክ በአስተያየት መልኩ አካፍሉን።

ሊንክ:- https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02vnHrq6Bet83DUc3qqtDJT7CqfVoezf6tjFzMTm6brTNJdAcUJAfFgDfWQRoqRr9nl&id=100071838582164&mibextid=qC1gEa

#አፍሪካ_አካዳሚ
#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት
በአላህ ፍቃድ ሆኖ የአፍሪካ አካዳሚ ሁለተኛ ዙር የዲፕሎማ ፕሮግራም ተማሪዎች የመጀመሪያውን ሴሚስተር አራተኛውን ኮርስ (የፊቅህ ኮርስ) በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል።
ይህ ኮርስ በዋንኛነት የዳሰሳቸው ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦
1. ጦሃራና የጦሃራ አይነቶች
- ሐይድ እና ኒፋስ
- ውሃ እና አይነቶቹ
- የዕቃዎች አይነት
- ነጃሳና የነጃሳ አይነቶች
- ተየሙምና ድንጋጌዎቹ
- ትጥበትና ድንጋጌዎቹ
2. ሶላት እና የሶላት ብይን
- አዛን እና ኢቃማ
- የሶላት ማዕዘናት፣ ግዴታዎችና ሱናዎች
- ሶላትን የሚያበላሹ ነገሮች
3. የዘካ ምንነት እና ዘካ ግዴታ የሚሆንባቸው ገንዘቦች
- የዘካ መስፈርቶች
- የወርቅ እና የብር ዘካ
- ዘካ የሚገባቸው ነገሮች እና የመሳሰሉት ነጥቦች በሰፊው ዳሷል።
የአካዳሚው አስተዳደር ለተማሪዎቹ ኮርስ በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ ምክንያት እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን ሊያስተላልፍ ይወዳል።

#አፍሪካ_አካዳሚ
#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ሐደስ (ውዱ የሚያስፈቱ ነገሮች) "

ከፊቅህ ኮርስ የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርቶች
#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት
#አፍሪካ_አካዳሚ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ውዱእ እና ብይኑ

ከፊቅህ ኮርስ የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርቶች
#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት
#አፍሪካ_አካዳሚ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የውዱእ ግዴታዎች

ከፊቅህ ኮርስ የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርቶች
#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት
#አፍሪካ_አካዳሚ
በአላህ ፍቃድ ሆኖ የአፍሪካ አካዳሚ ሁለተኛ ዙር የዲፕሎማ ፕሮግራም ተማሪዎች የመጀመሪያውን ሴሚስተር አምስተኛውን ኮርስ (የተርቢያ ኮርስ) በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል።
ይህ ኮርስ በዋንኛነት የዳሰሳቸው ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦
1. አላህ በባሪያዎች ላይ ያለው መብት
-አላህን (ሱ.ወ) የማላቅ መገለጫዎች
2. ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በህዝባቸው ላይ ያላቸው መብት
- በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ድንበር የማለፍ መገለጫዎች
- የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) መብቶች የመወጣት ጠቀሜታዎች
3. የሶሀቦች (ረ.ዐ) መብት
4. የዑለሞች መብት
- የዑለሞችን መብት አለመጠበቅ የሚያስከትለው ቀውስ
5. የወላጆች መብት
6. ልጆች በወላጆች ላይ ያላቸው መብት
- ልጁ ከመገኘቱ በፊት ያሉት መብቶች
- ልጁ ከተገኘ በኋላ ያሉት መብቶች
7. የባልና ሚስት መብቶች
- ባል በሚስቱ ላይ ያሉት መብቶች
- ሚስት በባል ላይ ያሏት መብቶች
8. የቤተ ዘመድ መብቶች
- ዝምድና መቁረጥ የሚያስከትለው መዘዝ
9. የጎረቤት መብቶች
10. የእንግዳ እና እንግዳ ተቀባይ መብቶች
- የእንግዳ ማክበር መገለጫዎች
11. የአሰሪና ሰራተኛ መብቶች
11. የመንግስትና የዜጎች መብት
12. የቀልብ ስራዎች
- ኢኽላስ
- ተቅዋ
- ተወኩል እና የመሳሰሉት ነጥቦች በሰፊው ዳሷል።
የአካዳሚው አስተዳደር ለተማሪዎቹ ኮርስ በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ ምክንያት እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን ሊያስተላልፍ ይወዳል።


#አፍሪካ_አካዳሚ
#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሶላት መቼ ተደነገገ?

ከፊቅህ ኮርስ የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርቶች
#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት
#አፍሪካ_አካዳሚ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሶላት መስፈርቶች

ከፊቅህ ኮርስ የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርቶች
#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት
#አፍሪካ_አካዳሚ
የአላህ ፍቃድ ሆኖ የአፍሪካ አካዳሚ ሁለተኛ ዙር የዲፕሎማ ፕሮግራም ተማሪዎች ሁለተኛ ሴሚስተር የመጀመሪያውን ኮርስ (የአቂዳ ኮርስ) በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል።

ይህ ኮርስ በዋንኛነት የዳሰሳቸው ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦

1, ተውሒድን የሚያበላሹና የሚያጎድሉ ነገሮች
2, የኩፍር(የክህደት) አይነቶች
- በትልቁ ክህደትና በትንሹ ክህደት መካከል ያሉ ልዩነቶች
3, ሺርክ እና አይነቶቹ
  - የትልቁ ሺርክ አይነቶች
   - የትልቁ ሺርክ መገለጫዎች
   -ወደ ሺርክ የሚያደርሱ መንገዶችን መዝጋት
   - ትንሹ ሺርክና ክፍልፍሎቹ
   - ዘመናዊው መጥፎ ገድ (ተሻኡም)
   -ከፍ ካለው ከአላህ ውጭ በሌላ መማልና መጥፎ ገድ ማየት
4, በኩፍርና ሺርክ መካከል ያለው ልዩነት
5, የቢድዐ መለኪያዎች
6, የማክፈር መለኪያዎች
7, የትንሳኤ ምልክቶች
8, ሶሀቦችና የነብዩ ቤተሰቦች
9, ወልዮችና ከራማቸው
10, ምልጃ

ለሁለተኛ ዙር ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እንወዳለን።አላህ የዕውቀትን ደረጃ እንዲሰጣችሁና እንዲቀበላችሁ ዱዐችን ነው።

#አፍሪካ_አካዳሚ
#ዲፕሎማ_የሸሪዓ_ትምህርት