አፍሪካ አካዳሚ || أكاديمية أفريقيا
8.23K subscribers
298 photos
43 videos
9 files
188 links
አፍሪካ ኦንላይን መድረክ ነፃ የሸሪዓ ትምህርት ማስተማሪያ

ለበለጠ መረጃ የአካዳሚውን ተቆጣጣሪ ያነጋግሩ: @ethio_africaacademy
Download Telegram
ራስህን አዘጋጅ

======

https://vt.tiktok.com/ZSa7c4vxV/
5👍2
"ይቅርታም ያድርጉ፤ ጥፋተኞችንም ይለፉ። አላህ ለእናንተ ሊምር አትወዱምን? አላህም መሓሪ አዛኝ ነው።" (ሱረቱ አል-ኑር፡ 22)


​በሻዕባን ማብቂያ ላይ ሆነን፣ ያንን ናፍቆት የበረታበትን የረመዳን ጨረቃ የምንጠባበቅበት ልዩ ወቅት ላይ እንገኛለን። ረመዳን የጾም ወር ብቻ ሳይሆን፤ የልቦናችንን "ቂምና ጥላቻ" አስወግደን፣ በይቅርታና በመከባበር ድልድይነት የምንሻገርበት ታላቅ ትምህርት ቤትም ጭምር ነው!

ለምን ይቅር እንላለን?

እኛ በአላህ (ሱ.ወ) ፊት ያለን ጥፋትና ጉድለት ሰዎች እኛ ላይ ካደረሱብን በደል ጋር ሲነጻጸር የቅንጣት ያህል ነው።



አምላካችን አላህ እኛን ይቅር እንዲለን በምንፈልገው ልክ፣ እኛም ለሰዎች ልባችንን ክፍት ማድረግ ይኖርብናል።

የዛሬ ​ዱዓችን፡

ያ አላህ! የሙሳን (ዐ.ሰ) ተከታይ ለ40 ዓመት ሲያምፅህ ደብቀህ ተውበትን እንደወፈቅከው፤ እኛንም ነውራችንን ደብቀህ መሀርታህን ለግሰን። ልባችንን አንጽተህ ለረመዳን አድርሰን።
መልካም ጁሙዓ!


አፍሪካ አካዳሚ
🥰149
​"ይህቺ 'Scroll' የምታደርጋት አውራ ጣትህ በቀን ስንት ኪሎ ሜትር እንደምትጓዝ ታውቃለህ?


👇👇👇👇👇👇

https://vt.tiktok.com/ZSaTUHeP9/
👍41
Akkaadaamiin Afrikaa gita hojii lamaa banaa qabu, Hoogganaa Garee Akkaadaamii Afaan Oromootii fi Itti gaafatamaa damee barnootaa Qacaruu waan barbaaduuf, namni fedha hojii qabuu fi ulaagaalee qacarrii kanaaf barbaachisu guutu, wal qabsiiftuu (link) armaan gadiitiin akka galmaa'u cimsinee beeksifna.
gucni galmee hanga Kiibxata Gurraandhala 10/2026 G.C banaa ta'ee tura.
🔗 *Guca nama damee Dura bu'ummaa irratti dorgomuu.*
https://forms.gle/VFGBfFraRK6aZsmq7
🔗 *Guca nama itti gaafatamaa Damee barnootaa irratti dorgomuu.* https://forms.gle/3DDFWuEsSVZFwfV36
5👍1
⭕️⭕️⭕️
URGENT
⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️

🔴 አስቸኳይ ማሳሰቢያ ለሁሉም ተማሪዎች

🚫 በቴሌግራም አዲስ የሪፖርት ማድረጊያ ፖሊሲ (Update) ምክንያት፣ በአሁኑ ሰዓት ተንኮል አዘል አካላት የሰዎችን ፕሮፋይል ፎቶ እንደ ምክንያት በመጠቀም "የሰው ማንነት መክተል" (Impersonation) በሚል ሪፖርት በማድረግ አካውንቶች እና ቻናሎች እንዲዘጉ እያደረጉ ይገኛሉ።

የኛም ቻናሎች ላይ ፕሮፋይሎች ተነስተዋል፣በዚህም መደናገጥ እንዳይፈጠርባችሁ


‼️ ይህ ችግር በእኛ ቻናልም ሆነ በእናንተ የግል አካውንት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች እንድታደርጉ እናሳስባለን፦

* አለመደናገጥ፦ የብዙ ሰዎች ፕሮፋይል መጥፋት የቴክኒክ ብልሽት ሳይሆን ለጥንቃቄ ሲባል እየተደረገ ያለ መሆኑን ተረድታችሁ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እንጠይቃለን።

- Two-Step Verification (ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫ) ማብራት

* ጥንቃቄ፦ ማንኛውንም አጠራጣሪ ሊንክ (Link) ከመጫን ተቆጠቡ።
ሁኔታው እስኪረጋጋ ድረስ ለምናደርገው ጥንቃቄ ትብብራችሁ አይለየን። ተማሪዎቻችን ትምህርታችሁን በሰላም እንድትከታተሉ የሁላችንም ደህንነት ያሳስበናል።


አፍሪካ አካዳሚ
👍7121
ረመዳን ነገ ነው ቢባል ....

👇👇👇👇👇
https://vt.tiktok.com/ZSmjjsrN2/
7👍2
ሀብታም መሆን ትፈልጋለህ??

👇👇👇

https://vt.tiktok.com/ZSmh9DLt6/
3👍2
የረመዳን ስንቅ፡ ልዩ የ20 ቀናት መንፈሳዊ ጉዞ!
ረመዳንን በዝምታ ብቻ ሳይሆን በብርሃን ያሳልፉ!
አፍሪካ አካዳሚ ለተከበረው ወር የሚመጥን፣ በ20 ቀናት ውስጥ የሚጠናቀቅ ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ይጠብቅዎታል።

ምን ይዞ ይሆን?
- በየቀኑ የሚቀሩትን ቃላት በልዩ እይታ የሚያስገነዝብ።
- የሶላት ተመስጦን የሚጨምር።
- ለህይወትዎ ቅርብ የሆነ ጥልቅ እውቀት።
> "ምስጢሩን ስታውቁት ደግሞ ድምቀቱ ይጨምራል!"
>
ይህ ፕሮግራም ምን እንደሆነ ሳንገልጽ ለእናንተ "ሰርፕራይዝ" አድርገነዋል!

ከበረከቱ ለመካፈል ግን አሁኑኑ ቦታዎን ይያዙ።

📍 ቦታ፡ አፍሪካ አካዳሚ
ቆይታ፡ 20 ቀናት ብቻ!

ለመመዝገብ ይቀላቀሉን ➡️ https://t.me/Africa_Academy1

#አፍሪካ_አካዳሚ
#አጫጭር_ኮርሶች
#ረመዳን
7👍4
የላቀው የረመዷን ወር ነገ እንደሚጀምር ተበስሯል !

የሻዕባን ወር ዛሬ ሌቱን በረመዷን የሚተካ ሲሆን ነገ የመጀመሪያው የረመዷን ቀን ይሆናል !

ከነገ ረቡዕ የካቲት 11/2018 ዓ.ል ጀምሮ የረመዷን ጾም ይጀምራል !

አፍሪካ አካዳሚም ታላቁን ወር ባማረ መልኩ እንድታሳልፉ መልካም ምኞቱን ይገልፃል ።

ረመዷን ሙባረክ

© መረጃውን ከኢንሳይድ ሀረመይን አግኘተነዋል !

#አፍሪካ_አካዳሚ
#አፍሪካ_ቲቪ
#የህይወት_ጎዳና
#ረመዷን_ለማህበረሰባዊ_ከፍታ
19👍4
ውድ የአፍሪካ አካዳሚ ተማሪዎች ዛሬ ይጀመራል ተብሎ የነበረው የረመዳን አጫጭር ኮርሶች የመጨረሻው ጁዝ የቁርኣን ማብራሪያ ፕሮግራም እድሉ ለብዙሃን እንዲደርስ በማሰብ ለረመዳን 5 ያዛወርነው መሆኑን እየገለፅን ፣ ይህንን ማስታወቂያ ለወዳጆቻችሁና ለምታውቃቸው በሙሉ ሼር በማድረግ የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የቡኩሎን ይወጡ


ቴሌግራም ሊንክ

🔗🔗🔗https://t.me/Africa_Academy1

===
#አፍሪካ_አካዳሚ
#አጫጭር_ኮርሶች
#የቁርኣን_የመጨረሻው_ጁዝ
17👍2🥰1
"ለሁሉም ክፍት ከሆነው የአፍሪካ አካዳሚ አጫጭር ኮርሶች ማዕድ ውስጥ አዲስ ፕሮግራም

ፕሮግራሙ አጫጭር የቁርኣን ምዕራፎችን ቀለል ባለ መልኩ አጠር ያለ ትንታኔ እና ማብራሪያ የሚሰጥ ነው። ተሳታፊዎቹ የእነዚህን ምዕራፎች ማብራሪያ ፣ አላማ እና የወረዱበትን ምክንያት በመማር ከአላህ ንግግር ጋር ይቆራኛሉ።

📝 ፕሮግራሙን ልዩ የሚያደርገው
- ነፃ ነው : - ፕሮግራሙን ለመከታተልም ይሁን የምስክር ወረቀት ለማግኘት ክፍያ አይጠይቅሞ።
- ትምህርቱ የርቀት ነው :-  በስልክዎ አልያም በኮምፕዩተሮ ካሉበት ሆነው መከታተል ይችላሉ።
- ጊዜው አጭር ነው : ፕሮግራሙ የአስራ አምስት ቀን ብቻ ነው።
- የምስክር ወረቀት : ፕሮግራሙን ሲጨርሱ የምስክር ወረቀት ያገኛሉ።
- የመማሪያ ብዙ አማራጮች፡ ፕሮግራሙን በቴሌግራም ፣ በዩቲዩብ፣ በአፍሪካ አካዳሚ ድህረገጽ እንዲሁም በአፍሪካ ቲቪ መከታተል ይችላሉ።

ምዝገባ ክፍት ነው።

ትምህርቱ ረመዳን 5  ይጀምራል

💥 ይህንን ሊንክ በመጫን ቴሌግራም ቻናላችን ላይ ይመዝገቡ።
=====
https://t.me/Africa_Academy1

=====
#አፍሪካ_አካዳሚ
#ጁዝእ_ዐመ_ማብራሪያ
11
ከአላህ ቃል ጋር ያለዎትን ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክሩበት አዲስ የአጫጭር ኮርሶች ፕሮግራም ይዘንልዎ መጥተናል።

በዚህ ልዩ ፕሮግራምመጨረሻው ጁዝ ላይ ያሉትን የቁርኣን ምዕራፎችን በቀላሉ እንማራለን። የተሳታፊዎችን ግንዛቤ ለማሳደግም የምዕራፎቹ ማብራሪያ (ተፍሲር)፣ ዋና ዓላማ እንዲሁም የወረዱበት ምክንያት በአጭሩ እና በግልፅ ይዳሰሳሉ።

📌 የፕሮግራሙ ልዩ ገፅታዎች፦

🎁 100% ነፃ ፦ ለትምህርቱም ሆነ ለምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ምንም ዓይነት ክፍያ አይጠየቁም።

📱 የርቀት ትምህርት ፦ ከቤትዎ ሳይወጡ ባሉበት ቦታ ሆነው በስልክዎ ወይም በኮምፒውተርዎ ይማራሉ።

አጭር ጊዜ ፦ ፕሮግራሙ የሚፈጀው 15 ቀናትን ብቻ በመሆኑ ጊዜዎን አይሻማም።

📜 የምስክር ወረቀት ፦ ትምህርቱን በተሳካ ሁኔታ ላጠናቀቁ ሁሉ ሰርተፍኬት ይበረከታል።

🌐 ሰፊ የመማሪያ አማራጮች ፦ እንደምርጫዎ ትምህርቱን በቴሌግራም፣ በዩቲዩብ፣ በአፍሪካ አካዳሚ ድህረ-ገጽ ወይም በአፍሪካ ቲቪ መከታተል ይችላሉ።

🗓 ትምህርቱ የሚጀምረው፦ ረመዳን 5
ምዝገባው አሁን ክፍት ነው!

👇 አሁኑኑ ይህንን ሊንክ በመጫን በቴሌግራም ቻናላችን ይመዝገቡ!
https://t.me/Africa_Academy1

=====
#አፍሪካ_አካዳሚ
#ጁዝእ_ዐመ_ማብራሪያ
19👍8
ዛሬ ይጀምራል


ውድ የአፍሪካ አካዳሚ ቤተሰቦች አዲሱን የረመዳን ያልተመዘገባችሁ ትምህርት የሚሰጥበት ቴሌግራም ቻነል ላይ በመቀላቀል የ እድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ

https://t.me/Africa_Academy1


አፍሪካ_አካዳሚ
አጫጭር_ኮርሶች
8
ዛሬ ይጀምራል


ውድ የአፍሪካ አካዳሚ ቤተሰቦች አዲሱን የረመዳን ያልተመዘገባችሁ ትምህርት የሚሰጥበት ቴሌግራም ቻነል ላይ በመቀላቀል የ እድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ

https://t.me/Africa_Academy1


አፍሪካ_አካዳሚ
አጫጭር_ኮርሶች
18👍7
ረመዳን 17

የምድር ላይ ስኬታማ ሰዎች!

የበድር ዘማቾች (ረዲየላሁ ዐንሁም)

የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስለ እነርሱ ሲናገሩ

"አላህ የበድር ዘማቾችን ሁኔታ ተመለከተና እንዲህ አለ፦ 'የፈለጋችሁትን ሥራ ሥሩ፤ በእርግጥም ምሕረት አድርጌላችኋለሁ።'"

💫 ኢብኑ ሐጀር (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
"ይህ ከእነርሱ ውጪ ለሌላ ለማንም ያልተሰጠ ታላቅ የምስራች ነው።"

مِنَ المُؤمِنِينَ رِجَالٌ صَدَقُوا مَا عَاهَدُوا اللهَ عَلَيهِ، رضيَ اللهُ عن الشُهداءِ وأرضاهُم.
"ከምእምናን መካከል በአላህ ላይ የገቡትን ቃል በዕውነት የፈጸሙ ወንዶች አሉ..." (አል-አሕዛብ፡ 23)።

አላህ ሰማዕትነታቸውን ይውደድላቸው፣ ያስውድዳቸውም።
🤍 አላህ ሆይ! ከታላቅ ችሮታህ እንለምንሃለን።
🤍 አላህ ሆይ! (በጥሩ ሥራ ላይ) አሰማራን፤


አፍሪካ አካዳሚ
33👍15

እንኳን ለ1447ኛው ዓ.ሂ የዒደል-ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
عيدكم مبارك وكل عام وأنتم بخير

​ባሳለፍነው የረመዳን ወር የነበረን ጾም፣ ዒባዳና በጎ ተግባራት በአላህ ዘንድ ተቀባይነትን እንዲያገኙ እየተመኘን፤ ይህ የዒድ በዓል ለእናንተና ለቤተሰባችሁ የሰላም፣የዒባዳ፣ የፍቅር እንዲሁም የመተሳሰብ እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን።

​አላህ ሀገራችንንና ህዝባችንን ይጠብቅልን።


አፍሪካ አካዳሚ
👍2316🥰14
በየወሩ በሂጅራ አቆጣጠር 13፣ 14 እና 15ኛው ቀናት "አያመድ ቢድ" ወይም ነጭ ቀናት በመባል ይታወቃሉ። በእነዚህ ቀናት መፆም ትልቅ ምንዳና በርካታ ጥቅሞች አሉት።
1. መንፈሳዊ ጥቅሞች (ሱናው) 🕋
የዓመት ፆም ምንዳ፦ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በእነዚህ ሶስት ቀናት መፆም እድሜ ልክን ከመፆም ጋር እኩል እንደሆነ ነግረውናል። ምክንያቱም አንዲት መልካም ስራ በአስር ትባዛለችና (3 ቀናት x 10 = 30 ቀናት)።
የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አደራ፦ ሰሀቦች ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በጉዞም ሆነ በቤት ባሉበት ወቅት እነዚህን ቀናት እንዳይተዉ አጥብቀው ይመክሩ እንደነበር ዘግበዋል።
2. አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጥቅሞች 🧠
የሰውነትን ስሜት መቆጣጠር፦ ጨረቃ ሙሉ በምትሆንበት በእነዚህ ቀናት በሰው ልጅ ስሜትና በባህሪ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደምታሳድር ጥናቶች ይጠቁማሉ። መፆም ስሜትን ረጋ ለማድረግና የተረጋጋ ስነ-ልቦና እንዲኖረን ይረዳል።
ሰውነትን ማጽዳት : በየወሩ ለሶስት ቀናት መፆም በሰውነታችን ውስጥ የተከማቹ መርዛማ ነገሮች (Toxins) እንዲወገዱና የምግብ መፍጫ ስርዓታችን እረፍት እንዲያገኝ ያደርጋል።
የደም ዝውውርን ማስተካከል፦ መፆም የደም ግፊትንና የኮሌስትሮል መጠንን ለማስተካከል ከፍተኛ እገዛ አለው።

​"የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ 'ከየወሩ ሶስት ቀናትን መፆም (13፣ 14 እና 15) ልክ አመቱን ሙሉ እንደመፆም ይቆጠራል።' (ቡኻሪና ሙስሊም)"

ውድ ወንድም/እህቶቼ! የፊታችን [እሮብ_ሀሙስ_ጁመዓ] ጀምሮ ያሉትን ሶስት ቀናት በመፆም የአጅሩ ተካፋይ እንሁን። ለሌሎችም በማጋራት የአጅሩ ተካፋይ ያድርጉን!


➡️https://t.me/Africa_Academy1


አፍሪካ አካዳሚ
👍3312