🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤
15.3K subscribers
1.04K photos
59 videos
58 files
393 links
ኦርቶዶክስ ኖት????

የዚህ ቻናል ዋና ዓላማ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳዮችን እና ትምህርቶችን ለሕዝብ ክርስቲያ ማስተላለፍ ነው።
ቤተሰብ ለመሆን ምንም መስፈርት አያስፈልግም ኦርቶዶክስ መሆን በቂ ነው ::
ለመረጃ
🤳🤳🤳🤳🤳
OWNER 🕺👉 @temaye
Download Telegram
"ጀግና ከሆንክ በራስህ ላይ ጦርነት አውጅበት!!!
መቆጣት ከፈለግህ መጀመሪያ በራስህ ላይ ተቆጣ።

ልክስክነትህን፤ ስግብግብነትህን፤ ክፋትህን፤ ዝርክርክነትህን፤ ዘማዊነትህን ተቆጣው፤ ስንፍናህን ተቆጣው።

በዲያብሎስ ላይ ጦርነት ክፈትበት፤ የዘላለም ዕረፍትህን ለሚነጥቅህ፤ ከዘላለማዊ ርስት ለነጠቀህ፤ ከልጅነት ለሚያዋርድህ፤ ከእግዚአብሔር ከሚያጣላህ፤ ከክብር ካዋረድህ በእርሱ ላይ መጀመሪያ ተነሥ።››
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
"ከቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ብርቱ (ጠንካራ) ምንም የለም። ይህችውም ከሰማይ ከፍ ያለች ከምድርም ይልቅ የሰፋች ናት። አታረጅም ነገር ግን ዘወትር ታበራለች።"…

"ቤተ ክርስቲያን በዘመናት ሁሉ ትሰፋለች። መታሰቢያዋም የሚጠፋ (የሚሞት) አይደለም።"…

"ቤተ ክርስቲያን በስንቶች ውጊያ ተደርጎባት ነበር? አልተሸነፈችም እንጂ። የተዋጓት አላውያን፣ የጦር መሪዎች፣ ነገሥታቱስ ምን ያህል ናቸው? የተማሩና ኃይልን የተሞሉ ጎበዞች ሐዲሲቷን ቤተ ክርስቲያን በብዙ ጎዳናዎች ተዋግተዋት ነበር። ሊነቅሏት ግን አልቻሉም። ነገር ግን እርሷን የተዋጉ ጥቂቶች ለዝምታና ቶሎም ለመረሳት ተላልፈው ተሰጥተዋል። የወጓት ቤተ ክርስቲያን ግን ከሰማይ በላይ ከፍ ከፍ ብላለች። ቤተ ክርስቲያንን ድል ከማድረግስ ፀሐይን ማጥፋት (ማጨለም) ይቀላል። ሰው ሆይ! ከቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ኃያል ምንም የለም። ከሰው ብትጣላ ወይ ታሸንፋለህ አልያም ትሸነፋለህ። ቤተ ክርቲያንን ግን ብትጣላ፣ ታሸነፍ ዘንድ የሚቻልህ አይደለም። እግዚአብሔር ከሁሉ ይልቅ ኃያል ነውና። እግዚአብሔር መስርቷታል፣ እንግዲህ ማን ሊነቀንቃት ይችላል? "

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
(በዲያቆን አቤል ካሳሁን የተተረጎመ)
ተወዳጆች ሆይ! እየጦሙ የጦምን ፍሬ ፃማ የማያገኙበት ሁኔታ እንዳለ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያላችሁኝ እንደሆነም፦

✟ ከምግበ ሥጋ ተከልክለን ከምግበ ኃጢአት
     ያልተከለከልን እንደ ሆነ፣
✟ ከጥሉላት ርቀን ነዳያንን ያልጎበኘን እንደ ሆነ፣
✟ ወይን ከመጠጣት ታቅበን በክፉ መሻት ከመስከር
     ያልራቅን እንደ ሆነ፣
✟ ጀምበር እስክትጠልቅ ድረስ ከእህል ከውኃ ርቀን
     በዓይናችን መልካም ያልሆኑ ትዕይንቶችን ከማየት
     ያልጦምን እንደሆነ ነው ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት
     እመልስላችኋለሁ፡፡

ስለዚህ እየጦሙ እንዲህ አለመጦም እንዳለ ዕወቁ፤ ተረዱም፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

      አምላከ ቅዱሳን እየጦሙ ካለመጦም ይሰውረን!

(እስኪ ጓደኞቻችሁን #join እንዲያደርጉ ጋብዙልንና 10 ሺህ እንሙላት)

@zena_tewahido @zena_tewahido
@zena_tewahido @zena_tewahido
@zena_tewahido @zena_tewahido
#ጸሎታቸው_የማይሰማው_ለምንድን_ነው?

ክቡር ዳዊት ሲናገር፡- “እግዚአብሔር ወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል” ብሏል (መዝ.4፡3)፡፡ በዚህ መነሻነትም፡- “ታዲያ ብዙ ሰዎች ጸሎታቸን የማይሰማው ለምንድን ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስለታለሁ፡- እነዚህ ሰዎች የማይጠቅማቸውን ጸሎት ስለሚጸልዩ ነው፡፡ አዎ! በዚህ ጊዜ ጸሎታቸው ባይሰ’ማ ለእነርሱ በጎ ነው፡፡ እግዚአብሔር የማይረባንን ነገር በለመንነው ጊዜ፥ ልመናችንን የሚሰማ ቢኾን ኖሮ ጸሎታችን በመሰማቱ ብቻ ደስ ባልተሰኘን ነበርና፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔርን ተጣርተን ባልሰማን ጊዜ እናመስግነው፡፡ የማይረባንን ነገር ለምነነው ጸሎታችን ከሚሰማን ባይሰማን ይሻለናልና፡፡

አንዳንድ ጊዜም ጸሎታችን በግድየለሽነት የሚቀርብ ከኾነ፥ እግዚአብሔር መልሱን ያዘገይብናል፡፡ ለምን? ከልብ የመነጨ ጸሎት እስክናደርስ ድረስ! ይህ በራሱ ለእኛ የሚሰጠው በቁዔት ቀላል አይደለምና፡፡ መጽሐፍ እንዳለ “እናንተ ክፉዎች ስትኾኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ ከእናንተ በላይ የስጦታን ምንነት፣ መቼ መስጠት እንደሚገባ፣ ምን መስጠትም እንዳለበት የሚያውቅ እግዚአብሔርም መስጠት ያውቅበታል።" (ማቴ.7፡11)፡፡ ለዚህም ነው ብፁዕ ጳውሎስ የማይረባውን ነገር ለምኖ እግዚአብሔር ጸሎቱን ያልሰማው! ለዚህም ነው የተወደደ ሙሴ “ፊትህን አሳየኝ” ብሎ በለመነው ጊዜ ልመናውን ያልተቀበለው።

ስለዚህ እኛም ጸሎታችን ባይሰ’ማ እንኳን እግዚአብሔርን እናመስግን እንጂ ተስፋ አንቁረጥ፡፡ ልል ዘሊል ኾነን ጸልየን ከኾነም ልል ዘሊልነታችንን አስወግደን እንጸልይ እንጂ ድኩማን አንኹን፡፡ እንደዚህ አድርገን ጸልየን ሳለ ጸሎታችን ባይሰ’ማ ግን አምላክ የሚያደርገው ኹሉ ለጥቅማችን ነውና በፍጹም አንዘን፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ)
ይህን ያህል ቀን ጾምኩ አትበሉኝ፡፡ ይህን አልበላሁም ወይም ያንን አልበላሁም፣ የወይን ጠጅ አልጠጣሁም አትበሉኝ።

ይልቁንስ ከግልፍተኝነት ወደ ገርነት፣ ከጭካኔ ወደ ደግነት የተሸጋገርኽ እንደሆነ አሳየኝ፡፡ በአንተ ውስጥ ጥላቻና ቂም ቢኖሩ፣ በወይን ፋንታ ውኃ ብትጠጣ ምን ይጠቅማል? ጾም ብቻውን ስማያዊ ምንዳ አያስገኝምና፤ ትርጉም በሌለው በባዶ የፆም ሥርአት ራስህን አታስገዛ።

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

@zena_tewahido @zena_tewahido
@zena_tewahido @zena_tewahido
#የትሕትና_ማደሪያ

ወደ ክብር የሚወስደው መንገድ ትህትና ነው፡፡ ይህን በጎነት ከየት እናገኘዋለን? ትህትና ወደሚኖርበት ወደ መልካም ማደሪያ መሄድ ትፈልጋለህ? በዚያም በየደረጃቸው በሀብታቸው የታወቁ፤ በኹሉም የሕይወት ዘርፍ ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉ፤ ሰዎችን እናገኛለን፡፡ በሕይወታቸውም ላይ "ትህትና" የሚለውን ቃል በብዕርና በቀለም ይጽፋሉ፡፡ የተንቆጠቆጡ አለባበሶች፤ የተንቆጠቆጡ ቤቶች ከንቱነትን ይወልዳሉና ብዙውን ጊዜ ሰዎች በትዕቢት ወጥመድ ይወድቃሉ፡፡ ኾኖም በትህትና ውስጥ የሚኖሩት እነዚህ ሰዎች ምንም ያህል አገልጋዮች ቢኖሯቸውም፤ የራሳቸውን እሳት ያቀጣጥላሉ የራሳቸውን እንጨት ይፈልጣሉ፤ የራሳቸውን ምግብ ያዘጋጃሉ በግላቸውም እንግዶቻቸውን ያስተናግዳሉ፡፡ ከእነርሱ በታች ያሉትን በስድብ ከፍ ዝቅ አያደርጉም፤ ማንም ሌላውን አይገዛም፡፡ ኹሉም በአገልግሎት ላይ ይሳተፋሉ፡፡ እያንዳንዱም ሰው የእንግዶችን እግር ያጥባል እናም እኔ አጥባለሁ እኔ በማለት ጠብን ያነሳሉ፡፡ እግሩንም የሚያጥቡለት ስው ባርያም ሆነ ባለስልጣን ግድ አይሰጣቸውም፡ በእነርሱ ፊት ማንም ትልቅም፤ ትንሽም አይደለም፡፡ ራሱን ከንቱ እንደሆነ የሚቆጠር ሰውም ከባርያ ጋር እኩል መቆጠሩ አያስከፋውም፡፡

ባሮችም የተከበሩ እንግዶች የሚቀርብላቸው ተመሳሳይ አይነት ምግብ፤ ተመሳሳይ ማረፊያ ነው፤ በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያም ይቀርባሉ፡፡ ታላቅነት የሚገኘው ትሑት በመሆን ነውና፡፡ “የእኔ” እና “ያንተ" የሚሉት ሃሳቦች ከንቱ ናቸው, ማለቂያ የሌለውን የግጭት ምንጭ ይፈጥራሉ፡፡ እነርሱን የሚያስተሳስራቸው አንድ መንፈስ ኖሮ ሳለ ስለምን አገልጋዮችና ጌቶች በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ መታደማቸው ያስገርመናል? በዚህ ድህነት እና ባለጠግነት ስልጣን የላቸውም፤ ዝናና ውርደትም የለም፡፡ ስለዚህም ስንፍናና ከንቱ ውዳሴ በመካከላቸው ቦታ አያገኙም፡፡

አብርሃምም በከነዓናውያን ፊት ራሱን ዝቅ አደረገ፣ ከአፈርና ከአመድ በላይ እንዳልሆነ ያውቅ ነበር። ዳዊት ምን ያህል እንኳ የታላቅ ግዛት ንጉስ ቢሆንም ራሱን ከትል በታች ዝቅ አድርጎ ገለጸ። ታዲያ ትሑት ላለመሆናችን ምን ሰበብ ልንሰጥ እንችላለን? ከአብርሃምና ከዳዊትስ በምን ብንበልጥ ነው?

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #የነፍስ_ምግብ #በፍሉይ_ዓለም_የተተረጎመ)
#ወደ_ትክክለኛው_መንገድ_መቅረብ

የሰው ልጅ በሚመርጠው ምርጫ ወጥነት የለውም። አንድ ጊዜ በጣም ለጋስ እና ራስን መስዋእት እስከማድረግ ድረስ ይደርሳል፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያው ሰው በስግብግብነት እና በራስ ወዳድነት ሲወድቅ እናገኘዋለን፡፡ እግዚአብሔር የመምረጥ ነፃነትን ስለሰጠን፤ ይህንን የባህሪ እንከን ለማስተካከል እጁን አላስገባም። ይህ ማለት የሰው ልጅ በተፈጥሮው ጠባዩ የክርስቶስን ህጎች መከተል አይችልም ማለት ነውን? እርሱ ከሰበከው የፍቅር መንገድ ዘውትር ይርቃልን? መልሱ አዎም አይደለምም ነው፡፡ እኛ ራሳችንን እንደ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት የምንቆጥር ከራሳችን የኃጢአት ጠባይ እንርቃለን፡፡ ይህም የሆነው በትክክል ክርስቶስን ስለምናውቀው እና ፍጽምናውን ስለምንመለከት ነው፤ የእኛንም ደካማነት ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ በራሳችንና ፍፁም ንጹህ በሆነው በክርስቶስ መካከል ያለውን ንጽጽር ማየት በራሱ ምንኛ ህመምን ይፈጥራል፡፡ ፍፁም መልካም የሆነውን የክርስቶስን መንገድ እንከተል፤ ትክክለኛውም መንገድ እርሱ ነውና።

ሁልጊዜ ከፍቅር መንገድ ለመውጣት እንገፋለን፣ ከቀን ወደ ቀን የተሳሳቱ ምርጫዎችን እናደርጋለን፡፡ ኾኖም “ከመንገዱ መራቅ” የለብንም፤ አቅጣጫው እስኪጠፋብንና መንገዱ ከአይናችን እስኪሰወር መራቅ የለብንም፡፡ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር መሆን ማለት፣ ሁልጊዜ፣ በየደቂቃው፣ በትክክለኛው መንገድ ላይ መሆን ማለት አይደለም፤ በዚያም ለመቀጠላችን ዋስትና አይሆንም፡፡ ይልቁንም የቁርጠኝነት ቃል ኪዳን ነው፡፡ እግዚአብሔር በሚፈቅደው መጠን ወደ ትክክለኛው መንገድ ለመቅረብ እና ከተሳሳትን በኋላ ዳግም ለመመለስ የምንገባው ቃል ኪዳን ነው፡፡ ይህ በራሳችን ጥንካሬ ማከናወን የምንችለውን ያህል ነው፤ በእግዚአብሔር ቸርነትም ጉዟችን ቀና እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #የነፍስ_ምግብ #በፍሉይ_ዓለም_የተተረጎመ)

https://t.me/zena_tewahido
"ወዳጄ ሆይ! በጎ ነገር አግኝተህ እንደ ኾነ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ነገር ከአንተ ጋር ጸንቶ ይኖራል፡፡ በጎ ያልኾነ ነገር ደርሶብህ እንደ ኾነም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ያልኾነ ነገር ወደ በጎ ነገር ይቀየራል፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ፈረስ የሚጋልብ ሰው ልጓሙን በአግባቡ ካልያዘው በቀር ፈረሱም ጋላቢውም ይጎዳሉ፡፡ አንድ እባብ የነደፈው ሰው ባለመድኃኒቶችን አግኝቶ መርዙ ወደ ሰውነቱ ኹሉ እንዳይሰራጭ ካላደረገ በቀር ወደ ሞት ሊደርስ ይችላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ አንድ ትንሽ ቁስል በጊዜው ጊዜ ካልታከሙት በቀር ሰፍቶና ተስፋፍቶ ትልቅ ቁስል ወደ መኾን ያድጋል፡፡

በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድም እንደዚህ ነው፡፡ የኃጢአት ቁስል የሚሰፋው ችላ ሲባል ነው፡፡ ገና ትንሽ ነው በሚባልበት ደረጃ ካላራቅነው በቀር ነገ ከነገ ወዲያ ትልቅ ቁስለ ነፍስ ይኾናል፡፡

ተመልከቱ! ዛሬ ላለመቈጣት የሚታገል ሰው ነገ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴን አይዘይድም፡፡ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴ ካልዘየደም ብዙ ባልንጀሮች ይኖሩታል፡፡ ብዙ ባልንጀሮች ካሉት የሚጠላቸውም የሚጠሉትም ሰዎች አይኖሩም፡፡ ባልንጀራ እንጂ ጠላት የሌለው ሰውም የምግባር ኹሉ ፍጻሜ የኾነውን ፍቅር ገንዘብ ያደርጋል፡፡

ስለዚህ ተወዳጅ ሆይ! ወደዚህ ምግባር ታድግ ዘንድ ወደዚህ እንዳታድግ የሚያደርጉህን ጥቃቅን ኃጢአቶችን ከአንተ አርቅ፡፡ ሰፍቶ ተስፋፍቶ ነገ እንዳይቸግርህ ዛሬ በእንጭጩ እያለ ችላ አትበለው፡፡

ይሁዳ ገና የገንዘብ ፍቅር ደረጃ ላይ እያለ ራሱን ቢመረምርና ይህን ለማራቅ ቢጥር ኖሮ በኋላ ከተሰበሰበው ገንዘብ ወደ መስረቅ ባላደገ ነበር፡፡ ገና ከመጀመሪያው ደረጃ እያለ ችላ ባይል ኖሮ የኃጢአት ኹሉ ራስ የኾነው ኃጢአት ወደ መፈጸም ባልደረሰ ነበር፡፡

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንደዚህ ልናደርግ እንደሚገባን ሲያስተምረን ከዝሙት ብቻ እንድርቅ ሳይኾን የእርሱ ሥር የኾነውንና አይቶ መመኘትን ችላ ልንለው እንደማይገባን ነገረን (ማቴ.5፡28)፡፡ ኃጢአት ሥር ሰዳና ሰፍታ ከመቸገራችን በፊት በችግኝ ደረጃ ላይ እያለች ነቅለን መጣል ቀላል ነውና፡፡ 

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
"የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡

የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡

ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
"ጸሎትን የምንጸልየው እግዚአብሔር የማያውቀው ነገር ኖሮ አይደለም፤ ወደ እርሱ እንድንቀርብ፣ ቀርበን ወዳጆቹ እንድንሆን፣ ዘወትር እንዲረዳን፣ ራሳችንን ዝቅ ለማድረግ፣ ኃጢአታችንንም እንድናሰብ ነው እንጂ።"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ:
#ግንቦት_12

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

በዚህችም ዕለት የዓለሙ ሁሉ መምህር የሆነ የከበረ አባት ዮሐንስ አፈወርቅ አረፈ፡፡ ይህም አባት ከእስክንድርያ አገር ሰዎች ወገን ነው የአባቱም ስም አስፋኒዶስ የእናቱም ስም አትናሲያ ነው እሊህም እጅግ ባለጸጎች ነበሩ ይህንንም ልጃቸውን በመልካም አስተዳደግ አሳደጉት ትምህርትንና ጥበብንም ሁሉ አስተማሩት እርሱ ወደ አቴና ሒዶ በመምህራን ቤት ተቀምጦ ትምህርትን ሁሉ ተምሮ በዕውቀቱ ከብዙዎች በላይ ከፍ ከፍ ብሏልና።

ከዚህም በኋላ ገና በታናሽነቱ መነኰሰ የዚህንም የኃላፊውን ዓለም ጣዕም ንቆ ተወ ከእርሱም ቀድሞ በዚሁ ገዳም ቅዱስ ባስልዮስ መንኵሶ ነበር በአንድነትም ተስማምተው ብዙ ትሩፋትን ሠሩ ወላጆቹም በሞቱ ጊዜ ከተውለት ገንዘብ ምንም ምን አልወሰደም ለድኆችና ለምስኪኖች ሰጠ እንጂ ከዚያም በምንኵስና ሥራ በመጠመድ ፍጹም ገድልን እየተጋደለ ኖረ።

በዚያም ገዳም ሶርያዊ ጻድቅ ሰው ስሙ ሲሲኮስ የሚባል መነኰስ ነበረ እርሱም ወደፊት የሚሆነውን በመንፈስ ቅዱስ ያይ ነበር በአንዲት ሌሊትም ለጸሎት እየተጋ ሳለ ሐዋርያትን ጴጥሮስንና ዮሐንስን አያቸው ወደ ዮሐንስ አፈወርቅ ገብተው ጴጥሮስ መክፈቻ ሰጠው ወንጌላዊ ዮሐንስም ወንጌልን ሰጠው እንዲህም አሉት በምድር ያሠርከው በሰማይ የታሠረ ይሆናል በምድርም የፈታኸው ደግሞ በሰማያት የተፈታ ይሆናልና በውስጥህ መንፈስ ቅዱስ ያደረብህ አዲስ ዳንኤል ሆይ የክብር ባለቤት ከሆነ ከታለቅ መምህር ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ወደ አንተ ተልከናልና ዕወቅ እኔም የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ የተሰጠኝ ጴጥሮስ ነኝ። ሁለተኛውም እኔም በመጀመሪያው ስብከቴ በከበረ ወንጌል ቃል አስቀድሞ ነበረ ያልኩ ይህም ቃል በጠላት ላይ የእሳት ሰይፍ የሆነ ዮሐንስ ነኝ። ለአንተም ከክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ወገኖችህ ምእመናንን በቀናች ሃይማኖት ታሳድጋቸው ዘንድ ዕውነተኛ አእምሮ ደግሞ ተሰጥቶሃል። ጻድቅ ሲሲኮስም ይህን ራእይ በአየ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ቸር ታማኝ እረኛ ሁኖ እንደሚሾም ዐወቀ። ከዚህም በኋላ በቅዱስ ዮሐንስ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በላዩ ወርዶ አደረበትና ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ ዲያቆን ሁኖ ሳለም የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ብሉያትንና ሐዲሳትን ተረጐመ።

በአንዲት ሌሊትም ቅዱስ ዮሐንስ ሲጸልይ የእግዚአብሔር መልአክ በድንገት እንደ በረድ ነጭ በሆነ ልብስ ተገለጠለት ቅዱስ ዮሐንስም ሲያየው ደንግጦ በምድር ላይ ወደቀ መልአኩም አርአያውን ለውጦ እንደ ሰው ሁኖ ታየው ወዳጄ አዲስ ዳንኤል ሆይ አትፍራ ተነሣ አለው የቅዱስ ዮሐንስም ልቡ ተጽናንቶ ጌታዬ አንተ ማነህ ግርማህ አስፈርቶኛልና አለው የእግዚአብሔር መልአክም ትሠራው ዘንድ የሚገባህን ልነግርህ ወዳንተ የተላክሁ ነኝ። አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ያዘዘህን ለመሥራት ልብህን አበርታ ቃልህ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በአራቱ ማእዘን ይደርሳልና እልፍ አእላፋትም ትምህርትህን ተቀብለው ትእዛዝህን ሰምተው ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር ተመልሰው ይድናሉና በእግዚአብሔር መንግሥትም ውስጥ የጸና የብርሃን ዐምድ ትሆናለህና። እነሆ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አንተ ይመጣል ከእርሱም ጋራ ሁሉም ካህናትና ዲያቆናት በየማዕረጋቸው የሚያዝህንም አድርግ የእግዚአብሐር ትእዛዝ ነውና ልትተላለፍ አይገባህም አለው።

ከዚህም በኋላ ያ መልአክ ለአባ ፊላትያኖስ ተገልጦ ቅዱስ ዮሐንስን ቅስና እንዲሾመው አዘዘው በማግሥቱም ሊቀ ጳጳሳቱ መጣ ከርሱ ጋራም ካህናት አሉ ይህን ቅዱስ ዮሐንስንም ይዞ ቅስና ሾመው። የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳትም በአረፈ ጊዜ ንጉሥ አርቃድዮስ ልኮ አስመጥቶ ቅዱስ ዮሐንስን በቍስጥንጥንያ ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾመው አባቶቻችን ሐዋርያት እንደሚአደርጉት በሊቀ ጵጵስናው ሥራ ላይ ጸና ሕይወትነት በአላቸው ትምህርቶችና ተግሣጾች ሕዝቡን ሁልጊዜ የሚአስተምር ሆነ። ከኤጲስቆጶሳትም ሆነ ከመንግሥት ወገን ሕግን የሚተላለፉትን ሁሉ ይገሥጻቸዋል ማንንም አይፈራም ፊት አይቶም አያደላም።

የንጉሥ አርቃድዮስ ሚስት አውዶክስያም ገንዘብ ወዳጅ ስለሆነች የአንዲት ድኃ መበለት ቦታዋን በግፍ ወሰደች ያቺ መበለትም ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መጥታ ንግሥት አውዶክስያ ቦታዋን እንደነጠቀቻት ነገረችው እርሱም የደኃዋን ቦታዋን መልሺላት ብሎ ከብዙ ምክር ጋር እንድትመልስላት ንግሥት አውዶክስያን ለመናት እርሷ ግን እምቢ በማለት አልታዘዘችለትም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውን ደሙን እንዳትቀበል አውግዞ ለያት።

ቍጣንና ብስጭትንም ተመልታ ስለ ክፉ ሥራቸው ከሹመታቸው እርሱ የሻራቸውን ኤጲስቆጶሳት ሰበሰበች እነርሱም ንግሥቲቱን ስለ ተቃወመ ስደት እንደሚገባው በእርሱ ላይ ተስማምተው ጻፉ እርሷም አጥራክያ ወደ ሚባል ደሴት ሰደደችው። ከዚያም በደረሰ ጊዜ የዚያች ደሴት ሰዎች በክፉ ሥራ ጸንተው የሚኖሩ ከሀድያን ሁነው አገኛቸው ቅዱስ ዮሐንስም አስተማራቸው ገሠጻቸውም በፊታቸው ስለ አደረጋቸው ድንቆች ተአምራት ወደ ቀናች ሃይማኖት አስገባቸው።

የሮሜ ንጉሥ አኖሬዎስና ሊቀ ጳጳሳቱ ዮናክኒዶስ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ስደት በሰሙ ጊዜ እጅግ አዘኑ በንጉሥ አርቃድዮስ ላይም በመቆጣት እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጽፈው ላኩ ከዚህ ከክፉ ሥራ ተጠበቅ ትእዛዛችንንም ተቀብለህ የከበረ ዮሐንስን ከስደቱ ከአልመለስከው በአንተና በእኛ መካከል ሰላም አይኖርም።

መልእክታቸውንም በአነበበ ጊዜ እጅግ አዘነ ሚስቱንም አግዶ ልኮ ቅዱስ ዮሐንስን ከስደቱ መለሰው በተመለሰ ጊዜም የቍስጥንጥንያ ሰዎች በመመለሱ ታላቅ ደስታ አደረጉ። ከጥቂት ቀኖች በኋላም ንግሥቲቱ ወደ ክፋቷ ተመልሳ ሁለተኛ ወደ አጥራክያ ደሴት ሰደደችውና በዚያው አረፈ።

ንጉሥ አኖሬዎስና ሊቀ ጳጳሳት ዮናክኒዶስም በሰሙ ጊዜ መልእክትን ላኩ ሊቀ ጳጳሳቱም የከበረ ዮሐንስን ከስደቱ እስከምትመልሰው ድረስ ሥጋውንና ደሙን እንዳትቀበል አውዶክስያን አወገዛት።

ከዚህም በኋላ የከበረ ዮሐንስን ይመልሱት ዘንድ ንጉሥ ላከ ግን ሙቶ አገኙት ሥጋውንም ተሸክመው ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ አደረሱት። የከበረ ዮሐንስም በተሰደደበት አገር እንደአረፈና ሥጋውንም ወደ ቍስጥንጥንያ ከተማ እንደአመጡ ወደ አባ ዮናክኒዶስ መልእክት ጽፈው አስረዱት። ሁለተኛም የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውንና ደሙን እንዳትቀበል ልኮ አውድክስያን አወገዛት እየለመነችውም ስምንት ወር ያህል ኖረች በብዙ ልመናም ፈታት። ነገር ግን ጭንቅ በሆነ ደዌ እግዚአብሔር አሠቃያት ያድኗት ዘንድ ገንዘቧን ለባለ መድኃኒቶች ጥበበኞች እስከ ሰጠች ድረስ ግን አልዳነችም ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መቃብርም ሔዳ በእርሱ ላይ ያደረገችውን በደል ይቅር ይላት ዘንድ እየሰገደችና እያለቀሰች ለመነችው እርሱም ይቅር አላት ከደዌዋም ፈወሳት። ጌታችንም ከሥጋው ታላላቅ ድንቆች ታአምራትን ገለጠ።

ስለርሱም እንዲህ ተባለ በአንዲት ዕለትም ከንጉሥ አርቃዴዎስ ጋር ተቀምጦ ሳለ ንጉሡ እንዲህ አለው አባቴ ሆይ ስለ አንድ ቃል እንድታስረዳኝ እለምንሃለሁ። ይህም ቃል ከብዙ ጊዜ ጀምሮ በልቤ ውስጥ ይመላለሳል ወንጌላዊ ማቴዎስ ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምን የበኵር ልጅዋን እስከ ወለደች ድረስ ዮሴፍ አላወቃትም ስለምን አለ ወንዶች ሴቶችን እንደሚአውቋቸው ዮሴፍ አወቃትን አለው።
#ግንቦት_12

የመምህር ወመገስጽ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የእረፍቱ ቀን፣ የአባታችን የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ፍልሰተ አጽም እና የእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የቃልኪዳን ዓመታዊ ክብረ በዓል ነወ።

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ባሕረ ምስጢራት የሆነ የሰውን ፊት አይቶ የማያደላ "መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ" (በርሱ ዘንድ ንጉሥ፣ ሐብታም፣ ደሃ፣ ነዳይ እኩል ነውና)፣ አፈ በረከት፣ አፈ መዐር (ማር)፣ አፈ ሶከር (ስኳር)፣ አፈ አፈው (ሽቱ)፣ ልሳነ ወርቅ፣ የዓለም ሁሉ መምሕር፣ ርዕሰ ሊቃውንት፣ ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)፣ የሐዲስ ኪዳን ዳንኤል፣ ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)፣ ጥዑመ ቃል... እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እረፍቱ ነው።

#ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ
ብፅዕት ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ሰይጣንን ከፈጣሪ ጋር ልታስታርቅ በሄደች ጊዜ ከሲኦል ቅዱስ ሚካኤል እየተራዳት ብዙ ነፍሳትን ያወጣችበት የቃልኪዳን በዓል ነው።

#አቡነ_ተክለሃይማኖት
የአባታቸንና የኢትዮጵያ ፀሐይ የፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ግንቦት 12 ከደብረ አሰቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ አጽማቸው የፈለሰበት (ፍልሰተ አጽም) ይከበራል።

አምላከ ቅዱሳን በቅዱሳኑ ጸሎት ልመናና ቃልኪዳን ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ከጭንቀትና ከመከራ ይጠብቀን።
#የንጉሥ_ግብዣ_አለ_ተጠርተሃል_እንዳትቀር

ወደ ቤተክርስቲያን አዘውትራችሁ የምትመጡ ይህን ልመናዬን ስሙ፤ ሰነፍ የኾኑትን ወደ ቤተ ክርስቲያን የመሄድን አስፈላጊነት አስተምሯቸው፡፡ የትምህርቷን ውበት ቀምሳችኋልና እናንተ ያወቃችሁትን ሳያውቁ እንዳይቀሩ፡፡

ቤተክርስቲያን ሀኪም ቤት እንጂ የነፍስ ፍርድ ቤት አይደለችም። የኃጢአትን ስርዬት ትሰጣለች እንጂ ኃጢአትን አትፈርድም፡፡

በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደምናገኘው ምስጋና በሕይወታችን ውስጥ እንደዚህ ያለ አስደሳች ነገር የለም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ፣ ደስተኞች ደስታቸው ይበዛላቸዋል፡፡ የሚጨነቁት፤ ያዘኑት፣ ሰላምን ያገኛሉ፡፡ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ፤ የተቸገሩ ሰዎች እፎይታ ያገኛሉ፤ ኹሉም ከተሸከሙት ያርፋሉ፡፡

ቤተክርስቲያን ኹሉን ታቅፋለች፡፡ ውስጥ ከሆንክ ተኩላው አይገባም፣ ብትሄድ ግን አራዊቶች ይይዙሃል፡፡ ከቤተክርስቲያን አትራቅ፣ ከቤተክርስቲያን የሚበልጥ ምንም ነገር የለም። ቤተክርስቲያን ተስፋህ ናት፡፡ ቤተክርስቲያን መዳንህ ናት፡፡ ቤተክርስቲያን ከሰማያት ከፍ ትላለች፡፡ ቤተክርስቲያን ከድንጋይ ትከብዳለች፡፡ ቤተክርስቲያን ከአለም ትስፋለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን አታረጅም፣ ነገር ግን ሁልጊዜ እራሷን ታድሳለች፡፡

"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበዳችሁ፤ በመከራና በኃጢአታችሁ የከበደ ኹሉ' ወደ እኔ ኑ" ይላል እግዚአብሔር፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ፡፡" (ማቴ ፲፩፥፳፰)

ይህንን ድምጽ ከመስማት የበለጠ ምን ደስታን ሊሰጠን ይችላል? ከዚህ ግብዣ የበለጠ ጣፋጭ ምንድነው? ጌታ ወደ ቤተክርስቲያን የሚጠራችሁ ለታላቅ ግብዣ ነው፡፡ ከትግል ወደ እረፍት፣ ከስቃይ ወደ እፎይታ ያሸጋግራችኋል፡፡ ከኃጢአታችሁ ሸክም ያገላግላችኋል፡፡ ጭንቀትን በምስጋና፣ ሀዘንንም በደስታ ይፈውሳል፡፡

ለክርስቶስ ከሚኖረው በቀር በእውነት ነጻ፣ በእውነት ደስተኛ የሆነ ማን ነው? እንዲህ ያለው ሰው ክፋትን ኹሉ ያሸንፋል ምንም አይፈራም!

ቤተ ክርስቲያን ለኹሉም መጠጊያ ሆና ቆማለች፡፡ የአምላክን ትዕዛዝ የምትፈጽም መልካም ሰው ከሆንክ ቅድስናህን ለመጠበቅ ግባ፤ ኃጢአተኛ ከሆንህ መዳንን ለማግኘት እርምጃህን ፈጠን አድርገው:: የቤተክርስቲያንን ትምህርት ሳይሰሙስ እንዴት ነፍስን ወደ መልካም መንገድ መምራት ይቻላል?

የእግዚአብሔር ቃል 'ብርሃን' በመባል ይጠራል፤ ፀሐይ ከምታፈልቀውና እኛም ከምናየው ብርሃን፣ እጅግ በጣም የከበረ ብርሃን፣ የነፍሳችንን ጥልቀት የሚያበራ ነው፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ስለዚህ እውነት እንዲህ ሲል መስክሯል፣ “በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው::"

ከእናንተ መካከል በታማኝነት ቤተ ክርስቲያን የምታገለግሉ፤ 'ስራ በዛብኝ፣ ልመጣ አልችልም' እንዳይሉ ሌሎቹን ምከሩ፡፡ ወደ ንጉሱ ግብዣ የተጋበዙ ግን መምጣት ያልቻሉትን እንደ ምሳሌ እንመልከት፡፡ አንደኛው አምስት ጥማድ በሬዎችን ሊገዛ እንደሄደ ተናገረ፣ ሌላው አዲስ መሬትን ሊገዛ እንደሄደ ሲናገር ሌላው ደግሞ ሚስት ማግባቱን ተናገረ፡፡ ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምን፣ ንጉሡ ግብዣውን ንቀው ስለቀሩ የሚታገሳቸው ይመስልሃል? እናም ንጉሡን በሰበብ አስባቡ አታናዱት፡፡

ከጊዜህ ላይ አንድ ሰዓት ያህል እንኳን መቆጠብ ያቅትሃል? ቤተክርስቲያንን ከተሳለሙ በኋላ ወደ ሥራ መሄድ በእውነት ይህን ያህል ከባድ ነውን? አንድ ሰው ወርቅ፣ ብር፣ ማር ወይም ወይን በነጻ እየሰጠ ነው ቢባል፤ ማንም ሳይቀድማችሁ ለመድረስ አትቸኩልም? ነገር ግን፣ ከወርቅ የሚበልጥ፣ ከማርም ከወተትም የሚጣፍጠውን የእግዚአብሔርን ቃል ለማድመጥ ወደ ቤተክርስቲያን የምትመጡት አልፎ አልፎ ነው፡፡

ስለዚህም፣ ይህን ችላ ማለታችሁን አውግዣለሁ፤ ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ያላችሁን ግድየለሽነት እቃወማለሁ፡፡ ከመንፈሳዊ ትምህርቶቿ በመራቃችሁ፣ በውስጣችሁ የእግዚአብሔር ፍራቻ የለም፤ እግዚአብሔርን የማትፈራ ነፍስም ለኃጢአት የተገዛች ትሆናለችና ነፍሳችንን እንጠብቃት፡፡

(#የነፍስ_ምግብ
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ እንዳስተማረው - ገጽ 105-107)

https://t.me/zena_tewahido
https://t.me/zena_tewahido
https://t.me/zena_tewahido
#ኃጢአትህን_ኹሉ_በዲያብሎስ_ላይ_አታሳብብ

በንስሐ ተስፋ ከቆረጥክ ዲያብሎስ ይወድሃል፡፡ ግን እርሱ እንዲረካ አታድርግ፡፡ ለድኅነት ቀንም ሁሌም ዝግጁ ሁን፡፡

እነዚህን ኹሉ የተናገርኩት ዲያብሎስን ከነቀፋ ነፃ ለማውጣት ሳይሆን እናንተን ከስንፍና ነፃ ለማውጣት ነው፡፡ ኃጢአታችንን ኹሉ በእርሱ እንዳናሳብብ በእውነት ይስፈልጋል፤ ለሁሉም ክፋታችን ሰይጣንን ተጠያቂ የምናደርግ ከሆነም የራሳችንን ቅጣት እንጨምራለን፤ ጉዳዩን ኹሉ ወደ እርሱ ስላስተላለፍንም ይቅርታ አናገኝም - ልክ ሄዋን ይቅርታን እንዳላገኘች ሁሉ፡፡

ግን ይህን አናድርግ፡፡ እራሳችንን እንወቅ፡፡ ቁስላችንን እንወቅ። ከዚያም መድኃኒቶቹን ተግባራዊ ማድረግ እንችላለን፤ ደዌውን የማያውቅ ሰው፣ ድካሙን አይፈውስምና፡፡

ብዙ ኃጢአት ሠርተናል፤ ይህን በሚገባ አውቃለሁ፡፡ ሁላችንም ቅጣት ይገባናል፡፡ እኛ ግን ያለ ይቅርታ አይደለንም፣ ከንስሐ አንቀርም፤ አሁንም በአደባባይ ቆመናል፤ በንስሐም ተጋድሎ ውስጥ ነን፡

አርጅተኻል እና በመጨረሻው የሕይወት ደረጃ ላይ ነህ? አሁን እንኳን ከንስሐ እንደወደቅክ አታስብ፡፡ በራስህ መዳን ተስፋ አትቁረጥ፤ በመስቀል ላይ ነፃ የወጣውን ዘራፊ አስብ፡፡ እርሱ ዘውድ ከተቀዳጀበት ጊዜ የበለጠ ምን አጭር ነገር አለ? ያም ሆኖ ይህ ለእርሱ መዳን በቂ ነበር፡

ወጣት ነህ? በወጣትነትህ አትተማመን፣ ከፊትህ ረዥም ጊዜም እንዳለ አታስብ “የእግዚአብሔር ቀን እንደ ሌባ በሌሊት ይመጣልና" (፩ኛ ተሰ. ፭፣፪) ለዚህም ነው ፍጻሜያችንን የማይታይ ያደረገው፣ ተግተን እንድንጸና።

ማንም ኃጢያተኛ ሊያደርግህ አይችልም ይላል አቡነ ቴዎድሮስ - ዲያብሎስም ቢሆን፡፡ ለኃጢአት የመስማማት ወይም የመቃወም ኃይል ያለው በአንተ ውስጥ ብቻ ነው፡፡

አሁን እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ክፋት እንዲሆን የፈቀደ እንደሆነ አልያም በሌላ ምክንያት እንደሆነ እንመርምር።

በስንፍና በልቡም ምኞት ወደ ራሱ ኃጢአትን ከሚያስገባ ሰው በቀር፣ ኃጢአት በማንም ላይ ሊጫን አይችልም፡፡ ፈቃደኛ ባልሆነው እና ኃጢአትን በሚቃወመው ሰው ላይ ዲያብሎስ ኃይል የለውምና፡፡

ዲያብሎስ በኢዮብ ላይ ይህን የኃጢአት ክፋት ለመጫን የክፋት ዘዴውን ኹሉ ከተጠቀመ በኋላ ዓለማዊ ንብረቱን ኹሉ ገፍፎት፣ በሞት ሰባቱን ልጆቹን ነጥቆት፣ ከጭንቅላቱ ፀጉር እስከ እግሩ ጥፍር ድረስ የሚያስፈሩ ቁስሎችን፣ የማያባሩ ስቃዮችን ከሰጠው በኋላ የኃጢአት እድፍ በኢዮብ ላይ እንዲጣበቅ ለማድረግ በከንቱ ሞከረ፤ ኢዮብ በዚህ ኹሉ ጸንቶአልና፤ ከቶ አምላኩን ለመሳደብ ፍቃደኛ አልነበረም።

(የነፍስ ምግብ - #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ እንዳስተማረው ገጽ 80-82 #በፍሉይ_ዓለም የተተረጎመ)
አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር። ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ። ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም። ስለዚህ ተማር! ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለህ። ይህች የንስሓ በር ትኾንልሃለች፡፡ አንድ ቀን ወደ ንስሓም ትመራሃለች።

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ




https://t.me/zena_tewahido
መልካም ምግባር ሰዎች እንዲያዩልን ብለን አናድርግ፡፡ ብንጾምም፣ ብንመጸውትም፣ ብንጸልይም፣ ሌላም በጎ ምግባር ብናደርግ የተገለጠውንም የተሰወረውንም ሁሉ ለሚያውቅ እግዚአብሔር ብለን የማናደርገው ከሆነ ከሰዎች አንዳች ጥቅም አያስገኝልንም፡፡ እንዲህ በማድረጋችን ሰዎች ቢያመሰግኑን እየጎዱን እንደሆነ ልናውቅ ልንረዳ ይገባናል፡፡

እንዲህ ከሆነ ታድያ ለምንድነው ሰዎች እንዲጎዱን ምቹ ሁኔታዎችን የምንፈጥርላቸው? ትክክለኛ ማንነታችን የሚያውቀው፣ የዘለዓለምን ሹመት ሽልማታችንን የሚሰጠን እግዚአብሔር አይደለምን? ታድያ ለምንድነው ጥቅም ከማይሰጠን ይልቁንም ከሚጎዳን አካል ውዳሴን የምንጠብቀው? ስለዚህ በቃላችንም፣ በግብራችንም፣ በሐሳባችንም እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን ደስ ልናሰኝ አይገባንም እላችኋለሁ፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ)

@zena_tewahido @zena_tewahido
አንድ ነዳይ አጥብቆ እየለመነህ በቸልታ ትተኸው ስትሔድ እግዚአብሔርን አጥብቀህ በምትለምን ጊዜ ቢተውህ የሚሰማህን አስብ።"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

"ክርስቶስን በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ወድቆ በሚለምነው ነዳይ ውስጥ ካላገኘኸው ውስጥ ገብተህ በመንበሩ ላይ ባለው ጽዋ ላይ አታገኘውም።"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ


@zena_tewahido @zena_tewahido
ፈረስ የሚጋልብ ሰው ልጓሙን በአግባቡ ካልያዘው በቀር ፈረሱም ጋላቢውም ይጎዳሉ፡፡ አንድ እባብ የነደፈው ሰው ባለመድኃኒቶችን አግኝቶ መርዙ ወደ ሰውነቱ ኹሉ እንዳይሰራጭ ካላደረገ በቀር ወደ ሞት ሊደርስ ይችላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ አንድ ትንሽ ቁስል በጊዜው ጊዜ ካልታከሙት በቀር ሰፍቶና ተስፋፍቶ ትልቅ ቁስል ወደ መኾን ያድጋል፡፡

በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድም እንደዚህ ነው፡፡ የኃጢአት ቁስል የሚሰፋው ችላ ሲባል ነው፡፡ ገና ትንሽ ነው በሚባልበት ደረጃ ካላራቅነው በቀር ነገ ከነገ ወዲያ ትልቅ ቁስለ ነፍስ ይኾናል፡፡

ተመልከቱ! ዛሬ ላለመቈጣት የሚታገል ሰው ነገ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴን አይዘይድም፡፡ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴ ካልዘየደም ብዙ ባልንጀሮች ይኖሩታል፡፡ ብዙ ባልንጀሮች ካሉት የሚጠላቸውም የሚጠሉትም ሰዎች አይኖሩም፡፡ ባልንጀራ እንጂ ጠላት የሌለው ሰውም የምግባር ኹሉ ፍጻሜ የኾነውን ፍቅር ገንዘብ ያደርጋል፡፡

ስለዚህ ተወዳጅ ሆይ! ወደዚህ ምግባር ታድግ ዘንድ ወደዚህ እንዳታድግ የሚያደርጉህን ጥቃቅን ኃጢአቶችን ከአንተ አርቅ፡፡ ሰፍቶ ተስፋፍቶ ነገ እንዳይቸግርህ ዛሬ በእንጭጩ እያለ ችላ አትበለው፡፡

ይሁዳ ገና የገንዘብ ፍቅር ደረጃ ላይ እያለ ራሱን ቢመረምርና ይህን ለማራቅ ቢጥር ኖሮ በኋላ ከተሰበሰበው ገንዘብ ወደ መስረቅ ባላደገ ነበር፡፡ ገና ከመጀመሪያው ደረጃ እያለ ችላ ባይል ኖሮ የኃጢአት ኹሉ ራስ የኾነው ኃጢአት ወደ መፈጸም ባልደረሰ ነበር፡፡

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንደዚህ ልናደርግ እንደሚገባን ሲያስተምረን ከዝሙት ብቻ እንድርቅ ሳይኾን የእርሱ ሥር የኾነውንና አይቶ መመኘትን ችላ ልንለው እንደማይገባን ነገረን (ማቴ.5፡28)፡፡ ኃጢአት ሥር ሰዳና ሰፍታ ከመቸገራችን በፊት በችግኝ ደረጃ ላይ እያለች ነቅለን መጣል ቀላል ነውና፡፡ 

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

https://t.me/zena_tewahido
በታመምህ ጊዜ ድካም ይሰማሃል፤ ብርታት ያንስሃል፤ ፊትህም ይገረጣል፡፡ የዕለት ተዕለት ሥራዎችህን በአግባቡ ማከናወን ይሳንሃል፡፡ በዚህ ጊዜም ሕመምህ ምን ያህል እንደበረታ ሰዎች ያስተውላሉ፤ መታከም እንደሚገባህም ይነግሩሃል፡፡ ስለዚህ ወደ ሐኪም ትኼዳለህ፡፡ ወደ ሐኪም የምትኼደው ግን ሐኪሙ ምን እንዲያደርግልህ ነው? አሁን ለሚሰሙህ ስሜቶች የሚሽሩ መድኃኒቶችን እንዲሰጥህ ነው፡፡ ኾኖም ይሰሙህ የነበሩ ስሜቶች ቢሻሉህም ሰውነትህ አሁንም እንደ ደከመ፣ ፊትህ እንደ ገረጣ ከቀረ፣ የዕለት ተዕለት ሥራዎችህንም በአግባቡ ማከናወን ከተሳነህ፥ በተሰጠህ ሕክምና ደስተኛ ትኾናለህን? አትኾንም!

እውነታው ምንድን ነው?” ስንል ወደ ሐኪሙ የኼድከው የበሽታህን ምንጭ ለመታከም ሳይኾን የበሽታህን ምልክቶች ለማስታገሥ ስለ ኾነ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ የበሽታህ መንሥኤ እስካልታከመ ድረስ የበሽታህ ምልክቶች ለጊዜው ቢታገሡም ቅሉ፥ ፈጽመው ሊወገዱ እንደማይችሉ ሐኪሙ በደንብ ያውቃል፡፡

በክርስቶስ ክርስቲያን፣ በወልድ ውሉድ፣ በመንፈስ ቅዱስም መንፈሳውያን የተባልን እኛም እግዚአብሔር መንፈሳዊ በሽታችንን እንዲያስወግድልን እንሻለን፡፡ እንደ እውነታው ግን ብዙዎቻችን ወደ እግዚአብሔር ቀርበን እንዲያስወግድልን የምንሻው ምልክቶቹን ነው፡፡ ለምሳሌ ችግርን፣ ኀዘንን፣ ቀቢጸ ተስፋንና የመሳሰሉትን እንዲያርቅልን እንፈልጋለን፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ የእነዚህ ምክንያት የኾነውንና ሥር የሰደደውን፣ ዋና ምክንያትም የኾነውን መንፈሳዊ በሽታችንን ሳይሽር እነዚህን ምልክቶች ሊያርቅልን አይፈልግም፡፡ ችግር የሚኾነውም ይህን ጊዜ ነው፡፡ ምልክቶቹን እንዲያርቅልን ስንደክም፥ ወደ ውሳጤያችን ገብቶ የችግሩን ምንጭ ሊያርቅልን የሚችለውን የእግዚአብሔርን ጸጋ (ኃይልን) አጥብቀን እንቃወማለንና፡፡ በውሳጤያችን የተሸሸገውን በሽታ ማስወገድ አንፈልግም፡፡ አመለካከታችን እንዲለወጥ አንፈቅድም፡፡ እውነተኛ ለውጥ የሚመጣውና አማን በአማን የምንታከመው ግን የልባችንን ውሳጤ ለእግዚአብሔር ስንከፍትለትና እርሱም በዚያ በመረቀዘው ቁስላችን ላይ ጽኑ መድኃኒት ሲያስርልን ነው፡፡ እንዲለወጡ የምንፈልጋቸው ምልክቶች በእርግጥም የሚለወጡት ይህ በልባችን ውስጥ የተደበቀው መንፈሳዊ በሽታችን ሲጠፋ ነው፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

https://t.me/zena_tewahido