🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤
14.3K subscribers
1.03K photos
59 videos
57 files
382 links
ኦርቶዶክስ ኖት????

የዚህ ቻናል ዋና ዓላማ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳዮችን እና ትምህርቶችን ለሕዝብ ክርስቲያ ማስተላለፍ ነው።
ቤተሰብ ለመሆን ምንም መስፈርት አያስፈልግም ኦርቶዶክስ መሆን በቂ ነው ::
ለመረጃ
🤳🤳🤳🤳🤳
OWNER 🕺👉 @temaye
Download Telegram
የ11.5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ11.5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገች፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የስብክተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ ማርቆስ ጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በመገኘት ድጋፉን አስረክበዋል፡፡

በደረሰው አደጋ ቤተ-ክርስቲያኗ ማዘኗን የገለጹት አቡነ ማርቆስ፤ ለተጎጂ ወገኖችም መጽናናትን እንደሚመኙ ተናግረዋል፡፡

አሁን እንደተቋም ቤተ-ክርስቲያኗ ካደረገችው ድጋፍ በተጓዳኝ ምዕመኑን በማስተባበርም በቀጣይ ድጋፍ እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡

ድጋፊን የተቀበሉት የጎፋ ዞን ዋና አስተዳደሪ ዳግማዊ አየለ፤ ቤተ-ክርስቲያኗ አደጋው ከደረሰ ጀምሮ ተጎጂዎችን ከማጽናናት ጀምሮ ባደረገችው ያልተቋረጠ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በቀጣይ ሌሎች ሀይማኖታዊ ይሁኑ ሀይማኖታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተጎጂ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የበለስ ቅጠል ሰፊና ደስ የምታሰኝ ናት፤ ወደ ጥፋት የምትወስደው የኃጢአት መንገድም ሰፊ በር ናት፡፡ የበለስ ፍሬ ሲበሏትና ሲያላምጧት ጣፋጭ ናት፤ ኃጢአትም ሲሠሯት ደስ ታሰኛለች፡፡ ከሠሯት በኋላ ግን (እንደ በለሲቱ) መከራን ታመጣለች። በሚሠሯት ጊዜ ጣፋጭ ከሠሯት በኋላ ግን መራር ናትና እርሷን ከመሥራት ሽሽ፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

@zena_tewahido @zena_tewahido
"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን። ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን።"

ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ
▪️ ሰው በልቶ ዕዳሪውን የሚያወጣበትን ባያዘጋጅለት ኖሮ እንዴት ይጨነቅ ነበረ? ይልቁኑም ሰው ኃጢአትን ሠርቶ መመለሻ ንስሐ ባያዘጋጅለት ኑሮ እጅጉን ተስፋ ይቆርጥ ነበር
▪️ ይህ ማለት ግን ንስሐ ኃጥአንን ለመደገፍ እንጂ ኃጢአትን ለመደገፍ ተሠራች ማለት አይደለም ! ንስሐ እገባለሁ ብለው ኃጢአትን መሥራት እንደ ሰብአ ትካት ራስን ለጥፋት መዘጋጀትን እና ዕጠገናለሁ ብሎ እንደመሰበር ነው::
▪️ ይልቁንም ሳራን እና የነነዌ ሰዎችን አብነት አድርገን ስተው ቢበድሉ ፈጥኖ ንስሐ መግባት ይገባል።
▪️ ጭቃን ቢያጥቡ እንደማይጠራ ሰውም ኃጢአት ሲያሳድፈው በንስሐ ዘወትር መታጠብ አለበት።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"እንደ ርግብ የዋህ፤ እንደ እባብም ጠቢብ ሁኑ"
🛑ለምን ተባለ?‼️

ርግብና እባብ በጠላትነት የሚፈላለጉ ፍጥረት ናቸው። እባብ ርግብን ካገኘ ይበላታል፤ ለምግብነት ይጠቀምባታል። ለዚህም ርግብን ሲያሳድድ ይኖራል። ርግብ ከእባብ እንደሸሸች ትኖራለች።
ታዲያ በኖኅ ዘመን ከእንስሳት ዘርን ሁሉ ለማስቀረት በኖህ መርከብ ከተጫኑት ውስጥ ርግብና እባብም ነበሩ። መርከቡ በእንስሳት ሞልቶ ነበር። ርግብም እንቁላል መጣል ፈለገች። ቦታም አሰሰች። መርከቡ ውስጥ ለእንቁላል መጠያ የሚሆን ባዶ ቦታ የለም። ዞር ስትል ሲያሳድዳት የኖረውን እባብን አየችው። እባብ አፉን ከፍቶ ምላሱን እያውለበለበ ተመለከተች። ጠላትነቱ ትዝ አላላትምና የእንቁላል መጣያ አገኘው ብላ ከእባብ አፍ ላይ እንቁላሏን ጣለች።
የርግብን የዋህነት ከዚህ ላይ ልብ ይሏል።
እባብ ደነገጠ። የሚያሳድዳት ርግብ ጭራሽ ከአፉ ላይ እንቁላል ጣለችለት። እንቁላሉንም እሷንም መዋጥ ይችላል። ነገር ግን እባብ አሰበ። የእባብ ዘር እንዲቀጥል በኖኅ መርከብ የተጫነ ብቸኛ እባብ ነውና ውጤቱን አሰበ። ይቺን ርግብ እስከ እንቁላሏ ብውጣት ጌታዬ ኖኅ ቢረግመኝና ከዚህ መርከብ ቢጥለኝ እባብ የሚባል ዘር መጥፋቱ አይደለምን አለ። ቀጠለና ዘሬ ከሚጠፋ ብታገሥ ይሻላል ብሎ ርግብ አፉ ላይ እንቁላል ጥላ፤ ታቅፋ ጫጬት እስከምትፈለፍል ድረስ አፉን ከፍቶ ጠበቀ። ዘሩንም በጥበቡ አስቀጠለ።
የእባብ ጠቢብነት ይህ ነው።
እነሆ በዚህ ምክንያት አበው "እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብም ብልህ/ጠቢብ ሁኑ" እያሉ ይመክራሉ።
"ኩኑ የዋሃነ ከመ ርግብ፤ ወጠቢባነ ከመ አርዌ ምድር"



https://t.me/zena_tewahido
https://t.me/zena_tewahido
https://t.me/zena_tewahido
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

🌿◉ጾመ ፍልሰታ እንኳን አደረሳችሁ◉🌿


                  ●ጾመ ፍልሰታ●

◉ "ፍልሰታ" የሚለው ቃል የሚገልጸው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለቆ መሔድን መሰደድን መፍለስን ያመለክታል። ይህም የእመቤታችንን ሥጋ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መፍለሱን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ስር ከነበረበት መነሳቱን ለማመልከት ይነገራል።

◉ ጾመ ፍልሰታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፷፬ ዓመት በዚች ምድር ኖራ እንደ አንድ ልጇ መሞቷን መነሳቷንና ማረጓን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት የጾሙት ጾም ነው። ጾሙ ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ነሐሴ ፲፮ ቀን ሲጾም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ከደነገገቻቸው ሰባቱ አጽዋማትም አንዱ ነው።

               ●ኃይማኖታዊ መሠረት●

◉ እመቤታችን ከአባቷ ከኢያቄም እና ከእናቷ ከሐና ነሐሴ ፯ ቀን ተጸንሳ ግንቦት ፩ ቀን በሊባኖስ ተወልዳለች። "እምሊባኖስ ትወጽዕ መርአት ፦ ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች " እንደተባለ ። እምቤታችን በእናት አባቷ ቤት ሦስት ዓመት፤ በቤተ መቅደስ አሥራ ሁለት ዓመት፤ ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ፡ ከዮሐንስ ወልደዘብዴዎስ ዘንድ አሥራ አራት ዓመት ከዘጠኝ ወር ቆይታ በ ፷፬ ዓመት ዕድሜዋ በ፵፱ ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። የእመቤታችንን ስም የሚገልጹ የውዳሴ ጽሑፎችም በእድሜዋ ልክ ተደርሰዋል። ለምሳሌ የውዳሴ ማርያም ቁጥር ፷፬ ነው፤ የመልክአ ማርያም ቁጥርም ፷፬ ነው።[1]

◉ ባረፈች ጊዜ ቅዱሳን ሐዋርያት ተሰባስበው አስከሬኗን ይዘው ወደ ጌቴሴማኒ መቃብር ለማሳረፍ ሲሄዱ አይሁድ ለተንኮል አያርፉምና ተተናኮሏቸው። ቀድሞ ልጇ ሞቶ ተነሳ፣ አረገ እያሉ ሲያስቸግሩን ይኖራሉ: ደግሞ አሁን እሷም ተነሳች፣ አረገች ሊሉ አይደል በማለት አይሁድ ተሰባስበው አስከሬኗን ለማቃጠል ሲተናኮሉ እግዚአብሔር በተአምር ከነዚያ አይሁዶች አድኗቸዋል ። የእመቤታችንንም አስከሬን ነጥቆ ከሐዋርያው ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር በገነት በዕፀ ህይወት ስር አኑሯቸዋል ። ከዚያ በኋላ ሐዋርያት ሥጋዋን አግኝተው ይቀብሩት ዘንድ በአረፈች በስምንተኛው ወር ከነሐሴ ፩ ጀምሮ እስከ ነሐሴ ፲፬ ቀን ድረስ ሁለት ሱባዔ ይዘው በአሥራ አራተኛው ቀን ሥጋዋን ከጌታ ተቀብለው በጸሎትና በምህላ በፍጹም ደስታ በጌቴሰማኔ አሳረፉት ። በ ሦስተኛውም ቀን ተነስታ ስታርግ ከሰዱቃዊያን ወገን የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ አያት። እርሱም በቀብር ስርዓቱ ጊዜም አልነበረም። ሀገረ ስብከቱ ህንድ ስለነበር ሊያስተምር ወደዛው ሂዶ ነበርና። በዚያም ሲያስተምር ሰንብቶ በደመና ተጭኖ ሲመጣ ያገኛታል። ትንሳኤዋን ከርሱ ሰውራ ያደረገች መስሎት አዝኖ "ቀድሞ የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ ነውን ?" ብሎ ቢያዝንባት እመቤታችንም ከርሱ በቀር ማንንም ትንሳኤዋን እንዳላየ ነግራ አጽናናችው። ለሌሎቹ ሐዋርያትም እንዲነግራቸው ለምልክትም /ለምስክርም እንዲሆነው ሰበኗን /መግነዟን ሰጥታው አረገች። ቶማስም ኢየሩሳሌም ደርሶ ሐዋርያትን "የእመቤታችን ነገርስ እንደምን ሆነ?" ሲል ቢጠይቅ "አግኝተን ቀበርናት እኮ" አሉት። እርሱ ምስጢሩን አዉቆ ደብቆ "ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር" እንዴት ይሆናል ? አይደረግም ይላቸዋል። ሊያሳያቸውም መቃብሩ ዘንድ ሂደው ቢከፍቱት አጧት። እርሱም "አታምኑኝም ብዬ እንጂ እርሷስ ተነስታ አርጋልች" በማለት ሁኔታውን ተረከላቸውና ለምስክር ይሁንህ ብላ የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው። ከዚህ በኋላ ለበረከት ይሆናቸው ዘንድ ሰበኑን ተካፍለው ወደየአህገረ ስብከታቸው ሄዱ። ዛሬ በቅዳሴ ጊዜ ዲያቆኑ በሚይዘው የመጾር መስቀል ላይ በሁለት ቀዳዳዎች አልፎ ተጠምጥሞ የምናየው መቀነት መሰል ጨርቅ የዚያ ሰበን ምሳሌ ነው።

◉ በዓመቱ ሐዋርያት ከያሉበት ተሰባስበው ቶማስ ትንሳኤሽን አይቶ እኛስ እንዴት ይቀርብናል ብለው ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምርው ሱባዔ ቢይዙ ከሁለት ሱባዔ በኋላ እንደገና ትንሳኤዋንና እርገቷን ለማየት በቅተዋል። ሐዋርያዊት የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናም ምእመኖቿ ከእመቤታችን በረከትን እንዲያገኙ ይጾሙ ዘንድ ይህን ሐዋርያት የጾሙትን ጾም እንዲጾሙ አዉጃለች። ምእመናንም በተለየ መልኩ በጾም በጸሎት በሱባዔ ጽሙድ ሆነው ይህን ወቅት ያሳልፋሉ።

◉ የእመቤታችን ትንሳኤ ድንገት እንደእንግዳ ደራሽ እንደ ዉሀ ፈሳሽ የተደረገ ሳይሆን በቅዱሳት መጻሕፍት በትንቢተ ነቢያት የተገለጸ ነው። ነቢዩ ዳዊት በመዝሙር ፻፴፩ ቁጥር ፲ ላይ "አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦትም" ይላል። በዚህም ምዕመናንን ወደ ምታሳርፍበት ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህ ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነስ አለ። ታቦት የጽላት ማደርያ እንደሆነ ሁሉ እምቤታችንም ለክርስቶስ ማደርያ በመሆኗ አማናዊት ታቦት ትባላለች።

◉ ንጉስ ሰሎሞንም በመኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፲ ላይ "ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፤ ወዳጄ ሆይ ተነሽ፡ ውበቴ ሆይ ነይ" ብሏል። እዚህ ላይ "ወዳጄ …ዉበቴ" የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ። ክቡር ዳዊት መዝሙር ፵፬ ቁጥር ፱ ላይ «በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች» እንደሚል ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛነቱን ከፈጸመ በኋላ ወደ ቀደመ ክብሩ እንዳረገ እመቤታችን ቅድስት ድንገል ማርያምም በቀኙ ትቀመጥ ዘንድ «ተነሽ ነይ» አላት ። እንግዲህ ይህንና የመሰለዉን ሁሉ ይዘን የእናታችንን እረፍቷን ትንሳኤዋን እንዘክራለን እንመሰክራለንም።

       🕊ጾሙን የበረከት ያድርግልን🕊

                ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                    ወለወላዲቱ ድንግል
                      ወለመስቀሉ ክቡር
                          
 https://t.me/zena_tewahido
https://t.me/zena_tewahido
https://t.me/zena_tewahido
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሰን አደረሳችኹ!

ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን ልበዎውን ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::

ጾሙን የፍሬ የትሩፋትና የበረከት ያድርግልን!
በጾም ሰዓታችሁ ጊዜም ይሁን በሌላ ጊዜ ሦስት ነገሮችን በሕሊናችሁ ትይዙ ዘንድ እመክራችኋለሁ፡፡
እነርሱም፡-
   ✞ ክፉ ከመናገር መከልከልን
   ✞ ማንንም ሰው እንደጠላት ከማየት መቆጠብንና
   ✞ እንደልምድ አደርጋችሁ ከያዛቸሁት መሐላ ትርቁ ዘንድ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@zena_tewahido
አንድ ነዳይ አጥብቆ እየለመነህ በቸልታ ትተኸው ስትሔድ እግዚአብሔርን አጥብቀህ በምትለምን ጊዜ ቢተውህ የሚሰማህን አስብ።"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

"ክርስቶስን በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ወድቆ በሚለምነው ነዳይ ውስጥ ካላገኘኸው ውስጥ ገብተህ በመንበሩ ላይ ባለው ጽዋ ላይ አታገኘውም።"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ


@zena_tewahido @zena_tewahido
✥✥✥ ቡርክት ✥✥✥

ድንግል ማርያም ቡርክት ለምን ተባለች? መርገም የወደቀበት ሁሉ ርጉም እንደሚባል የታወቀ ነው። ርግማንን የሠራ ርጉም ፥ በረከትን የሠራ ቡሩክ ይባላል። ድንግል ማርያም መርገመ አዳም ወሔዋን የለባትምና ቡርክት ናት፡፡

እመቤታችን በመላእክት ወገን በቅዱስ ገብርኤል ፤ በሰውም ወገን በቅድስት ኤልሳቤጥ ቡርክት ተብላ ተመስግና ክብርዋ ተገለጿል። ( ሉቃ .፩፤ ፳፰ / ሉቃ ፩፥፵፪ )

እንዴት ከሰው ተለይታ መርገም ሳይወድቅባት ቀረ የሚል ካለ እንዴት ከሴቶች ተለይተሽ ቡርክት ነሽ ተባለች? ብለን እንመልስልታለን፡፡

ከሴት ተወልዳ እንዴት ርግማን ኣልወደቀባትም? የሚል ቢኖር እንደሚከተለው እንመልስለታልን፡፡
እግዚኣብሔር ኣዳም በበደለ ጊዜ " ርግምተ ትኩን ምድር በተግባርከ....... ኣሥዋክ
ወኣሜከላ ይብቁልከ- ምድር ከኣንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን እሾህና ኣሜኬላን ታበቅልብሃለች” ብሎታል (ዘፍ፫፥፲፯)፡፡ ምድር የተረገመች ትሁን ካለ ምድርም ሁሉ በእርሱ ምክንያት የተረገመ ሁኗል ማለት ነው፡፡

ሌላ ጊዜ ደግሞ ለሙሴ “ሙሴ ሙሴ የቆምኽባት ስፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን ከእግርህ ኣውጣ ኣለው” (ዘጸ.፫፡፭)። እንግዲህ በኣዳም በደል ምድር ሁሉ የተረገመች ከሆነ ሙሴ የቆመባት ብቻ እንዴት ተለይታ ቅድስት ሆነች? ነውስ ምድር ስትረገም
ደብረሲና ኣልተረገመችም? ነው ወይስ ምድር ሁሉ የተረገመ ከሆነ ያቺ ምድር ኣይደለችም? ኣብራ ከተረገመች የእርስዋ መርገም መቼ ተነሥቶላት ቅድስት ምድር ለመሆን የበቃች? ወይስ እግዚኣብሔር እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነገር ኣለውን? በፍጹም!

ታዲያ ምሥጢሩ እንደ ምንድን ነው? ካሉ ምድር ሁሉ የተረገመ ይሁን የተባለ ከምድር የተፈጠረ የሰው ልጅ ሁሉ ርጉም ይሁን ሲል በኣንተ ምክንያት ማለትም " በጌጋየ ኣሐዱ ብእሲ ቀነዮሙ ሞት - ከኣዳም እስከ ሙሴ ያሉትን በኣንድ በኣዳም ምክንያት ሞት ገዛቸው” ማለት ነው፡፡ እስከ ሙሴ ማለትም ከኦሪት በፊት ያሉትንም በሙሴ ኦሪት የጸኑትንም ማለት ነው።

ምድር ሁሉ ተረግሞ ሣለ በመሃል የተገኘችው ቡርክት ምድር ግን ድንግል ማርያም ናት። ሙሴ
የቆመባት ማለትም ሙሴ የጸናበት በሙሴ ትንቢት የተወለደች በሙሴ ትንቢት የምትወልድ ሙሴን ያዳነችው ሙሴ የዳነባት የሙሴ መሠረቱ ማለት ነው።

ቅድስት ናትና ጫማህን ከእግርህ ኣውጣ ማለትም የዳንክባት ድንግል ማርያም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት ቡርክት ናትና የትም የሰበሰብከውን በእግረ ልቡናህ ያጠለቅኸውን የክሕደት ሸቀጥ ወዲያ ጣል ማለት ነው፡፡

በተረገመ ዓለም ውስጥ ቡርክት፡ በጎሰቆለው ዓለም ውስጥ ንጽሕት ቅድስት ሆና የተገኘች ንጽሕት ምድር ወላዲተ ኣምላክ ናት። ስለዚህ ነው ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ ኣፈወርቅ “ ተፈሥሒ ኦ ማርያም ምድር ቅድስት ዘበጽሓኪ እግዚኣብሔር እንዘይጼዓን ዲበ ደመና ብሩህ ወቦአ ውስቴትኪ - እግዚኣብሔር በብሩህ ደመና ሆኖ ወደ አንቺ የመጣ በኣንቺም ያደረ ምድር ቅድስት እመቤቴ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ ” ኣለ።

ይኸም ቅዱስ ገብርኤል ቡርክት ኣንቲ እም ኣንስት ማለቱ ለሙሴ ቅድስት ምድር ናት ተብላ የተነገረችው ከሰው ተለይተሸ መርገም የሌለብሽ ያቺ ምድር ኣንቺ ነሽ ማለቱ ነው ብሎ ሲተረጉምልን ነው ቅዱስ ዮሓንስ ኣፈወርቅ፡፡

ቅድስት እናታችን ኤልሳቤጥም ከሴቶች ተለይተሽ ስትል ራሷንም ኣጠቃልላ ነው። ተመልከቱ ኤልሳቤጥ በጽድቅ ሕይወት የምትኖር ናት። ግን መርገመ ኣዳም ወሔዋን ኣለባትና ራሷን ምንም ጻድቅ ብትሆን በመርገሙ እንደ ሌሎች ናትና ኣብራ ቆጠረች። ድንግል ማርያም ግን ንጽሕናዋ ከፍጥረት እንደሚበልጥ ከፍጥረት ተለይታ መርገም የሌለባት ናትና “ተለይተሸ” ኣለቻት።

ኣንዳንዶቹ በኋላ መንፈስ ቅዱስ መጥቶ ስለሚያነጻት ነው ይላሉ። መንፈስ ቅዱስማ በኋላ ሌሎች ሴቶችንስ ያነጻቸው የለምን? በጊዜ ልዩነት ብቻ ነው እንዴ ልዩነቷ? በኋላስ በክርስቶስ ደም ሁላችንስ ነጽተን የለ እንዴ? “ ነውር የሌለበት ሆኖ በዘለዓለም መንፈስ ራሱን ለእግዚኣብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውና እግዚኣብሔርን ልታመልኩ ከሞት ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን? ” ተብሎ ተስፋ
ሰጥቶናልና (ዕብ.፱፥፲፬)፡፡ ነገር ግን የእርስዋ ከሴቶች መለየት ቀድሞ “ እምከርሰ ኣዳም ወሔዋን” ንጽሕት በመሆኗ ነው፡፡

ከሴቶች ተለይታ ኣምላክን መውለድ ለእርስዋ ብቻ እንደ ተቻለ፥ ከሴቶች ተለይታ ቡርክት መሆንም ለእመቤታችን ብቻ የተቻለ ነው:: ይቆየን

የትንሣኤዋንና የዕርገትዋን ብርሃን ለማየት ታብቃን

✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ

@zena_tewahido @zena_tewahido
@zena_tewahido @zena_tewahido
✥✥✥ ፅንሰታ ለእግዝእትነ ✥✥✥

👉 ነሐሴ 7 እመቤታችን የተፀነሰችበት ነው። ቤተክርስቲያናችንም ከምታከብራቸው ዓበይት በዓላት መካከልም ነው።

👉  አባ ሕርያቆስ ስለ እመቤታችን የመፀነስዋን ነገር ሲናገር ድንግል ሆይ በልተው ጠጥተው ጾር ሲጸናባቸው በሚያደርጉት ግንኙነት የተፀነሽ ኣይደለሽም ጋብቻ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ነው ብዙ ተባዙ ባለው ፈቃድ በሩካቤ ዘበሕግ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ በማለት ያደንቃል!

👉  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም " የእግዚኣብሔር ልጆች የቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ማኅበር እንግዲህ ይህችን ንጽሕት ሙሽራ የወለዱልንን ኢያቄምንና ሐናን እናድንቃቸው የማትነቀፍ የእስራኤል ድንግል የተባረከችይቱም ፍሬ የተፈራችባት የሩካቢያቸው ንጽሕት ቀን እንደምን ያለች ናት፡፡ ከይሁዳ ወገን የምትሆነውን ንጽሕት ርግብ ለመፀነስሽ ለእግዚኣብሔር ፈቃድ የሆነው የመገናኘታቸው ቀን እንደምን ቅድስት ናት፡፡ የንጉሥ አዳራሽ የምትሆን የርሷ መሠረት የተመሠረተባት ዕለት እንደምን ደስ ያለች ናት፡፡

➛   ነቢዩ ኢሳይያስም እንዲህ አለ " ከዕሤይ ሥር በትር ትወጣለች፡፡ ከግንዱም አበባ ይወጣል በላዩም የእግዚኣብሔር መንፈስ ያርፍበታል፡፡ " (ኢሳ ፲፩፣ ፩፣ ፪)

-    ይኸውም ትንቢት በጽዮን የተነገረው በኢየሩሳሌም የተሰበከው በነቢያት አንደበት የተሰማው በሌዋውያን እጅ በዕብራይስጥ ልሳን የተጻፈው ሊፈጸም የክህነት በትር በቀለችልን፡፡ የመንግሥትና የኃይል የሕይወትና የመድኃኒት የሃይማኖት የንጽሕና የቅድስና በትር የኃይል የመዊዕ በትር በቀለችልን፡፡

➛  "ከዕሴይ ዘር በትር ትወጣለች፤ ከግንዱም አበባ ይወጣል የሚለው እንደተጻፈ፤ ያሰበውን ለማድረግ የሚከለክለው የለም፤ ከኢያቄም ኣብራክ ተከፍላ በሐና ማህፀን ከተፀነሰች ከቅድስት ድንግል የትውልድ ዘር በቀር የበትር ከሥሩ መውጣት ምንድነው? የእመቤታችን የማርያም ኣባቷ ኢያቄም ከዕሴይ ዘር ነውና፤ ዳግመኛም ከኢያቄም ሴት ልጁ የመለኮት ሰው መሆን በቀር የአበባ የግንድ መውጣት ምንድነው?"

👉   የልደትዋን ነገር አያይዞ ሲናገርም ፦  በኢያቄም በኣባትሽ ወገን የንጉሥ ልጅ ሆይ አመሰግንሻለሁ፡፡ የዳዊት ልጅ ነሽና የሊቀ ካህናት ልጅ ሆይ ውዳሴሽን አቀርባለሁ፡፡ ከእናትሽ ወገን የኣሮን ልጅ ነሽና፡፡ ገናንነትሽንም አደንቃለሁ፡፡ የነገድሽን ወገን አመሰግናለሁ ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ተገኝተሻልና፡፡

➛  ስለዚሀም የነጎድጓድ ልጅ ነሽ እልሻለሁ ያዕቆብና ዮሓንስን ኣኔሬጌስ ብሎ እንደጠራቸው ይኸው የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው፡፡ ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ናቸውና፡፡ ስለዚህም የነጎድጓድ ልጆች ተባሉ፡፡

➛  እኔም የነጎድጓድ ልጅ ነሽ ኣልሁሽ፡፡ የመወለድሽ ድምፅ (ወሬ) እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ይሰማልና፡፡

 ከሁለቱ ከተቀቡት ነገድ በነቢያት አለቃ በሙሴ እጅ ለክህነት ከተቀባው ከኣሮን ቤት፡፡ በሳሙኤል እጅ ለመንግስት ከተቀባው ከዳዊት ዘር፡፡ (፩ ሳሙ ፲፮፣ ፲፫) (ዘሌዋ ፰፣ ፲፪)
 
👉  ደግሞም ያንበሶች ልጅ ነሽ እልሻለሁ እንደ አንበሳ ግልገል ጩኸት እንደ ሴትም አንበሳ ድምፅ የልደትሽ ወሬ ይሰማልና፡፡ አባቱ ያዕቆብ ይሁዳን ያንበሳ ግልገል ብሎታልና፡፡ (ዘፍጥ ፵፣ ፱፣ ፱)

➛ ስለዚህም ያንበሶች ልጅ እልሻለሁ፡፡ ሰሎሞን እንደተናገረ እንዲህ ሲል ኣንቺ ሙሽራ ከሊባኖስ ጋራ ነይ ከሊባኖስ ጋራ ነይ፡፡ ከአንበሶችም ጉድጓድ ወጥተሽ ነይ፡፡ (መኃ ፬፣ ፰)
ከተመረጠ ነገዱ የተነሣ ከሚመካ ወገን የመወለድሽ ወሬ እጅግ ግሩም ነው፡፡ በማለት ያደንቃል።  ይቆየን

ፍቅርዋን ከልቡናችን ጣዕመ ምስጋናዋንም ከአንደበታችን ታሳድርልን አትለይብን።

➛ ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ( አባ ሕርያቆስ )
➛ መጽሓፈ አርጋኖን ፣ መጽሐፈ ምሥጢር  (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ )

https://t.me/zena_tewahido
ፈረስ የሚጋልብ ሰው ልጓሙን በአግባቡ ካልያዘው በቀር ፈረሱም ጋላቢውም ይጎዳሉ፡፡ አንድ እባብ የነደፈው ሰው ባለመድኃኒቶችን አግኝቶ መርዙ ወደ ሰውነቱ ኹሉ እንዳይሰራጭ ካላደረገ በቀር ወደ ሞት ሊደርስ ይችላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ አንድ ትንሽ ቁስል በጊዜው ጊዜ ካልታከሙት በቀር ሰፍቶና ተስፋፍቶ ትልቅ ቁስል ወደ መኾን ያድጋል፡፡

በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድም እንደዚህ ነው፡፡ የኃጢአት ቁስል የሚሰፋው ችላ ሲባል ነው፡፡ ገና ትንሽ ነው በሚባልበት ደረጃ ካላራቅነው በቀር ነገ ከነገ ወዲያ ትልቅ ቁስለ ነፍስ ይኾናል፡፡

ተመልከቱ! ዛሬ ላለመቈጣት የሚታገል ሰው ነገ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴን አይዘይድም፡፡ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴ ካልዘየደም ብዙ ባልንጀሮች ይኖሩታል፡፡ ብዙ ባልንጀሮች ካሉት የሚጠላቸውም የሚጠሉትም ሰዎች አይኖሩም፡፡ ባልንጀራ እንጂ ጠላት የሌለው ሰውም የምግባር ኹሉ ፍጻሜ የኾነውን ፍቅር ገንዘብ ያደርጋል፡፡

ስለዚህ ተወዳጅ ሆይ! ወደዚህ ምግባር ታድግ ዘንድ ወደዚህ እንዳታድግ የሚያደርጉህን ጥቃቅን ኃጢአቶችን ከአንተ አርቅ፡፡ ሰፍቶ ተስፋፍቶ ነገ እንዳይቸግርህ ዛሬ በእንጭጩ እያለ ችላ አትበለው፡፡

ይሁዳ ገና የገንዘብ ፍቅር ደረጃ ላይ እያለ ራሱን ቢመረምርና ይህን ለማራቅ ቢጥር ኖሮ በኋላ ከተሰበሰበው ገንዘብ ወደ መስረቅ ባላደገ ነበር፡፡ ገና ከመጀመሪያው ደረጃ እያለ ችላ ባይል ኖሮ የኃጢአት ኹሉ ራስ የኾነው ኃጢአት ወደ መፈጸም ባልደረሰ ነበር፡፡

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንደዚህ ልናደርግ እንደሚገባን ሲያስተምረን ከዝሙት ብቻ እንድርቅ ሳይኾን የእርሱ ሥር የኾነውንና አይቶ መመኘትን ችላ ልንለው እንደማይገባን ነገረን (ማቴ.5፡28)፡፡ ኃጢአት ሥር ሰዳና ሰፍታ ከመቸገራችን በፊት በችግኝ ደረጃ ላይ እያለች ነቅለን መጣል ቀላል ነውና፡፡ 

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

https://t.me/zena_tewahido
✝️  በቅዳሴ ጊዜ ወንጌልን ስንሳለም ምን ማለት ይገባል?

በቅዳሴ መሐል ወንጌልን ስንሳለም
-  የሚያሳልመው (ወንጌሉን የያዘው ) ወንጌል ቅዱስ ይላል
- ተሳላሚው ነአምን በቃለ ወንጌልከ ቅዱስ ይላል

ሥርዓተ ቅዳሴ አንድምታ ላይ ይህንን ይላል :-  ካሁኑ ወንጌሉን አንብቦ በጨረሰ ጊዜ
ነአምን በቃለ ወንጌልከ ቅዱስ ፥ ቃሉን እናምናለን ለትእዛዙ እንገዛለን እያሉ ካህናት
ዲያቆናት ከነሱ ቀጥለው ሕዝቡ ሁሉ በየማ
እርጋቸው ወንጌልን ይሳለሙት፡፡

➙ ይህም ፦ " ደቂቅየ ተፋቀሩ / እርስ በርሳችሁ ተፋቀሩ "  ባላት በወንጌል አንድ ነን ስንል ነው።


✝️ ወንጌልን ሲሳለሙ ክንብንብን ማውለቅ እንደሚገባ ሥርዓተ ቅዳሴ ላይ ይህንን ይላል :-

" ከሳቸው ወገን አንዱም አንዱም ራሱን ይግለጽ ሴት ብትሆን ሰርመዲዋን ክንብንቧን ታውርድ ፡፡ ካህን ቢሆን ህባኔውን ቀጸላውን መጠምጠሚያውን ንጉሥ ቢሆን ዘውዱን ያውርድ፡፡ ይህንን ማድረጋቸው ትምሕርተ ትሕትና ነው ።  እንደ ገድል አድርጎ እንደ አክሊለ ሦክ አድርጎ ከራሱ ያደረገ ቢሆን ከራሱ ገመድ ያደረገ ቢሆን ራሱን በመላው ጸሎት በመላው ቅዳሴ መግለጽ የማይቻለው ቢሆን እንኳን ወንጌል በሚነበብበት ጊዜ ግን ዘወር አድርጎ  ራሱን በመግለጽ መሳለም ይገባዋል ፡፡

✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ

https://t.me/zena_tewahido
✝️ ከመስከረም 1 ጀምሮ እስከ መስከረም 7 ድረስ ያለው ሳምንቱ (ወቅት) ዮሐንስ ይባላል፡፡
-> እነዚህ ሰባቱ ዕለታት ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የተሰጡ የጸጋው (ሀብቱ ) ምሳሌዎች ናቸው። እነዚህም፦
- ጻድቅነት
- ስብከት
- ክህነት
- ብህትውና
- ድንግልና
- ሰማዕትነት
- ትንቢት ናቸው።

->  የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓላት ፦

መስከረም 26፡ በዓለ ጽንሰቱ
ሰኔ 30፡ በዓለ ልደቱ
መስከረም 2፡ ራሱ የተቆረጠበት
መስከረም 15፡ ነፍሱ ከራሱ የወጣችበት
የካቲት 30፡ ራሱ የተገኘችበት
ሰኔ 2፡ ራሱ በኤልሳዕ መቃብር የተቀበረበት
መስከረም 1፡ ርእሰ ዐውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ


-> .የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች
1.ነቢይ
2.ሐዋርያ
3.ሰማዕት
4.ጻድቅ
5.ካሕን
6.ባሕታዊ/ገዳማዊ
7.መጥምቀ መለኮት
8.ጸያሔ ፍኖት (መንገድ ጠራጊ)
9.ድንግል
10.ተንከተም (የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ)
11.ቃለ አዋዲ (አዋጅ ነጋሪ)
12.መምሕር ወመገሥጽ
13.ዘየዐቢ እምኩሉ (ከሁሉ የሚበልጥ)

=>  መስከረም ሁለት ምትረተ ርዕሱ ነው :: ከበረከቱ ያሳትፈን።
በታመምህ ጊዜ ድካም ይሰማሃል፤ ብርታት ያንስሃል፤ ፊትህም ይገረጣል፡፡ የዕለት ተዕለት ሥራዎችህን በአግባቡ ማከናወን ይሳንሃል፡፡ በዚህ ጊዜም ሕመምህ ምን ያህል እንደበረታ ሰዎች ያስተውላሉ፤ መታከም እንደሚገባህም ይነግሩሃል፡፡ ስለዚህ ወደ ሐኪም ትኼዳለህ፡፡ ወደ ሐኪም የምትኼደው ግን ሐኪሙ ምን እንዲያደርግልህ ነው? አሁን ለሚሰሙህ ስሜቶች የሚሽሩ መድኃኒቶችን እንዲሰጥህ ነው፡፡ ኾኖም ይሰሙህ የነበሩ ስሜቶች ቢሻሉህም ሰውነትህ አሁንም እንደ ደከመ፣ ፊትህ እንደ ገረጣ ከቀረ፣ የዕለት ተዕለት ሥራዎችህንም በአግባቡ ማከናወን ከተሳነህ፥ በተሰጠህ ሕክምና ደስተኛ ትኾናለህን? አትኾንም!

እውነታው ምንድን ነው?” ስንል ወደ ሐኪሙ የኼድከው የበሽታህን ምንጭ ለመታከም ሳይኾን የበሽታህን ምልክቶች ለማስታገሥ ስለ ኾነ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ የበሽታህ መንሥኤ እስካልታከመ ድረስ የበሽታህ ምልክቶች ለጊዜው ቢታገሡም ቅሉ፥ ፈጽመው ሊወገዱ እንደማይችሉ ሐኪሙ በደንብ ያውቃል፡፡

በክርስቶስ ክርስቲያን፣ በወልድ ውሉድ፣ በመንፈስ ቅዱስም መንፈሳውያን የተባልን እኛም እግዚአብሔር መንፈሳዊ በሽታችንን እንዲያስወግድልን እንሻለን፡፡ እንደ እውነታው ግን ብዙዎቻችን ወደ እግዚአብሔር ቀርበን እንዲያስወግድልን የምንሻው ምልክቶቹን ነው፡፡ ለምሳሌ ችግርን፣ ኀዘንን፣ ቀቢጸ ተስፋንና የመሳሰሉትን እንዲያርቅልን እንፈልጋለን፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ የእነዚህ ምክንያት የኾነውንና ሥር የሰደደውን፣ ዋና ምክንያትም የኾነውን መንፈሳዊ በሽታችንን ሳይሽር እነዚህን ምልክቶች ሊያርቅልን አይፈልግም፡፡ ችግር የሚኾነውም ይህን ጊዜ ነው፡፡ ምልክቶቹን እንዲያርቅልን ስንደክም፥ ወደ ውሳጤያችን ገብቶ የችግሩን ምንጭ ሊያርቅልን የሚችለውን የእግዚአብሔርን ጸጋ (ኃይልን) አጥብቀን እንቃወማለንና፡፡ በውሳጤያችን የተሸሸገውን በሽታ ማስወገድ አንፈልግም፡፡ አመለካከታችን እንዲለወጥ አንፈቅድም፡፡ እውነተኛ ለውጥ የሚመጣውና አማን በአማን የምንታከመው ግን የልባችንን ውሳጤ ለእግዚአብሔር ስንከፍትለትና እርሱም በዚያ በመረቀዘው ቁስላችን ላይ ጽኑ መድኃኒት ሲያስርልን ነው፡፡ እንዲለወጡ የምንፈልጋቸው ምልክቶች በእርግጥም የሚለወጡት ይህ በልባችን ውስጥ የተደበቀው መንፈሳዊ በሽታችን ሲጠፋ ነው፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

https://t.me/zena_tewahido
Forwarded from ዘ-ተዋሕዶ ቦት
1⃣7⃣ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ