✿✟ የ҈ ዳ҈ ዊ҈ ት҈ ዜ҈ ማ҈ ✟✿
15.3K subscribers
226 photos
22 videos
51 files
444 links
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮╭━─━─━─
ገና እንዘምራለን
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት @Zemaryan
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯╰━─━─━─
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት ጥያቄ> creator ለማግኝት @kidanemiherat_bot
@yita21
@Binyam
https://youtu.be/Fz4JARE6-DI
Download Telegram
🌸🍂 ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ብር አዘዛት

🌸 #ቅድስት_አፎምያም የከበረ መልዘመብረቅ
ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ሚካኤል 🍂🌸
#ሰኔ_12

🍂 የከበረች አፎምያ ያረፈችበት ዕለት ነው
እግዚአብሔርን የሚፈራ የአንድ ሰው ሚስት ነበረች ።
ባሏ ብዙ ምጽዋትን ያደርግ ነበር በየወሩም ሦሶቱን በዓላት ያደርግ ነበር ፤ እነዚህም ፦
* በ29 /የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት መታሰቢያ /
* በ21 /የቅድስት ድንግ ማርያምን /
* በ12 / የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤልን /

🍂 የሚሞትበት ቀን በደረሰም ጊዜ እርሱ ያደርገው የነበረውን ምጽዋት እንዳታስታጉል እነዚህንም 3 በዓላት እንድታከአክ የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አስሎ ይሰጣት ዘንድ ባሏን ለመነችው። እርሱም አደረገላት

🍂 እርሱም ካረፈ በኋላ ያደርገው የነበረውን እያደረገች በቅድስና ሕይወት ጸንታ ትኖር ጀመር። ጸላዔ ሠናይ የሆነ ሰይጣን ስለቀናባት ይፈትናት ዘንድ መነኩሲት ተመስሎ ፤ ባልሽ በስጋ ተለይቶሻል ከእንግዲህ ምጽዋትን አታድርጊ፣ ሌላ ባል አግብተሽ በደስታ ኑሪ እያለ ክፉ ምክርን ይመክራት ጀመር ።

🍂 እርሷም ሌላ ላላገባ ለእግወዚአብሔር ምያለው ፤ ርግቦችም እንኳን ከአንድ በቀር ሌላ አያውቁም ፤ አለችው ምክሩንም እነዳልተቀላት ባወቀ ጊዜ መልኩን ለውጦ ጮኸባት በሌላም ቀን እመጣለው ብሏት ጥሏት ሄደ።

#በሰኔ_12 ቀንም የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ስታከበር ሰይጣን አንደለመደው ይፈትናት ዘንድ መልአክ ተመስሎ ወደርሷ መጣ ። የቀደመ ክፉ ምክሩን ከመጻህፍት እየጠቀሰ ያስታት ዘንድ ይነግራት ጀመር። የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክስ የያዝከው በትረ መስቀልህ ወዴት አለችው።

🍂 #ሥዕለ_ቅዱስ_ሚካኤልን አምጥታ ብታሳየው ፤ ወደ ከበረ ሚካኤል ብትለምን ፈጥኖ ደርሶ አዳናት። ዲያብሎስንም ከእርሷ አሳደደው።

🌸 የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ቅድስት አፎምያን አንቺ በዚህች ቀን ከዚህ ዓለም ወደማያልፈው ዓለም በምት ትለያለሽና ሄደሽ ስራሽን አከናውኚ ። እነሆ እግዚአብሔር ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡና ያልታሰበውን አዘጋጅቶልሻልና አላት ሰላምታም ሰጥቷት ወደ ሰማይ ዓረገ ።

የበዓሉንም ሥርዓት በሚገባ ፈጸመች ።
ኤጲስ ቆጶሱን ካህናቱን ወደ ጠራች እነርሱም መጡ ።
ገንዘቧን ሁሉ ለዳያን መጸወተች

ከዚህም በኋላ ቆማ ጸለየች
የከበረ መልአክ የሚካኤልን ሥዕል ከፊቷ አደረገች
በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ
#በሰኔ_12_ቀንም_አረፈች

🌸 አፎምያን ከመከራ ከመከራ ነፍስ የታደጋት
የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃ አይለየን🌸🙏

@zemaryan
@zemaryan