Yop Poem ️
4.96K subscribers
84 photos
5 videos
25 files
58 links
፨Yop Poem
አዳዲስ እና የቆዩ ግጥሞችና ወጎችን በቀላሉ ያገኙበታል። 🤲
እርስዎም የግጥም ተሰጥዖ ካልዎት መልቀቅ ይችላሉ።👐
Our main channale :- @Utophiainfo

ቻናላችንን #share ያድርጉ👍

for promo & cross 👉 @Yared642
Download Telegram
ግጥም ልፃፍልሽ🤗


ሹመት ቀባብቼ
ከነገስታት እኩል ዙፋን ባልሰጥሽም
ከአየር ጋር ተንፍሼሽ
ሁሉምጋ ማገኝሽ ነፍስ ባላረግሽም

ኮከብ ባልሰርቅልሽ
ጨረቃ ባላገኝ ምታስሪው ከአንገትሽ
ከአራዊት ታግዬ
የዱር ፍሬ ባለቅም ጠብ የሚል ከአንጀትሽ

እሳት ባልጨብጥም ባህር ባልከፍልልሽ
ፍቀጅልኝና
መውደዴን የሚገልፅ ግጥም ልፃፍልሽ!

እንደሰው ወደድኩሽ እንደህፃን ሳሳሁ
ሳቅሽን ስስቀው በልክሽ ተሰፋሁ🙈

እንደልቤ አፈቀርኩ እንደጅል አሳቅሽኝ
አንድ ጊዜ ባሰብኩሽ ደጋግመሽ ናፈቅሽኝ🥹

ቤቴን አደማምቂ ነይ ግጥም ሁኝልኝ
ነፍሴን አሳምሪ ነይ ዜማ ሙይልኝ
በቆንጆ ንግስት ስር ዘመኔን ምሪልኝ😍

ከቀለም አ'ብሬ ይሄንን መልክሽን
       ከንፁህ ሸራ ላይ ችየ እንኳን ባልስልሽ
እስኪ ምንአለበት
ስለእዚህ ውብ ሳቅሽ ግጥሞ ብፅፍልሽ

ለሰጠሽኝ ደስታ ወጥቼ ባልፎክር
አሁን ምናለበት
በጠያይም ቃላት ስንኝ ብደረድር

ለዘመኔ ድምቀት
ለሰበብነትሽ ሻማ ባላበራ
ልክ አይደለሁም ወይ
ለምስክርነት ቃላትን ብዘራ

ይመስክሩ ሁሉም
ኮከብ ከላይ ሆኖ አበባ ከመሬት
አላየንም ብለው
ያንቺ አይነት ፍቅር ሴት

የጧት ፀሀይ እዪ ታምራለች እንዳንቺ
ለመልካም ምኞቴ እቺን ግጥም እንቺ😘

          (እንኳንም ወለዱሽ😍)
@Yoppoem
ምጨነቅ ይመስልሻል?

አንድ አሮጌ የአፍሪካ መሪ ሞተ ቢሉ ሞቱን ?
ህዝብ ግልብጥ ቢል ትቶ ያደረገውን ?
ከንፈሬን መጥጬ  ይመስልሻል ማዝን?

አንድ የአፍሪካ መሪ ከወንበር ተቀምጦ ስላመሼና
አገሩም ስርአቱም አስረጅቶ አረፈደና
ቂጡ  ስለተላ ሱፉ እንደላላ ከዛው እንደሸና

(ማስብ ይመስልሻል)..አቦ ጉዳዬ😏....

ደሞስ መሪው ሁሉ
የእንግሊዝ ቶክሲዶን መነፀር ሰክቶ
አበባ ቢታቀፍ ከአስክሬኑ ታይቶ
ስለተነሳ...የሚዲያ ፎቶ

(..ምደነቅ.. ይመስልሻል😏 )

ፓርላማ ላይ ቢሰበሰቡ...
ዝግ ምክክር በአዋጅ ቢቃለቡ ፣
እዛው ተኝተው ሲጨበጨብ ነቅተው ስላጨበጨቡ ።
ዜና ላይ ወጠው ሀይለ ቃል ስላረበረቡ ፣
ይመስልሻል የኔ ልብ ማሰቡ ?

አይደለም እናቴ
የኔ ጭንቀት ሀዘን ነው የኔ ዕንባ አንታርቲካ
በውስጥ ሀዘን ሞልቶ በበርሃ የተለካ

የኔ ጭንቀት...
አንዲት እናት  አርግዛ  ሳትገደል
በሰላም ማዬት ነው የአራስ ጨቅላን ገድል

የኔ መደነቅ የኔ ይላቅ...
ሰው መንገስ አቁሞ መለኮታዊ ቢላክ
በምዕናብ መዳከር በህልም ሰላም ነበር የኔ  ስላቅ ¡?

ወከባ ስለበዛ ሱፍ የለበሰ አዋቂ ቢመስልም
ባታውቂኝ እንኳ ስለብልጭልጭ ሀገር ምጨነቅ አልመስልም
'
'
አቦ ጉዳያቸው

@Yoppoem
'ለምን አልፈጠርክም.. ?'

(ኤፍሬም ስዩም)

ሳይደምን ሳይዘንብ ሳይጨልም ሳይነጋ ፤
ምድርና አርያምን ቀድሞ ሳትዘረጋ ፤
ፊተኛው ኋለኛው አልፋና ኦሜጋ ፤
እንዴት ነበር ኑሮህ ስፍራህስ ምኑጋ ?
ምንት ሳይኖር በፊት ኢምንት እያለ ፤
ያሁኑ ዙፋንህ ኪሩቤል ከሌለ ፤
ያኔ ያንተ ሀገር ከየት ነበር ያለ ?
ሀገርህ እንዳልል ያኔ ሀገር የለም ፤
ምንም ሳይኖር በፊት ስትኖር በምንም ፤
በእግዚአብሔርነትህ እግዜር ከሌለብህ ፤
ሁሉንም አዋቂ አንተ ብቻ ከሆንህ ፤
ስንት ዘመን ሆነህ ሆነህ ከተገኘህ ?
ፍጥረትስ ነበረ ከመፍጠርህ በፊት ?
ቀድመው የተሰሩ ከሰው ከመላዕክት ?
ካልነበረም ፍጥረት ፤
የዘመናት አምላክ የዘመናት ንጉስ ጥያቄዬን መልስ ፤
ለምን አልፈጠርክም እስክትፈጥር ድረስ ?
.



@Yoppoem
ፍቃዱ ግርማ

    አያድርስ ከቶ

እማታገኝውን ሺህ ግዜ መናፈቅ
ለማይሆነው ነገር ሺህ ግዜ መጨነቅ
እራስክን ከማጣት ምንም አታተርፍም
ዝብርቅርቅ ባለበት በዚህ ከንቱ አለም
አይጣልብህ እንጂ አያድርስ ከቶ
በዚች አለም ኑሮ ማንስ ያቃል ረክቶ ። ?
  
        ማንም

@Yoppoem
Messages in this channel will no longer be automatically deleted
Asmarino
Dawit Tsige
❤️❤️❤️
@Yoppoem
Forwarded from Quality button
ፎቶዋቹ  ባማረ መልኩ #edit እንዲደረግ ከፈለጋ


Editer mirgo
Forwarded from Private
🎉5M free ለ 15 ሰው ቶሎ Start ያደረገ ብቻ ነው Gift ሚሰጠው 5M 🎁🎁 ቶሎ ብላቹ Start በሉ 👇

START START START

https://t.me/preton_drop_bot?start=271e20ea-0162-474f-9aa0-a8c4b4a6b278
Forwarded from Quality button
ፎቶዋቹ  ባማረ መልኩ #edit እንዲደረግ ከፈለጋ


Editer mirgo
Forwarded from 𝕛o̸n̸a̸h̸𓃵
💠 ይህ በጣም አሪፍ ቦት ነው ሰው በመጋበዝ Ton❄️ መስራት ትችላላችሁ

🌀 0.5 Ton ስደርሱ ማውጣት ይቻላል

💰 1 ሰው ስትጋብዙ 0.0075 Ton ይሰጣቹሃል

💠 አሁኑኑ ጀምሩ 👇👇👇

https://t.me/preton_drop_bot?start=6e6c8142-c490-415f-8154-0ede7c803ff0