Yop Poem ️
7.75K subscribers
89 photos
6 videos
25 files
61 links
፨Yop Poem
አዳዲስ እና የቆዩ ግጥሞችና ወጎችን በቀላሉ ያገኙበታል። 🤲
እርስዎም የግጥም ተሰጥዖ ካልዎት መልቀቅ ይችላሉ።👐
Our main channale :- @Utophiainfo

ቻናላችንን #share ያድርጉ👍

for promo & cross 👉 @Yared642
Download Telegram
የማለዳ ራእይ!
(በእውቀቱ ስዩም)

ናፍቆትሽ ፀናብኝ
ብየ ስልክልሽ
‘አይዞህ ' አይባልም
መከሰት ነው እንጂ በገሀድ ወይ በህልም !
ካጨሽ አሰናብቺ
ትዳር ካለሽ ፍቺ
ለኔ ለምመኝሽ ሁሉን ነገር ስጪ
የህሊና ቀጪ
የልቦና ስሜት
ይሉንታና ሀሜት
ያገር ሰው ሽሙጥም
ከምኞቴ አይበልጥም ::
ተሊቀመላኩ
ክንፍ ተበድረሽ
ነፋስ ቀድመሽ በረሽ
ባለሁበት አገር
እንደ ሸዋዚንገር
ብረት ለበስ ጡንቻ
ባንድ ርግጫ ብቻ
የቤቴን በር ሰብረሽ
ዐይነ ርግብሽ ወድያ
ቀሚስሽ ወደ ላይ
ወደኔ በጥድፍያ
ወዳልጋው በዝላይ
በጀርባየ ሁኘ
ከእግሮቼ መካከል የጠላ ምልክት
አንቺ ጆሮ ሆነሽ
እኔ ሎቲ ሆኘ-ተጣጥሞ ስክት !
እንዲህ እያሰበ ገላየ ሲቸገር
መጣሁ ትያለሽ ስል
“አይዞህ “ ብሎ ነገር፤
የማለዳ ራእይ፤ ምኞቴን በማመን
በገሀድም ይሁን፤ ወይም በሰመመን
አሳትፊኝ አልሁ እንጂ
ከገላሽ በረከት፤ ከሙቀት ከለዛው
የቃል ምፅዋትማ ሞልቷል በየታዛው!



t.me/Yoppoem
የውበት ጀርባው
(በእውቀቱ ስዩም)

   ላንተ የሚታይህ፤ የሚያምር ፈገግታ
ያበባ  ጉትቻ
ላንተ እሚታይህ ውብ ገፅታ ብቻ
ጥርሷን ጉራማይሌ፤ የተነቀሰች ቀን
ያየቺው መከራ፤ ያየቺው ሰቀቀን
የጆሮዋን ጫፉን ፤ በሾህ  ስትበሳ
የበላችው ፍዳ ፤ ያየቺው አበሳ
የዋጠችው ህመም፤  ከሬት የመረረ
የቀመሰው ማነው፤ከሷ በስተቀረ?  
ከያንዳንዱ ታላቅ ፤ ውበት በስተጀርባ
  ሲንዠቀዠቅ ኑሯል ፤ ብዙ ደምና እንባ
ይሄም ታላቅ ዜማ
ይሄም ታላቅ ስእል
ይሄም ታላቅ ተረት
ይሄም ታላቅ ድርሰት
ከፊትህ አልቆመም፤ እንደመና ወርዶ 
ስቃይ ያቃልላል፤ ከስቃይ ተወልዶ ፤ 👍


|በዕውቀቱ ስዪም|

t.me/Yoppoem
"ሆጵላስ..!"

ይህ ቃል የተፈጠረበት አጋጣሚ  አንድ ፈረንጅ በሀገራችን የድንጋይ ናዳ መንገድ ይዘጋበታል..!

ከኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ድንጋዩን ከዘጋው መንገድ ለማስወጣት አብሮ መግፋት ይጀምራል..!

እየገፋም "hopeless..!" (ተስፋ የለሽ..!) ይላል..!
ይህንን በሰሙት የአበሻይቱ ልጆች አማካኝነት "ሆጵላስ..!" ማበረታቻ ሆና በቋንቋችን ውስጥ ተፈጠረች..!

©ዘነበ ወላ ፣ መልህቅ

t.me/Yoppoem
ተአምር ፈልቋል በየመንገዱ

💥💥💥💥💥💥💥💥💥

  ዐይኔን ጨፍኜ -እስከምከፍተው
ስንቱ ታሪክ ነው- የተከሰተው
አፌ ላይ ሳይደርስ -  ያፈስኩት ቆሎ
ስንቱ ተተክሏል- ስንቱ ተነቅሎ  
በፊት በር ሲዘልቅ -ብስራት አብሳሪ
በጉዋሮ ገብቱዋል- መርዶ ነጋሪ ::

እባብ በረረ- ያለ ልማዱ
ርግብ መሬት ላይ -ሲሳብ በሆዱ
ተአምር ሞልቷል-  በየ ሰከንዱ
ተአምር ፈልቋል- በየመንገዱ
አንዴ ከመላክ- አንዴ ከሰይጣን
ለመደነቂያ ጊዜ ነው  ያጣን



t.me/Yoppoem