Yop Poem ️
5.38K subscribers
96 photos
5 videos
25 files
80 links
፨Yop Poem
አዳዲስ እና የቆዩ ግጥሞችና ወጎችን በቀላሉ ያገኙበታል። 🤲
እርስዎም የግጥም ተሰጥዖ ካልዎት መልቀቅ ይችላሉ።👐
Our main channale :- @Utophiainfo

ቻናላችንን #share ያድርጉ👍

for promo & cross 👉 @Yared642
Download Telegram
በኦንላይን አማራጭ ካሉበት ሆነው ይማሩ፤ ሁልጊዜም ምዝገባ ሁልጊዜም ትምህርት አለ!
ይህን መልእክት ሌሎችም ያጋሩ !
በማኅበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን
ፌስቡክ ፦ https://www.facebook.com/AmdehaymanotSundayschool/
ዩትዩብ ፦ https://youtube.com/channel/UC_USHmHSlXg_-g0wwsPcQCg
ቲክ ቶክ፦ https://vm.tiktok.com/ZML9jVNJW/
ቴሌግራም፡ https://t.me/Amde_Haymanot_Sunday_School
◦◦●◉ የግጥም ጥም

ግጠም ግጠም ሲለኝ ስገጥም ስገጥም፣
ይኸው ደርሻለኹ እስከ... የግጥም ጥም።
አልገጥምም አልኩና ብቀመጥ አርፌ፣
ይወጋጋኝ ጀመር ውስጤ እንደ መርፌ።
ደግሞ ልጻፍ ብዬ አቅጄ ብነሣ፣
የትኛውን ትቼ የትኛውን ላንሣ?
      ብዬ ስወላውል
ሳድር... ደግሞም ስውል

ግጥም ማ'ነሽ አንቺ ብዬ ብጠይቃት፣
       ዝም አለችኝ...
ለካ ይህቺም ግ ጥ ም ናት
በዝምታም መልስ ያላት

ቢጽፉሽ ቢጽፉሽ አታልቂም እያልኳት።
ግጥምን እሷን ነው የጻፍኳት
ንገሯት ... ገጠምኳት

ለ ግ ጥ ም ግጥም ገጠምኩላት!

@Yoppoem
!!!!

ፈገግ ብየ አልፌው ተታለለ ስንቱ
አሁን ግን ደከመኝ
ለጠየቀኝ ሁሉ ደህና ነኝ ማለቱ
አጣጥፎ ጥሎኛል ችሎ ባይሰብረኝም
ከመሞት በልጦብኝ መኖር አይስበኝም
እኔም ህልሜን አልተው እሱም አይደረስ
                        ...ምናምን አትበለኝ
አይጥለኝም እንጂ እኔም ህመም አለኝ

ይልቅ እሱን ተወው..
አባብሎ ያቀፈህ ምቾትህን እርሳው
ብሶትህን ጣልና ብርታትህን አንሳው
ዳህ ተራመድ ሩጥ ህልምህን ብለጠው
ነገህ ላይ ለመቆም ትናንትን እርገጠው
በትልቁ አልመህ ትልቅ ነገር ሥራ
ከመውደቅህ በላይ ተስፋ መቁረጥ ፍራ

ግድየለም ሞክረው እንደው ባይመስልህም
መሮጥ እንደመቆም ቶሎ አያዝልህም🥵
ያስጎመዠ ሁሉ አይበላም ጣፍጦ
አንተ ህልምህን እመን
ማረፍ አያሾምም ከድካምህ በልጦ

ውደቅ ጣር ተነሳ ተጋጋጥ ይድከምህ
እንቅልፍህን እጣው ለነገ ላይጠቅምህ
ሚያባብልን ሙቀት
ሚሸፋፍን ምቾት ወደዛ ጣልና
ለራስህ አሳምን
አልችልም አትበለው ሞክር እንደገና
በብዙ ስትቆፍር ባንዱ ታገኛለህ
    ድል የሚሰጥህን የህይወትን መፍቻ
ካንተ ሚጠበቀው
     የላዩን ጌታ አምኖ መጣር መጋር ብቻ!


         @Yoppoem
Forwarded from ❤Ⓢⓔⓛⓘⓝⓐ🥰
Forwarded from .
Forwarded from .
Audio
Yop Poem ️ pinned an audio file
Forwarded from ❤Ⓢⓔⓛⓘⓝⓐ🥰
የ 18 አመቷ ወጣት እዉነተኛ አሳዛኝ ታሪክ ክፍል 2
Forwarded from ❤Ⓢⓔⓛⓘⓝⓐ🥰
የ 18 አመቷ እዉነተኛ አሳዛኝ ታሪክ ክፍል 3...
Forwarded from ❤Ⓢⓔⓛⓘⓝⓐ🥰
ክፍል 4
Forwarded from ❤Ⓢⓔⓛⓘⓝⓐ🥰
የ18 አመቷ ወጣት እዉነተኛ አሳዛኝ ታሪክ ክፍል 5
የዜግነት ክብር
     ተምሬ ያደግሁት...
የዜግነት ክብር በማለት ዘምሬ
   class የምገባ...
ስለ ሰንደቅ ክብር ብዙ ተመክሬ
ከክላስ ውስጥ ደግሞ...
የቀለሙን ትርጉም በ civics ተምሬ
   እንዲህ ነው ያደግሁት...
  ሶስቱንም ቀለም...
በወርድ እና እርዝመት በእኩል ቀምሬ
እንዲህ ነው ያደግሁት...
.ልዩነታችንን እንደ ጌጥ ቆጥሬ
እንዲህ ነው ያደግሁት...
የክልልን ትርጉም
ብዙውን ሳላውቀው ብዙ ሳልረዳ
አስራ አንዱን ክልል
ሁሉንም አይቼ እንደ እናቴ ጓዳ
ሁሉን ቋንቋ ልወርስ
ሀሳቤን ስሸክፍ ምኞቴን ስነዳ
እንዲህ ነው ያደግሁት...
በሶስቱ ቀለም በአንድ ሰንደቅ ታጥሬ አረንጓዴ...ቢጫ...ቀይ
በልቤ ዙፋን ላይ በእኩል ቀምሬ
       ታድያ ምነው ዛሬ
አረንጓዴ ቢጫው ቀለሙ እየጠፋ
  ቀዩ ቀለም ብቻ ከሰንደቁ ሠፋ
የዜግነት ክብር...

                     
@Yoppoem
Forwarded from ❤Ⓢⓔⓛⓘⓝⓐ🥰
Forwarded from ❤Ⓢⓔⓛⓘⓝⓐ🥰
Forwarded from ❤Ⓢⓔⓛⓘⓝⓐ🥰
ሊዘጉብኝ ሲታገሉ ለማመንመን የኔን
                  መክሊት
በቀን ፀሀይ ያበረቱኝ በሩን ገፉ ያው
                   በለሊት
  ፍሙን እሳት አመድ ሊያሹ ወዳጅ
        መስለው ሲጠጋጉኝ
በድን አርገው ለመጣሉን የዋሁ እኔ
               መች አወኩኝ !

ግን ባነንኩኝ
ሊሰብሩኝ ሲል ደነደንኩኝ
ማን አለው ብለው በድቅድቅ ሲርቁኝ
            ጋኑን ከርችመው
ከፍቶታል የልቤን መስኮት እምነትን ከስሬ
                  አክርመው !

@Yoppoem
#code01

1500
Only 1000 birrr
Cargo suri & T-shirt

Inbox
@Yared642
አምላክን አመስግን
       

በምግብ እጦት ቢገረጣ ፊትህ
ልክ እንደአውሬ ሰው ሁሉ ቢሸሽህ
ቤተሰቤ ያልከው እንደባዳ ቢያይ
የልብ ጓደኛ ቢሆንም ገዳይ

የለበስከው ልብስህ ከብርድ ባያድንም
የምቆጥረው ገንዘብ ከኪስህ ባይኖርም
ምትመኘው ነገር ሆኖቢቀር ቅዠት
ያፈቀርካት ላንተ ክብር ባይኖራት

ሞላውትም ያልከው ሁሌም ቢጎልብ
በጎ ያልከው ነገር ክፋ ቢመዝብ
እጅ ስትዘረጋ ሰጪ ባታገኝም
የሰጠከው ሁሉ ምላሽ ባይሰጥህም

ጊዜ ያንተ ጠላት ሆኖ ቢዋጋህ
አምላክ ነው ብለህ አትዘን በድልህ
ይቺን እንድታነብ እድል የሰጠህን
ጎንበስ በልና አምላክን አመስግን

              ተ መ ስ ገ
n

@Yoppoem