የገጣሚያን ማኅበር
19.1K subscribers
244 photos
13 videos
11 files
511 links
እዚህ ማኅበር ውስጥ የሚካተቱ የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች፦
👉መንፈሳዊ ግጥም
፦ስለ ሀገር ፦ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ፦ስለ ወንጌል ፦ስለቤተክርስቲያን👉መነባነብ
👉ግጥማዊ ትረካ
ይቀላቀሉን
Channel👉 @Ye_Getamian_Mahiber
Group👉 @yegetamianmahiber
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA
Download Telegram
እኔ ምለው ወገኖቼ 🤔

ሁላችንም ሙሴ ከሆንን የማይታዘዘው የእስራኤል ህዝብ ማነው?
ሁላችንም ዳዊቶች ከሆንን የዳዊት ጠላቶችስ እነ ማን ናቸው?
ሁላችንም ያዕቆቦች ከሆንን ላባ ማነው?
ሁላችንም እውነተኞች ከሆንን በውሸት ያቀፈን ሸንጋይ ማነው?
ሁላችንም ዮሐንሶች ከሆንን የካደው ጴጥሮስ ማነው?
ሁላችንም ጳውሎሶች ከሆንን ዴማስ ማነው?
ሁላችንም የተሸጠው ኢየሱስ ከሆንን የሸጠው ይሁዳስ ማነው?

ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገረን አያመቻምችም።

አንዳንዶቻችን ግን የሚመቸንን ጥቅስ እና ታሪክ ለራሳችን ማድረግ እንወዳለን።

#ለምሳሌ

”እውነት የሚናገሩ ከንፈሮች ለዘላለም ጸንተው ይኖራሉ፤ ሐሰተኛ አንደበት ግን ለቅጽበት ያህል ብቻ ነው።“
ምሳሌ 12 : 19

ይሄ ጥቅስ

''እውነት የሚናገሩ ከንፈሮች ለዘላለም ጸንተው ይኖራሉ፤ ''
ይሄ ለኛ የተጻፈ

''ሐሰተኛ አንደበት ግን ለቅጽበት ያህል ብቻ ነው።“

ይሄ ደግሞ ለሌላ ሰው የተጻፈ እና እኛን የማይመለከት ይመስለናል።

ብናስተውል መልካም አይደለምን?

የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነው።
ያጽናናል፣ ይፈውሳል፣ ያበረታል፣ ሃያል ያደርጋል ደግሞም ይመረምረናል፣ ይቆጣናል፣ ይገስጸናል፣ ይመልሰናል፣ ወደ ትክክለኛው መንገድ ይመራናል እንጂ ሁሌም አያባብለንም።

ቆንጆ ቆንጆው የኛ እና ጠንከር ጠንከር ያለው ለጎረቤት አንዳንዴ ለአሽሙር ስንፈልገው የተጻፈ አይደለም።

"12፤ የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤"
(ወደ ዕብራውያን 4:12፤)

በቀኝ ዋሉ! 😉
Leah Jacob