የገጣሚያን ማኅበር
17.2K subscribers
187 photos
9 videos
10 files
278 links
እዚህ ማኅበር ውስጥ የሚካተቱ የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች፦
👉መንፈሳዊ ግጥም
፦ስለ ሀገር
፦ስለ እግዚአብሔር ፍቅር
፦ስለ ወንጌል
፦ስለቤተክርስቲያን
👉መነባነብ
👉ግጥማዊ ትረካ
ይቀላቀሉን
Channel👉 @Ye_Getamian_Mahiber
Group👉 @yegetamianmahiber
YouTube https://www.youtube.com/@Poetscoun
Download Telegram
17k Followers Thank You🥰🥳🥳 20k soon...
“እናት ልጅዋን እንደምታጽናና እንዲሁ አጽናናችኋለሁ፥ በኢየሩሳሌምም ውስጥ ትጽናናላችሁ።”
  — ኢሳይያስ 66፥13

Say Amen🥹
የመኖሬ ትርጉም

ምንድነው መኖሬ፣ምንድነው ትርጉሙ፤
ከኢየሱስ ትዕዛዝ ጋር፣መኖር ሳይስማሙ፤
አልታዘዝ ብሎ፣እንዲያው መዋተቱ፤
ሲወጡ ሲገቡ፣እንዲያው መተበቱ፤
ምንድነው ትርጉሙ፣የመኖሬሚስጥር፤
የሞተልኝ ጌታ፣በኔ ህይወት ሳይከብር፤

እድሜዬን በሙሉ፣እሱን ካላከበርኩ፣
ከአለም ኮተት ጋር፣ተስማምቼ ከኖርኩ፣
ምንድነው ትርጉሙ ፣ምንድነው መኖሬ፤
በማያገባኝ ላይ፣እያወራሁ ወሬ፤
እንዲው ማውራት ብቻ፣የለው እኮ ፍሬ።
የመኖሬን ትርጉም፣ዝምብዬ ሳስበው፣
የተተወልኝን፣ዞር ብዬ ሳየው፤

የመኖሬ ትርጉም፣የመውጣት መግባቴ፤
ምክንያት ለመሄዴ፣ ለመመላለሴ፤
ኢየሱስ እኮ ነው፣የከፈለው እዳ፤
በመስቀል ተሰቅሎ፣ለኔ እየተወጋ፤
በደም የሚተመን፣የከፈለው ዋጋ።

አሁንማ ገባኝ፣የመኖሬ ትርጉም፣
ተገዝቻለሁኝ፣የራሴ አይደለሁም፣
የገዛኝን እሱን፣በህይወቴ ላከብረው፣
ከአለም ኮተት ይልቅ፣እሱን እንድወደው፣
ጉብዝናዬን ሁሉ፣ለጌታ እንድሰጥ፣
ከሀጥያት እርቄ፣ራሴን እንድለውጥ፣
የህይወቴ ዋና፣አድርጌ እንድሾመው፣
ለዚች አለም ሞቼ፣ለርሱ እንድኖር ነው።

@Meta_01234

📥Group :  @yegetamianmahiber
📥Channel : @Ye_Getamian_Mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
      🔺🀄️🀄️ሉን🔺
           Join us
         🎯     ♡         ❍ㅤ    ⌲ 
ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

    
🥰
እኔ ምለው ወገኖቼ 🤔

ሁላችንም ሙሴ ከሆንን የማይታዘዘው የእስራኤል ህዝብ ማነው?
ሁላችንም ዳዊቶች ከሆንን የዳዊት ጠላቶችስ እነ ማን ናቸው?
ሁላችንም ያዕቆቦች ከሆንን ላባ ማነው?
ሁላችንም እውነተኞች ከሆንን በውሸት ያቀፈን ሸንጋይ ማነው?
ሁላችንም ዮሐንሶች ከሆንን የካደው ጴጥሮስ ማነው?
ሁላችንም ጳውሎሶች ከሆንን ዴማስ ማነው?
ሁላችንም የተሸጠው ኢየሱስ ከሆንን የሸጠው ይሁዳስ ማነው?

ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገረን አያመቻምችም።

አንዳንዶቻችን ግን የሚመቸንን ጥቅስ እና ታሪክ ለራሳችን ማድረግ እንወዳለን።

#ለምሳሌ

”እውነት የሚናገሩ ከንፈሮች ለዘላለም ጸንተው ይኖራሉ፤ ሐሰተኛ አንደበት ግን ለቅጽበት ያህል ብቻ ነው።“
ምሳሌ 12 : 19

ይሄ ጥቅስ

''እውነት የሚናገሩ ከንፈሮች ለዘላለም ጸንተው ይኖራሉ፤ ''
ይሄ ለኛ የተጻፈ

''ሐሰተኛ አንደበት ግን ለቅጽበት ያህል ብቻ ነው።“

ይሄ ደግሞ ለሌላ ሰው የተጻፈ እና እኛን የማይመለከት ይመስለናል።

ብናስተውል መልካም አይደለምን?

የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነው።
ያጽናናል፣ ይፈውሳል፣ ያበረታል፣ ሃያል ያደርጋል ደግሞም ይመረምረናል፣ ይቆጣናል፣ ይገስጸናል፣ ይመልሰናል፣ ወደ ትክክለኛው መንገድ ይመራናል እንጂ ሁሌም አያባብለንም።

ቆንጆ ቆንጆው የኛ እና ጠንከር ጠንከር ያለው ለጎረቤት አንዳንዴ ለአሽሙር ስንፈልገው የተጻፈ አይደለም።

"12፤ የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤"
(ወደ ዕብራውያን 4:12፤)

በቀኝ ዋሉ! 😉
Leah Jacob
# ውለታህ

ህይወትክን ሰውተህ ለኔ ተሰቃይተህ
በጂራፍ ተገርፈህ በሰው ፊት ተዋርደህ
ራስክን ዝቅ አርገህ ፊት ላይ ሲተፉብህ
ይህን ቃል ተናገርክ አባቶይ ማራቸው
እየተሰቃየህ ሞት አፋፍ ላይ ደርሰህ
ይቅር በላቸው አልክ ለእሱ ተጨንከህ
ምን አይነት ድንቅ ነህ ምን አይነት አባት ነህ
ይቅርታውን ጠየክ ሚያደርጉህ ትተህ
ከጠላት ታደከን በህይወት አኖርከን
የእኛ አባት ልዩ ነህ እንወድሀለን
እናት እና አባቴ በድንገት ወለዱኝ
ከክፉ ጠብቀህ እዚህ አደረስከኝ
ድንቅ አባት ስላለን በጣም ደስተኛ ነኝ
ሁሌም ከእኔ ጋር  ነው መቸም አይለየኝ
ምንም ሳይጎድልብኝ በፍቅር አሳደገኝ
ህይወቱን ሰውቶ በህይወት አኖረን
እስከ መጨረሻው የመንግስት ወራሽ ነን
እየሱስ የኔ አባት አከብርሀለሁኝ 🙏
^^ ^^  ^^  ^^    እወድሀለሁኝ
^^ ^^ ^^ ^^ ^^    አመልክሀለሁኝ




ገጣሚ አንዷለም ሰማው የ እየሱስ 🙏

   ከ ካራ ቆሬ 


@Jissusup

Subscribe Our YouTube channel
Link👇
https://youtu.be/Fptbiq71Xxs
መዝሙር 46
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።
² ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም።


ሰናይ ቀን❤️❤️
ያልተሳሉ ውበቶች✍️

    አንዳንድ ውቦች አሉ
ባለም አደባባይ ያልተንጠለጠሉ
ያልወጡ ከመቅረዝ፣ ጠቢብ ያላያቸው
ተዘለው በታሪክ  ፣ እግዚያር የሳላቸው
   (አሉ ቆንጆ ልቦች)
በዳቪንቺ ጥበብ  ፣ እንደ ሞናሊዛ
በገብረክርስቶስ ስራ፣ በውብ ስዕል ለዛ
    (ያልተሙነሸነሹ)
በፀጋዬ ግጥም ፣ ገብተው ቤት ያልመቱ
በውበት ገብያ ፣ አንድም ቀን ያልረቱ
     ሳይታወቁ ኖረው
     ሳይታዩ ተቀብረው
እንደ ዳይኖሰር ዘር ፣ የተፋቁ ካለም'
ሰማይ የተሳሉ ፣ በእግዚያሩ ቀለም
   (አሉ አንዳንድ ልቦች)
በሰው የተናቁ ፣ በአምላክ የከበሩ
በጨለማው ዘመን ፣ ለእውነት የኖሩ
ሆነው ለዚህች ዓለም ፣ የመስዋዕት ሻማ
እያነቡ ያበሩ ፣ ስጋቸው እየደማ
ራሳቸውን አርክተው ፣ በአሰስ ገሰሱ
ከቶ ለነፍሳቸው ፣ ሞት ያላወረሱ
   (አሉ ያልተሳሉ ውቦች)
በድቅድቁ ጊዜ ፣ ደምቀዉ እያበሩ
በብርሃን ታጅበው ፣ ፋናውን የመሩ
ያልወጡ ከመቅረዝ፣ ጠቢብ ያላያቸው
ተዘለው በታሪክ  ፣ እግዚያር የሳላቸው
   (የእግዚያር ስዕሎች)


እንግዳዬሁ ዘሪቱ✍️


Subscribe Our YouTube channel
Link👇
https://youtu.be/Fptbiq71Xxs
# ቃልህን ልኑረው

ቃልህን ልኑረው፣ አዳኜ ኢየሱስ
ለዚያች ለመዳን ቀን፣ ወዳንተ እንድደርስ
ፈቃድህን ልኑር ፣ አንተን ደስ ላሰኝ
ተቀይጦ መኖር፣ይኸው አሁን ይብቃኝ
ለምን ጥቂት እያልኩ፣እርሾ እጠቀማለሁ
ሊጡን እንዲያቦካ፣በርግጥ እኮ አቃለሁ

አሮጌን ማንነት፣በጥቂት ወስዳለሁ
ደሞ ለስህተቱ ፣ጥቅስ እፈልጋለሁ
ፈቃድህ እንዳልሆነ፣ ልቤ እያወቀው
መታዘዝ የሚለው፣ እየተናነቀው
ፈቃድህ ነው ፣ እያልኩ ሁሌ ናገራለው
ደግሜ ለራሴ ፣ ለልቤ አወራለሁ
አቤት እኔ ስገርም፣ደግሞ ፀልያለሁ
ፈቃድህን አስታውቀኝ፣እያልኩ እጮሀለሁ

ከእንተ ፈቃድ ጋር፣ታዲያ እንዴት ላስታርቀው
ያንተን ፈቃድናየራሴን ፍላጎት፣አንድላይ አድርጌው
አሮጌውን እርሾ፣ ከቤቴ አስቀምጬ
ፈቃድህን እያወኩ፣ አለመመለሴ
ምን ይሉታል አሁን፣ እያወቁ አላውቅም
ቀናው መንገድ ሳለ፣ሁልጊዜ መጣመም

ሲናገር ሲናገር፣ እኔኮ አልስማ
እኔ ምፈልገው፣እኔኑ ልሰማ
በውስጤ ያለዉን፣ካሳቤ ሚስማማ
ኢየሱስ እባክህ😭፣ፈቃድህን ልኑረው
የማውቀውን ሁሉ፣ልፈፅም ላድርገው
የማውቀውን ያክል፣ሳልቀይጥ ልኑረው
ጌታዬ ኢየሱስ፣ ቃልህን ልኑረው።

@Meta_01234

📥Group :  @yegetamianmahiber
📥Channel : @Ye_Getamian_Mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
      🔺🀄️🀄️ሉን🔺
           Join us
         🎯     ♡         ❍ㅤ    ⌲ 
ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
Forwarded from Light (Selam 🦋)
🛑 #የእግዚአብሔርን_ድምፅ_መስማት_ተስኖህ_ከሆነ፣ መስማት የተሳነህ እግዚአብሔር ሳይናገርህ ቀርቶ ሳይሆን ከአንተ የአደማመጥ ችግር ስለሆነ፣ መንፈሳዊ ጆሮህን ቃኝ።

▶️ እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ስለሆነ፣ ኃጢያት ብትሰራ እንኳ አንተን ከመናገር ወደ ኃላ አይልም። ይወድኃልና!
                      
    💕@sela3m

@worlds_light
@worlds_light
join & share
ማጣት አበሳው
    
ከየት ተገኘ የድሃ አፈር ?
እንክርዳድ ብቻ ዘሩ ሲሰፈር
ሰው ሆኖ መኖር በምን ይገኛል ?
ምነው ግን ደሃ ሞቱን ይመኛል?
ቤት አለው እንዴ መንግስተ ሰማይ
ጣራው ማያፈስ ?
የብረት ለበስ ?
ሚመክትለት ብርድ እንደ ጋሻ
ሚጠለልበት ማረፍያ ሲሻ
ቤት አለው እዛ ?
ቀን ሌት ሮሮ ለዓለም ያሰማል
መኖርን ጠግቦ ሞትን ይጠማል
ከአምላክ ነኝ የሚል እየሳሳላት
ምነው ግን ድሃ ዓለምን ጠላት ?
ከመሬት ዘሮች ሁሉም ቀፎታል
ዝናብን እንኳ ለዓይን ጠልቶታል
የመጠላያው ላስቲኩን በስቶ
ከመሬት ጋራ ሲቆራኝ አይቶ

እርዳው ቸር ጌታ...

ዓይኑን አብራለት ይሳቅ ይይና
ዋስ እንደሆንከው በሀብታም ህሊና
ህይወት ሲያያዝ በዓለም ርግብግብ
ለሀብታም ድሃ ነው የህሊና ምግብ

አንተ ቸር ጌታ ቃልን አሰማው
ምንጮች እንዳሉክ ተስፋ ለጠማው
ለተስፋ ይመጣል በደረቅ ከንፈር
እስቲ ና ቤቱ ጠላቱ ይፈር
ድኽነት ይፈር
ረሃብ ይፈር
ጥማትም ይፈር
አንከባል'ለት ሸክሙን ለቅመ
ድንኳኑ ዝለቅ ዝናብን ቀድመ

ⒺⒸ2016
➫Ⓓ የሱመልስ

Subscribe Our YouTube channel
Link👇
https://youtu.be/Fptbiq71Xxs
❤️❤️
👆👆👆👆
No reaction
There is
No post ☹️ የምር
ሰሞኑን ሶል ትንሽ የማይባል ህመም አጋጥሞት ነበር እና አሁን ጌታ ይመስገን ደህና ነው ሁላችሁም እየገባችሁ ሰላም በሉት😊🙏🙏🙏🙌🙌

እንኳን ደህና ሆንክልን ሶል❤️🙏
❤️❤️
ወገኖቼ መጽሐፍ ቅዱስ

”በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ፣ እርሱም ከፍ ከፍ ያደርጋችኋል።“
ያዕቆብ 4 : 10

” ስለዚህ እርሱ በወሰነው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከእግዚአብሔር ብርቱ እጅ በታች ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤“
1 ጴጥሮስ 5 : 5 - 6

እግዚአብሔር ያከብራል ❤️❤️
በትህትና እንመላለስ።🙏

የተባረከ ምሽት 😊
ቴሌግራም ልክ እንደ ቲክቶክ ብዙዎችን ባለሀብት ሊያደርግ ነው በተጨማሪም ቴሌግራምን ተወዳጅ ሊያደርጉት ከሚችሉ ነገሮች አንዱ ይህ ነው 🤩

⭐️ አሱም MAJOR Telegram Stars ይሰኛል🔴

እንደሚታወቀው TikTok በፈጠረው የቲክቶክ ኮይን ጊፍት አማካኝነት ብዙዎቹ ህይወታቸውን እንዲቀይሩ ረድቷል።

ቴሌግራምም የቲክቶክን ፈለግ በመከተል አዲስ Telegram Stars የተሰኘ Gift Coin አምጥቷል ይህም የቴሌግራም ክሬተሮች የተሰጣቸውን ጊፊት ወደ ገንዘብ መቀየር እንዲችሉ ተደርጓል።

ቴሌግራምም ይህንን ነገር ለማስተዋወቅ Major በተሰኘ Airdrop መሰል ነገል መጥቷል ይህም ሰው invite በማድረግ በቀላሉ የቴሌግራም Star Coin መስራት እንድችሉ ያደርጋል።

በተጨማሪም Verify የሆነ Airdrop ነው ከመጣም 5 ቀን አልሆነውም ይህንንም በደንብ የሰራ ሰው የTON ሽልማት እንዳለው አሳውቀዋል

1 ሰው invite ስታደርጉ 15 star ታገኛላቹ ⭐️⭐️

ይህንን እንደ ኤርድሮፕ እንዳትቆጥሩት ሊስት ብሎ ነገር የለውም ትክክለኛ ገንዘብ ነው ስለዚህ Guys አሁኑኑ ጀምሩት💥👇🏻

https://t.me/major/start?startapp=1888081646
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
1 star = 2.5 etb ብር ነው።
በደንብ ስሩ በ TON ነው ማውጣት የሚቻለው።

አሪፍ ብር መስራት ትችላላችሁ ጥሩ እድል ነው።
ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና።
¹⁶ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።
¹⁷ ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።

በክብር ዋሉ ሰናይ ሰንበት❤️

Subscribe Our YouTube channel
Link👇
https://youtu.be/Fptbiq71Xxs