ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
22.4K subscribers
379 photos
97 videos
169 files
284 links
This channel is not operated by Deacon Yaregal Abegaz

https://youtube.com/@yaregalabegaz?si=1f5NHTaQ2l2LbxWQ

“ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።”
— 2ኛ ቆሮ 11፥28
Download Telegram
"ብዙዎች ቢጾሙም ለእነርሱ መጾም ማለት የጾም ምግብ መብላት ማለት ነው። እነርሱ በጾም ወቅት ለራሳቸው የሚበሏቸውን በጣም ጣፋጭና ገንቢ ምግቦችን ያዘጋጃሉ አልፎ ተርፎም ውድና የማይገኙ ቅመማ ቅመም ይጨምሩባቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ የጾም ቅቤ፤ የጾም አይብ፤ የጾም ቸኮላታ እንዲያገኙ ይጠይቃሉ። በአጠቃላይ የጾም ምግቦቻችን ብዛትና ዓይነት ከልክ እጅግ ያለፈ ነው።

በዚህም ነብዩ ዳንኤል ስለ ጾም የተናገረውን ይዘነጉታል። "በዚያ ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ። ማለፊያ እንጀራ አልበላሁም ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም ሦስቱንም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም።" (ዳን 10፥2-3) በዚህ አባባሉ ውስጥ "ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም" የሚለው ላይ ማተኮር እፈልጋለሁ ። አንድ ሰው በጾም ወራት በየዕለቱ ጥሩ ጥሩ ምግቦች እየበላና የሚናፍቀውን ምግብ ለሰውነቱ እየሰጠ የሥጋውን ፈቃድ እንዴት ሊቆጣጠር ይችላል? አይችልም።

መንፈሳዊው ሰው የጾም ትክክለኛ ፍቺ ሥጋን በማዋረድ የምግብን ፋላጎት ድል ለማድረግ ካበቃ በኋላ ከቁሳዊው ዓለም በላይ ከፍ የሚያደርግ መሆኑን ያውቃል። በመሆኑም የጾም ምግቦችን መብላት ብቻ መሆን የለበትም እርሱ በሚጾምበት ጊዜ ግድ የሚለው መታቀብ ነው ። ይህም ማለት የሚመገበው ሙሉ ለሙሉ የጾም ምግብ ቢሆንም ሥጋው ሊያገኛቸው የሚናፍቃቸውን ነገሮች በሙሉ መከልከል ማለት ነው ።

ብዙ ሰዎች የሚጾሙት በልምድ ወይም በፊደል ስለሆነ ምንም የሚጠቀሙት ነገር የለም ። እነዚህ ሰዎች ጾምን መለኮታዊ ዓላማውን በመገንዘብ ስለማይጀምሩት ወደ ጾም መንፈሳዊነት ወይም ስለ ትእዛዙ መንፈሳዊነት ሊገቡ አይችሉም። በመሆኑም ሰውነታቸው ይጹም እንጂ መንፈሳቸው አይጾምም።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
የኃጢአት ምኞትህን የሚዛን ልክ በልብህ ውስጥ ያመጣጥን ዘንድ ማንኛውንም ዓይነት መንፈሳዊ ሥራ በመሥራት የክፋታቸውንና የአደጋቸውን መጠን ቀንስ። የምኞት ኃጢአት እስክታስወግደው ድረስ መልካም ፈቃድ በልብህ ውስጥ ቀስ በቀስ እንደሚያብብ እርግጠኛ ሁን። መንፈስ ቅዱስ በውስጥህ እንደሚሰራ ሲታወቅህ ችላ አትበለው፤ ከእርሱ ጋር ሥራ እንጂ በምኞትህ ልትቀጥል አትሞክር።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
#እግዚአብሔርን_ጠብቅ

እግዚአብሔርን የሚጠብቅ ሰው እርሱን በተስፋ፤ በእምነት፤ በተሞላ ሙሉ ልብና ያለምንም ድካም ይጠብቀዋል። ይህ በመሆኑም እንደዚህ ዓይነቱ ሰው እግዚአብሔር በመካከል ገብቶ እንደሚሰራና ሁሉም ነገር ለበጎ እንደሚሆን ያምናል። "እግዚአብሔር ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።" [ሮሜ 8፥28] "እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ አይታክቱም ይሄዳሉ አይደክሙም።" [ኢሳ 40፥31] ኃይላቸው በመከራ የተናወጠባቸው ሁሉ እግዚአብሔርን በተስፋ በመጠባበቅ ኃይላቸውን ያድሳሉ ማለት ነው። "ጎልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል" የሚል ቃል ተጽፏል [መዝ 102፥5] ስለሆነም ማንም ቢሆን እግዚአብሔር እምነት በተሞላ ብርቱ ልብና በእርሱ ላይ በመተማመን ይጠብቀዋል።

ነገር ግን አንድ ሰው እግዚአብሔር እርምጃ እንደሚወስድና እርምጃውም ግልጽና ኃያል እንደሆነ መተማመን አለበት። ከዚሁ ጋር እርምጃው በተመቻቸ ሰዓት ፍሬያማ በሆነ መንገድ የሚከናወን ነው። እግዚአብሔር አንድ የሆነ እርምጃ ለመውሰድ ከወደደ ምንም የሚጠባበቀው ሰዓት አይኖርም። ኢየሱስ ክርስቶስ " ... አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም አላለምን ? [ሐዋ 1፥7] አንተ ችግርህን እግዚአብሔር እንደሚያቃልልህ በማመን መቼ ለችግርህ መፍትሔ እንደሚሰጥህ ሳታስብ በእርሱ እጅ ላይ ብቻ ጣለው።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው። ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

(#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ)