አንድ ወንድም ወደ ቅዱስ መቃርዮስ ሄደና “እድን ዘንድ የሚረዳኝን ምክር ምከረኝ" አለው፡፡ መቃርዮስም "ወደ መቃብር ቦታ ሒድና ሙታንን ስደባቸው" አለው፡፡ ያ ወንድምም ወደዚያ ሄዶ ሰድቧቸውና ድንጋይ ወርውሮባቸው ተመለሰና ይህንኑ ማድረጉን ነገረው፡፡ መቃርዮስም “ምን አሉህ?” ሲለው እርሱም “ምንም ነገር አላሉኝ" አለው። አረጋዊውም “ነገ ተመልሰህ ሒድና
አመስግናቸው” አለው፡፡ ያ ወንድምም ተመልሶ ሔደና “እናንተ እናንተ ሐዋርያት፣ ቅዱሳንና ጻድቃን ሰዎች ናችሁ" እያለ ሲያመሰግናቸው ውሎ ተመለሰ፡፡ አረጋዊውም “ምንም አልመለሱልህም?" አለው፡፡ እርሱም “የለም” አለ፡፡ መቃርዮስም “ሙታንን እንደ ሰደብካቸውና ምንም እንዳልመለሱልህ፣ እንደ
ገናም እንዳመሰገንካቸውና ምንም ነገር እንዳልተናገሩህ አይተሃል፡፡ አንተም ልትድን ከፈለግህ እንዲሁ ማድረግና የሞትህ መሆን
አለብህ። ልክ እንደ ሙታን የሰዎችን ነቀፌታቸውንም ሆነ ምስጋናቸውን ከቁም ነገር አትቁጠረው፣ ቦታም አትስጠው፣ እንዲህ ብታደርግ ትድናለህ” አለው፡፡
++++++++~++++++
በአንጾኪያ የነበረ አንድ ደግ መነኩስ እንዲህ አለ፦ “እጸልይ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ሄድሁ፤ በዚያም የምመገበው ስላልነበረኝ እንደ ራበኝ አዝኜ ተኛሁ:: ክርስቶስ ሌሊት ታየኝና «ጎልጎታ
ወዳለ ቄስ ሂድና አንዲት ዲናር ትሰጠኝ ዘንድ ክርስቶስ ወዳንተ ልኮኛል፣ እርሱ መጥቶ ይከፍልሃል በለው» አለኝ:: በነቃሁ ጊዜ
ወደ ቄሱ ሄድሁና ነገርሁት:: እርሱም «ክርስቶስ የሚመጣና ገንዘቤን የሚሰጠኝ መቼ ነው?» አለኝ፡፡ እኔም እርሱ ያለኝን ነግሬሃለሁ፣ ከዚህ በኋላ የወደድከውን አድርግ አልሁት፡፡ እርሱም
«ጻፍልኝ» ኣለኝ፡፡ እኔም እኔ የአንጾኪያው ዮሐንስ ከኢየሩሳሌሙ ቀሲስ እስጢፋኖስ አንድ ዲናር ወስጃለሁ፤ ክርስቶስ መጥቶ ዲናሩን እንደሚከፍለው ይኸው በእጄ ጽፌአለሁ ብዬ ጻፍሁለት፡ እርሱም ሰጠኝ። በዚያው ሌሊት ክርስቶስ ታየውና «ዲናርህን ውሰድና ያ መነኰስ የጻፈውን ጽሑፍ መልስልኝ» አለው᎓᎓ እርሱም «ክርስቶስ መጥቶ ይመልስልሃል ብሎኝ አልነበረምን?» አለው፡፡ እርሱም «ዲናርህን ውሰድና የዚያን መነኰስ ጽሑፍ መልስልኝ የምልህ እኔ ራሴ ክርስቶስ ነኝ» አለው:: ያም ቄስ እየፈራና እየተንቀጠቀጠ ከእንቅልፉ ነቃ፡፡ ወደዚያ መነኰስም ወደ እርሱ በፍቅር ይመጣ ዘንድ ላከበት፡፡ መነኲሴው ግን ያቺን ዲናር አምጣ ሊለኝ ነው ብሎ ፈራ፡፡ ኣብረው ሲበሉም «ከገንዘቤ የፈለግከውን ሁሉ ውሰድ» አለው፡፡ መነኲሴው ግን ከታዘዘልኝ በቀር ሌላ አልፈልግም” አለው፡፡ ቄሱም በሀልሙ የሆነውን ነገር ነገረውና “አሥር መክሊት ወርቅ ውሰድና ጻፍልኝ” አለው። እርሱ ግን “ከአንድ ዲናር በቀር ሌላ እወስድ ዘንድ አምላኬ አላዘዘኝም፡፡ ነገር ግን በፍጹም ልብህ
ካመንህ ብዙ ነዳያንን ታገኛለህ፤ እነርሱም እንዲህ ይጽፉልሃል” አለው::
++++++++++++~~~~+++++++++
ነፍስህ የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ ስትሰለች ፣ ቃለ እግዚአብሔር ማንበብና መስማት ደስ የማይላት ሲሆንና ሲያስጠላት፣ እንዲሁም መንፈሳዊ ተግሳፅን ስታቃልል ካየሀት በክፉ ደዌ ላይ እንደወደቅህ ተገንዘብ፤ ሰዎች የሞትን ፍሬ የሚቀጥፉበት መጀመሪያው ይህ ነውና።
#ከበረሐውያን_አንደበት
#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
አመስግናቸው” አለው፡፡ ያ ወንድምም ተመልሶ ሔደና “እናንተ እናንተ ሐዋርያት፣ ቅዱሳንና ጻድቃን ሰዎች ናችሁ" እያለ ሲያመሰግናቸው ውሎ ተመለሰ፡፡ አረጋዊውም “ምንም አልመለሱልህም?" አለው፡፡ እርሱም “የለም” አለ፡፡ መቃርዮስም “ሙታንን እንደ ሰደብካቸውና ምንም እንዳልመለሱልህ፣ እንደ
ገናም እንዳመሰገንካቸውና ምንም ነገር እንዳልተናገሩህ አይተሃል፡፡ አንተም ልትድን ከፈለግህ እንዲሁ ማድረግና የሞትህ መሆን
አለብህ። ልክ እንደ ሙታን የሰዎችን ነቀፌታቸውንም ሆነ ምስጋናቸውን ከቁም ነገር አትቁጠረው፣ ቦታም አትስጠው፣ እንዲህ ብታደርግ ትድናለህ” አለው፡፡
++++++++
በአንጾኪያ የነበረ አንድ ደግ መነኩስ እንዲህ አለ፦ “እጸልይ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ሄድሁ፤ በዚያም የምመገበው ስላልነበረኝ እንደ ራበኝ አዝኜ ተኛሁ:: ክርስቶስ ሌሊት ታየኝና «ጎልጎታ
ወዳለ ቄስ ሂድና አንዲት ዲናር ትሰጠኝ ዘንድ ክርስቶስ ወዳንተ ልኮኛል፣ እርሱ መጥቶ ይከፍልሃል በለው» አለኝ:: በነቃሁ ጊዜ
ወደ ቄሱ ሄድሁና ነገርሁት:: እርሱም «ክርስቶስ የሚመጣና ገንዘቤን የሚሰጠኝ መቼ ነው?» አለኝ፡፡ እኔም እርሱ ያለኝን ነግሬሃለሁ፣ ከዚህ በኋላ የወደድከውን አድርግ አልሁት፡፡ እርሱም
«ጻፍልኝ» ኣለኝ፡፡ እኔም እኔ የአንጾኪያው ዮሐንስ ከኢየሩሳሌሙ ቀሲስ እስጢፋኖስ አንድ ዲናር ወስጃለሁ፤ ክርስቶስ መጥቶ ዲናሩን እንደሚከፍለው ይኸው በእጄ ጽፌአለሁ ብዬ ጻፍሁለት፡ እርሱም ሰጠኝ። በዚያው ሌሊት ክርስቶስ ታየውና «ዲናርህን ውሰድና ያ መነኰስ የጻፈውን ጽሑፍ መልስልኝ» አለው᎓᎓ እርሱም «ክርስቶስ መጥቶ ይመልስልሃል ብሎኝ አልነበረምን?» አለው፡፡ እርሱም «ዲናርህን ውሰድና የዚያን መነኰስ ጽሑፍ መልስልኝ የምልህ እኔ ራሴ ክርስቶስ ነኝ» አለው:: ያም ቄስ እየፈራና እየተንቀጠቀጠ ከእንቅልፉ ነቃ፡፡ ወደዚያ መነኰስም ወደ እርሱ በፍቅር ይመጣ ዘንድ ላከበት፡፡ መነኲሴው ግን ያቺን ዲናር አምጣ ሊለኝ ነው ብሎ ፈራ፡፡ ኣብረው ሲበሉም «ከገንዘቤ የፈለግከውን ሁሉ ውሰድ» አለው፡፡ መነኲሴው ግን ከታዘዘልኝ በቀር ሌላ አልፈልግም” አለው፡፡ ቄሱም በሀልሙ የሆነውን ነገር ነገረውና “አሥር መክሊት ወርቅ ውሰድና ጻፍልኝ” አለው። እርሱ ግን “ከአንድ ዲናር በቀር ሌላ እወስድ ዘንድ አምላኬ አላዘዘኝም፡፡ ነገር ግን በፍጹም ልብህ
ካመንህ ብዙ ነዳያንን ታገኛለህ፤ እነርሱም እንዲህ ይጽፉልሃል” አለው::
++++++++++++