Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
494 subscribers
3.21K photos
224 videos
46 files
2.17K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
ከነቢያትና ከሩሱሎች መካከል እረኛ፣ ነጋዴ፣ ባል፣ አባት፣ ተዋጊ፣ መሪ፣ ፖለቲከኛ፣ቃዲ፣ የሀገር መስራች፣ ገዥና ሰባኪ የነበሩ ብቸኛ የአላህ መልእክተኛ ተወዳጃችን እና አርአያችን የሆኑት ነቢያችንﷺ ናቸው።
ዛፍ እርጥብ እያለ ብዙ አገልግሎት አለው ፍሬዎችን ይሰጣል፣ለመጠለያ ይሆናል፣ ኦክስጅን ይለግሳል። ሲደርቅ ግን እሳት ማቀጣጠያ ይሆናል::

የሰው ልጅም ልክ እንደ ዛፉ ነው።ልብህ ለስላሳ ሲሆን ፈጣሪህን ትፈራለህ !!ለሁሉም ታዝናለህ!! ፈጣሪህን ትገዛለህ!!

የሰው ልጅ ልቡ ሲደርቅ ልክ ዛፉ ሲደርቅ ለማገዶ እንደ ሚሆነው ሁሉ ለጀሀነም ማገዶ ብቻ ነው ሚሆነው:: ጌታችን ሆይ በእዝነት ይሁንብህ ልባችንን አለስልሳት 🥹 🤲

ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
የሳዑዲ ዐረቢያ ባለሥልጣናትን አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው የፀሓይ ንዳድ የሞት ዜና

#Ethiopia |~ ሳዑዲ ዐረቢያ በዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዓት ለመከወን ከመላው ዓለም የተሰባሰቡ ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ምዕመናንን አስተናግዳ ወደመጡበት መሸኘት ጀምራለች። በምዕመናን ዘንድ የዕድሜ ዘመን ናፍቆት ለሆነው የሐጅ ክንውን የተቀመጡ ቀናት አልፈው ምዕመናን ወደመጡበት መመለስ የጀመሩት ዛሬ ሐሙስ ነው።

የሳዑዲ ባለሥልጣናት ምዕመናን መካን መልቀቅ መጀመራቸውን ይፋ ሲያደርጉ፣ ጎን ጎን እየወጣ የሚገኘው ዜና አጣብቂኝ ውስጥ የከተታቸው ይመስላል። ዜናው የሞት ነው፤ በፀሓይ ንዳድ ከምድር ሕይወት የተለዩ ምዕመናን ሞት።

በተለይ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ሲከወን እምብዛም ሽፋን በመስጠት በማይታወቁ ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን እየተንሸራሸረ የሚገኘው ዜና፣ በሐጅ ሥነ ሥርዐት ወቅት በሳምንቱ መጀመሪያ ከሃምሳ ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ የተመዘገበው ሙቀት ያስከተለው የጤና መቃወስ ቢያንስ የአንድ ሺሕ ምዕመናን ሕይወት ነጥቋል የሚል ነው።

መረጃው ከሲኤንኤን እስከ ሲቢኤስ፤ ከአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እስከ ሬውተርስ እየተዘዋወረ ይገኛል። ማክሰኞ እለት ቀድሞ 550 ምዕመናን ሞተዋል ያለው የፈረንሳዩ የዜና ወኪል አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ፣ ዛሬ ሐሙስ አመሻሽ የሟቾቹን አሐዝ 1 ሺሕ 81 አድርሶታል። የዜና ወኪሉ ከሟቾቹ ውስጥ ከፍተኛው ቁጥር የግብጻዊያን ነው ያለ ሲሆን፣ የተመዘገበው ቁጥር 658 ነው።

ከእነዚህ ውስጥ 630 ምዕመናን በሐጅ ክንውኑ ላይ ሲሳተፉ የነበረው ለሥነ ሥርዐቱ በተዘጋጀው ቪዛ ሳይሆን በሌላ ዐይነት ቪዛ ቅድስቲቱ መካ ከተማ ተገኝተው ነው። የዜና ወኪሉ በሳዑዲ ባለሥልጣናት ሕገ ወጥ በሚል የተለዩት እነዚህ ምዕመናን፣ ከፖሊስ ለመደበቅ በሚያደርጉት ጥረት የአየር ማቀዝቀዣ የተገጠመላቸው ሥፍራዎች መግባት ስለማይችሉ ለፀሓይ ንዳድ ተጋላጭ ሆነዋል ሲል ለኅልፈታቸው ሰበብ መላ ምት አስቀምጧል።

አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው፣ እስካሁን የሞቱት ከአንድ ሺሕ በላይ ምዕመናን ከአስር ሀገራት የተውጣጡ መሆናቸውን ዲፕሎማቶች እንደነገሩት ነው የጠቀሰው። የዜና ወኪሉ ይህን ቢልም ምዕመናን ራሳቸውን ከፀሓይ ንዳድ ለመከላከል አዘውትረው ዣንጥላ እንዲጠቀሙ ሲመክሩ የቆዩ የሳዑዲ ዐረቢያ ባለሥልጣናት የየትኛውም ሀገር ዜጋ ስለመሞቱ ማረጋገጫ ሲሰጡ አልታዩም።

ሬውተርስ የዜና ወኪል በአንፃሩ አንድ የሳዑዲ ጤና ሚኒስቴር ኃላፊ ሰኞ እለት በምዕመናን ላይ እስካሁን ድረስ ከሌላ ጊዜው የተለየ የሞት ምጣኔ እንዳልተመዘገበ ነግረውኛል ብሎ ዘግቦ ነበር። ኃላፊው የሳዑዲ ጤና ባለሞያዎች በፀሓይ ንዳድ ለተመቱ 2 ሺሕ 700 ምዕመናን የሕክምና ድጋፍ መስጠታቸውን እንደገለፁም አስፍሯል።

የምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን የሑጃጅን የሞት ዜና ሲሸፍኑ በዋሉበት ዛሬ ሐሙስ፣ 12 ሺሕ ምዕመናንን የላከው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በተቃራኒው ለሐጅ ክንውን ከተጓዙ ኢትዮጵያውያን ውስጥ በፀሓዩ ንዳድ ሳቢያ ሕይወቱ ያለፈ ምዕመን አለመኖሩን አስታውቋል፡፡ ምክር ቤቱ በንዳዱ የሞተ እንደሌለ ቢጠቅስም አምስት ኢትዮጵያውያን በሌላ ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን ግን በመረጃው አሥፍሯል፡፡ ከምዕመናኑ መካከል አንደኛው የሞቱት በተሽከርካሪ አደጋ መሆኑን የገለፀው ምክር ቤቱ፣ ለቀሪዎቹ የሞት መንስዔ ብሎ የጠቀሰው ሕመም ነው። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሟቾቹ ኢትዮጵያውያን ሕመም ድንገተኛ ይሁን አልያም ቀድሞ የተለየ የጠቀሰው ነገር የለም። (ሚንበር ቲቪ)

የፎቶ ምንጭ፡ ኤኤፍፒ
© Minber TV

ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢላሂ እኛንም በኛ ላይ ሀቅ ካላቸው ወላጆቻችን እንዲሁም ቤተሰቦቻችን ጋር በአብሮነት ይህንን እድል ወፍቀን 🥹 🤲

@ https://t.me/Xuqal
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ረሱል ﷺ እንዲህ አሉ፦

'' ዑመር ሆይ፣ የሮምና የፋርስ ንጉሶች በዚህ ዓለም ይደሰቱ! ለኛ ግን የቀጣዩ ዓለም ደስታ በቂያችን ነው! ይህ አለም ለእኔ ከቶ ምን ያደርግልኛል?! የኔና የዚህች አለም ግንኙነት እንደ በጋ መንገደኛ ነው! ከዛፍ ጥላ ስር አረፍ ብሎ ሲነጋ መልሶ እንደሚጓዘው።''

አለይሂ አፍደሉ ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ አለይህ

ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
عليه افضل الصلاه والسلام اللهم صلي وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى اله وصحبه اجمعين

የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
መዳረሻዬ አንተ ከሆንክ… መንገዱ እንዴት ያለ ውብ ነው! ደጃፍህ እስክደርስ ክብደቱ ቢያንገዳግደኝም፣ የነፍስያ ጉትጎታ ቢያደናቅፈኝም ፍላጎቴ አንተ ነህና በመንገድህ እንድበረታ አግዘኝ ኢላሂ!! 🥹 🤲

ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
የታሰሩ ነገሮች ሁሉ...አላህ በራህመቱ አንድ ቀን ይፈታቸዋል።