Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
466 subscribers
3.04K photos
187 videos
46 files
2.1K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
«አላህ ሆይ! መንገዳችንን ምሪት ወዳለበት፣ ጓደኝነታችንን ውዴታ ወዳለበት፣ ልባችንንም ደስታ ወዳለበት አድርግልን!»
አላህ ሆይ በየቀኑ ራሣቸዉን ገምግመው ከሚታረሙት አድርገን። ከነፍሳችን ተንኮል ባንተ እንጠበቃለን።ከባህሪያችን ክፋትም አንተው ጠብቀን 🤲
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጎንደር ከተማ እየሰጠ ባለው ስልጠና ላይ ሙስሊሞች እንዳይሳተፉ መከልከሉ ተገለፀ!
...
(ሀሩን ሚዲያ፦ግንቦት 9/2016)

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጎንደር ክላስተር በአጀንዳ ማሰባሰብና ምክክር ላይ የሚሳተፉ የማህበረሰብ አባላትን ለመመልመል የሚያግዙ ተባባሪ አካላት ስልጠና እየሰጠ ሲሆን በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ የመጡ ሙስሊሞችን እንዳይገቡ መከልከሉን የሀሩን ሚድያ ምንጮች ገልፀውልናል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጎንደር ከተማ እየሰጠ ባለው ስልጠና አስመልክቶ "ሀሩን ሚድያ" ጉዳዩን አስመልክቶ ስልክ ደውልን ባጣራነው መረጃ መሠረት የደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ከተማ መጅሊስ አመራሮች ስልጠናው ላይ ለመሳተፍ ወደቦታው ቢያቀኑም ከበር እንዳይገቡ እንደተከለከሉ አንስተዋል።
...
ስልጠናውን እየሰጡ ያሉት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አመራሮች ምልመላ ያደረጉት ከክልሉ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ እንደሆነ በመግለፅ የክልሉ መጅሊስ ወክሏቸው ለመሳተፍ የመጡ ሙስሊሞችን አናስገባም ማለታቸውን ለሀሩን ሚድያ ተናግረዋል።

በጎንደር ከተማ እየተሰጠ በሚገኘው የጎንደር ክላስተር ተባባሪ አካላት ስልጠና ከ75 ወረዳዎች የተውጣጡ ከ500 በላይ ሰልጣኞች እየተሳተፉ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ነገር ግን የሙስሊሙ ቁጥር አነሳ መሆኑን እና የክልሉ መጅሊስ ባላወቀው መልኩ እንደተደረገ ተገልጿል፡፡

ሀሩን ሚድያ ያነጋገራቸው አካላት እንደገለፁት ሙስሊሙን ያላሳተፈ ምክክር ውጤታማ አይሆንም በማለት ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ እየሄደበት ያለው መንገድ አግባብ ባለመሆኑ ሙስሊሙን እንዲያካትት ጥሪ አቅርበዋል።

©ሀሩን ሚድያ
የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ሀገራዊ ምክክሩ ሙስሊሙን ያገለለ የተሳታፊ ልየታ እንደተደረገበት ተገለፀ!

(ሀሩን ሚድያ፦ግንቦት8/2016፤ አዲስ አበባ )

በኢትዮጲያ በመጪው ለሚካሄደው ሀገራዊ ምክክር የሙስሊሙ ቁጥር አነሳ በመሆኑ የተሳታፊዎች ልየታ  በድጋሚ እንዲካሄድ እና በሙስሊሙ በኩል የቀረቡ አጀንዳዎች በሀገራዊ ምክክሩ እንዲካተቱ  የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ባቀረበው ጥያቄ የሙስሊሞች ተሳትፎ በሕዝባችን ቁጥር ልክ መሆን ያለበት በመሆኑ የተሳታፊዎችና የአወያዮች ቁጥር በዚሁ መሠረት በኮሚሽኑ "የአካታችነት መርህ መሠረት ጠ/ም/ቤቱ ያቀረበውን የሕዝበ ሙስሊሙ የምክክር እጀንዳዎች ለጉባኤው ለማሰማት፤ ለማብራራት የሚችሉ ተገቢ ቁጥር ያላቸው ሙስሊም ተወካዮች እንዲካተቱ ይቻል ዘንድ የህዝብ ጥያቄዎች ከፍተኛ እየሆነብን በመምጣቱ ሥብጥሩ በፍትሃዊነት እንደገና እንዲቃኝ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የበላይ ጠባቂ ለሆኑት  ለፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በፃፈው ደብዳቤ ጠይቋል።

በኢትዮጵያ የተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ለመፍጠር ይችላል የተባለው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ተቋቁሞ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን  ኮሚሽኑ ከትግራይ ክልል ውጪ እና ግጭት ባለባቸው የአማራ እና የኦሮሚያ ክልልች አንዳንድ አካባቢዎችን ሳያካትት በ10 ክልሎችን እና የከተማ አስተዳደሮች ለምክክሩ የሚሳተፉ አካላትን ልየታ ቢያካሂድም የሙስሊሙ ቁጥር አነስተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ተወካዮች ከሀገራዊ ምክክሩ "3"ኮሚሽነሮች ጋር  ውይይት ማድረጋቸው የተገለፀ ሲሆን በባለሙያ በተሰጠ መግለጫ ላይም  በተሳታፊና በአወያይ ደረጃ የሙስሊሞችን ተሳትፎ እንዲነገረን ብንጠይቅም ከምክክር ኮሚሽኑ ምላሽ እንዳልተሰጠ በሰጠው መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ውሳኔውን በድጋሚ እንዲያጤነው እና
በኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አማካኝነት የቀረቡ የመስሊሙ አጃንዳዋች እንዲካተቱ እና ህዝበ ሙስሊሙም በቁጥሩ ልክ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።

©ሀሩን ሚድያ
የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ኢና ሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን !

ከጎንደር ከተማ ወደ መተማ ስንሄድ በማእከላዊ ጎንደር ደንቢያ ወረዳ አየንባ ቀበሌ ሸኽ ሲራጅ የመስጅዱ ኢማም መግሪብ ሰላት ሰግደዉ ሲወጡ በታጣቂዎች ተይዘዉ ከሄዱ በሃላ በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ደብድበዉ ገድለዋቸዋል ።

ሸኽ ሲራጅ በዛዉ መስጅ ለረጅም አመት ደረሳዎችን እስከዛሬዋ እለት ያቀሩ የነበሩ ሲሆን መግሪብን አሰግደዉ ሲወጡ ታጣቂዎቹ እየጎተቱ የወሰዷቸዉ መሆኑና ይህን የሀገር ሽማግሌ የሁሉ አባት የሆኑት የመስጅድ ታላቁን ሸኽ ገድለዉ ጥለዋቸዉ እንደሄዱ ሰማን ።

በተፈጠረዉ ነገር በጣም እያዘንኩ ሸኻችን አሏህ ከሸሂዶች ተርታ እንዲያደርጋቸዉ እየለመንኩ ለቤተሰቦቻቸዉ መፅናናትን እመኛለሁ ።
©Abdurahman Sultan

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ብቻውን ሲዋጋ ውሎ ተሰዋ።  አራት ጥሎ ወደቀ። 
ኢናሊላሂወኢናኢለይሂ ራጁኡን

በጎንደር  በወገራ ወረዳ  ጉንትር ቀበሌ  አቶ ካሳው ሲሳይ አብድቃድር ለረጅም ሥዓት ከተዋጋ በሗላ   ከቀኑ በስምንት ሰዓት  ተሠዉቷል፡፡ ቦታ እየቀያየረ አላስጠጋ ብሎ ለረዥም ሰአት የተዋጋ ሲሆን በወቅቱ የነበረው መሪያቸውን ጨምሮ አራት ፋኖ ጥሎ ጥይት ሲጨርስ ተሰዋ። 

ፋኖ በወሰደው የበቀል ርምጃ
   1. አንድ ቤት ሙሉ ንብረት እንደያዘ ተቃጥሏል
   2.400ሽ ብር የሚገመት ሁለት ክላሽ ኮፕ መሣሪያ
   3.50 ሽ የሚገመት አምሥት የፍየል ሙክት
   4. 500ሽ የሚገመት ጤፍ ፡ እና አብሽ
    5.160ሽ ብር የሚገመቱ ሁለት በሬዎች ፡፡
በአጠቃላይ 1,110,000 ሽ ብር የተቃጠለውን ቤቱና ንብረቱን ሣይጨምር ዘርፈዋል፡፡

Via Adugnaw Muche

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቱርክ ወደ መስጊድነት የቀየረችው ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን

ቱርክ ወደ መስጊድነት የተቀየረችውን ጥንታዊት የቾራ ቤተ ክርስቲያን ለእስልምና እምነት ተከተዮች ክፍት አድርጋለች።

ቤተ ክርስቲያኒቱ ለ70 ዓመታት በሙዝየምነት ስታገለግል የቆየች ሲሆን፤ በፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ውሳኔ ነው ወደ መስጊደነት ተለውጣ ክፍት የተደረገችው።

ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ቤተከስርቲያኒቷ ወደ መስጊደነት እንድትለወጥ ውሳኔ ያሳለፉት በፈረንጆች 2020 ሲሆን፤ በእድሳት ላይ ቆይታ ነው ባሳለፍነው ሳምት ለእስልምና እምነት ተከተዮች ክፍት የተደረገችው።

ቾረሰ ቤተ ክርስቲን በ4ኛው ክፍለ ዘመን የተገነባች ሲሆን፤ በኦቶማን ቱርክ ዘመን ወደ መስጊነነት ተቀይራ ቆይታለች፤ ከ1945 ጀምሮ ደግሞ ለ70 ዓመታት ሙዚየም ሆና ቆይታለች።

ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ጥንዊ ቤተ ክርስቲያን ወደ መስጊድ ሲለውጠ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም በዓለም ታዋቂ የነበረች ሃጊያ ሶፊያ ቤተ ክርስቲያንን ወደ መስጊድነት እንዲለወጥ አድርገዋል።

Via Alain Amharic

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
#ለፈገግታ
ሚስት እቤት ቁጭ ብላ ለባለቤቷ text አደረገች🤳

"ከቢሮ ስትወጣ እግረመንገድህን ከጉሊት አትክልት ይዘህ መምጣትህን እንዳትረሳ፡ ሳራም ሰላም እያለችህ ነው

ባል--"ሳራ ደግሞ ማናት?"

ሚስት--"ዝም ብዬ ነው ባክህ ሚሴጁን ማየትህን ለማረጋገጥ ነው

ባል ተበሳጭቶ ትንሽ ካሰበ በኋላ text አደረገ፡

"ግን እኮ እኔ ከሳራ ጋ ነው ያለሁት፡አንቺ ስለየትኛዋ ሳራ ነው ያወራሽው?"

ሚስት--"የት ነው ያለሀው?"

ባል---"ጉሊቱ ጋ ነዋ"

ሚስት---"አሁኑኑ መጣሁ"

ከ10 ደቂቃ በኋላ፡

ሚስት---"የቱ ጋ ነህ ጉሊቱ ጋ ደርሻለሁ"

ባል--" ምን ጥሩ ነዉ ቢሮ ነኝ በቃ የፈለግሽውን አትክልት ገዝተሽ ቤት ሂጂ ማታ መጣው"😂😜

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ኢና ሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን !

በጎንደር በግፍ የተገደሉት የመስጂድ ኢማም ሸይኽ ሲራጅ አብድሬ እኚህ ናቸዉ!

በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ደንቢያ ወረዳ አየንባ ቀበሌ የመስጂድ ኢማም የሆኑት ሸይኽ ሲራጅ አብድሬ በግፍ ተገድለዋል::

አላህ(ሱ.ወ) ይዘንላቸዉ። አሚን🤲

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal