Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
494 subscribers
3.21K photos
224 videos
46 files
2.17K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
በወቅታዊ የሙስሊሙ ዓለም ጉዳዮች ላይ የሚመክር የሊቃውንት ጉባዔ በዛሬው እለት ተጀመረ

በወቅታዊ የሙስሊሙ ዓለም ጉዳዮች ላይ የሚመክረው የዓለም ሙስሊም ሊቃውንት ጉባዔ ዛሬ ግንቦት 5/2016 በቱርክ ኢስታንቡል ተጀመረ፡፡ በዚህ ጉባዔ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ለሁለት ቀናት የሚቆየው ጉባዔ በሙስሊሙ ዓለም ላይ የተጋረጡ ፈተናዎች እና ቀውሶችን ለመፍታት እንዲሁም የሙስሊሙን ዓለም አንድነት የሚሸረሽሩ የአካሄድ ችግሮችን ለመቅረፍ የመፍትሔ ሐሳቦችን ያቀርባል ተብሏል፡፡ ጉባዔው በዛሬው እለት ከመጀመሩ አስቀድሞ ትናንት ምሽት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን ለታዳሚዎች የራት ግብዣ አድርገውላቸዋል፡፡

በዚህ የራት ምሽት ላይ ንግግር ያደረጉት ኤርዶጋን፣ እስራኤል በጋዛ በፍልስጤማዊያን ላይ የምትፈጽውን ጥቃት በማንሳት ኮንነውታል፡፡ ፕሬዝዳንቱ እስራኤል በንጹሐን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ማስቆም ሀገራቸው ብር ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡

በጉባዔው ላይ የዓለም አቀፍ የሙስሊም ሊቃውንት ኅብረት ሊቀመንበር ሸይኽ ዓሊ አልቀራዳጊ እና ሌሎችም ዕውቅ የሙስሊሙ ዓለም ሊቃውንት ንግግር እና ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መረጃ ከሆነ ከጥናት አቅራቢዎቹ መካከል ፕሬዝዳንቱ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ይገኙበታል፡፡

★ ★ ★
ምንጭ | Minber TV

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
"የተወለድነው ከፍቅር ነው። ፍቅር ደግሞ እናት ናት።" ይላሉ ጀላሉዲን አር-ሩሚ قدس الله سره ♡

አላህ በህይወት ያሉ እናቶቻችንን ረጅም እድሜ ከአፊያ ጋር ይስጥልን! በህይወት የሌሉትን ደግሞ በጀነቱ ጨፌ ይሞሽርልን!

ጌታዬ የእራሱን እዝነት እንኳን ከእናት ጋር ነውና ያወዳደረው የእናት'ን ዋጋ ተረድተን ሐቃችንን የምንወጣ ያድርገን! አሚንን 🤲🏽

“أُمِّي وَمَنْ غَيْرُ قَلْبِ الأُمِّ يَسْتَمِعُ ؟
‏لِنَبْضِ قَلْبِيْ صَحِيحًا أَمْ بِهِ وَجَعُ !

‏أُمِّيْ، أَيَا حُبُّ لا يَنْفَكُّ يَغْمُرُنِيْ
‏يَا دِفْءُ لَيْسَتْ لَهُ الأكْوَانُ تَتَّسِعُ !”

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Photo
#እናት
አንድ ኩራተኛና ከእናቱምጋ ያለው ግንኙነት ጥሩ የማይባል የሆነ ወጣት ነበር !
ይህም የሆነው እናቱ እድሜዋ የገፉ ነበር የልጇን እንክብካቤ መጣም ሚያስፈልጋት ግዜ ላይም ነበረች እሱ ግን በመሰላቸትና በመበሳጨት እናቱን በተገቢው ሁኔታ ሊንከባከባት አልቻለም.😓

እናቱ ልጇ ከጎኗ እንዲሆን ትመኝም ነበር ውሀ እንዲያጠጣት ምግብ እንዲያጎርሳትም ትፈልጋለች በቃ በጣም ተዳክማ ነበር .
እጆቿም በእርጅና ምንም ነገር መያዝ አልቻለም ጉልበቷም ተዳክሞ ወደ መፀዳጃ እንኳ ሚደግፋት ሰው ትፈልጋለች.😓

ልጇ በቃ ሀቋን መጠበቅ አልቻለም እንደውም ይጮህባትና ይቆጣት ጀመር ከእለታት አንድ ቀን የሻይ ቡሹ ከእጇ ወድቆ ሲሰበር ልጇ መጥቶ ጮሀባት ተገላምጦና ተበሳጭቶ ከቤት ወጣ .😓

በሁኔታው ያዘነች እናት ወረቀት ላይ ደብዳቤ ፅፋለት ወንበሩ ላይ ጋደም አለች .
ልጁም ሲመለስ እንደ ከዚህ በፊቱ እናቱ ወንበሯ ላይ ሸለብ አርጓታ ከጠረንቤዛውም ላይ ወረቅ ተመልክቶ አንስቶ ማንበብ ጀመረ...

#ውዱ_ልጄ_ያይኔ_ማረፊያ ይላል  መግቢያው
«ይቅር በለኝ እጄ ከእርጅና ሚንቀጠቀጥ ሁኛለው የያዝኩትም ነገር ከእጄ ይወድቅብኛል 😓በዚህም አንተን አስቆጣው አዎ እኔ በአሁን ሰአት ቆንጆ አደለውም ጥሩ እይታም የለኝም አርጅቻለዋ አትውቀሰኝ የኔ ልጅ😓ልብሴን መልበስ ሲያቅተኝ እንኳ አንተ መጥተህ እንድታለብሰኝ እመኝ ነበር ግን አልሆነም😓 ወደ መፀዳጃም ደግፈህ እንድትወስኝ እከጅል ነበር እሱም አልሆነም አህ ልጄ ,ያንተን እጆች መራመድ ትችል ዘንድ ስንት ግዜ ይዣቸው እንደነበር አስታውስ!😓
አንድም ቀን ሰልችቸህ አላቅም ልጄ አሁን ደካማ በመሆኔ አትሰልችብኝ  😓
አለኝ ምለው ደስታዬ በአሁን ሰአት አንተጋ መሆኔ ነው ደስታዬ እንዳላጣጥም አትቆጣኝ😓
በልጅ እድሜህ ፈገግታህ እኔን በጣም ያስደስተኝ ነበር አሁንም ፈገግታህን አትንፈገኝ እኔኮ ወደሞት እየተቃረብኩ ነው ከጎኔ ሁን አትራቀኝ 😭»የሚል ነበር!

ልጁም ከገፍላው በመንቃት እያለቀሰ የናቱን እጅ ያዘ እናቴ ይቅር በዪኘ ዱንያ ሸውዳኝ ያንቺብ ደረጃ ዘነጋሁ አዚህ በኋላ ከጎንሽ ሆናለው አልቆጣሽምም ፈገግታዬንም አልነፍግሽም እያለ መወትወት ጀረ.!

ነገር ግን ግዜው አልፎ ነበር አዎ እናቱ ወደ አኺራ ሂዳለች😭
አሁን ልጁ ግዜውን በቁጭት ማሳለፍ እጣ ፈንታው ሆነ በልቡም ላይ ማይድን ቁስል አረፈበት .!

#ኡሚ
እድሉ ሳያልፈን እናቶቻችንን እንንከባከብ

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
የሁሉም ነገር መጀመሪያ ከአላህ ጋር አደብ ማረግ ነው !
#ዱዐችን ለምን ምላሽ አጣ 🤔

ሰዎች ተሰብስበው ኢብራሂም ኢብኑ አድሀም ዘንድ መጡና <<ለምንድነው ዱዐችን ምላሽ ያጣው?>> ሲሉ ጠየቁ

ኢብራሒም ሲመልሱ. .... ቀልባችሁ ውስጥ ባለው 10 በሽታዎች ምክንያት ነው አሉ።

1) በአላህ መኖር ታምናላቹ ትዕዛዙን ግን አትፈፅሙም

2) ረሱል (ሰ.0.ወ) እንወዳለን ትላላቹ ሱናቸውን ግን አትፈፅሙም

3) ቁርዐንን ታነባላችሁ ነገር ግን በተግባር ላይ ስታውሉት አትታዩም

4) የአላህን ፀጋ ትሻማላችሁ ነገር ግን ተገቢው ምስጋና አታደርሱም

5) ሸይጣን ጠላታችሁ እንደሆነ ታውቃላችሁ ነገር ግን ጠላታችሁ አድርጋችሁ አትጠነቀቁትም

6) ጀነትን ለመግባት ትመኛላችሁ ነገር ግን ለጀነት አትዘጋጁም

7) ወደ ጀሀነም መወርወር አትፈልጉም ነገር ግን ከጀሀነም ለመዳን አትጥሩም

8) ሁሉም ፍጥረት ሞትን እንደሚቀምስ ታምናላችሁ ግን ለሞት አትዘጋጁም

9) ሰውን ታማላችሁ የሰውን ነውር ትከታተላላችሁ ነገር ግን የራሳችሁን ስህተትና መጥፎ ፀባይ ትረሳላችሁ

10) ሙታንን ትቀብራላችሁ ነገር ግን ከሟች ትምህርትን አትወስዱም!

ኢላሂ ከሚያስተነትኑት ባሮችህ መካከል አድርገን 🤲

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
በዳዮች እርስ በርሳቸው ወዳጆች ሲሆኑ
አላህ እርሱን ለሚፈሩት ወዳጅ ነው
ቁርአን 45:19
የሰው ልጅ ከሆዱ እና ከብልቱ ውጪ ሚያሳስበው ነገር ከሌለ ሰውነቱ የአደም ልጅ መሆኑ ያበቃል ሙሉ በሙሉ እንስሳ ይሆናል ምኞቱን እና ስሜቱን(ሸህዋውን) መሙላት እንጂ ሌላ ምንም አይፈልግም የሙስሊሞች ጠላቶች ሙስሊሞች እንደዚህ እንዲሆኑ ነው ሚፈልጉት ወንዶች ከሴቶች እንዲለዩ አይፈልጉም ከእስልምና ዑማህ የስሜት የሸህዋ ዑማ እንድትቀር ነው ሚፈልጉት"

ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁሏህ

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Photo
ሙስሊሞች እባካችሁ ሼር ሼር አድርጉ ይሄንን ጉድ!!!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሙስሊም ስም ያላቸው እንዲሁም አንዳንዶቹ ሂጃብ ጣል ያደረጉ ሁነው በቲክቶክ ስለክርስትና ሲሰብኩና እስልምናን ሲሰድቡ ገጥሟችሁ አያውቅም? ብዛታቸውስ አስገርሟችሁ ያውቃል?አዎ በጣም በርካታ ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሚሽነሪዎችን በመላክ ስመ ጥር የሆነ ግሬት ሚሽነሪ ከአመት በፊት ከአንድ ሚዲያ ጋር ዳይሬክተሩ ቆይታ አድርጎ ነበር። በቆይታውም ስለቀጣይ እቅዶቻቸው ሲናገር ይሰማል። የገጠር ሰበካ ከ30 አመት በላይ መስራታቸውንና ስኬት ማስመዝገቡን ገልጾ ቀጣይ ግን ወጣቱን የምናገኘው ገጠር ሳይሆን ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ በመሆኑ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራው ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ነው ሲል ይገልጻል። በርካታ የማኅበራዊ ሚዲያ "ሚሽነሪዎችንም" ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ጋር በመተባበር እያሰለጠኑ ላፕቶፕና ሞባይል በማደል አሰራጭተዋል። እነዛን ሁሉ ሰዎች የምታዮቸው ተራ መገጣጠም ተፈጥሮ አይደለም።

ሌላ ታሪክ ልጨምርላችሁ...

ከወር በፊት በመካነ ኢየሱስ በኩል የተዘጋጀ ሴሚናር ነበር። ፕሮግራም አዘጋጋጁ ደግሞ በይተል መሲህ የተሰኘ ሙስሊሞችን ታርጌት ያደረገ ድርጅት ከመካነ ኢየሱስ ጋር በመተባበር ነው። ፕሮግራም አቅራቢውም ሙሐመድ ሱሩር የተሰኘ የድርጅቱ መሪ የሆነ ከ*ፈርቴ ሰው ነው። መሠል ስልጠና ሲኖራቸው ቀድመው ይፋ የማድረግ ባህል ስላልነበራቸው ማስታወቂያውን ስናየው ተገርመን ነበር። ግን ወዲያው ሰረዙት..! ጹሁፉንና ፒክቸሩን ወዲያው ይዠው ስለነበር ፋይሉን ማስቀረት ቻልኩ።

የሚሽነሪው አካል መቸም የሚተኛ አይደለም። ስልቶቹን እየቀያየረ የሚታገልና ፈጽሞ የማይደክም አካል ነው። ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ያለው አብዛኛው የንጽጽር ስራ ከድሮው የፌስቡክ ጠንካራ ስራ መዳከም በኃላ የተወሰነ ጭላንጭል የተፈጠረው በቴሌግራምና በቲክቶክ ስራዎች ነው። ከብዛታቸውና ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው ከሚያደርጉት ትግል አንጻር በእርግጥ ለሙስሊሙ ፈታኝ መሆኑ አይቀርም። ግን ትልቁ ብርታት ሀቅ እኛ ጋር መኖሩ ነው። በቁጥር ሙስሊሙ ትንሽ እንኳን ቢሆን በምትሰራዋ ትንሽ ስራ የተጽእኖው ባለቤት የሀቁ ጌታ በመሆኑ ስራው አልመነመነም።

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
የሚሽነሪዉ አካል ሙሀመድ ሱሩር  ማን ነዉ ?!!

ቢስሚላህ  !
ክፍል 1 እና 2👇
ከ 25 አመት በሗላ የጠፋኝን ሰዉ ወንድሜ የህያ ኢብኑ ኑህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለጥፎት ባይ ገረመኝ !!

የዛን ዘመን አፍላ የቁርአንና የዳዕዋ ንቅናቄን ከየት እንደመጣ ሳናዉቅ ነበር የተቀላቀለን ።

ፂሙ ያደገ የፓኪስታን ልብስ የለበሰ በቀኝ እጁ ሲዋክ በግራ እጁ ሙስበሃ ይዞ የፈጅርን ሰላት ለመስገድ የሂፍዝ ተማሪዎች ዉዱእ ማድረጊያ ላይ በዛ ብርድ ወቅት እንጣደፋለን ። ከመሀላችን ሞቅ ባለ ከፍ ባለ ድምፅ “ እናንተ ወጣቶች በናንተ ጊዜ ዲን ሲደፈር ነብያችን ሰ.ዐ.ወ ክብራቸዉ ሲነካ እናንተ እያላችሁ እንዴት ይሆን ለጅሀድ ተነስ እኔ አሰለጥንሀለሁ !” የሚል የወጣቱን ስሜት በሚቀሰቅስ መልኩ በቁጣ ንግግር አደረገ ። ብዙዎቻችን ሙሀመድ ሱሩር በሚል የቀረበንን ሰዉ ያኔ ተዋወቅነዉ ከፈጅር ሰላት በሓላ የቁርአን ሀለቃ ላይ አብሮን ተቀመጠ ። መስጅድ ላይ በተበላሸ ምላስ የቁርአን አያቶችን እየሰባበረ ዳዕዋ ማድረግ ጀመረ የዋሁ ማህበረሰባችን እና ወጣቱ ተከተለዉ ። በጣም የሚገርሙ ሊታመኑ የማይችሉ ለሀገር ሲል ከኤርትራ ጋር በተደረገ ጦርነት መሳተፉንና ለኢስላም ሲል አፍጋኒስታን ድረስ ዘልቆ የተዋጋበትን ባዶ ታሪክ ለወጣቱ ይግተዉ ጀመር አንዳንዱ በየት ብለን ጅሀድ በወጣን እስኪል ድረስ ፣

የማልረሳዉ ሁሌ ግን ጥያቄ የሚሆንብኝ የነበረዉ ጠዋት ከሀለቃ በሗላ ከቁርስ በፊት ወደ ዉጭ እንዳንወጣ እንከለከል ነበር ። ለምን አትሉም ?
ሙሀመድ ሱሩር ካራቴ እየሰራ ጩሀቱን እንጅ ስራዉን ማየት እንዳንችል ምክኒያቱም በጩሀቱ ብቻ ካራቲስት እንደሆነ እንድንመሰክር ።

ማህበረሰባችን በዚህ ብቻ አልቆመም በዲኗ ጠንካራ የሆነች ልጅ ተፈልጋ ተዳረ ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ የሙሀመድ ሱሩር ማንነት ይጋለጥ ጀመረ ።
ከላይ እንደተገለፀው  ሙሀመድ ሱሩር ቤተሰቦቹ የጁ ዉስጥ እንደ ሆኑ ያወራል ( በርግጥ አንዳቸዉም ቤተሰቡ ነኝ ብሎ የመጣ አላዉቅም ) ሰዉየዉ በአንድ ወቅት መርሳ ከተማ ላይ ለትልቅ እስላማዊ ዝግጅት ስንጓዝ ከፊት ወንበር ጋቢና ላይ ተቀምጧል ታላላቅ ዓሊሞችና ጎደኞቼ ከሓላ ተቀምጠን ከካራቲስትነት ከፍ ብሎ በሆነ ጦርነት ( ስሙን ረሳሁት ሀገር ዉስጥ በተደረገ ) ላይ ከሄሊኮብተር ሲወርድ እንደተጎዳ አገግሞ እንደ ዳነ ያወራል ።

ይህ ሰዉ በማበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት አገኘ የቁርአን ሂፍዝ ማእከሉ አድራጊ ፈጣሪ ሆነ ሚስትም አገባ ትንሽ ቆይቶ ሀኪም ነኝ የህክምና ት/ት መማር አለባችሁ ብሎ ከመርከዝ ልጆች አምስት ሰዉ መርጦ በጊዜዉ እኔ አብዱራህማን ሱልጧን ዶ/ር አህመድ ኑርየ ኢንጂነር ሙሀመድ ጀዉሀር ( አሏህ ይማረዉ ሁላችሁም ዱዓ አድርጉለት ) ሌሎች ሁለት ወንድሞቼ ረሳሃቸዉ ሁነን ለአንድ ሳምንት መርፌ እንዴት እንሚሰጥ አስተማረን እኔም በሳምንት የመርከዙ ሀኪም ሆኜ እርፍ !።

በጊዜዉ ለህክምና ብዙ ትልልቅ ሰዎች ይመጡ ነበር ቪ B2 ወግቶ በጊዜዉ የማይታመን ብር ነበር የሚጠይቀዉ ለምን የሚለዉም አልነበረም ።

ሚስት የሓላ ሓላ ስቃዪ በዛ ከአንድ የዲን መምህር ነኝ ከሚል ሰዉ የማይጠበቁ ነገሮችን ስታይ ለማን ትናገር ማንስ ያምናታል ።

የመርከዝ ልጆችም ለሁለት መከፈል ጀመሩ የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅም ያዮትንና የጠረጠሩትን ልጆች የኢማን ድክመት አለባቸዉ ፡ ጅሀድ ይጠላሉ የተለያዮ ስም እየለጠፈ የመርከዙ ልጆችን ከፋፈላቸዉ በመሀባ እንባ ይራጩ የነበሩ ወንድማማቾች ተኮራረፉ ።

ባጭሩ የወልዲያ ሰዉ ዳዒ አለመሆኑን እየተረዳ ይመስላል ስለዚህ ክትትል ጀምሯል ።

የሚገርሙ ታሪኮች ይቀጥላሉ ወልዲያ የጀመዓዉና የሚስቱ ታሪክ ከቆቦ እስከ ኮምቦልቻ  …..።

© Abdurahman Sultan

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Photo
በህንድ የአእምሮ ጤና እክል ያለባት ወጣት መለኮታዊ ኃይል አላት በሚል በመመለክ ላይ ትገኛለች

በታሚል ናዱ ግዛት የሂንዱ ከተማ በሆነችው ቲሩቫናማላይ ውስር ሚስጥራዊ ኃይል አላት የተባለችው ግለሰብ የአእምሮ የጤና ችግር ላይ ብትሆንም የሕንድ ማህበረሰብን ግን እያመለካት ይገኛል።

ህንዳውያን በርከት ያሉ አምላክ እና አማልክቶች ያሏቸው ሲሆን የሂንዱ አማልክቶች ሚስጥሮች እና እውነተኛ ህይወት ላይ በርካታ አወዛጋቢ ጉዳዮች ይነሳሉ። ከነዚህ መካከል ቶፒ አማ የምትባለው ኮፍያ የምታደርገው ሴት ብዙ ጊዜ ‘ሲድዳ’ እየተባለች በቅፅል ስም ትጠራለች። ይህችው ግለሰብ አዳኛችን ናት በማለት መመለክ ላይ ትገኛለች። አማኞች ፍፁም የሆነች ብሩህ ፍጡር ናት ይሏታል። ነገር ግን ዓለማዊ አመለካከት ላላቸው ሰዎች የህክምና እርዳታ የምትፈልግ የአእምሮ እክል ያለባት ሴት ናት።

ለአማኞች የሚታየቸው በቲሩቫናማላይ ጎዳናዎች ውስጥ ስትንቀሳቀስ ማንም በማይረዳው ጥንታዊ የታሚልኛ ቋንቋ ስትናገር ሲያዩ፣ ሌሎች ደግሞ ቤት የሌላት ምስኪን ሴት ያለ አላማ ስትቅበዘበዝ እና ስታጉረመርም ትውላለች ይላሉ። ሁሉም ነገር የአመለካከት ጉዳይ በመሆኑ ልዩነቶች መስተናገዳቸው ግድ ሆኗል።ቶፒ አማ የቲሩቫናማላይ ምልክት ከመሆኗ እና ብዙ ተከታዮችን ከመሳቧ በፊት የነበራት ህይወት እንቆቅልሽ ሆኖ በመቆየቱ ለታዋቂነቷ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል።

ሁለት ወጥ ቃላቶችን እንኳን በአንድ ላይ አሰካክታ መናገር አለመቻሏን መለኮታዊ ኃይል ቢኖራት ነው ብለው ህንዳውያኑ እንዲያስቡ አስገዷቸዋል። በህንዳውያኑ የማህበራዊ ድህረ ገፅ ተጠቃሚዎች ዘንድ ቶፒ አማ ከተማዋን እየዞረች የጠጣችውን የቡና ትራፊ የተባረከ መስዋዕት ነው በማለት ሰዎች አንስተው ሲቀምሱ ይታያል። በሌላ በኩል ይህችኑ ሴት የአዕምሮ ጤና ችግር ያለባት ፣ የቆሸሸ ልብስ የለበሰች ፣ ሰውነቷ ከመታጠብ የራቀ እና በአንዳች እክል ውስጥ እንዳለች ማስተዋል ይችላል።

አንድ የኤክስ ተጠቃሚ ባጋራው ፅሁፍ አንዳንዶች በአእምሮ ህመም እየተሰቃየች ነው ብለው የሚያስቡ እና እርዳታ ትሻለች የሚል ሰዎች ቢኖሩም ስለ እርሷ ውዳሴ የሚያቀርቡና የሚዘምሩ በርካቶች መሆናቸውን ፅፏል።ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ ጥበቧ ካልተገለጠልህ እሷን ማግኘት የሚችሉት የታደሉት ብቻ ናቸው ሲሉም አማኞች ይደመጣሉ።

አስደናቂው ጉዳይ የአእምሮ እክል ላይ የምትገኘው ቶፒ አማ በአብዛኛው አምላኪዎቿን ችላ ብላ የእለት ውሎዋብ ስታሳልፍ አንዳች ምስጢራዊ ኃይል እየተገለጠላት ነው ብለው የሚያስቡ አሉ። በዚህም የተነሳ በሄደችበት ቦታ ሁሉ በርካቶች ይከተሏታል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal