Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
465 subscribers
3.04K photos
187 videos
46 files
2.1K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
ኢናሊላሂ ወኢና ኤለይሂ ራጂኡን

ለኡስታዝ አቡበከር አህመድ ፈርድ ወንድም፣የወንድማችን አብዱሰላም ድንገተኛ ሞት ለሁላችንም አይቀርምና አላህ የወሰነው ውሳኔ በፀጋ መቀበል ብቻ ነው ምርጫችን። አላህ ይዘንልህ። ለመላው ቤተሰቡ ፣ የሥራ አጋሮችህ በሙሉ መፅናናትን እመኛለሁ። አላህ በጀነት ይሞሽርህ
በዚህ አመት ሐጅ ላልተሳካለት
~
ኢብኑ ረጀብ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:–

★ በዐረፋ መቆም ላልቻለ ከአላህ ወሰኖች ዘንድ ይቁም።

★ በሙዝደሊፋ ማደር ላልቻለ ወደ አላህ ያቃርበው ዘንድ ለትእዛዙ ይደር።

★ ሀድዩን (እርዱን) ሚና ላይ ማረድ ያልቻለ ከምኞቱ ይደርስ ዘንድ ስሜቱን ይረድ።

★እሩቅ በመሆኑ ቤቱ (በይተል ሐራም) መድረስ ያልቻለ የቤቱን ባለቤት ያስብ። ወደ እርሱ ከደም ጋኑ የቀረበ ነውና።"

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
አንዱ ፍልስጤማዊ አንዲህ ያወጋናል:-
ይህን አንቀፅ በፊት አነበው ነበር።ግን ዛሬ (በመጠለያ ሆኜ) ሳነበው ለኛ ለጋዛዊያን የወረደች እስኪመስለኝ ነው አዲስ የሆነብኝ።

فَالَّذِينَ هَاجَرُوا وَأُخْرِجُوا مِن دِيَارِهِمْ وَأُوذُوا فِي سَبِيلِي وَقَاتَلُوا وَقُتِلُوا لَأُكَفِّرَنَّ عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَلَأُدْخِلَنَّهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ثَوَابًا مِّنْ عِندِ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عِندَهُ حُسْنُ الثَّوَابِ
"እነዚያም የተሰደዱ ከአገሮቻቸውም የተባረሩ በመንገዴም የተጠቁ የተጋደሉም የተገደሉም ክፉ ሥራዎቻቸውን ከእነርሱ በእርግጥ አብሳለሁ፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በእርግጥ አገባቸዋለሁ፡፡ ከአላህ ዘንድ የኾነን ምንዳ (ይመነዳሉ)፡፡ አላህም እርሱ ዘንድ መልካም ምንዳ አልለ፡፡ »

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ጥቁር የለበሰው ሐምዛህ ሙስጠፋ ይባላል።ጋዛዊ የነሕዉ ኪታቦች ሙሐቂቅ ነው።ቀይ ሁዲ የለበሰው ጓደኛው ደግሞ መዕሩፍ ይባላል። መዕሩፍ ሸሂድ ከሆነ ወራት ተቆጥረዋል።ሐምዛ ሙስጠፋ በአሁን ሰዓት በስደተኞች ካምፕ ይገኛል።ስለ ጓደኛውም እንዲህ ያወጋል:-
"በህልሜ ሳላየው ቀርቼ አላውቅም።የመዕሩፍ አባት በህልሜ ደጋግሜ እንደማየው ሲያውቅ እያነባ ወደኔ መጣ።
"መዕሩፍን አባትህን ናና ዘይረው በልልኝ።" አሉኝ።ማዕሩፍ ሸሂድ ከሆነ አንስቶ ማየት አልቻሉም።
እኔም:-"ኢንሻ አሏህ እነግረዋለሁ።" ብይ ተለያያን።
ትናንት ማታ በህልሜ ተመለከትኩትና ስለሁኔታው ጠየቅኩት።ጥቂት ካወጋንም ወዲያ:-
"አባትህ በህልም ናና ዘይረኝ ይሉሃል።እንዴት እስከዛሬ ሳትዘይራቸው ቆየህ?"ስልም ቆጣ አልኩበት።

መዕሩፍም:-"ኢንሻ አሏህ እዘይራቸዋለሁ።"አለኝ።
ከነጋም ወዲህ ከአባቱ ጋር ተገናኘን።መዕሩፍ እንደዘየራቸውም ጠየቅኳቸው።
አባትም ፊታቸው በደስታ ተሞልቶ:-
"አልሐምዱሊላህ ሌሊት ጣፋጭ ኬክ እየበላ ተመለከትኩት።" አሉኝ።

በል አሕያእ

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ብንሄድ ይሻለናል

🥹🤌🏾🤎

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ለ ሐረመይን እንቅስቃሴ ይረዳ ዘንድ  መካ ፈጣን ባቡር 1.6 ሚሊዮን መቀመጫዎች የያዘ ፈጣን ባቡር በማቅረብ የሐጅ ወቅት ዝግጅት የሁጃጆችን እንቅስቃሴ ለማመቻቸት ነው ።

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
"የሙባረክ ልጅ ሆይ! ራስህን ካወቅክ ስላንተ የሚወራው ወሬ አይጎዳህም።"
አብዱላህ ቢን ሙባረክ
«"የኃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ " መጠነኛ ማሻሻያ ተደርጎበታል!» ተባለ።

" በሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ " ላይ የመጨረሻ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ረቂቁ ከባለፈው መጠነኛ ማሻሻያዎች ተደርጎበት መቅረቡን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
.
በመጀመሪያው ረቂቅ አዋጅ ያልነበረና የመንግሥትንና የክልሎችን ግዴታና ኃላፊነት በመዘርዘር የተቀመጠው ክፍል አንዱ ነው።

በዚህ ክፍል ላይ መንግሥት በሃይማኖት አስተምህሮና የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንደማይችል ተደንግጓል፡፡

በተጨማሪ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ አገር የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት ተደንግጎ የነበረው የረቂቅ አዋጁ ክፍል ከተሻሻለው ረቂቅ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

ነገር ግን ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ፦

° የሃይማኖት ተቋሙን ኦዲት ሪፖርት ለሰላም ሚኒስቴር እንዲያቀርብ፣

° የበጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ በ3 ወራት የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በገለልተኛ ኦዲተር ማስመርመር እንደሚኖርበት የተቀመጠው የረቂቁ ክፍል በተሻሻለው ላይ ተካቷል፡፡

ሌላኛው ተሻሽሎ የቀረበው የረቂቅ ክፍል አለባበስን እና የተማሪዎች አመጋገብን ጨምሮ በማንኛውም የትምህርት ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚደረግ ሃይማኖታዊ ተግባር የመንግሥትና ሃይማኖት መለያየት መርህንና የሃይማኖት ነፃነትንም በጠበቀ መንገድ መከናወን አለበት የሚለው ነው፡፡

የሰላም ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ምን አሉ ?

የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኩ የመጨረሻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በመንግሥት እና በሃይማኖት መካከል ያለው ልዩነት ምን ድረስ እንደሆነ ሳይታወቅ ቆይቷል ብለዋል።

አዋጁን ማዘጋጀትም ያስፈለገው ይህን ጉዳይ በግልጽ ለማስቀመጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

መንግሥት በሃይማኖት ተቋማት ነፃነት ውስጥ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው  ፤ ነገር ግን አብረው በሚሠሩባቸው ጉዳዮች በሕግ የተቀመጠ አሠራር ሊኖር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የተነሱ ሐሳቦችን በግብዓትነት ወስዶ ለሚመለከተው አካል የሚቀርበውን ረቂቅ አዋጅ እንደሚያዘጋጅ ተገልጿል፡፡»

©: Reporter Newspaper



የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
4_5969541672814515322.pdf
262.9 KB
የተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ
==================

«ማንነትን ለመለየት በማያስችል መልኩ» የምትለዋን የአንቀፅ 19 ቁጥር 6 ሃሳብ ቀይረዋታል።
ነገር ግን የኒቃብን ጉዳይ በግልፅ ቢያስቀምጡት ያዋጣቸው ነበር። ነገሩን ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ስላዞሩት፤ ትምህርት ሚኒስተር በዚህ ረገድ በዝርዝር የሚያወጣውን መረጃ አብረን እናያለን። ኒቃብን ከተቃወመ ትግላችን ከርሱ ጋር ይሆናል። ግን የነዚህን «ማንነትን ለመለየት» ብለዋት የነበረችውን ኒቃብን መከልከያ ዘዴ መሆኗ ስለተነቃባቸው ቀይረዋታል።

እስኪ አብረን እናያለን።

ግን ዝም ብሎ ከማንቀላፋት በግልፅ መናገር እንደሚያዋጣ እየተዛባችሁ! መብታችንን ለምነን ሳይሆን ማስከበር መቻል አለብን።

አሁንም ትኩረት ወደ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ እናዙር። ረቂቅ አዋጁም ላይ በቡድን አምልኮ በሚል ሽፋን የጀማዓህ ሶላት እንዳይከለከል ማስረገጥ ግድ ይላል።

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
የኢብራሂም ﷺ ጎዳና ሽብርተኝነት ነው?

በአላህ ﷻ መንገድ ጥሪ ላይ ከባባድ ፈተናዎችን  ካስተናገዱ ነብያት የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው ኢብራሂም ነው። ለኢስላም ሲል ከነህይወቱ እሳት ውስጥ የተወረወረ ብቸኛ ነብይ!

ታሪክ ሆኖ ስለሚነበብ ቀላል ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ወደራስህ መልሰህ ስታየው  ከባድነቱ  ይገለፃል። "አላህን ብቻውን አምልኩት ጣኦታትንና አምላኪዎቻቸውን እርግፍ አድርጋችሁ ተው" ብለህ ተጣርተህ የአንድ ከተማ ሙሉ ህዝብ ተሰብስቦ አንድም ረዳት ላንተ በሌለበት ተጨባጭ እጅህ ወደ ኋላ ተጠፍሮና  ታስሮ  የተጋጋመ እሳት ውስጥ ልትወረወር ነው።የነበልባሉ ወላፈን ከቅርብ ርቀት እየደረሰህ ነው  ምን ይሰማሃል !?

... ከዚያም ሁለት ምርጫ ቀረበልህ ።ይህን ጥሪህን ማቆም አለያም እዚህ እሳት ውስጥ መወርወር። የትኛውን እንደምትመርጥ ግልፅ ነው። "ይሄ ዑዝር ነው አላህም ቀልቤ ካልካደ አይቀጣም"  ብለህ ማቆም ነው።

የኢብራሂም ﷺ ፅናት ልዩ የሆነው ለዚህ ነው።
ከአቋሙ አልተመለሰም ፤ ይልቁንም ያለበት አቋም ሐቅ መሆኑን ይበልጥ አወቀ ፤ በአላህ ላይ ኢማኑ ይበልጥ ጠነከረ። ወደ እሳቱም በሙሉ የአላህ ወዳጅነት ተወርወረ።

ምን ይህ ብቻ ! የአላህ ኸሊል ኢብራሂም እሳት ውስጥ ተወርውሮ እገዛን ከፍጡራን አልተመኘም፤  አልፈለገም። ጂብሪል ምን ልርዳህ ቢለው "ካንተ ከሆነ ተወው ከአላህ ከሆነ ብቻ"  ነበር ምላሹ። የየቂን ጥግ ማለት ይህ ነው ፤ የልጅ ልጁ ሙሐመድም  ﷺ እንዳደረገው ሰይፍ ተመዝዞበት ማን ያድናሃል ቢባል "አላህ"  ሲል መለሰ

ይህን ታላቅ ነብይ ታዳ አላህ መልእክተኛውንም እኛንም አርአያ እንድናደርገው ደንግጓል። መልእክተኛውን  ﷺ   እንዲህ ይላቸዋል፦

"ከመልክተኞችም የቆራጥነት ባለቤቶች የኾኑት እንደ ታገሱ ሁሉ ታገስ፡፡ " [አል አሕቃፍ፤ 35]

በሌላም አንቀፅ፦
"ከዚያም ወደ አንተ የኢብራሂምን ሃይማኖት ቀጥተኛ ሲኾን ተከተል፤ ከአጋሪዎቹም አልነበረም ማለት አወረድን፡፡"
[አን ነሕል፡ 123]

አላህ የኢብራሂምን ልቅና ከፍ ሲያደርገው ከእስልምና ማእዘናት  አንዱ የሆነውን ዒባዳ በርሱና በቤተሰቦቹ ታሪክ ላይ የተመሰረተ አደረገ።

ከዘምዘም ብትጎነጭ ኢስማዒል ይታወሳል፣ ሶፋና መርዋ ላይ ብታሶመሱም እናታቸው ሃጀር ትዘከራለች። የእርድ ስነስርአቱ የኢስማዒልን  ፊዳእ  ያስታውሳል፣ ጠጠር ውርወራው ኢብሊስ ኢስማዒልን እንዳያርድ ሊወሰውስ ሲመጣ በጠጠር መደብደቡን ያስታውሳል፣ መቃሙ ኢብራሂም  ጋር ብትሰግድ ካዕባን ሲገነባ እንደ አሳንሰር ሲያገለግል የነበረው ድንጋይ ታሪክ አለበት። ጠዋፍ የሚደረግበት ካዕባህ ደግሞ ኢብራሂምና ልጁ  መሰረቱን ከፍ ያደረጉት ቤት ነው።

ከዚህና ከሌሎች የኢብራሂም ﷺ  የልቅና መገለጫዎች በኋላ አላህ የኢብራሂምን መንገድ እንድንከተል አዘዘ። የኢብራሂም መንገድ ምንድን ነው? ስንል በዋናነት ጣኦታትን መሰባበር በውስጡ አለበት።

በዚህ 21ኛው ክ/ዘመን እያሉ በሚቀድሱት የጃሂሊያ ዘመን አንድ የኢብራሂምን ﷺ መንገድ ተከታይ ነኝ የሚል ሙወሒድ  ቤተ ጣኦት ገብቶ ጣኦታትን ቢሰባብርና ይህ የረሱል  ﷺ መንገድ ነው ቢል  ከሌላው በፊት ቀድሞ የሚስቅበትና ሽብርተኛ የሚለው "ሙስሊሙ" ነው። እርሱ ግን የጠላም ቢጠላ የኢብራሂም መንገድ ነው።

አላህ እንዲህ አለ ፦
«በአላህም እምላለሁ ዟሪዎች ኾናችሁ ከሄዳችሁ በኋላ ጣዖቶቻችሁን ተንኮል እሠራባቸዋለሁ »  (አለ)፡(ዘወር ሲሉ) ስብርብሮችም አደረጋቸው፡፡ ለእነሱ የኾነ አንድ ታላቅ (ጣዖት) ብቻ ሲቀር ወደርሱ ይመለሱ ዘንድ (እርሱን ተወው)፡"
[አል አንቢያእ 57_58]

በዚህ አንቀፅ ውስጥ አላህ የኢብራሂምን ድርጊት አውግዞ ሳይሆን ወድዶትና አርአያ እንዲደረግ ሽቶ  ተርኮልናል። የኢብራሂምን ጎዳና ተከተል ሲል መልእክተኛውንም  ﷺ ያዘዘው በዚሁ ላይ ነው።

ኢብራሂም ﷺ ካልሰለሙ መቻቻል ነው  ብሎ አልተቀመጠም ፤ ይልቁንም በግልፅ ቋንቋ ከአላህ ውጭ ለሚያመልኳቸው ጣኦታት እንደሚያሴርባቸው  ገልፆላቸው አማልክቶቻቸውንም አውድሟል።

አላህ ኢብራሂምን ተከተሉ ሲል ይህ የኢብራሂም ድርጊቱ ትክክል ነው ብሎ እያፀደቀ መሆኑ ግልፅ ነው።

ሌላው የኢብራሂም ﷺ ጎዳና ልዩ የሚያደርገው በውስጡ ካሀዲያንን መጥላትና ከነርሱም መጥራራትን የያዘ መሆኑ ነው ። ይህ ደግሞ ዛሬ ላይ በፅንፈኝነትና በአክራሪነት የተፈረጀ አስተሳሰብ ሆኗል። ምሳሌ አንድ ዳዒ ይህንን በአደባባይ ወጥቶ ቢናገር በምን እንደሚፈረጅ ግልፅ ነው። 

"በኢብራሂምና በእነዚያ ከእርሱ ጋር በነበሩት (ምእምናን) መልካም መከተል አለቻችሁ፡፡ ለሕዝቦቻቸው «እኛ ከእናንተ ከአላህ ሌላ ከምትግገዙትም ንጹሖች ነን፡፡ በእናንተ ካድን፡፡ በአላህ አንድ ብቻ ሲኾን እስከምታምኑ ድረስ በእኛና በእናንተ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር ተገለጸ፡፡» ባሉ ጊዜ (መልካም መከተል አለቻችሁ)፡፡ ኢብራሂም ለአባቱ «እኔ ለአንተ ከአላህ (ቅጣት) ምንም የማልጠቅም ስኾን ለአንተ በእርግጥ ምሕረትን እለምንልኻለሁ» ማለቱ ብቻ ሲቀር፡፡ «ጌታችን ሆይ! በአንተ ላይ ተመካን፡፡ ወደ አንተም ተመለስን መመለሻም ወደ አንተ ብቻ ነው፤» (ባለው ተከተሉት)፡፡"  [አልሙንተሒና፡ 4]

በዚህ አንቀፅ ውስጥ "በአላህ አንድ ብቻ ሲኾን እስከምታምኑ ድረስ በእኛና በእናንተ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር ተገለጸ፡፡»" የሚለው አንቀፅ ዛሬ ላይ የሚጣራበት እርሱ ፅንፈኛና የሃይማኖት መቻቻልን የማይቀበል ወንጀለኛ የሚያስብል መሆኑ ማስረጃ አይሻም።

ወደ ማጠቃለያው ስመጣ ዛሬ ላይ ሽብርተኝነት ተብሎ የተፈረጀው የኢብራሂም ﷺ ጎዳና ነው ለማለት ነው።ሽብርተኛ የሚባሉትም የኢብራሂምን ጎዳና የሚከተሉ ሙወሒዶች ናቸው።

ሽብርተኛ ላለመባል ከኢብራሂም መንገድ መሸሽ ወንጀላችን ሆኖ ሳለ በርሱ የሚጣራን ማንቋሸሽ ደግሞ ተውሒዳችንን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ አደጋ ነው ።  አላህ ይድረስልን!

Via ismail nuru

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal