Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
462 subscribers
3.03K photos
184 videos
46 files
2.1K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
እውቀት ማለት የተሸመደደ ሳይሆን የተጠቀምክበት ነው !
       ኢማሙ ሻፊዒይ ረሂመሁላህ
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Photo
ልዩ “ኸበር” - ከ6 ዓመት ሕፃን ዕድሜ የጀመረ የሐጅ ትዝታ

ኤንዶኔዥያዊቷ እናት መርየም ሙሐመድ ሙኒር፣ ከሰሞኑ ሳዑዲ ዐረቢያ ተገኝተዋል፡፡ እናት መርየም ሳዑዲ የተገኙት ለዓመታዊው የሐጅ ሥርዐት ክንውን ነው፡፡ የ66 ዓመት ዕድሜ ያላቸው እናት፣ ከ60 ዓመት በፊት በ6 ዓመታቸው በተመሳሳይ አሁን የተገኙት ሥፍራ ላይ ነበሩ፡፡

ያን ጊዜ ግን ዕድሜያቸው 6 ዓመት ብቻ ነበር፡፡ ክፉ እና ደግ የሚለዩም አልነበሩም፡፡ ወላጆቻቸው ለሐጅ ሲያቀኑ አስከትለዋቸው ነው፡፡

እናት መርየም በ6 ዓመት ዕድሜያቸው ጀምረው በተደጋጋሚ ለሐጅ እና ዑምራ ሳዑዲ ዐረቢያ ተመላልሰዋል፡፡ የሳዑዲ ዜና አገልግሎት እንዳለው ከሆነ ኢንዶኔዥያዊቷ እናት የዘንድሮው ጉዟቸው ለ22ኛ ጊዜ የተከናወነ ነው፡፡

እናት መርየም በእነዚህ ስድስት ዐስርት ዓመታት የቆየ የሐጅ ትዝታቸው ውስጥ፣ የሚያስገርሟቸው ነገሮች ምን እንደሆኑ ተጠይቀው ነበር፡፡ ኢንዶኔዥያዊቷ እናት አንደኛው ጉዳይ ከሀገራቸው ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ለመጓዝ የመንገዱ ማጠር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

እናት መርየም ከ60 ዓመት በፊት ከወላጆቻቸው ጋር ወደ ሐጅ ሲጓዙ አሁን እንዳደረጉት በአውሮፕላን አልበረሩም፡፡ ባይሆን አነስተኛ መጠን ያላቸው መርከቦች እየተፈራረቁ አድርሰዋቸዋል፡፡ መርከቦቹ ከኢንዶኔዥያ ተነስተው ሳዑዲ ለመድረስ ሕንድን፣ ዐረቢያ እና ቀይ ባህርን ማቋረጥ ነበረባቸው፡፡ እንደ እናት መርየም አገላለጽ ያን ጊዜ የነበረው ከአምስት እስከ ስምንት ሰዓት የሚፈጅ የሐጅ ጉዞ፣ ከሚበላው ገንዘብ እና ጊዜ በተጨማሪ አደገኛ እና አስፈሪ ነበር፡፡

እናት መርየም ከ60 ዓመት በኋላ ከጃካርታ ሳዑዲ ዐረቢያዋ ቅድስት ከተማ መዲና ለመድረስ 9 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ብቻ በአየር ላይ በአውሮፕላን በርረዋል፡፡

የእናት መርየም ሀገር ኢንዶኔዥያ፣ በዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት እርሳቸውን ጨምሮ 241 ሺሕ ምዕመናንን ወደ ሐጅ ሥነ ሥርዐት ትልካለች፡፡

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቁርአን ልባችን ላይ እንዲቀመጥ ከፈለኝ አካላችንን ብቻ ሳይሆን ልባችንንም ማጽዳት አለብን! ቁርአን የሚነበብ ብቻ ሳይሆን ለሁለት ዓለም ስኬት የሚያበቃ የህይወት መንገድ ነው።

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Photo
ልዩ “ኸበር” - የሳዑዲ ዐረቢያ የሐጅ ሽር ጉድ በመጨረሻው ሰዓት

ከመላው ዓለም ለሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ወደ ሀገሯ ይገባሉ ተብለው የሚጠበቁትን ከሁለት ሚሊዮን የሚልቁ ምዕመናንን መቀበል የጀመረችው ሳዑዲ ዐረቢያ፣ የአላህ እንግዶች ከቤት የወጡበትን ውጥን እንዲሞሉ ሽር ጉድ ማለቷን ቀጥላለች፡፡ ሳዑዲ እንግዶችን መቀበል የጀመረችው ግንቦት 1/2016 ነበር፡፡ እስካሁን ከተቀበለቻቸው ውስጥ ከእኛዋ ኢትዮጵያ የተነሱ ምዕመናን ይገኙበታል፡፡ 12 ሺሕ ኢትዮጵያውያን እስከ ሰኔ 2/2016 ድረስ ሳዑዲ ዐረቢያ ተጠናቀው ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በርግጥ ሳዑዲ ዐረቢያ ሑጃጆችን መቀበል ጀምራም ቢሆን ለዑምራ እና ሌላ ጉዳይ (ለምሣሌ ለጉብኝት) በተለይ መካ ከተማ የሚጓዙ የሀገሯን ሰዎችም ሆነ እንግዶችን ስታስገባ ቆይታለች፡፡ ሆኖም ከዛሬ ሐሙስ ግንቦት 15/2016 አንስቶ ለሐጅ ካልሆነ በስተቀር የከተማዋን በር መቆለፏን እወቁት ብላለች፡፡ በዚህም ወደ ቅድስቲቱ መካ ከተማ የሚያስገቡ የፍተሻ ጣቢያዎች፣ ከሑጃጅ ውጪ ሌላ ሰው ወደ ውስጥ እንዳይዘልቅ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ሳዑዲ ዐረቢያ ከሚቀጥለው ሳምንት ግንቦት 25/2016 ጀምሮ ደግሞ፣ በድንገት ያለ ሐጅ ቪዛ ወደ መካ ከተማ ዘልቆ ያገኘችውን ግለሰብ እንዲሁ አትለቀውም፤ 10 ሺሕ ሪያል መቀጮ እንደምታስከፍለው ቀድማ አሳውቃለች፡፡ ቅጣቱ በዚህ ብቻ ላይቆም ይችላል፤ ከተደጋገመ ከምድሯ ያስባርራል፡፡

ሳዑዲ ዐረቢያ ወደ ሐጅ ቀናት ስትቃረብ፣ ከሐጅ ቪዛ ውጪ የያዙ ምዕመናንን ወደ መካ እንዳይገቡ ከማገድ ጎን ለጎን ሐጅ መድረሱን ጠቋሚ የሆነውን የካዕባን ልብስ ከፍ አድርጋለች፡፡ ሳዑዲ በየዓመቱ የሐጅ ቀናት ሲቃረቡ ይህን የምታደርገው በጥንቃቄ ነው፡፡ ዘንድሮም ኪስዋውን ከመሬት ከፍ ለማድረግ 36 ባለሞያዎችን ከአስር “ክሬን” ጋር መድባለች፡፡ ባለሞያዎቹ ልብሱን ከፍ አድርገው በአራቱም ማዕዘን በነጭ የጥጥ ጨርቅ እንዲሸፈን (ኢህራም) አድርገውታል፡፡

ኢህራም የተደረገው ኪስዋ በየዓመቱ የሚቀየር ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚጀምረው በዙልሒጃ ወር 9ኛው ቀን ይቀየር የነበረ ቢሆንም በቅርብ ጊዜያት በአዲሱ ዓመት መግቢያ ሙሐረም ወር የመጀመሪያው ምሽት እንዲቀየር ተወስኗል፡፡

ኪስዋ የዓለማችን ውዱ ልብስ ነው፡፡ የልብሱ ክብደት 850 ኪሎ ግራም ሲመዝን፣ ወጪው ደግሞ 6.5 ሚሊዮን ዶላር ይገመታል፡፡ ኪስዋ ሲዘጋጅ ቢያንስ 200 ባለሞያዎች ይሳተፋሉ፡፡ የኪስዋ 670 ኪሎ የሚመዝነው ጥቁር ሀር ነው፡፡ በዚህ ሀር ላይ ለሚጻፉ የቁርኣን አንቀፆች 120 ኪሎ 21 ካራት ወርቅ እንዲሁም 100 ኪሎ ግራም ብር ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ሁልግዜ መልካም ነገርን ስራ...ያ መልካም ስራህ ባላሰብከው መንገድ ወዳንተ ይመለስልሀል!!
“ውዱዑ አድርጎ ውዱዑን ያሳመረው ሰው፤ ኃጢአቶቹ ከጥፍሮቹ ስር እንኳ ሳይቀር ከአካላቱ ይወጣሉ።”
ረሱል ﷺ
“በምድር ላይ ካሉት ውሃዎች ምርጡ የዘምዘም ውሃ ነው። በምግብነት ለተጠቀመው ምግብ ለበሽታ ለተጠቀመው ደግሞ መድኃኒት ነው።”
ረሱል ﷺ
አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት ወርቃማ ቀናቶች

ጌታችን አላህ በራሱ ካላቃቸው እና ካከበራቸው አራት ወራቶች መካከል የዙልሒጃ ወር አንዱ ነው:: ከቀናቶች ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስር ቀናቶችም ያሉት በዚሁ በተከበረው የዙልሒጃ ወር ውስጥ ነው::

እነዚህ አስር ውድ ቀናቶችም ጌታችን አላህ(ሱወ) ምሎባቸዋል::

የአላህ መልዕክተኛ (الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል፤

ጃቢር ኢብኑ ዓብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል «ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው፤ አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው » አልበዛር እና አልሐይሰሚይ ዘግበዉታል አልባኒም ሰሂህ ብለዉታል (ሰሂሁል ጃሚዕ 1133)

በነዚህ ውድ ቀናቶች የሚሰሩ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ እና በላጭ ናቸው::

ከኢብኑ ዓባስ በተዘገበ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፤ «በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈጸም መልካም ስራዎች በበለጠ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆኑባቸው ቀናት የሉም፤ “በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሀድም ጭምር?” ተባሉ። እርሳቸውም፤ “ራሱንና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ምንም ያልተመለሰለት ሰው ሲቀር ጂሀድም ከዚህ አይበልጥም” አሉ።» ቡኻሪ ዘግበውታል

በመሆኑም እነዚህን ውድ ቀናቶች በተገቢው መልኩ ልንጠቀምባቸው ይገባል:: በነዚህ ውድ ቀናቶች ከሚወደዱ ኢባዳዎች መካከል:-


1. ጾም ከስራዎች ሁሉ በላጭ ነውና በእነዚህ ቀናት መጾም እጅግ የተወደደ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ዘጠኙን የዙልሂጃ ቀናት ይጾሙ እንደነበር ተዘግቧል። (አስረኛው ቀን ግን ዒድ ስለሆነ አይጾምም)

2. ዚክሮችን ማብዛት ቁርዓን መቅራት ፤ አላህን ማመስገን (አልሀምዱሊላህ) ፣ ተክቢር፣ ተስቢህ(ሱብሀነላህ) እና ተህሊል (ላ ኢላሀ ኢለላህ)፤ ኢባዳዉን ለማስታወስና የአላህን ስም ከፍ ለማድረግ በተለያዩ አጋጣሚዎች ድምጽን ከፍ አድርጎ እነዚህን ዚክሮች ማድረግ ይወደዳል።

ዓብዱላህ ኢብኑ ዑመር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩه እንዲህ ብለዋል፤«ከእነዚህ አስር ቀናት በበለጠ አላህ ዘንድ ታላቅ የሆኑና መልካም ስራ እጅግ የተወደደባቸው ቀናት የሉም፤ ስለዚህ ተህሊል ተክቢር እና ተህሚድ አብዙ» አል ኢማም አህመድ ዘግበውታል

3. ሐጅ ማድረግ በነዚህ ቀናት ውስጥ ከሚፈጸሙ መልካም ስራዎች መካከል ሐጅ ማድረግ ይገኝበታል፤ በነዚህ አስር ቀናት አቅሙ ለቻለ ሰው የሐጅ ዒባዳ ላይ ተገኝቶ በተገቢው መልኩ ከፈጸመው በአላህ ፍቃድ ከተከታዩ የአላህ መልዕክተኛه ብስራት ድርሻ ይኖረዋል፤

ከአቡ ሁረይራ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛه እንዲህ ብለዋል፤ «ከወንጀል የራቀና ተቀባይነት ያለው ሐጅ (አል-ሐጅ አል-መብሩር) ምንዳው ጀነት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡» ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል

4. ኡድሂያ- በነዚህ አስር ቀናት ከተወደዱ ተግባሮች መካከል ኡድሂያን በማረድ ወደአላህ መቃረብ ነው።
ኡድሂያን ለማረድ ያቀደ ሰው የዙልሂጃ ወር ከገባ ጥፍሩንና ጸጉሩን መቁረጥ የለበትም::

5. የፈርድ ሰላቶችንን ጠብቆ በጀምዓ መስገድ፣ የሱና እና የለሊት ሰላቶችን ማብዛት

6. ለወላጆች መልካም መዋል

7. ለተቸገሩ ወገኖች ሰደቃ ማብዛት

8. የታሰረን ወይም የታመመን ሰው መጠየቅ፣

9. ዝምድናን መቀጠል፣

10. ለራሳችንም ለሀገራችንም ለኡማውም በብዛት ዱዓን ማብዛት ያስፈልጋል።

11. ተውበት ማድረግ

በነዚህ ውድ ቀናቶች ከተጠቀሱት ውጪ ያሉትንም መልካም ስራዎች በሙሉ መስራት ምንዳው ላቅ ያለ ነው::

እነዚህን ወርቃማ ቀናቶች በኢባዳ ከሚያሳልፉት አላህ ያድርገን 🤲

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ቁርኣንን ለልባቸው ቀለብ ያደረጉ፤ ምንኛ ታደሉ?
ሚና!
"ደስታ ማለት አላህን ለመታዘዝ መወፈቅ ነው አንድ ሰው አላህን ለመታዘዝ ተወፍቆ ካየሀው ደስተኛ መሆኑን እወቅ"
ያኔ ላቦራቶሪ ባልነበረበት፤ ደምህ ከፍ ብሏል፣ ሙቀትህ ጨምሯል፣ ስኳርህ ተባብሷል ... የሚል ወሬ በማንሰማበት ዘመን እኮ በጣም ተረጋግተን ነበር የምንኖረው።
ዛሬ ላይ የሚያሸብረን ነገር በዝቷል። ደሜ ከፍብሎ፣ ስኳሬ ጨምሮ፣ ሪሕ ተገኝቶብን .. እያልን በራሣችን ላይ ሽብር !!

አንዳንድ ጊዜ በሽታን በመሸሽ ብቻ በሽታ ላይ እንወድቃለን ።
ሞትን በመፍራትም በተደጋጋሚ እንሞታለን ።
በጣም ተጠንቅቀን ከምንኖረው ይልቅ ዝምብለን የምንኖረው ኑሮ እንዴት ደስ ይላል መሠላችሁ ።

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal