Bilaluna Edris
559 subscribers
3.35K photos
276 videos
50 files
2.3K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
4_5850471465538818397.mp4
1.9 MB
🇵🇸🇮🇱🚨 የእስራኤል ወታደሮች ወደ ጋዛ ነዋሪዎች የሚያስተላልፈውን የውሃ አቅርቦት ሲቆርጡ..

በሮም ስምምነት መሰረት "ሆን ብሎ የሲቪሎችን ረሃብ እንደ ጦርነት ዘዴ በመጠቀም ለህይወት አስፈላጊ የሆኑትን እንደ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ውሃውን መመረዝ እንደ የጦር ወንጀል ይቆጠራሉ።" ሲል ይደነግጋል።

#Gaza #ጋዛ #Palestine #Israel #ፍልስጤም #እስራኤል #peaceandlove

Via esleman abay

https://t.me/Xuqal
Forwarded from Esleman Abay የዓባይ ልጅ (Esleman)
በመጋቢት 16 2003 በፈረንጆቹ የዘመን ቀመር፣ አሜሪካዊቷ የመብት ተሟጋች ራቸል ኮሪ እስራኤል የፍልስጤማውያኑን መኖሪያ ቤት እንዳያፈርሱ ለመቃወም በእስራኤል ቡልዶዘር እና በፍልስጤም መኖሪያ ቤቶች መካከል የፍትህ ብርታትን ተመርኩዛ ቆመች - አታፈርሱም አለቻቸው - የእስራኤል ቡልዶዘሮች ታዲያ ያለ ርህራሄ እየተመላለሱ ነበር የገደሏት።

አሜሪካዊት ራቸል(23) ከዋሽንግተን ነበር በወቅቱ ወደ ፍልስጤም ያመራችው። የፍልስጤም አለም አቀፍ ተሟጋቾች ቡድንን የተቀላቀለች ሰትሆን የእስራኤልን የሰብአዊ መብት ረገጣ በአመፅ ቀጥተኛ እርምጃ ነበር።

በተገደለችበት ዕለት እሷ እና ሌሎችም የበጎ ፈቃደኞች ቡድን አባላት በግልፅ መታየት እንዲችሉ ፍሎረሰንት ጃኬቶችን እና ምልክቶችን ለብሰው በራፋ ጋዛ የሚገኙ የፍልስጤም መኖሪያ ቤቶችን ከእስራኤል አፍራሽ ቡልዶዘሮች ለመታደግ ቆመዋል።

የእስራኤላውያን ቡልዶዘሮች፣ ለሁለት ጊዜ ያህል እየተመላለሱ ዳምጠው ገደሏት።

"መጥፎ ቅዠት ነው ያየሁት ዛሬ - ከቤታችን አጠገብ እኔና አንቺ ከቡልደዘር ውስጥ ሆነን .. [...] ብቻ ... እዚህ ለሚኖሩ ሰዎች በእውነት በጣም ነው የምሰጋላቸው።" - ራቸል ኮርሪ የእስራኤል ቡልዶዘር ህይወቷን ከመቅጠፋቸው ሶስት ሳምንታት በፊት ለእናቷ በላከችው የኢሜይል መልእክቷ የከተበችው ነበር...።

በወቅቱ የትልቁ ቡሽ አስተዳደር እስራኤል "በአደጋ የተከሰተ ሞት" ሲል የሰጠው ምላሽ ፍፁም ውሸት መሆኑን ቢገነዘብም ተጠያቂ ለማድረግም ሆነ የሚመራው መንግስት የራሱን ምርምራ እንዲያደርግ ፈቃዱ ሳይሆን ቀርቷል።

የልጃቸውን ግድያ ተከትሎ ወላጆቿ ከአሜሪካ እና ከእስራኤል አንዳች አይነት ፍትህ እና ተጠያቂነት እንዲመጣ ለአስር ያህል አመታት ያደረጉት ያላሰለሰ ድካም በከንቱ ነበር የቀረው።
በአንፃሩ ፍልስጤማውያኑ ራቼልን እስከ ዛሬም ድረስ ሲያወሱ ለፍትህ እና ከተበዳዮች ጎን የቆመችበት ፅኗቷን በተለዬ በመዘከር ነው።

#የዓባይልጅ Esleman Abay #ፍልስጤም #Israel #ጋዛ #Gaza #Palestine #peaceandlove
"አላህ ህዝቦችን ሲወዳቸዉ በችግር ይፈትናቸዋል"
ረሱል ﷺ

#ጋዛ #ፊሊስጢን 🇵🇸
ፍልስጤም በሚያማምሩ የወይራ ዛፎቿ ትታወቃለች።  ፍልስጤማውያን ከመሬታቸው ጋር ያላቸውን ሥር የሰደደ ትስስር ይወክላሉ ይባልላቸዋል። ፍልስጤማውያኑ የወይራ ዛፎቻቸውን በፍቅር እና በአድናቆት ነው የሚንከባከቧቸው። ከ 4,000 ዓመታት በላይ እድሜ ካላቸው ጥቂት የዓለማችን ጥንታዊ የወይራ ዛፎች መካከል ናቸው በፍልስጤም የሚገኙት። በጥራቱ ምርጥ የተባለለትን የወይራ ዘይት ያቀርባሉ። በእስራኤል ወረራ በተያዙት ዌስት ባንክ እና ጋዛ በሚገኙ የእርሻ መሬቶቻቸው ግማሹ የፍልስጤም የወይራ ዛፍ ተተክለው የሚገኙበት ነው። በነዚህ ቦታዎች ብቻ የተተከሉ ወይራ ዛፎች ቁጥር 10 ሚሊዮን ይደርሳል።
ለእያንዳንዱ ፍልስጤማዊ የወይራ ዛፍ ማለት የትውልድ ትስስርና የፅናት ተምሳሌት ነው። እናት ልጆቿን እንደምትንከባከበው ሁሉ የወይራ ዛፍ መሬታቸውን በየቀኑ በመንከባከብ ያሳልፉ ከነበሩ ቅድመ አያቶቻቸው ጋር ያሰናስላቸዋል።
ወይራ በእስልምና የተባረከ ፍሬ ነው። ይህም በቁርኣንና በሐዲስም በተደጋጋሚ ተጠቅሷል።  የወይራ ዛፍ መትከል ለብዙ አመታት የወይራ ፍሬዎችን ለትውልድ ያበረክታል። ይህ የማይቋረጥ ልግስና ተግባር (ሰደቃህ ጃሪያህ) ምንዳ ያጎናፅፋል። እርሶንም ሆነ የሚወዷቸውን ሰዎች ከህልፈትዎ በኋላም ሊጠቅም ይችላል።  የወይራ ዛፍ "የሕይወት ዛፍ" ተብሎም ይጠራል።
    ይህ በንዲህ እንዳለ እስራኤል በዚህ አመት ፍልስጤማውያኑ የወይራ ፍሬ እንዳይለቅሙ ከልክላቸዋለች። ይህ ወቅት ለፍልስጤማውያን የወይራ ፍሬያቸውን ለቅመው ትኩስ የሆነውን የወይራ ዘይት ለገበያ የሚያጓጉዙበት የአመቱ ወሳኝ የመኸር ወቅት ነው።

#Gaza #ጋዛ #israel #ፍልስጤም #Palestine #olivetree #OlivePalestine #PaleatineOlive

https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
"የጋዛው ጦርነት በተራዘመ ቁጥር እስራኤል እና የአሜሪካ (ዓለም አቀፋዊ) መገለል ይበልጥ እየከፋ ይሄዳል"
    - The New York Times

በርካታ ሀገራት የተኩስ አቁም ጥሪ በማቅረብ ላይ ናቸው' ያለው ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ፣ ነገር  በርካታ የአሜሪካ ባለስልጣናት በጋዛ እስራኤል የምታደርገው ጥቃት ለሐማስ ጥቃት ጠንካራ ምላሽ በመስጠት "የታገቱ ዜጎቿን ለማስለቀቅ ነው ሲሉ ነግረውኛል" ይላል። ይሁንና በጋዛ የ 10,000 ሰዎች መሞት ነው የተከሰተው ብሏል ጋዜጣው።

በአሜሪካ ስለሚደገፈው የእስራኤል ጥቃት ሌላው መነሳት ያለበት ነጥብ በማለት የፃፈው Ne York Times "በሲቪሎች ላይ እየደረሰ ያለው አስከፊ ጥቃት አዲሱን የፍልስጤም ትውልድ እልክና ቁጣ ውስጥ የሚከት መሆኑ ነው።" ብሏል።

የእስራኤል የውስጥ ደኅንነት አገልግሎት ኃላፊ የነበሩት ያኮቭ ፔሪ የተናገሩትን የጠቀሰው ጋዜጣው “በአራት ወይም በአምስት ዓመታት ውስጥ እንደገና ከልጆቻቸው ጋር እንዋጋለን” ብለዋል።

#ጋዛ #GAZA #PALESTINE 🇵🇸

https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
#ስለፍልስጢን_ምንአዲስ?
ዛሬ የሃማስ የፖለቲካ ቢሮ ከፍተኛ ባለስልጣን #ዒዘት_አልሪሽቅ መግለጫ ሰጥቷል!
ከንግግሮቹ መካከል የተወሰኑት የሚከተሉት ናቸው!👇
•ባይደን በጋዛ የዘር ማጥፋት ጦርነት ውስጥ #ሙሉ አጋር ነው! ህዝባችን ከእርሱ ምንም ጥሩ ነገር አይጠብቅም።
•ባይደን ስለ ፍልስጤም መንግስት ምስረታ እና  የመንግስቱ መዋቅር ምን መምሰል እንዳለበት ለመናገር እየሞከረ ያለበት #ቅዠት ህዝባችንን አያታልለውም!
•እራሳቸውን እንደ ፍልስጤም ህዝብ ጠባቂ አድርገው የሚያስቡ አካላት(ማህሙድ ዐባስ የሚመራውን የፋታህ ሬብ አስተዳደር ለማለት ይመስለኛል)ለእነርሱ የሚስማማቸውን መንግስት መምረጥ ይፈልጋሉ።
•በጋዛ ሰርጥ እና በዌስት ባንክ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰማዕታት እና ቁስለኞች የፍልስጤም ህዝብ ለከፈሉት መስዋዕትነት #የሚመጥነውን በነጻነት እና በክብር የሚኖሩበትን ሃገራቸውን ይወርሳሉ!
•ከመቶ ቀናት በፊት የአሜሪካው ንግግር #ከሃማስ መወገድ በኋላ በ #ጋዛ ስለሚኖረው አስተዳደር ነበር!
ዛሬ ደግሞ ከ #ኔታንያሁ በኋላ ስለ #እስራኤል እጣ ፈንታ  ሆኗል!

https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
#Breaking
"በ #ጋዛ ከተማ ውስጥ ከአል-ዘይቱን ሰፈር በስተደቡብ የሚገኘውን ሁለት ማኦዝ አጥፍቶ ጠፊ አውሮፕላኖችን ጨምሮ 3 የጽዮናውያን አውሮፕላኖችን ተቆጣጠርን!”
#አልቀሳም_ብርጌዶች!

https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“ፕሬዘዳንት #ሲሲ ወደ #ጋዛ የሚያሻግረውን #የራፋህ ማቋረጫ ለመክፈት ፍቃደኛ #አልነበሩም!
ነገር ግን መክፈት እንዳለበት እኔ በስልክ አሳምኜዋለሁ!”
#ጆ_ባይደን!
ይሄ ሞት ነው!ውርደት ነው!
إنالله وإنا إليه راجعون!

ቴሌግራም Channel፦
https://t.me/Xuqal