Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
468 subscribers
3.05K photos
188 videos
46 files
2.11K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
#Breaking
የማእከላዊ ላቲን አሜሪካዊቷ ሃገር #ኒካራጓ🇳🇮 ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ በነበረው የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ ላይ ለመሳተፍ ለአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ጥያቄ ማቅረቧን አስታወቀች።
መንግስት በመግለጫው ላይ “ኒካራጓ በጋዛ ሰርጥ የተባበሩት መንግስታት የዘር ማጥፋት ስምምነትን በመጣስ ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ ባቀረበችው የዘር ማጥፋት ክስ ውስጥ እንዲትካተት ለአለም አቀፍ የፍትህ ፍርድ ቤት አመልክታለች!”ብሏል።
በማስስከተልም ኒካራጓ ከፍርድ ቤት ሊሰጡ  ሚችሉት የህግ ውጤቶች ሁሉ አካል መሆን ትፈልጋለች፤እናም #የዘር_ማጥፋት ወንጀልን ለመከላከል ያለብንን #ግዴታ ለመወጣት እና የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙትን #ለመቅጣት የበኩሏን አስተዋፅኦ ለማድረግ ትፈልጋለች።”ይላል።
መግለጫው በተጨማሪም #ኒካራጓ ጥያቄዋ ተቀባይነት ካገኘ በጠቅላላው የክስ ሂደት ውስጥ እንደ ሀገር ጣልቃ ለመግባት እንደምትፈልግ ለአለም አቀፍ የፍትህ ፍርድ ቤት ማሳወቋን ገልጿል።  “ኒካራጓ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንደገለጸው፣ የእስራኤል ድርጊት የዘር ማጥፋት ስምምነትን ህግጋት እንደሚጥስ ያምናል” በማለት አብራርተዋል በመግለጫቸው።
መግለጫው አክሎም “የእስራኤል ወታደራዊ ጥቃት በፍልስጤም ህዝብ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት #በአስቸኳይ እንዲያቆም የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣናት በፍልስጤም ህዝብ ላይ የሚሰነዝሩት የዘር ማጥፋት ድርጊት እና የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣናት በፍልስጤም ህዝብ ላይ የሰጡት ኢሰብአዊ መግለጫዎችም አመላካች ናቸው” ብሏል።
በጃንዋሪ 11, የአለም አቀፍ የፍትህ ፍርድ ቤት ችሎት ደቡብ አፍሪካ በጋዛ ሰርጥ "የዘር ማጥፋት" ወንጀል በእስራኤል ላይ ባቀረበችው ክስ የተጀመረ ሲሆን፣
ባለ 84 ገፆች ማስታወሻ ላይ ጠበቆቹ እስራኤል "በጋዛ ውስጥ የምታደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንድታቆም" ዳኞች እንዲያዝዙ አሳስበዋል።
ምንጭ፡RT

ለወቅታዊ ሃገር አቀፍና አለምአቀፍ መረጃዎች ይሄን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ!👇
https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1