Bilaluna Edris
543 subscribers
3.35K photos
275 videos
50 files
2.3K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
#Breaking
የማእከላዊ ላቲን አሜሪካዊቷ ሃገር #ኒካራጓ🇳🇮 ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ በነበረው የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ ላይ ለመሳተፍ ለአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ጥያቄ ማቅረቧን አስታወቀች።
መንግስት በመግለጫው ላይ “ኒካራጓ በጋዛ ሰርጥ የተባበሩት መንግስታት የዘር ማጥፋት ስምምነትን በመጣስ ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ ባቀረበችው የዘር ማጥፋት ክስ ውስጥ እንዲትካተት ለአለም አቀፍ የፍትህ ፍርድ ቤት አመልክታለች!”ብሏል።
በማስስከተልም ኒካራጓ ከፍርድ ቤት ሊሰጡ  ሚችሉት የህግ ውጤቶች ሁሉ አካል መሆን ትፈልጋለች፤እናም #የዘር_ማጥፋት ወንጀልን ለመከላከል ያለብንን #ግዴታ ለመወጣት እና የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙትን #ለመቅጣት የበኩሏን አስተዋፅኦ ለማድረግ ትፈልጋለች።”ይላል።
መግለጫው በተጨማሪም #ኒካራጓ ጥያቄዋ ተቀባይነት ካገኘ በጠቅላላው የክስ ሂደት ውስጥ እንደ ሀገር ጣልቃ ለመግባት እንደምትፈልግ ለአለም አቀፍ የፍትህ ፍርድ ቤት ማሳወቋን ገልጿል።  “ኒካራጓ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንደገለጸው፣ የእስራኤል ድርጊት የዘር ማጥፋት ስምምነትን ህግጋት እንደሚጥስ ያምናል” በማለት አብራርተዋል በመግለጫቸው።
መግለጫው አክሎም “የእስራኤል ወታደራዊ ጥቃት በፍልስጤም ህዝብ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት #በአስቸኳይ እንዲያቆም የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣናት በፍልስጤም ህዝብ ላይ የሚሰነዝሩት የዘር ማጥፋት ድርጊት እና የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣናት በፍልስጤም ህዝብ ላይ የሰጡት ኢሰብአዊ መግለጫዎችም አመላካች ናቸው” ብሏል።
በጃንዋሪ 11, የአለም አቀፍ የፍትህ ፍርድ ቤት ችሎት ደቡብ አፍሪካ በጋዛ ሰርጥ "የዘር ማጥፋት" ወንጀል በእስራኤል ላይ ባቀረበችው ክስ የተጀመረ ሲሆን፣
ባለ 84 ገፆች ማስታወሻ ላይ ጠበቆቹ እስራኤል "በጋዛ ውስጥ የምታደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንድታቆም" ዳኞች እንዲያዝዙ አሳስበዋል።
ምንጭ፡RT

ለወቅታዊ ሃገር አቀፍና አለምአቀፍ መረጃዎች ይሄን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ!👇
https://t.me/Xuqal 
https://ummalife.com/BilalunaEdris1
የጋዛን 'ዘር ማጥፋት' በመቃወም እራሱን ያቃጠለው የአሜሪካ አየር ሀይል አባል በሆስፒታል ውስጥ ህይወቱ አለፈ!
የ25 አመቱ #አሮን_ቡሽኔል የዩኤስ አየር ሃይል ንቁ ተረኛ አባል በጋዛ እየደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ በመቃወም እራሱን ካቃጠለ በኋላ በሆስፒታል ውስጥ እያለ ህይዎቱ አልፏል።
የዩናይትድ ስቴትስ አየር ኃይል አባል በጋዛ ጦርነት ምክንያት በዋሽንግተን በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ደጃፍ ላይ ነበር ራሱን ያቃጠለው።
የጋዛን ግጭት በመቃወም በዋሽንግተን በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ደጃፍ ላይ ራሱን ያቃጠለው የአየር ሃይል አባል በአካባቢው በሚገኝ ሆስፒታል ህይወቱ ማለፉን ፖሊስ አረጋግጧል።
የ25 አመቱ #አሮን_ቡሽኔል የዩኤስ አየር ሃይል ንቁ አባል የነበረ ሲሆን በጋዛ እየተካሄደ ያለውን ዘግናኝ #የዘር_ማጥፋት_ወንጀል በመቃወም ትላንት እሁድ ራሱን በእሳት አቃጥሏል።
የዲሲ የእሳት እና ድንገተኛ ህክምና አገልግሎት መምሪያ "ለህይወት አስጊ በሆኑ ጉዳቶች" ምክንያት ወደ አካባቢው ሆስፒታል መላኩን አስታውቆ ነበር።
“ከእንግዲህ በዘር ማጥፋት ወንጀል ተባባሪ አልሆንም!ከፍተኛ የሆነ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ልፈፅም ነው!ነገር ግን ሰዎች በፍልስጤም #በቅኝ_ገዥዎቻቸው እየደረሰባቸው ካለው ነገር ጋር #ሲወዳደር ፈፅሞ #ፅንፈኝነት አይደለም!”በማለት
ቡሽኔል እራሱን ከማቃጠሉ በፊት ተናግሮ ነበር!
በተሰራጨው ቪዲዮ ወታደሩ በእሳት እየነደደ “ነፃ ፍልስጤም!”እያለ ሲጮህ ያሳያል!
ባለፈው ታኅሣሥ ወር አንድ ሰው በጋዛ ላይ የእስራኤልን ጥቃት በመቃወም አትላንታ ጆርጂያ በሚገኘው የእስራኤል ቆንስላ ውጭ ራሱን ማቃጠሉ ይታወሳል።
#አናዶሉ እንደዘገበው!

ቴሌግራም Channel፦
https://t.me/Xuqal