ቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ
277 subscribers
315 photos
11 videos
15 files
82 links
“ዋይ ዜማ ዘሰማዕኩ በሰማይ እመላእክት
እምዘይብሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር”
Download Telegram
እንኳን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ በዓለ ዕረፍት መታሰቢያ በሰላም አደረሳችኹ!!

ሐምሌ ፭ ቀን ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስና ንዋይ ኅሩይ ቅዱስ ጳውሎስ በኔሮን ቄሳር ዘመን ሰማዕትነት የተቀበሉበት በዓለ ዕረፍት ይዘከራል፡፡ በተጨማሪም የጾመ ሐዋርያት ፋሲካ ይከበራል፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ የቀድሞ ስሙ ስምዖን ይባል ነበር፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጴጥሮስ ብሎ ጠርቶታል፡፡ ትርጓሜው ዓለት (መሠረት) ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ከጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግር ሥር ተቀምጦ በዋለበት ውሎ ባደረበት አድሮ፣ የቃሉን ትምህርት ሰምቶ የእጁን ተአምራት አይቶ በአንብሮተ እድ ሥልጣነ ክህነትን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል የተላከ ሐዋርያ ነው፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ስሙ ሳውል ይባል ነበር፡፡ ክርስትናን ተቀብሎ ወንጌልን ለመስበክ ሲነሣ ጳውሎስ ተብሎ ተጠርቷል፡፡፡ ትርጓሜው ብርሃን፣ አመስጋኝ፣ ደስታ፣ ልሳነ ዕፍረት፣ ልሳነ ክርስቶስ፣ ሰላም፣ ፍቅር ማለት ነው። ሳውል ገማልያል ከሚባለው መምህረ ኦሪት ሕገ ኦሪትንና መጻሕፍተ ነቢያትን ተምሯል፡፡ ለሕገ ኦሪት ቀናኢ ከመኾኑ የተነሣም የክርስቶስ ተከታዮችን ዅሉ ያሳድድ ነበር፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ ተደብድቦ በሰማዕትነት በሞተ ጊዜ ቅዱስ ጳውሎስ የገዳዮቹ ልብስ ጠባቂ ነበር (ሐዋ. ፯፥፶፰፤ ፳፪፥፳)፡፡ ክርስቲያኖችን እያሳደደ ሳለ በደማስቆ ጎዳና በታላቅ ብርሃን በተገለጠለት በጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ልቡ ተነክቶ ከአሳዳጅነት ወደ ተሳዳጅነት የተለወጠ በጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ንዋይ ኅሩይ(የተመረጠ ዕቃ) ተብሎ የተጠራ ታላቅ ሐዋርያ ነው፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ ኹለት መልእክታትን ሲጽፍ ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ፲፬ መልእክታትን ጽፏል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ በልብሱ ድውያንን ፈውሰዋል፡፡ (የሐዋ፭፤፲፭ የሐዋ፲፱፤፲፪)፡፡

ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ሐምሌ ፭ ቀን ፷፯ ዓ.ም. በ ፹፭ ዓመቱ በሮም ከተማ በመስቀል ላይ ቁልቁል ተሰቅሎ በሰማዕትነት አርፏል፡፡ የሮም ክርስቲያኖች ሥጋውንም በሮም ከተማ አሳርፈውታል፡፡ በመቃብሩ ላይም ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ቤተ ክርስቲያን አሠርቶበታል፡፡ ንዋይ ኅሩይ ቅዱስ ጳውሎስም በምድረ አሕዛብ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ በንጉሥ ኔሮን ትእዛዝ ተይዞ በሮም ከተማ አንገቱን በሰይፍ ተቀልቶ በሰማዕትነት አርፏል፡፡ ክርስቲያኖችም በየዓመቱ ከመቃብሩ በረከት ለማግኘት ወደ ባቲካኖ(Vatican) እየሄዱ ይሳለማሉ፡፡

የሀገራችን ኢትዮጵያ ነገሥታትና ሊቃውንት ለብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ለቅዱስ ጳውሎስ የተለያዩ መታሰቢያዎችን አቁመዋል፡፡ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስና ንዋይ ኅሩይ ቅዱስ ጳውሎስ በስማቸው ጽላት ተቀርጾላቸው፣ ቤተ ክርስቲያን ታንጾላቸው ይታሰባሉ፡፡ በተጨማሪም በቅዱስ ጳውሎስ ስም አንድ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ተከፍቶ እገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በቅዱስ ጴጥሮስና በቅዱስ ጳውሎስ መታሰቢያ የሚጠሩ ኹለት ታዋቂ የሕክምና ማዕከላት ይገኛሉ፡፡

አምላካችን አግዚአብሔር በሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስና በንዋይ ኅሩይ ቅዱስ ጳውሎስ ጸሎት ይማረን፣ በረከታቸውም ዘወትር ከእኛ ጋር ትኹን፡፡ አሜን!
የአባቶቻችን ጥርጥር የሌለባት የቀናች ሃይማኖታቸው፣ ድል የማትነሣ ተጋድሏቸው በኹላችን ላይ ለዘለዓለሙ ጸንቶ ይኑር፡፡ አሜን፡፡
ይህንን ማስፈንጠርያ ይጠቀሙ
https://www.youtube.com/channel/UC9HCZKEuvymsChwLuR2lTsw
ዛሬ ከ2:00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የሚኖረንን ቆይታ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይከታተሉ። እንዳያመልጦት!
#ስለ ታሰሩ አባላት፣ ለምን ታሰሩ? #ወቅታዊ ጉዳዮች
=>+"+ እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም #ሥላሴ እና ለቅዱሳን
አበው #አብርሃም: #አባ_ሲኖዳ እና #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ
ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

+"+ #ሥሉስ_ቅዱስ +"+

=>በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት)
የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ
#እግዚአብሔር ነው:: #አብ : #ወልድ : #መንፈስ_ቅዱስ
በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና
በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ
ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::

+ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት " #ቅድስት_ሥላሴ "
እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም::
የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው
ያድራሉ::

+ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል
በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን
#ቅዱስ_አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን
በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ
አኀዜ ዓለም (ዓለምን በእጁ የያዘ) ነው:: ነገር ግን በፍቅር
ለሚሻው በፍቅር ይመጣል::

+አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ
ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን
አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!)
ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው
ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: #ቅድስት_ሣራ ሳቀች::
እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት
የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ"
ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው " #ይስሐቅ" የተባለው::

+ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል
እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ #አብ
ለአጽንኦ: #መንፈስ_ቅዱስ ለአንጽሖ: #ወልድ በተለየ አካሉ
ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::

+"+ #ታላቁ_አባ_ሲኖዳ +"+

=>የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ:-
¤በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ
¤በእናቱ ማሕጸን ሳለ መላእክት በሰይፈ እሳት ይጠብቁት የነበረ
¤የታላቅነት ትንቢት የተነገረለት
¤ገና ሳይወለድ ሥውራን አበው የሰገዱለት
¤በሕጻን ሰውነቱ ጾምና ጸሎትን የጀመረ
¤የልጅነት ቁርስና ምሳውን ለነዳያን ያካፍል የነበረ
¤በ9 ዓመቱ ወደ በርሃ የመነነ
¤የአባ አብጐል ደቀ መዝሙር የሆነ አባት ነው::

+ሲመነኩስም በእግዚአብሔር ትእዛዝ #የሠለስቱ_ደቂቅ
አስኬማ: #የኤልያስ ቆብዕ እና የመጥምቁ #ዮሐንስ ቅናትን
(መታጠቂያ) ከያሉበት መላእክት አምጥተውለት የመነኮሰ
¤ዓለምን በሙሉ በጸሎቱ ይጠብቅ የነበረ
¤የግብፅን በርሃ በብርሃን የሞላ
¤በርካታ ድርሰቶችን የደረሰ
¤ያለ ማቇረጥ በየቀኑ ከ100 ዓመታት በላይ ከጌታችን ክርስቶስ
ጋር የተነጋገረ
¤ደመናትን ተጭኖ ይሔድ የነበረና
¤ያለ ዕረፍት ለ111 ዓመታት ከ2 ወራት ፈጣሪውን ያገለገለ
አባት ነው::

+በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ገዳማውያን ሁሉ እየሰሙ
እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ:: "ሲኖዳ ተሠይመ
#አርሲመትሪዳ " (ሲኖዳ አርሲመትሪዳ ሆኗል:: ማለትም
ለባሕታውያን ሁሉ አለቃ ሁኖ ተመርጧል ማለት ነው:: )

+ቅዱሱ የጌታችንን እግር እያጠበም ይጠጣ ነበር::
+በዚህች ዕለት በ120 ዓመቱ ጌታችን ወርዶ ሲያሳርገው
#አቡነ_ኪሮስ "ታላቅ ምሰሶ (ታላቅ ዛፍ) ወደቀ" ብለው
አልቅሰዋል:: #ሲኖዳ ማለት "ደግ ሰው" ማለት ነው::

+"+ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ ( #GIYORGIS_OF_SEGLA )
+"+

=>ታላቁ ኢትዮዽያዊ ሊቅና ጻድቅ የተወለደው ወሎ #ጋስጫ
ውስጥ በ1358 ዓ/ም ነው:: ከልጅነቱ ትምሕርት አልገባሕ
ቢለውም በልቡናው ግን ቅን እና ታዛዥ ነበር:: መምሕሩ
"ትምሕርት አይገባውምና ውሰዱት" ቢላቸው "የእግዚአብሔር
ነውና ያገልግላችሁ" ብለው መለሱት:: መገፋቱን የተመለከተ
#አባ_ጊዮርጊስ #እመቤታታችንን ከልቡ ይወዳት ነበረና
ይማጸናት ገባ::

+ቀን ቀን ገዳሙን ሲረዳ: እሕል ሲፈጭና ሲከካ: ላቡንም
ሲያፈስ ውሎ ሌሊት ደግሞ ሲጸልይ ያነጋ ነበር:: ድንግል
እመቤታችን ጸሎቱን ሰምታለችና #ቅዱስ_ዑራኤልን አስከትላ
መጣችለት:: በንጹሐት እጆቿ ባርካው ምሥጢርንም ነገረችው::
"ወነገረቶ ሐምስተ ቃላተ" እንዲል:: ጽዋዐ ልቡናን አጠጥታው
ተሠወረችው::

+ከዚህች ሰዓት ጀምሮ አባ ጊዮርጊስ ፍጹም ተለወጠ:: በጽድቁ
ላይ የሊቅነትን ካባ ደረበ:: ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተነትናቸው:
መናፍቃንንም ምላሽ ያሳጣቸው ገባ:: የተረጐማቸውና
ያተታቸውን ሳይጨምር 41 ድርሰቶችን ደረሰ:: (መጽሐፈ
ሰዓታት: መጽሐፈ ምሥጢር: አርጋኖን: ኆኅተ ብርሃን: ውዳሴ
መስቀል: ወዘተ . . . የእርሱ ድርሰቶች ነበሩ)

+ስለ ሃይማኖትም ጠበቃ ነበር:: ስለ ቅድስናውና ውለታው የኢ/
ኦ/ተ/ቤ እንዲህ ትጠራዋለች:-
1. #ሊቀ_ሊቃውንት
2. #በላዔ_መጻሕፍት
3. #ዓምደ_ሃይማኖት
4. #ዳግማዊ_ቄርሎስ
5. #ጠቢብ_ወማዕምር

+ጻድቁ ሊቅ በተወለደ በ60 ዓመቱ በ1418 ዓ/ም በዚህች ቀን
ዐርፏል:: አባ ጊዮርጊስ የተወለደውም ያረፈውም ሐምሌ 7 ቀን
ነው::

=>የሥላሴ ቸርነት: የአብርሃም ደግነት: የአበው አባ ጊዮርጊስና
አባ ሲኖዳ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::

=>ሐምሌ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን አብርሃምና ሣራ (ሥላሴን ያስተናገዱ)
2.ብሥራተ ልደተ ይስሐቅ
3.ታላቁ አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን ሁሉ አለቃ)
4.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (ሊቀ ሊቃውንት: ኢትዮዽያዊ
የሃይማኖት ምሰሶ)
5.ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ (ምጥው ለአንበሳ)
6.አባ መቃቢስ
7.አባ አግራጥስ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
2.አባ ባውላ ገዳማዊ
3.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ

=>+"+ እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ:-
'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ:: እያበዛሁም አበዛሃለሁ'
ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ::
እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ:: +"+ (ዕብ.
6:13)
=>+"+ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር:
የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን:: +"+
(ቆሮ. 13:14)
የእግዚአብሔር፣ ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡ አነሳስቶ ያስጀመረኝ አስጀምሮ ያስጨረሰኝ የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ ይክበር ይመስገን አሜን፡፡

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
ሥርዓተ ማኅሌት ዘሐምሌ /፯/ ሥላሴ

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

ነግሥ
ሰላም #ለአብ ዘእምቅድመ ዓለም ነጋሢ: #ለወልድ ሰላም ሥጋ ማርያም ለባሲ: #ለመንፈስ_ቅዱስ ሰላም ኃጢአተ ዓለም ደምሳሲ: ኃይልየ #ሥላሴ ወፀወንየ #ሥላሴ: በስመ #ሥላሴ እቀጠቅጥ ከይሴ።

ዚቅ
አምላክነሰ ኃይልነ አምላክነሰ ፀወንነ: አምላከ አሕዛብ ዕብነ ወዕፀ ኪነት ኢኮነ።

መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለአጽፋረ እግርከ ፍናዋተ ረድኤት በተኃልፎ: ዘኢተዳደቆን እብነ አዕቅፎ: ሚካኤል ቀዳሲ ትሥልስተ አካላት በኢያዕርፎ: ኢትኅድገኒ በዓለም እስመ ኪያከ እሴፎ: አልቦ ብእሲ ዘየኀድግ ሱታፎ፡፡

ዚቅ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር: ዘይሴባሕ እምትጉሃን: ወይትቄደስ እምቅዱሳን፡፡

ማኅሌተ ጽጌ
ተፈሥሒ ማርያም እንተ ኢተአምሪ ብእሴ: ዘጸገይኪ ለነ አሐደ እምነ #ሥላሴ: እንዘ እዘብጥ ከበሮ ቅድመ አዕላፈ ኤፍሬም ወምናሴ: ለተአምርኪ እነግር ውዳሴ: ማርያም እኅቱ ለሙሴ።

ወረብ
ተፈሥሂ ማርያም እንተ ኢተአምሪ ብእሴ ተፈሥሂ ማርያም/፪/
ዘጸገይኪ ለነ አሐደ እምነ #ሥላሴ ዘጸገይኪ ለነ/፪/

ዚቅ
ይሴብሑኪ ወይገንዩ ለስምኪ: ዘእምሥሉስ ቅዱስ ቃል ኃደረ ላዕሌኪ: ወትሰመዪ ማኅደረ መለኮት።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለህላዌክሙ ዘይመውዕ ህላዌያተ: ለረኪበ ስሙ ኅቡእ አመ ወጠንኩ ተምኔተ: እምግብርክሙ #ሥላሴ ሶበ ረከብኩ አስማተ: መለኮተ ለለአሐዱ ዘዚኣክሙ ገጻተ: እንበለ ትድምርት እሰሚ ወእሁብ ትድምርተ።

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ: አአትብ ወእትነሣእ: በስመ #አብ #ወወልድ #ወመንፈስ_ቅዱስ: ሠለስተ አሥማተ ነሢእየ እትመረጎዝ: እመኒ ወደቁ እትነሣእ: ወእመኒ ሖርኩ ውስተ ጽልመት: እግዚአብሔር ያበርህ ሊተ በእግዚአብሔር ተወከልኩ፡፡

አመላለስ
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ/፪/
ሃሌ ሃሌ ሉያ/፪/

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለሕጽንክሙ ምርፋቀ ጻድቃን አግብርቲሁ: ማያተ ኢያሱ #ሥላሴ እለ ትውኅዙ እምሕሊናሁ: እንዘ በአፍአሁ አንትሙ ወአንትሙ በውሣጤሁ: ኢነጸረ ኀበ ሐይመት ከመ አብርሃም አቡሁ: ወመስኮተ ነቢይ ዳንኤል ኢፈቀደ ያርኁ።

ዚቅ
በአፍዓኒ አንትሙ: ወበውሣጤኒ አንትሙ: በገዳምኒ አንትሙ: ብርሃኑ ለኢያሱ አንትሙ ፡፡

ወረብ
በአፍአኒ አንትሙ ወበውሣጤኒ አንትሙ/፪/
በገዳምኒ አንትሙ ብርሃኑ ለኢያሱ ንጉሠ ነገሥት/፪/

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለኅሊናክሙ በከዊነ ኄር ዘተሐምየ: እምከላውዴዎን አብርሃም ዘምድረ ካራን ኀረየ: #ሥላሴክሙ_ሥላሴ ሶበ ይኔጽር ዕሩየ: ፫ተ ዕደወ ሊሉያነ ውስተ ርእሰ ኀይምት ርእየ: ወለ፩ዱ ነገሮ ረሰየ።

ዚቅ
ወጽአ አብርሃም እምድረ ካራን: ወቦአ ብሔረ ከነዓን: ተአመነ አብርሃም በእግዚአብሔር: እንበይነዝ ጽድቀ ኮኖ፡፡

ወረብ
ወጽአ እምድረ ካራን ወቦአ ዝየ ረከብነአ/፪/
ተአመነ "አብርሃም"/፪/በእግዚአብሔር/፪/

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለሐቌክሙ ዘቅናተ ኂሩት ቅናቱ: ሊሉያነ ፆታ #ሥላሴ እምአምላከ በለዓም ከንቱ: ኀበ መስፈርትክሙ ጽድቅ እስመ ያበጽሕ ትእምርቱ: ተደለዉ ከመ ይሑሩ ምሕዋረ ዕለታት ሠለስቱ: በዓለ መሥዋዕት አብርሃም ወይስሐቅ መሥዋዕቱ።

ዚቅ
አብርሃም ወሰዶ ለይስሐቅ ወልዱ ከመ ይሡዖ: አውረደ ሎቱ ቤዛሁ በግዓ: እኁዝ አቅርንቲሁ በዕፀ ሳቤቅ: ዕፀ ሳቤቅ ብሂል ዕፀ ሥርየት መስቀል: አብርሃምኒ ርእዮ በውስተ ምሥዋዕ: ሕዝቅኤልኒ ርእዮ በልዑላን: ሙሴኒ ርእዮ በዓምደ ደመና: በነደ እሳት: ፈያታዊኒ ርእዮ በዲበ ዕፀ መስቀል አምነ፡፡

ወረብ
አብርሃም ወሰዶ ለይስሐቅ ወልዱ ከመ ይሡዖ/፪/
አውረደ ሎቱ "ቤዛሁ በግዐ"/፪//፪/

መልክዐ ሥላሴ
ለዘበነጊድ አቅረብኩ መካልየ ልሳን ስብሐታተ: መጠነ ራብዕ ዐሥር እንዘ አተሉ ስብዐተ: ህየንተ ፩ዱ #ሥላሴ እለ ትፈድዩ ምእተ: ጸግዉኒ እምገጽክሙ ንዋየ ገጽ ትፍሥሕተ: ወዲበ ፲ቱ አህጉር ሀቡኒ ሢመተ።

ዚቅ
ስብሐት ለአብ ለአኃዜ ኲሉ ዓለም: ስብሐት ለወልድ ለዘአክበራ ለማርያም: ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ለዘያርኁ ክረምተ በበዓመት።

ወረብ
ስብሐት ለአብ ለአኃዜ ኲሉ ዓለም ስብሐት ለወልድ ለገባሬ ኲሉ ዓለም/፪/
ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ለዘያርኁ ክረምተ በበዓመት/፪/

መልክዐ ተክለሃይማኖት
ሰላም ለኅሊናከ ዘኮነ መምለኬ: ሥላሴ ዕሩየ እንበለ ውሳኬ: ተክለሃይማኖት ቄርሎስ ዘላፌ ረሲዓን እለ እውጣኬ: ባርከኒ አባ ለወልድከ ዝኬ: እስመ ልማዱ ለመምህር ቡራኬ።
ዚቅ
አንትሙሰ ከመ ዕብነ ህይወት ተሐነጹ ቤቶ ለመንፈስ ቅዱስ: ወለክህነቱ ቅዱስ: ከመ ታዕርጉ መሥዋዕተ ወትንግሩ ሠናይቶ ለዘጸውዓክሙ: አባ ባርከኒ ተክለሃይማኖት አባ: ከመ ባረኮ አብርሃም ለይስሐቅ ወልዱ።

ወረብ
አንትሙሰ ዕብነ ህይወት ተሐነጹ ቤቶ ለመንፈስ ቅዱስ/፪/
ወለክህነቱ ቅዱስ ታዕርጉ ከመ ታዕርጉ መሥዋዕተ/፪/

ምልጣን
በእምርት ዕለት እንተ ርእያ አብርሃም መዘምራኒሃ ለደብረ ብርሃን አርያም እንዘ ይብሉ ይዜምሩ በልሳን ዘኢያረምም አማን መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም።

አመላለስ
አማን በአማን/፬/
መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም/፬/

ወረብ
በእምርት ዕለት እንተ ርእያ አብርሃም መዘምራኒሃ ለደብረ ብርሃን አርያም ደብረ ብርሃን/፪/
እንዘ ይብሉ ይዜምሩ በልሳን ዘኢያረምም አማን መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም/፪/

እስመ ለዓለም
ሰአለ ሙሴ በእንተ ዘስሕቱ ሕዝብ: ኀበ አቡነ አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ: ወይቤሎ አብርሃም ንግሮ ለእግዚአብሔር: እንዘ ትብል ተዘከር እግዚኦ ኪዳነከ: አብርሃም ፍቊርከ ይስሐቅ ቊልዔከ: ወያዕቆብሃ ዘአስተባዛህከ: ነሥአ ሙሴ ፫ተ አስማተ: ከመ ዘይወስድ አምኃ ለንጉሥ: ወሰማዕትኒ ይጸውሩ ሥላሴ።

ወረብ
"ሰአለ ሙሴ"/፪/ በእንተ ዘስሕቱ ሕዝብ/፪/
ኀበ አቡነ አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ/፪/
መዝሙር ንጉሥ ውእቱ ከሐምሌ ፲፩ እስከ ሐምሌ ፲፮


(በ፮/ዕ) ንጉሥ ውእቱ ክርስቶስ ንጉሥ ውእቱ ክርስቶስ መሐሪ ውእቱ ይሁብ ዘርዐ ለዘራዒ (ን) ያሠምር እክለ ለሲሳይ ያነሥኦ እምድር ለነዳይ (ን) ዘኢየኃይድዎ ሥልጣኖ ዘይኤዝዝ ትፍሥሕተ ለጻድቃኒሁ (ን) ወሠርዐ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ ገባሬ ሕይወት ያርኁ ክረምተ በበዓመት ንጉሥ ውእቱ ክርስቶስ ንጉሥ ውእቱ ክርስቶስ።

ትርጕም፦

ክርስቶስ ንጉሥ ነው ይቅር ባይ ነው ለዘሪ ዘርን ይሰጣል ለምግብ እህልን ያዘጋጃል ድኃውን ከመሬት ያነሣዋል ሥልጣኑን የማይቀሙት ነው ለጻድቃኑ ደስታን ያዛል (ለፍጥረት ፀሐይን ያወጣል) ሰንበትን ለሰው ዕረፍት ሠራ ሕይወትን የሠራ በየዓመቱ ክረምትን ይከፍታል።

የዕለቱ ምንባባት፦

፩ጢሞ ፩፥፲፪ -፲፰፤
ራእይ ፲፱፥፲፩ - ፲፯፤
ግብ ፭፥፳፯ - ፴፫፤
የዕለቱ ወንጌል፦ ማቴ ፳፪፥፩ - ፲፭፤ ወይም ማቴ ፲፫፥፲፰ - ፳፬
ቅዳሴ፦ ዘኤጲፋንዮስ፤

የዕለቱ ምስባክ፦

ዘያበቊል ሣዕረ ለእንስሳ፤
ወሐመልማለ ለቅኔ እጓለ እመሕያው፤
ከመ ያውጽእ እክለ እምድር። መዝ ፻፫፥፲፬

ትርጕም፦

ለእንስሳ ሣርን የሚያበቅል እርሱ ነው፤
ለሰው ልጆች አገልግሎት ለምለሙን የሚያበቅል እርሱ ነው፤
እህልን ከምድር ያወጣ ዘንድ።

ምሥጢር፦

ለእንስሳ ምግብ ይሆን ዘንድ ሣርን የሚያበቅል ዝናም ነው አንድም ጌታ ነው፤
ለሰው ለሚያገለግል እንስሳ ልምላሜ ያለውን የሚያበቅል ዝናም ነው አንድም ጌታ ነው። አንድም ቅኑይ ሲል ነው ለእግዚአብሔር ለሚገዛ ለሰው እህሉን ተክሉን የሚያበቅል ዝናም አንድም ጌታ ነው። ሰው ያንን (እህሉን) እየተመገበ ለእግዚአብሔር ይገዛ ዘንድ ነው።
ከወደኋላ እምፍሬ ተግባርከ ትጸግብ ምድር - ከሥራህ ፍሬ ምድር ትጠግባለች (ምድር ከደመና የተገኘውን ዝናም ረክታ ትጠግባለች አንድም ከደመናው ለይተህ ያወረድኸውን ዝናም ጠጥታ ትጠግባለች ፍሬ አለው? ፍሬ መስሎ የሚወርድ ነውና ሲል ነው) ብሎ ነበርና ዝናም ከምድር እህሉን ያበቅል ዘንድ ነው።

ማሳሰቢያ፦

ንጉሥ ውእቱ ለሚለው መዝሙር ምስባኩ እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ የሚለው ቢሆን ጥሩ ይመስለኛል። ምክንያቱ ደግሞ አንዳንድ የግጻዌ መጻሕፍት ንጉሥ ውእቱን ከመዝሙር ተራ አስገብተው ስላልጻፉ ነው። በመሆኑም ዘያበቊል ሣዕረ የሚለውን በቀዳሚ ገብረ ለሚለው መዝሙር ይጽፋሉ ምሥጢሩ ለሁለቱም ይስማማል፤ ለንጉሥ ውእቱም ለበቀዳሚ ገብረም።

አንዳንድ የግጻዌ መጻሕፍት ለበቀዳሚ ገብረ እስመ ትቤ ለዓለም የሚለውን ይጽፋሉ። አነ አቀውም ኪዳንየ ዘምስሌከ የሚል ኃይለ ቃል በመዝሙሩ ውስጥ ስላለ ነው። እንዲህ ያለ ነገር ሲያጋጥም መምህራንን መጠየቅና በእነሱ ቃል መመራት አላስፈላጊ ከሆነ ሙግትና የኃይለ ቃል ልውውጥ ይጠብቃል።
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ሥርዓተ ማህሌት ዘ ሐምሌ ቅዱስ ገብርኤል << ፲፱ >>
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸

በመጀመሪያ ሥርዓተ ነግስ፦

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለአቁያጺክሙ እለ ተኀብአ እምዐይን: አናምያኒሁ ሥላሴ ለሜላተ ሰማይ ብርሃን: ልብሰ ሰማዕትና ይኲነኒ ምሕረትክሙ ክዳን: ላዕሌየ እስመ ኢሀሎ ልብሰ እስጢፋኖስ እብን: ወሥርጋዌሁ እሳት ለቂርቆስ ሕጻን፡፡

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: አንቃዕዲዎ ሰማየ: ጸለየ ወይቤ ቅዱስ ቂርቆስ እጼውዓከ እግዚእየ: ዘኢትሠዓር ንጉሠ ነገሥት መዋዒ: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘሰቀልኮ ለሰማይ ከመ ቀመር: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘበሥላሴከ ዓመድካ ለምድር: እጼውዓከ እግዚእየ: ኢየሱስ ክርስቶስ ጸግወኒ ስእለትየ።

ነግሥ
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል: እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል፡፡

ዚቅ
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል: ወብሥራት ለገብርኤል: ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል።

ዘጣዕሙ፦
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣእሙ: ለወልድኪ አምሳለ ደሙ: መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ:ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ:እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡

ዚቅ
ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም
መሠረተ ጽድቅ ኀደረ ላዕሌሃ: ወአዘዘ ደመና በላዕሉ።

መልክአ ቂርቆስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ቂርቆስ ሕጻን: ዘፍካሬሁ ተብህለ ጽጌ ምዑዝ ዕፍራን: ለዝ ስምከ ነጋሢ ዘኢየዓርቆ ሥልጣን: ሶበ ይጼውዖ ልሳንየ ውስተ ገጸ ኲሉ መካን: ይደንገፅ ሞት ወይጒየይ ሰይጣን፡፡

ዚቅ
ኢየሉጣ ወለደት ነቅዓ ጽጌ ረዳ: ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ: መላእክት ይትዋነይዋ: ኢየሉጣ ምስለ ወልዳ እሳተ ገብሩ ሐመዳ: ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ ጻድቃን: እስመ በጸሎተ ጻድቅ ትድኅን ወኢትማስን ሀገር።

ወረብ
"ኢየሉጣ ወለደት"/፪/ ነቅዓ ጽጌ ረዳ ወለደት/፪/
ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ ፀሐየ ጽድቅ/፪/

መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለልሳንከ ለዐቃቤ ሥራይ በዕዱ: እንተ ተመትረ እምጒንዱ: ሕፃን ቂርቆስ ለጽሕርት ዘኢያፍርኀከ ነጐድጓዱ: ዮም ባርክ ማኅበረነ ለለ፩ዱ ፩ዱ: ከመ ባረኮ አብርሐም ለይስሐቅ ወልዱ።

ዚቅ
ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ: ድምፃ ለጽሕርት ከመ ነጎድጓደ ክረምት: ኢፈርህዎ ለሞት ቅዱሳን ሰማዕት።

ወረብ
ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ/፪/
ድምጻ "ለጽሕርት"/፪/ ከመ ነጎድጓደ ክረምት/፪/

መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለእንግድዓከ ልቡና ዘከብዶ: ከመ እንግድዓሁ ለዕዝራ መጽሐፍ እንተ ይንዕዶ: ሕጻን ቂርቆስ ምስለ ወላዲትከ በተዋሕዶ: መኑ ከማከ ለእቶን አምሳለ አሣዕን ዘኬዶ: ወመኑ አምሳለ ማይ ዘአቊረረ ነዶ።

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ይቤላ ሕጻን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ኢትፍርሂ እም ንፈጽም ገድለነ።

ወረብ
ይቤላ ሕፃን ለእሙ ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት/፪/
ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ኢትፍርሂ እም/፪/

መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለመልክዕከ በማየ ዮርዳኖስ ጥሙቅ: ወቅቡዕ በሜሮን ቅብዐ ሰላም ወእርቅ: በጸሎትከ ነጐድጓድ ወስዕለትከ መብረቅ: አቊረርከ ቂርቆስ ነበልባሎ ለእቶነ እሳት ምውቅ: ከመ ነደ እሳት አቊረሩ ሠለስቱ ደቂቅ።

ዚቅ
በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት: ወኮነ ጥምቀተ ለአግብርተ እግዚአብሔር: ጽዋዓ ሕይወት ወሀቦሙ: መገቦሙ ወመርሆሙ: እስመ ክርስቶስ ሀሎ ምስሌሆሙ፡፡

ወረብ
በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ እምውስተ ጽሕርት ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት/፪/
ለአግብርተ እግዚአብሔር ኮነ ወኮነ ጥምቀተ/፪/

መልክዐ ቂርቆስ
ሰላም ለህላዌከ ማዕከለ ሰብአቱ ነገድ: እለ ሥዑላን በነድ: አስተምሕር ቂርቆስ ቅድመ መንበረ አብ ወወልድ: ኀበ ተሐንፀ መርጡልከ ወዘዚአከ ዐጸድ: ኢይምጻእ ለዓለም ዘይቀትል ብድብድ፡፡

ዚቅ
በዛቲ መካን ኢይምጻእ ሞተ ላሕም: ወኢብድብድ በሰብእ: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ: ወኢአባረ እክል: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: ቂርቆስ ሕጻን አንጌቤናይ: ወልደ አንጌቤናይት፡፡

ወረብ
በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ/፪/
ባርካ ቂርቆስ ለዛቲ መካን ባርካ ለዛቲ መካን/፪/

መልክዐ ኢየሉጣ
ሰላም ለመልክአትኪ አርብዓ ወሠለስቱ: ዓዲ ሰላም ለጠብአያትኪ አርባዕቱ: ኢየሉጣ ቅድስት ለቂርቆስ ወላዲቱ: ሰአሊዮ በእንቲአየ ከመ አይጥፋዕ በከንቱ: ለእግዚአብሔር አምላከ ጽድቅ ዘብዙኅ ምሕረቱ።

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሰላማዊት: ሰላም ለኪ: ሰላመ ወልድኪ የሃሉ ላዕለ ኩልነ: ኢየሉጣ እምነ: ወእሙ ለቂርቆስ እግዚእነ: ሰአሊ ለነ አስተምሕሪ ለነ: ከመ ኢንቁም አንቀጸ፡፡

መልክዐ ገብርኤል
ሰላም ለልሳንከ ወለቃልከ ማኅተሙ: ለእስትንፋስከ ጠል ለእሳተ ባቢሎን አቊራሬ ፍሕሙ: ገብርኤል ዉኩል ለረድኤተ ጻድቃን ኲሎሙ: አንግፈኒ እምነበልባል ኢያንጥየኒ ሕማሙ: ከመ አንገፍኮሙ ቅድመ ለቂርቆስ ወእሙ።

ዚቅ
ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት: ወበላሕኮሙ እምእሳት: አድኅነነ እግዚኦ ሃሌ ሉያ: እምዕለት እኪት።

ወረብ
ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት ወባላሕኮሙ እምእሳት ሊቀ መላእክት/፪/
እግዚኦ አድኅነነ "ሃሌ ሉያ"/፪/ እም ዕለት እኪት/፪/

ምልጣን፦
ይቤላ ሕፃን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ዘአድኃኖሙ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ
አመላለስ:
ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/
ውእቱ ያድኅነነ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ/፪/

ወረብ
ይቤላ ሕፃን ለእሙ "ኢትፍርሂ እም"/፪/ ነበልባለ እሳት/፪/
ዘአድኃኖሙ "ለአናንያ"/፪/ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/

እስመ ለዓለም
ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ: አምላኮሙ ለቂርቆስ ወእሙ: በብዝኃ ኃይሉ ወበጽንዓ ትዕግሥቱ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ሕፃን ዘኮና መርሐ ለእሙ ዘሠለስቱ ዓም: ኢፈርሐ ነበልባለ እሳት ዘይወጽእ እምአፈ ዕቶን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: አኃዘ ለእሙ ዕዳ ዘየማን ወሰሀባ ቅድመ መኮንን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ: እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: አእኰትዎ ወሰብሕዎ: ወባረክዎ ለአብ፡፡

አመላለስ
አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፪/
አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፬/

ወረብ
ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ/፪/
እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ እምዝ ዳግመ/፪/
✥✥✥✥✥✥✥
"የወንዙን ውሃ ሙላልን ብለን እግዚአብሔር እነሱን እስከ ልካቸውና እስከ ወሰናቸው ይመላ ዘንድ ስለ ወንዝ እንማልዳለን"
በእንተ ቅድሳት

ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን እንኳን ደስ አለን
#ሐምሌ_15

ሐምሌ ዐሥራ አምስት በዚህች ቀን የሶርያ ሰው #ቅዱስ_አባት_ኤፍሬም አረፈ፣ #ቅዱሳን_ሐዋርያት_ጴጥሮስና_ጳውሎስ በንጉሥ ጰራግሞስ ላይ ተአምራትን አደረጉ፣ የዋልድባው #አቡነ_ተስፋ_ሐዋርያት የተሰወሩበት ዕለት ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ (አፈ በረከት)

ሐምሌ ዐሥራ አምስት በዚህች ቀን የሶርያ ሰው ቅዱስ አባት ኤፍሬም አረፈ። ይህም ቅዱስ ከዋክብትን ከሚያመልኩ ሰዎች ሀገር ነው አባቱም ክብር ይግባውና የክርስቶስን አምልኮት የሚጠላ የጣዖት ካህን ነበር።

በዚያን ጊዜም የእግዚአብሔር ቸርነት ቀሰቀሰችውና አነሳሥታ የንጽቢን ጳጳስ ወደሆነው ወደ አባ ያዕቆብ ወሰደችው እርሱም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው በእርሱም ዘንድ በጾምና በጸሎት ያለማቋረጥ እየተጋደለ ለብዙ ዘመናት ኖረ።

የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ አደረበት አሕዛብን ተከራክሮ ይረታቸው ነበር። ኒቅያ በሚባል ከተማ የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት አባቶች ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ በተደረገ ጊዜ ይህ ቅዱስ ኤፍሬም ከመምህሩ ከአባ ያዕቆብ ጋራ ወደ ቅዱሳን ጉባኤው ሔደ።

ከሀዲው አርዮስንም አውግዘው ከለዩት በኋላ ይህ ቅዱስ ኤፍሬም በዚያች ሌሊት ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ አየ ከዚህ ራእይም የተነሣ አደነቀ ይገልጽለትም ዘንድ ወደ ጌታ ጸለየ ይህ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ባስልዮስ ነው የሚል ቃል ከሰማይ ወደርሱ መጣ።

ቅዱስ ኤፍሬምም ያየው ዘንድ ወድዶ ወደ ቂሣርያ ሀገር ተጓዘ በደረሰም ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በማእዘኑ በኩል ቆመ ቅዱስ ባስልዮስንም ወንጌልን ሊያነብ በወጣ ጊዜ ዋጋው ብዙ የሆነ ከወርቅ የተሠራ ልብሰ ተክህኖ ለብሶ አየው። ሦስት ምልክቶችንም እሰኪያይ ድረስ ተጠራጠረ ምልክቶችም እኒህ ናቸው ነጭ ርግብ መጥታ በራሱ ላይ አረፈች ሁለተኛም በልብሱ ላይ የሚያርፉ ተዋሐስያን ይቃጠሉና ይረግፉ ነበር። ሦስተኛም ከአፉ የእሳት ነበልባል ወጥቶ በምእመናን ላይ ያድር ነበር።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ባስልዮስ ቅዱስ ኤፍሬምን በስሙ ጠራውና እርስ በርሳቸው ሰላምታ ተለዋወጡ። በአስተርጓሚ ይነጋገሩ ጀመሩ። የየራሳቸውንም ቋንቋ ይገልጽላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልይ ቅዱስ ኤፍሬም ቅዱስ ባስልዮስን ለመነው። በጸለየ ጊዜም ተገልጾላቸው ያለ አስተርጓሚ ተነጋገሩ።

ከዚህ በኋላም ቅዱስ ኤፍሬምን ዲቁና ሾመው ከጥቂት ወራትም በኋላ ቅስና ሾመው ከእርሱም ብዙ ትሩፋቶች ተገለጡ በመንፈሳዊ ተጋድሎ ሁሉ ተጋደለ። አንዲት በወገን የከበረች ባለ ጸጋ ሴት ነበረች ራስዋንም ለካህን ለማስመርመር ታፍር ነበር ከታናሽነቷ ጀምራ የሠራችውን ኃጢአቷን ሁሉ ጽፋ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ አመጣች። አባቴ ሆይ በዚህ ክርታስ ውስጥ ያሉት ኃጢአቶቼ ይደመሰሱ ዘንድ ተናገር ብላ ለመነችው እርሱም እንዳልሺው ይሁንልሽ አላት።

እርሷም ክርታሱን በገለጠች ጊዜ ከአንዲት ኃጢአትዋ በቀር ኃጢአቷ ሁሉ ተደምስሶ አገኘች ያችም ኃጢአት አስጨናቂና ታላቅ ኃጢአት ነበረች።

ባገኘቻትም ጊዜ ያቺን የቀረች ኃጢአቷን ያጠፋላት ዘንድ አልቅሳ ለመነችው እርሱም ወደ ቅዱስ ኤፍሬም ሒጂ እርሱ ይህችን የቀረች ኃጢአትሽን ያስተሠርይልሻል አላት። ወዲያውም ወደ ቅዱስ ኤፍሬም ሔዳ ከርሷ የሆነውን ሁሉ ነገረችው። እርሱም እንዲህ አላት ፈጥነሽ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ሒጂ ግን ሙቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዱት ታገኝዋለሽ ሳትጠራጠሪም ይህችን ክርታስ በላዩ ጣይ ይደመሰስልሻል።

ያቺም ሴት ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ተመለሰች ሙቶ ተሸክመው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዱትም አገኘችው። ያንንም ክርታስ በአስክሬኑ ላይ ጣለችው ወዲያውኑም ተደመሰሰላት። ይህም ቅዱስ ኤፍሬም ብዙ ተአምራቶችን አድርጓል በዘመኑም ዲዳን የሚባል አንድ ከሀዲ ተነሣ ይህም አባት ኤፍሬም ተከራክሮ ረታው።

እጅግም ብዙ የሆኑ ዐሥራ አራት ሽህ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ ከእርሳቸውም ውስጥ አምላክን የወለደች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ውዳሴዋ ነው። አቤቱ የጸጋህን ማዕበል ግታልኝ እስከሚል ድረስ ድርሳናትን ደርሶአል። መልካም የሆነ ገድሉንም በፈጸመ ጊዜ ወደ ወደደው ወደ እግዚአብሔር ሔደ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱሳን_ሐዋርያት_ጴጥሮስና_ጳውሎስ

በዚህችም ቀን ለአባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ በንጉሥ ጰራግሞስ ላይ ተአምራትን አደረጉ። አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሰት በኋላ ደመና ነጥቆ ወሰዳቸውና በቤተ መንግሥት መካከል አወረዳቸው ንጉሥ ጰራግሞስም በአያቸው ጊዜ ደንግጦ እናንተ ምንድን ናችሁ አላቸው። እነርሱም መንግሥታትን ሁሉ የሚያጠፋ የሚሰሙትንም ማዳን የሚችል የሕያው እግዚአብሔር ልጅ የክርስቶስ ባሮች ነን አሉት።

ንጉሡም ነገራችሁ ትክክለኛ መሆኑን እንዴት ማወቅ እችላለሁ አላቸው። ከዚህ በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ያደረጋቸውን ድንቆችንና ተአምራቶቹን ነገሩት።

የቀኝ ዐይኗን ወፍ ያወጣው አንዲት ልጅ አለችኝ እርሷን ካዳናችኋት በአምላካችሁ አምናለሁ አላቸው ልጅህን ወደ እኛ አምጣ አሉትና ልጁን ወደ እነርሱ አመጣት። ሐዋርያትም ወደ እግዚአብሔር ጸልየው እጆቻቸውን በዐይኗ ላይ አኖሩ። ያን ጊዜም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ዳነች። ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ አይተው ከሐዋርያት እግር በታች ሰገዱ ክብር ይግባውና በጌታችንም አመኑ።

ከዚህም በኋላ ሐዋርያት ክብር ይግባውና ጌታችን እንዳዘዛቸው ወደ ሀገረ ፊልጶስ ሔዱ። ሰይጣንም በእንዶር ንጉሥ ተመስሎ አጋንንትን በጭፍራ አምሳል አስከትሎ ወደ ንጉሥ ጰራግሞስ መጣ በሥራያቸው አገርን ሳያጠፉ እኒህን ሁለቱን ሥራየኞች ፈጥነህ የማታጠፋቸው ለምንድነው አለው።

የንጉሥ ጰራግሞስም ልብ ወደ ክህደት ተመለሰ። ሐዋርያትንም ያመጧቸው ዘንድ ዐሥር ሺህ ጭፋሮችንና ሁለት መቶ ፈረሰኞችን ላከ ጭፍሮችም ሔደው ከተማዋን ከበቧት የከተማዋ ሰዎችም ደንግጠው ለሐዋርያት ነገሩዋቸው። ሐዋርያትም ከከተማው ወጥተው በጭፍሮቹ ፊት ቁመው ርዳታን ይልክላቸው ዘንድ ወደ ጌታችን ጸለዩ።

ያንጊዜም የጭፍሮቹ ፈረሶች ወደ ሐዋርያት ተመለሱ እግሮቻቸውንም አስተካክለው ተንበርክከው ሰገዱ እንደሚያለቅስም በቃጪን ድምጽ ጮኩ። ከፈረሶችም አንዱ ድምፁን ከፍ ከፍ አድርጎ እንዲህ ብሎ እንደ ሰው ተናገረ እናንት ሰነፎች የጰራግሞስ ጭፍሮች ክብር ይግባውና የክርስቶስን ጭፍሮች ጴጥሮስንና ጳውሎስን ለምን ትፈልጓቸዋላቸሁ ሥራየኞችስ ለምን ትሏቸዋላችሁ እነርሱ ግን ሥራይንና የሰይጣንን ሥራ ሁሉ ሊያጠፉ መጥተዋል። ክብር ይግባውና ከንጉሣቸው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በነጫጭ ፈረሶች ተቀምጠው አታዩአቸውምን ለክብር ንጉሥ ለክርስቶስ ጭፍሮቹ ትሆኑ ዘንድ ስሞቻችሁም በሕይወት መጽሐፍ ይጻፍ ዘንድ ስለ እናንተ ይለምናሉ። እኛ እንኳ እንስሳ ስንሆን ለአምላካችው እንሰግዳለን ፈረሱም ይህንን ተናግሮ ዝም አለ።

ከዚህም በኋላ እንዲህ የሚል ቃል ተሰማ ሐዋርያቶቼ ሆይ ሐዲሶች አትክልቶችን ቸለል አትበሏቸው። ያን ጊዜም ሕዝቡ ሁሉ ዐይኖቻቸውን ቀና አድርገው በታላቅ ክብር ወደ ሰማይ ሲዐርግ ጌታችንን አዩት እነዚያም ዐሥር ሺህ ሁለት መቶ ጭፍሮች ክብር ይግባውና በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስ አመኑ ለሐዋርያትም ተገዙላቸው።
ሐዋርያትም የምድራዊ ንጉሥ ጭፍራ መሆንን እንዲተዉ ፈረሶቹንና የጦር መሣሪያውንም እንዲመልሱለት ክብር ይግባውና በክርስቶስ በግልጥ እንዲአምኑ አዘዟቸው። እነዚያ ጭፍሮቹም ወደ ንጉሣቸው ጰራግሞስ ሔደው በፊቱ ቆሙ ታመጧቸው ዘንድ የላክኋችሁ እነዚያ ሁለት ባለ ሥራዮት ወዴት አሉ አላቸው። የልጅህን ዐይኗን በማዳን በጎ በሠሩልህ ፈንታ ለምን በክፋት ትፈልጋቸዋለህ አሉት። ከዚህም ጥሩራቸውንና ትጥቃቸውን ፈትተው ገንዘብህን ውሰድ እኛ ግን ከአንተ የተሻለ ንጉሥ አግኝተናል ይኸውም የጴጥሮስና የጳውሎስ አምላክ ነው ብለው ከፊቱ ጣሉለት። በሰማ ጊዜም ደነገጠ ተቆጥቶም እስከሚገድላቸው ድረስ በወህኒ ቤት ይጨምሯቸው ዘንደ አዘዘ።

ከዚህ በኋላም ራሱ ይይዛቸው ዘንድ ተዘጋጀ የጦር መሣሪያውንም አዘጋጀ ወደ ፊልጶስ አገር ሔደው እስከ መሠረቷ ያጠፏት ዘንድ ሃያ ሺህ አራት መቶ እግረኞች ጭፍሮችን አዘዛቸው። ቅድስ ጴጥሮስም በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ቅዱስ ጳውሎስን እንዲህ አለው። ወንድሜ ሆይ አገርን እንዳያጠፋ ሳይወጣ ወደ ጰራግሞስ ተነሥ እንሒድ አለው ከዚህም በኋላ ጸሎትን ጸለዩ ወጥተውም በደመና ተጫኑ በቤተ መንግሥት መካከልም አወረዳቸውና በጰራግሞስ ፊት ቆሙ እንዲህም አሉት እነሆ እኛ በፊትህ ነን ስለ እኛ አገርን አታጥፋ። ያን ጊዜም ጭፍሮች እንዲመለሱ አዘዘ።

ሐዋርያትንም እንዲህ አላቸው አገሩን ሁሉ በሥራይ የምታጠፉ ሥራየኞች አናንተ ናችሁን እነርሱም ይህ ሥራ ለእኛ አይገባም አሉት። ሁለተኛም ኃጢአታችሁ ነው ወደዚህ ያመጣችሁ አላቸው።

ችንካር ያላቸው ሁለት የራስ ቁሮችን ከብረት እንዲሠሩ አቃቂርንም እንዲመሉአቸው በእሳትም አግለው በሐዋርያት ራስ ላይ እንዲደፉአቸው አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው። ያን ጊዜም ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ ብሎ ጸለየ አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ የጌትነትህን ኃይል በጰራግሞስ ላይ ግለጽ። ያን ጊዜም ጰራግሞስ ከወገኖቹ ሁሉ ጋር በነፋስ ውስጥ ተዘቅዝቆ ተሰቀለ። በዚያን ጊዜም ጌቶቼ ሆይ ይቅር በሉኝ ከዚህ ፆዕርም አድኑኝ እያለ ጮኸ የእንዶር ንጉሥ አስቶኛልና የተረገመ ይሁን በእናንተም ላይ ክፉ የሚናገር ሁሉ የተረገመ ይሁን አለ። ቅዱስ ጴጥሮስም የታሠሩትን ጭፍሮች ይፈቷቸው ዘንድ እስከምታዝ ከዚህ ስቅላት አትወርድም አለው እርሱም ወደ ልጁ ወደ ሎይ ተጣርቶ ትፈታቸው ዘንድ አዘዛት እርሷም አንዳዘዛት ፈታቻችው።

ቅዱስ ጴጥሮስም ዳግምኛ አለው አሁንም ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም በምድር ላይም እንደእኔ ያለ ርኩስ የለም ብለህ ካልጻፍህ አትወርድም ይህችንም በከተማው መካከል ያነቧት ዘንድ ታዝዛለህ። ንጉሡም ወረቀትንና ቀለምን ታቀብለው ዘንድ ወደ ልጁ ተጣራ እርሷ ብቻዋን ከስቅላት ቀርታ ነበርና ባመጣችለትም ጊዜ ቊልቊል ተሰቅሎ እያለ ጻፈ በከተማውም መካከል ያነቧት ዘንድ ላካት።

ያን ገዜም ጰራግሞስንና ወገኖቹን አወረዷቸው ወደ ሐዋርያትም መጥተው ከእግራቸው በታች ሰገዱላቸው ንጉሡም ጌቶቼ ይቅር በሉኝ እኔ በአምላካችሁ አምናለሁ አለ ሕዝቡም ሁሉ ሕያው በሆነ አምላካችሁ እናምናለን እያሉ ከሐዋርያት እግር በታች ወድቀዉ ሰገዱ።

እነርሱም ሃይማኖትን አስተምረው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው ጭፍሮችንም አጠመቋቸው። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን አንድ ሆኑ። ቤተ ክርስቲያንንም ሠሩላቸው ከአዋቂዎቻቸውም ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾሙላቸው። ነገረ ምሥጢርንም እያስገነዘቡአቸው በእነርሱ ዘንድ ኖሩ። ሃይማኖታቸውንም ይጸና ዘንድ ቅዱሳት መጻሕፍትን ሰጧቸው። እንዲህም አሏቸው በሃይማኖታችሁ ጽኑ እኛ ካስተማርናችሁ ትምህርት አትናወጹ ወደ እናንተም እንመለሳለን። ከዚህም በኋላ ሰላምታ ሰጥተዋቸው ወደ ፊልጶስ ሀገር ሔዱ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ተስፋ_ሐዋርያት_ዘዋልድባ

ዳግመኛም በዚህች እለት የዋልድባው አቡነ ተስፋ ሐዋርያት የተሰወሩበት ዕለት ነው፡፡ አባታቸው ተክለ ሐዋርያት ሲባሉ እናታቸው ወለተ ሐዋርያት ይባላሉ፡፡ የአባታቸው የትውልድ ቦታ ሰሜን ጎንደር ሲሆን የእናታቸው ደግሞ ሽሬ ነው፡፡

በዋልድባ ከሳሙኤል ዘዋልድባ ቀጥለው በገዳሙ የተሾሙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ይኸውም የሆነው በአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ትእዛዝ መሠረት ነው፡፡

አቡነ ተስፋ ሐዋርያት በአቡነ ሳሙኤል መቃብር ላይ የፈለቀውን ፀበል ለአትክልት አንድ ጊዜ ብቻ በማጠጣት ለብዙ ጊዜ ዳግመኛ አያጠጡትም ነበር፡፡ ዛሬም ድረስ በዋልድባ አካባቢ ያለው የለምነት ምሥጢር ይኸው ነው፡፡

አቡነ ተስፋ ሐዋርያት ልዩ ስሙ አባ ነፅዓ በተባለው ቦታ ገዳማቸውን ከመሠረቱ በኋላ በዋልድባ ያለውን የአንድነት ማኅበሩን በከፍተኛ ሁኔታ አጠናክረውታል፡፡ በጣም ብዙ መነኮሳትንም አፍርተዋል፡፡ ጻድቁ በታላቅ ተጋድሎአቸው በእጅጉ ይታወቃሉ፡፡

በመጨረሻም ሞትን ሳይቀምሱ በዚህች ዕለት ተሰውረዋል፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)
መዝሙር በቀዳሚ ገብረ

ከሐምሌ ፲፯ እስከ ሐምሌ ፳፫

በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ ወኲሎ ፈጺሞ አዕረፈ በሰንበት ወይቤሎ ለኖኅ አመ አይኅ ግበር ታቦተ በዘትድኅን አነ አቀውም ኪዳንየ ዘምስሌከ ለዓለም ከመ ዳግመ ለምድር ኢያማስና በአይኅ ከመ አሀባ ለምድር ሣዕረ ሐመልማለ ክረምተ ወሐጋየ ዘርዐ ወማዕረረ ዝኬ ውእቱ ጸጋሁ ለእግዚአብሔር በአማን ኢይኄሱ ቃሎ ዘነበበ

ምስባክ፦

እስመ ትቤ ለዓለም አሐንጽ ምሕረተ
በሰማይ ጸንዐ ጽድቅከ
ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ መዝ ፹፰፥፪

የዕለቱ ወንጌል፦

ማቴ ፳፬፥፴፮ - ፍ፤ ወይም ማር ፮፥፵፯ - ፍ

ቅዳሴ - ዘኤጲፋንዮስ
ሥርዓተ ማኅሌት ዘመስከረም አስተርእዮተ መስቀል "መስከረም ፲፯"

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ለአብ ንሴብሕ፤ በኦሪተ ሙሴ ዘተነግረ ስኑ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ ዕፀ አንህዮ ለባሕር ዛህኑ፤ መስቀለ አልፋ ተረክበ ዮም በቅዱስ መካኑ፤ አፅደለ ውስተ ዓለም ብርሃኑ።

ነግሥ
ኦ ማርያም መንክር ልደትኪ፤ ወዕፁብ ግብርኪ፤ ዓምደ እሳት ዘፆርኪ፤ ወልድኪ መድኃኔዓለም ዲበ ዕፅ ተቀነወ፤ ወዘተጼወወ ሕዝበ በደሙ ቤዘወ።

ዚቅ
ዮመ መስቀል አስተርአየ እለ ማሰኑ ፍጥረተ አሠነየ፤ ዮም መስቀል ተኬነወ ወዘተጼወወ ሕዝበ በደሙ ቤዘወ፤ ዕፀ መስቀሉ ለወልድ ተረክበ ዮም በቀራንዮ መካን፤ ዘደፈኑ አይሁድ መስቀል ዕፀ ሕይወት፤ ዕፀ መድኃኒት።

ወረብ
በቀራንዮ መካን ዘደፈኑ አይሁድ/፪/
መስቀል ዕፀ ሕይወት ዕፀ መድኃኒት/፪/

መልክዐ መስቀል
ሰላም ለዝክረ ስምከ በመጽሔተ መስቀል ዘተለክዐ፤ ወለስእርትከ ጸሊም ዘደመ ተኮርዖ ተቀብአ፤ ሰዋስወ ፍቅር ክርስቶስ ትኩል ዲበ እንግድዓ፤ አስትየኒ ለተሳትፎ እንተ ሰተይከ ጽዋዓ፤ በዋዕየ ፍቅርከ አምላካዊ ሕሊናየ ጸምዓ።

ዚቅ
ይትቀደስ ስምከ በኃይለ መስቀልከ፤ በዕፀ መስቀልከ ክቡር ዘአዕበይኮ ለስምከ፤ ስብሐት ለከ ለባሕቲትከ ልዑል፤ ወሠራዕከ በዓለ ለኲልነ ዕረፍት።

ወረብ
"ይትቀደስ ስምከ"/፪/ በኃይለ መስቀልከ/፪/
ዕፀ መስቀልከ ዘአዕበይኮ ለስምከ ስብሐት ለከ ለባሕቲትከ/፪/

መልክአ መስቀል
ሰላም ለመዝራዕትከ በደመ ማዕሠር ዘተሤረየ፤ ወለኲርናዕከ ክቡር እንተ ተመሰለ ብየ፤ ለወሀቤ ዝናም ክርስቶስ ዘከልዑከ ማየ፤ ምንተ እነግር ወእዜኑ ዘመስቀልከ ዕበየ፤ እስመ ኃይለ ነገር ጽኑዕ እምአፉየ በልየ።

ዚቅ
ርእዩ ዕበዮ ለዕፀ መስቀል እግዚኡ ዘከመ ከለሎ፤ ዮም በምድር ተዝካሩ በሰማያት በላዕሉ፤ ርእዩ ዕብዮ ለዕፀ መስቀል፤ ይቤሎ መድኃኒነ ለዕፀ መስቀል፤ ዕውራን ይሬእዩ ወጽሙማን ይሰምዑ፤ እለ ለምጽ ይነጽሑ እለ መጽኡ ኀቤየ።

ወረብ
ርእዩ ዕበዮ ዕበዮ ለዕፀ መስቀል/፪/
ዮም በምድር ተዝካሩ በሰማያት በላዕሉ በሰማያት/፪/

መልክአ መስቀል
ሰላም ለገቦከ ኲናተ ሐራዊ ዘወግዖ፤ ወለአዘቅተ ማይ ከርሥከ ለደመ ሥርዓት እንተ አንቅዖ፤ ሐዋርያ አብ ክርስቶስ ዘፈጸምከ ግብረ ተሰብኦ፤ ዕቀበኒ በመስቀልከ ለመልአከ ዓለም ዘሞዖ፤ ከመ ኖላዊ የዓቅብ እምተኲላ በግዖ።

ዚቅ
እምገቦከ ውኅዘ ነቅዓ ማይ፤ ዘቀደሶ ለፈያታይ፤ መስቀልከ እግዚኦ ምስካይ ለነዳይ።

ወረብ
እምገቦከ ውኅዘ ነቅዓ ማይ ዘቀደሶ ለፈያታይ/፪/
ለነዳይ ምስካይ መስቀልከ እግዚኦ ለነዳይ ምስካይ/፪/

አንገርጋሪ
ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአይሁድ እመኑ ብየ፤ ወእመኑ በአቡየ፤ ዮምሰ ለእሊአየ፤ አበርሕ በመስቀልየ

አመላለስ
ዮምሰ ለእሊአየ/፪/
አበርሕ በመስቀልየ/፬/

ወረብ
"ይቤሎሙ ኢየሱስ"/፪/ ለአይሁድ/፪/
እመኑ ብየ ወእመኑ በአቡየ አበርሕ በመስቀልየ ለእሊአየ/፪/

እስመ ለዓለም
ብከ ንወግዖሙ ለኲሎሙ ፀርነ፤ ይቤ ዳዊት በመንፈሰ ትንቢት፤ በእንተ ዕፀ መስቀል ዘተሰቅለ ዲቤሁ ቃለ አብ፤ ወበስምከ ነኃሥሮሙ ለእለ ቆሙ ላዕሌነ፤ ወካዕበ ይቤ ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ፤ ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅስት ወይድኃኑ ፍቁራኒከ፤ ወንሕነኒ ንትፈሣሕ ዮም ወንግበር በዓለ፤ በዛቲ ዕለት በዓለ እግዚእነ።

ዓዲ (ወይም)
እስመ ለዓለም
መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ፤ እምኲሉሰ ፀሐየ አርአየ፤ መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ።




🌼 መልካም በዓል 🌼
“በኢየሩሳሌም ቆዩ”!

ኢየሩሳሌም ማለት የሰላም ከተማ ማለት ነው። ደቀመዛሙርቱም “ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ከሰማይ እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ቆዩ” ተብለው ነበር። ሁለት ደቀ መዛሙርት ግን ይህን ቃል ረሱና ከኢየሩሳሌም ከተማ ወጡ! እነማን ይሆኑ?
እነሆ ሁለት መንገደኞች የጌታችንን ነገረ ሕማሙን የእለተ አርብ የቀራንዮ ውሎውን እየተነጋገሩ ከኢየሩሳሌም 60 ምዕራፍ ወደምትገኘው ወደ ኤማሁስ ይጓዙ ነበር። ጌታችን ያዘዛቸው ግን ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ ነበር። የኤማሁስ መንገደኞቹ ሉቃስና ቀልዮጳ ይህን ቃል ረሱና ከኢየሩሳሌም ለመውጣት ጉዟቸውን ጀመሩ።
የኤማሁስ መንገደኞቹ በጉዟቸው ላይ ይነጋገሩ የነበረው ስለ ቃለ እግዚአብሔር ነበርና “ቃል” በመካከላቸው ተገኘ። ሁለት ወይም ሦስት ሆናችሁ በስሜ ብትሰበሰቡ በመካከላችሁ እገኛለሁ ያለ ጌታ በመካከላቸው ተገኘ። ልባቸውን ከፈተ። ያን ጊዜም “በኢየሩሳሌም ቆዩ” የሚለው ቃል ትዝ አላቸውና በዛች ሰአት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። ሉቃስ [24: 13-33]
ይህ ወንጌል እኛም እንደ ኤማሁስ መንገደኞች ስለ ነገረ ቤተክርስቲያን እየተነጋገርን ከቤተክርስቲያን እርቃ ወደምትገኘው ወደ ዓለም እንዳንጓዝ ያስተምረናል። በተለያዩ ምክንያት ከቤተክርስቲያን ስንርቅ በሥጋም በነፍስም መጠውለግ ቀጥሎም መድረቅ ይመጣል! ለዚህ እኮ ነው ጌታችን “እየጠወለጋችሁ ስትሄዱ እርስ በእርሳችሁ የምትነጋገሩት ስለምንድን ነው?” ያለው። ሉቃስ [24:16]
ኢየሩሳሌም ማናት
1-ኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን ናት
ጌታችን በከበረ ደሙ ፈሳሽነት የዋጃት ናት
ሥጋ ወደሙ እንዲፈተትበት የመረጣቸውን
ማቴ ፣16-18
★የክርስቲያኖች ሰውነት ቤተክርሰቲያን ይባላል
★የክርስቲያኖች ስብስብ ቤተክርሰቲያን ይባላል
★ህንጻ ቤተክርሰቲያን ቤተክርሰቲያን ይባላል
ሐዋርያት በኢየሩሳሌም በመቆየታቸው 3ቱንም አሟልተዋል
★በነጠላ ሰውነታቸው በእምነት ፀንተው
★እንደ ማህበር መቶ ሃያው ቤተሰብ በአንድ ሀሳብ በአንድ ልብ ሆነው
★እንደ ሕንጻ በማርቆስ እናት ጣሪያ ስር ሆነው በመቆየታቸው መንፈስ ቅድስን ለመቀበል በቅተዋል ዛሬስ እኛ እንዴት ነን በእምነታችን ጠንክረናል በአገልግሎታችንስ በአንድ ሀሳብ በአንድ ልብ ሆነን እያገለገልን ነው ዘወትር በቤቱ ለቅዳሴው ለኪዳኑ ለማሕሌቱ እንመላለሳለን
በጊዜ የለንም ሰበብ ምክንያት እየደረደርን ከቤቱ ከአገልግሎት እየራቅን ነው

2ኛ ኢየሩሳሌም እመቤታችን ናት
በኢየሩሳሌም ቆዩ ማለቱ ከእመቤታችን ጋር ኑሩ ማለቱ ነው ሐዋርያትም በአንድ ልብ በጸሎት ሲተጉ ነበር እመቤታችንን ይዘው
3ኛ ኢየሩሳሌም መንግስተ ሰማያት ናት
የሰው ልጅ ከትንሳኤ ዘጉባዔ ፍርድ በኀላ በአካለ ነፍስ ይኖርባት ዘንድ የተዘጋጀች ቦታ ዕብ 12÷22
በኢየሩሳሌም ቆዩ መባላቸው በእምነት በምግባር ፀንተው የመንግስተ ሰማያት ባለቤት እንዲሆኑ ነው ይሁዳ ጌታዉን ሸጦ ከእግዚአብሔር መንግሥት ተለይቷልና
እግዚአብሔር አምላክ የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ወራሾች እንድንሆን በአምልኮተ እግዚአብሔር ፀንተን በእመቤታችን አማላጅነት ታምነን በቅድስት ቤተክርስቲያን እያገለገልን እንድንኖር ይርዳን፡፡

ምንጭ ፡-ሐመር መጽሔት ግንቦት/ሰኔ 1983 ዓ.ም

@wwwyarede
አንድ ፡ አምላክ ፡ በሚሆን ፡ በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ስም ፡ ታኅሣሥ ፳፬ በዚህ ፡ ቀን ፡ የከበረና ፡ የተመሰገነ ፡ አዲሱ ፡ ሐዋርያ ፡ አባታችን ፡ ተክለ ፡ ሐይማኖት ፡ ተወለደ።

በፀሎቱ ፡ የምትገኝ ፡ በረከቱ ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ትኑር ፡ ለዘልዓለሙ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምስጋና ፡ ይሁን ፡ አሜን።

ስንክሣር ፡ ዘወርሃ ፡ ታሕሳስ

የሕይወት ፡ እናቱ ፡ ሆይ፤ ተቀዳሚ ፡ ተከታይ ፡ በሌለው ፡ በአንድ ፡ ልጅሽና ፡ በእኛ ፡ መካከል ፡ አስታርቂን።