#ዕርገት በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የዛሬው በዓል ምን ይደንቅ! እነሆ ነገደ መላእክት ኹሉ ሲዘምሩ፣ አንዳንዶቹ ከኋላው ተከትለዉት፣ አንዳንዶቹ ከፊቱ ቀድመዉት፣ አንዳንዶቹ በዙሪያው ከብበዉት፣ ሌሎቹ ከሐዋርያት ጋር ኾነው፡- “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ! ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል” ሲሏቸው እናያቸዋለንና፡፡
ብዙ ድንቅ ምልክቶችን ያደረገው ይህ ኢየሱስ ነው፡፡ በዚህ የጌታችን በዓል፣ በዚህ በዕለተ ዕርገት ቀድመን እንደ ተናገርን ዲያብሎስ አለቀሰ (አዘነ)፤ ምእመናን ግን ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ እነሆ አሁን ደስ የሚያሰኘው ምንጭ ፈለቀ፤ እነሆ አሁን አበቦች ፈኩ፡፡ የወይን ቅርንጫፎች ደረሱ፤ የወይራ ዛፎችም ጥዑም መዓዛቸውን ሰጡ፡፡ በለሶችም እሸት ፍሬያቸውን ለገሱ፡፡ ነፋሱም ሐመልማላትን እንደ ባሕር ጨዋታ እያወዛወዘ ነፈሰ፡፡ ኹሉም ከእኛ ጋራ በጌታችን ዕርገት ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ ስለዚህ፡- “አሕዛብ ኹላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር ዕልል በሉ፡፡ እግዚአብሔር በዕልልታ፣ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዓረገ” እያልን ወደ ላይ ወደ ሰማያት ላረገው ለጌታችን እንዘምር ዘንድ ከእኛ ጋር የክቡር ዳዊትን ቃለ መዝሙር አምጡ፡፡
እነሆ ጌታችን ወደ ሰማያት ዓረገ፤ ነገር ግን ከእኛ አልተለየም፡፡ የወደቀውን አዳም ያነሣው ዘንድ የወረደው እርሱ እነሆ ዛሬ ከሰማየ ሰማያት በላይ ዓረገ፡፡
ነቢያት በትንቢት መነጽር ያዩት እርሱን እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሐዋርያትም የበሉት ከእርሱ ጋር እንጂ ከሌላ ጋር አይደለም፡፡ በአባቱ ዕቅፍ የነበረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በጲላጦስ የተፈረደበትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በመስቀል ላይ በሚስማር የተቸነከረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በዘባነ ኪሩብ ላይ የነበረውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ጻድቁ ዮሴፍ በጨርቅ የጠቀለለው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በእጁ መዳፍ ፍጥረታትን የያዘውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ በመቃብር ያደረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሱራፌል ያመሰገኑትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በአባቱ ቀኝ የተቀመጠው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ነስቶ ሰው የኾነውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
እግዚአብሔር በዕልልታ ዓረገ፡፡ አምላክ በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡ ከዘለዓለም አንሥቶ ፈጣሪ የኾነው፣ ኹሉንም ነገር ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው፣ አዳምን የሠራው፣ የሰው ልጆችን የፈጠረው፣ ደስ ያሰኘውን ሄኖክን ወደ ሕይወት ያሸጋገረው፣ ኖኅን ከዓለም ጋር የጠበቀው፣ አብርሃምን ከከለዳውያን ምድር የጠራው፣ ይስሐቅን የነገረ መስቀል ምሥጢር ምልክት እንዲኾን ያደረገው፣ ያዕቆብን የዐሥራ ኹለቱ አዕማድ ሥር እንዲኾን ያደረገው፣ ለኢዮብ ትዕግሥትን የሰጠው፣ ሙሴን የሕዝቡ መሪ እንዲኾን አድርጎ የሾመው፣ ሳሙኤልን ከእናቱ ማኅፀን አንሥቶ በትንቢት የሞላው፣ ከነቢያት መካከል ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ የቀባው፣ ለሰሎሞን ጥበብን የሰጠው፣ ኤልያስን በእሳት ሰረገላ የወሰደው፣ ነቢያት መጻእያትን እንዲያዩ ያደረጋቸው፣ ለሐዋሪያት ሀብተ ፈውስን የሰጣቸው፥ “አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” ብሎም አሰምቶ የነገራቸው እርሱ ዛሬ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡
ወደ ሰማያት በዕልልታ ያረገው፣ በአባቱም ቀኝ የተቀመጠው የክብር ጌታ ይህ ነው፡፡ መላእክትና አለቆች ኃይላትም ይገዙለታል፡፡ ቁርጥ ልመናችንን የሚቀበል፣ ወደረኞቻችንን ድል እንድንነሣቸው ኃይልን የሚሰጠንም እርሱ ነው፡፡ “እባቡን ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ እነሆ ሥልጣን ሰጠኋችሁ” እንዳለ በክፉ መናፍስት ኹሉ ሥልጣን ያለው እርሱ ነው፡፡
ነውር ነቀፋ የሌለብህ ንጹሃ ባሕርይ ሆይ! በነፍስ፣ በሥጋና በመንፈስ ጠብቀን፡፡ ይህን በዓል እናከብረው ዘንድ የሰበሰብከን የኹሉም አምላክ የኾንህ ጌታችን ሆይ ! በጽድቅ ፍሬ የተሞላን አድርገን፡፡
ለአንተም ከባሕርይ አባትህ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወትህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ክብር፣ ኃይልና ስግደት ኹሉ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ይገባል፥ አሜን፡፡
© ምንጭ፦ የክርስቲያን መከራ መጽሐፍ፥ ገገ. 162-164

ሥርዓተ ማኅሌት ዘሰኔ ሚካኤል "ሰኔ ፲፪"
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለጒርኤክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ: ብኡላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ: እመትትኃየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ: ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ስጋየ ጌሠ: ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ።
ዚቅ
ኢይጽሕቅ ዘይመክሮ ወኢየኀሥሥ ዘይመክሮ: አልቦቱ ጥንት ወኢተፍጻሜት: ኢየኀልቅ መንግሥቱ ወአልቦ ዘይክል መዊዓ ኀይሉ: ወአልቦ ኁልቊ ለሠራዊተ መላእክት እለ ይትለአክዎ: አንተ ውእቱ አቡሃ ለጥበብ: ገባሬ ኲሉ ፍጥረት ወገባሪሃ ለሕግ።
ነግሥ
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሳሕል: እንበለ ባህቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል።
ዚቅ
አመ ይነፍህ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት።
መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ: ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ፀሃፈ: ሶበ እጼውእ ስመከ ከሢትየ አፈ: ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ: ለረዲኦትየ ነዓ ሠፊሐከ ክንፈ።
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ዓቢተነ በመድኃኒትከ: ጸግወነ ንጸውዕ ስመከ: ኖላዊነ ኄር ትጉሕ ዘኢትነውም ሰላመከ ሀበነ።
ወረብ
ሀበነ ሰላመከ ንጸውዕ ስመከ/፪/
ዘኢትነውም ትጉሕ "ኖላዊነ ኄር"/፪//፪/
መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተኃበለ: በእንተ ስጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበኃለ: ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ: ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ: በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ።
ወረብ
ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ/፪/
"በብሂለ ኦሆ"/፪/ ፍጡነ አስምአኒ ቃለ/፪/
ዚቅ
አመ ይነፍሕ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት።
መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ዕብል ለአስናኒከ ዘመንፈስ: ዘኢይረክቦን ጥረስ: ሚካኤል ረዳኢ ለእለ ውስተ ባሕር ወየብስ: እስመ ረሰይከ ካህነ ምሥዋኡ ክርስቶስ: መፍትው ሊተ ትተንብል ቀሲስ።
ዚቅ
ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ ምስሌሁ: ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ: ዮም ሰማያዊ በምድር አስተርአየ።
ወረብ
ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ/፪/
ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ ስዕንኩ/፪/
መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለእስትንፋስከ ቁሱላነ ነፍስ ለአጥዕዮ: ዘይነፍሕ ፄና አንህዮ: ሚካኤል ነዓ ኲናተከ በተረስዮ: ለገቢር ከመ ቀዳሚ ለአርዌ አመፃ ደርብዮ: እስመ ኢኃደገ እንከ ዘትካት እከዮ።
ዚቅ
ወከሢቶ ረከበ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ: ወእከስተ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን: ወእፈውስ ሎሙ ለቁሱላነ ልብ: ወእሰምዮ ለባሕራን ኅሩየ: ዝኬ ዘተነግረ በመዋዕለ ትካት: ለ፳ኤል ኅብስተ መና ዘአውረደ በገዳም: ወርእየቱ ከመ ተቅጻ ወከመ አያያተ መዓር ጥዑም ፈድፋደ።
ወረብ
"ወከሢቶ ረከበ"/፪/ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ/፪/
ወእስብክ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን ወእስምዮ ለባሕራን ኅሩየ/፪/
መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለአጻብኢከ መጽሐፈ እለ ለክዑ: ዕጒለ አባግዕ እምኖሎት በጊዜ ተመልዑ: ሚካኤል አንተ ለንጉሠ ነገሥት ካህነ ምሥዋኡ: አሣዕነ መድኃኒት ለእገርየ አጻብኢከ ይቅጽዑ: ከመ በፍናውየ የኀዝ ለሰላም ቅብዑ።
ዚቅ
ቅዱሳት አጻብኢከ ለጽሒፈ መጽሐፍ እለ ተቀንያ: ወብጹዓት አዕይንቲከ ምስጢረ መለኮት ዘርእያ: ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ።
ወረብ
ምስጢረ መለኮት ዘርእያ አዕይንቲከ/፪/
ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ "ሚካኤል መልአክ"/፪//፪/
መልክዐ ሚካኤል
አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክዕከ ኲሉ: ለለአሐዱ አሐዱ ዘበበክፍሉ: ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ: ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኃ ሰማያት ዘላዕሉ: ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ።
ዚቅ
መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል: ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ: አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዓቢይ።
ወረብ
መልአከ ሰላምነ/፬/
ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል በእንቲአነ/፪/
ምልጣን
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ: ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ: ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ: ወሪዶ እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ።
አመላለስ
ወሪዶ እመስቀሉ/፪/
እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ/፬/
ወረብ
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ/፪/
ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ/፪/
ቅንዋት
ተሰቅለ ወሐመ ከመ እቡዕ ማዕከለ ክልኤ ፈያት፤ ዘይትዓፀፍ ብርሃነ ፤ከመ ልብሰ ሰማዕት ሠያሜ ካህናት ፤ማ፦ዓርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት አእኰትዎ መላእክት
አመላለስ፦
ዓርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት/2/
አእኰትዎ መላእክት/4/
መልካም በዓል

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
እንኳን ለማር ገላውዴዎስ ሰማዕት (ሕይወቱ መላእክትን የመሰለ)፣ ለአንድ ሺ ሰማንያ ስምንት ሰማዕታት (የቅዱስ ገላውዴዎስ ማኅበር)፣ ለአባ ክርዳኑ ሊቀ ጳጳሳት፣ ለእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ክብራ ኢትዮጵያዊት (የአቡነ በጸሎተ ሚካኤል እህት) እንዲኹም ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዳሴ ቤቱ (ግብጽ) ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ
"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም!"
ዳግመኛም ዛሬ ሰኔ 11 ቀን ቅዱስ ያሬድ ካህን፣ ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት፣ ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና እንዲኹም አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው
አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን አሜን!
"የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯

https://youtu.be/RSIv8boo6TE
በደ/ነ/ቅ/ዮሐንስ እና መ/ጎ/ቅ/ማርያም ቤተክርስቲያን የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ት/ቤት የ ቲዩብ ቻናል የተወሰደ

YouTube
የሆነብንን አስብ (ጭውውት)
"ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ ስለ መንግስተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ" የሐሙስ ውዳሴ ማርያም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የምርጫ ካርዴ ለቅድስት ቤተክርስቲያኔና ለሀገሬ
"አንተም ከህዝብ ሁሉ አዋቂዎችን እግዚአብሔርን የሚፈሩት፥ የታመኑ የግፍን ረብ የሚጠሉትን ሠዎች ምረጥ " ዘፀ 18:21

ጾመ ሐዋርያት
ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገር ሁሉ መከልከል ማለት ነው፡፡ ወይም ለሥጋ የሚመቸውን ነገር መተው ማለት ነው፡፡ ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ጾም አለ ጾም ከሃይማኖት ጋር ዘለዓለማዊ ዝምድና አለው፡፡ ይልቁንም በብሉይ ኪዳን ጾም ከፍተኛ ቦታ ነበረው፡
የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ጋር በሚገናኙበት ወራት እህል ውኃ ለአፋቸው አይገባም ነበር፡፡
/ዘዳ 34፥28/ በኃጢአታቸው ብዛት የመጣባቸው መዓት የሚመልሰው ቁጣውም የሚበረደው ሕዝቡ በጾም ሲለምኑትና ሲማልዱት ነበር፡፡ /ዮና 3፥5-10/፡
በአዲስ ኪዳንም ጾም ሰው ሠራሽ ሕግ ሳይሆን ራሱ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕል ሥጋዌው መጀመሪያ አድርጎ የሠራው ሕግ ነው፡፡ /ማቴ 4፥21/ ጌታችን በሦስት በፍቅረ ንዋይና በትዕቢት የሚመጣበትን ጠላት ዲያብሎስ በጾም ድል እንድምንነሣው አሳየን፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር ጠላት ሰይጣንን በጾም የሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግሯል /ማቴ 17፥21/፡
ስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናትና ቀሳውስት የሚሾሙትም በጾምና በጸሎት ነበር፡፡ /የሐዋ13፥3፤4፥25/ እነ ቅዱስ ቆርኔሌዎስ ያላሰቡትን ክብር ያገኙት በጾማና በጸሎት ፈጣሪያቸው ማልደው ነው /የሐዋ 10፥20/
ጾም እንኳን የጠበቅነውንና ያሰብነውን ቀርቶ ያላሰብነውንና ያልጠበቅነውን ፈጽሞም የማይገባንን ጸጋና ክብር የሚያሰጥ ነው፡ በሐዋርያት መሠረት ላይ የተመሠረተች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የጾም ሕግና ሥርዓት አላት እነዚህም የፈቃድና የአዋጅ አጽዋማት ይባላሉ፡፡ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ የሐዋርያት (የሰኔ) ፆም ነው፡፡
ይህም ጾም በሕዝብ ዘንድ የወታደር ጾም ይባላል፡፡ ለስብከተ ወንጌል ዘመቻ የተዘጋጀ በጾሙት ተምሣሌት በድሮ ዘመን ወታደሮች ለዘመቻ ሲነሱ ወይም ከዘመቻ ሲመለሱ በተሳተ በተገጸፈ ይቅር በለን በማለት ይጾሙት ነበር፡፡ ይህም ጾም የሚፈሰክበት ከሐምሌ 5 የማይለቅ ቢሆንም የሚጀመርበት ግን የተወሰነ ቀን የለውም በዚህም ምክንያት የጾሙ ዕለት ቁጥር ከፍና ዝቅ ይላል አንዳንድ ጊዜ ከአርባ ይበልጣል አንዳንድ ጊዜ ከ30 ያንሣል የ2013 ዓ.ም. ጾም ሰኔ 14 ገብቶ ለሦስት ሳምንት ይጾማል፡፡
ሐዋርያት መቼ ጾሙ?
ቅዱሳን ሐዋርያት የአምላካቸውን የመምህሮቸዋል አርአያ ተከትለው እርሱ ወደ ማዳን ሥራው /ሕሙማነ ሥጋን በተዓምህራት/ ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት ከማዳን አስቀድሞ የሥራውን መጀመሪያ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ 40 ቀን 40 ሌሊት እንደ ጾመና እንደጸለየ ሁሉ ቅዱሳን ሐዋርያትም አብነቱን ተከትለው ጾመዋል፡፡ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ዓለምን ዕጣ ተጣጥለው (ተከፈፍለው) ዞረው ከማስተማራቸው አስቀድመው የሥራቸው መጀመሪያን ጾምን አድርገዋል፡፡
ሐዋርያትም ይህንን ጾም እንደሚጾሙ ጌታችን አስቀድሞ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው በጠየቁት ጊዜ ተናግሮ ነበር፡፡ “እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለምንድን ነው? አሉት ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉ? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል በዚያን ጊዜም ይጦማሉ” /ማቴ 9፥15-16/፡፡
የሰኔ ጾም የቄስ ብቻ ነውን?
ይህ ጥያቄ ብዙ ሰዎች የሚነሣ ጥያቄ ነው ብዙ ምእመናን የሰኔን ጾም አይጾሙም ለመጾም የሚፈልጉትንም ሰዎች የቄስ ነው እያሉ ሲነቅፉ ይታያሉ ነገር ግን ይህ ጾም ከሰባቱ የአዋጅ ጾም አንዱ ነው፤ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታቸንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት እኛም እነርሱን አርአያ አድርገነው ልንጾመው የሚገባ የበረከት ጾም ነው፡፡ በዘመናችን ያሉ አንዳንድ “ክርስቲያኖች ነን” ባዮች “ከመጾም ተቆጥበው ቀሳውስት ብቻ የሚጾሙት ነው!” ይላሉ ለራስ የከበደን ነገር በሌላው ላይ መጫን ተገቢ አይደለም ካላወቁ ለማወቅ መማር ዐውቆ ከማጥፍት መቆጠብ ተገቢ መሆኑን መዘንጋት አይገባም
እኛ ይህን ጾም የምንጾመው የሐዋርያትን በረከት ለመካፈል፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን በመሆኑ ይህንን ዲያብሎስን ድል ማድረጊያ መሣሪያ አንጣለው ጾሙም ለመላው ክርስቲያን የተሰጠ እንጂ የቀሳውስት ብቻ አይደለም ለቄስና ለምእመናን ተብሎ በክህነት ደረጃ የተለየ ጾምም የለም፡፡
እንዴትና ከምን እንጹም?
የጾም ሃይማኖታዊ ትርጉም ፈጣሪን መለመኛ ከኃጢአት ቁራኛ መላቀቂያ መሣሪያ ስለሆነ በጾም ወራት ለአምሮት ለቅንጦት የሚበሉ ወይም ለመንፈሳዊ ኃይል ተቃራኒ የሆኑ የአልኮል መጠጦች ሥጋና ቅቤ ወተትና እንቁላል ማራቅ ተገቢ ነው፡፡
ሥጋዊ ጉልበትን በጾም የማድከም ቅብአት ካላቸው ምግቦች መከልከልም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አለው፡፡ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር “ጉልበቶቼ በጾም ደከሙ ሥጋዮም ቅቤ በማጣት ከሳ” ብሏል /108፥24/፡፡ ሠለስቱ ደቂቅና ነቢዩ ዳንኤልም የቤተ መንግሥቱን ሥጋና የጸሎት ምግብ ትተው በጥሬና በውኃ መቆየታቸው ተጽፏል /ት.ዳን 1፥8-21፣ት.ዳን10፥2/ ዋናው ነገር ጾም እንጂ መብል ወደ እግዚአብሔር አያቀረበንም ብንበላም የምናተርፈው ባንበላም የሚጎዳን ነገር የለም፡፡ /1ኛ ቆሮ8 ፥8/ ከአዳም ጀምሮ መብል ሲጥል እንጂ ሲያነሣ አላየንምና ጾሙን ከኃጢአት በመራቅ ለራስ ያስብነውን ለነዳያን በመስጠት፣ ጾም ከጸሎት ጋር ሲሆን ጸጋን እንደ ሐዋርያቱ ያሠጣልና በጸሎት በመትጋት በስግደት ወደ እግዚአብሔር በፍጹም ልብ በመመለስ ልንጾመው ይገባል፡፡
ቅዱስ ኤፍሬም “ጾም የነፍስ ድግስ፣ ክብረ በዓል ነው” ብሎ ተናግሯል፡፡ ጾም ነፍስን ሐብታም ያደርጋታል፡፡ አዕምሮውን ንጹህ ከማድረጉም ባሻገር በጠላት ላይ መንፈሰ ጠንካራ ያደርጋል ጾም ጥሩ ሥነ-ምግባራትን የሚያዳብር መንፈሳዊ ሕይወት ነው፡፡ ይኸውም ንጽህናን፣ ትዕግስትን ድንግልናን፣ ደስታን ……ወዘተ በተጨማሪም የታላቁ ንጉሥ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተመቅደስ የሆነውን አካላትንን ለንጽህና ለእርሱ እንድናስገዛ ያደርገናል፡፡
ጾም ወደ እግዚአብሔር እንድንመለስ ያደርገናል፡፡ /ት.ኢዩ 2፥12/ “አሁንስ ይላል እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁ በጾምም በለቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ!” ወደ እግዚአብሔር የምንመለስበትን የልብ መነሳሳት እውነት ያደርግናል በጾማችን እግዚአብሔርን የምናደበት የቅድስና ሕይወት እንፈጥራለን ታላቁ ነቢዩ ኢሳይያስ በኃጢአቱ ተጸጽቶ የጾመው ጾም ለኃጢአቱ ሥርየት ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርንም ክብር ለማየት አብቅቶታል /ት.ኢሳ6፥1/፡፡ በአጠቃላይ ጾም የመንፈሳዊ ሕይወታችን መሠረት ነው የአገልግሎትና የቅድስናችንም መጀመሪያ ሊሆን ይገባል፡፡
🔔የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የግንቦት ቅዱስ ሲኖዶስ ከግንቦት 17 እስከ ግንቦት 23/2013 ዓ.ም ለስድስት ቀናት ባደረገው ምልዓተ ጉባኤ ከተወሰኑ ውሳኔዎች መካከል አንዱ የሆነው ጸሎተ ምሕላ ማወጅ ነው፡፡
“‼️ሁሉን ቻይና ሁሉን አድራጊ የሰላም አምላክ እግዚአብሔር አገራችንና ሕዝባችንን በሰላምና በምሕረቱ እንዲጐበኝ ሁላችንንም ይቅር እንዲለን ከአሁን ጀምሮ በግልም ሆነ በማህበር ጸሎት በማድረግና ችግረኞችን በመርዳት እንድንተባበር ሆኖ ከምርጫው ሰኔ 14 ቀን 2013ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሐምሌ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ በመላው አገራችንና በውጭም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል‼️”
ስለዚህ ሁላችንም በዚሁ አግባብ በርተትን እንድንሳተፍ እና ላልሰሙት የማሰማት ሥራ እንድንሠራ ይሁን፡፡

" ኪዳነ ምሕረት "
በብሉይ ኪዳን የነበሩ 6ቱ ኪዳናት በዘመናቸው ክቡርና ሕዝቡን ከመቅሰፍት ይታደጉ የነበሩ ቢሆንም ከሲዖል ማዳን ግን አልቻሉም:: ስለዚህም አንድ ፍጹም ኪዳን ያስፈልግ ነበር:: ይህን ፍጹም ኪዳን ይፈጽም ዘንድም ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ ከሰማያት ወርዶ በድንግል ማርያም ማሕጸን አደረ::
በፍጹም ተዋሕዶም በሕቱም ድንግልና ተወልዶ: አድጎ: ተጠምቆ: አስተምሮ: ሙቶ: ተነስቶና ዐርጐ ሥጋ ማርያምን በዘባነ ኪሩብ አስቀመጠው:: ኪዳነ ምሕረት (የምሕረት ኪዳን) የምንለው አንዱ ታዲያ ይሔው ነው::
የጌታችን መጸነሱ: መወለዱ: መሰደዱ: መጠመቁ: ማስተማሩ: ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ: መሰቀሉ: መሞቱና መነሳቱ: ማረጉና መንፈስ ቅዱስን መላኩ በአንድ ላይ ኪዳነ ምሕረት ይባላል:: ታዲያ ይህ ሁሉ የተደረገው በሥጋ ማርያም ነውና የኪዳኑ ባለቤት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት::
የእርሷ ኪዳን የ6ቱን አበው ኪዳናት ፍጹም በማድረጉ "የኪዳናት ማሕተም" ይባላል:: የድንግል ማርያም "ኪዳኗ ከሲዖልና ከገሃነም ሊታደገን አቅሙ አለውና:: መድኃኒታችን" ክርስቶስ ለድንግል እናቱ ቃል ኪዳኑን ያጸናላት ደግሞ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ ጐልጐታ ላይ ነው:: እመ ብርሃን በዚያ ቁማ ስለ ኃጥአን ስታለቅስ "እናቴ ሆይ! በስምሽ ያመነውን: በቃል ኪዳንሽ የተማጸነውን እምርልሻለሁ" ብሎ ደስ አሰኝቷታልና::, ይሔው በእመ ብርሃን ምልጃና ቃል ኪዳን ምዕመናን ከመቅሰፍትና ከገሃነመ እሳት ማምለጥ ከጀመሩ 2ሺ ዓመታት ሆኑ:: ዛሬም, እኛ ኃጥአን ልጆቿ ከእሳ,ት እንደምታድነን አምነን
በጥላዋ ሥር እንኖራለን::
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
እንኳን ለቅድስት ኪዳነ ምሕረት ወርሃዊ በዓ አደረሰን! አደረሳችሁ!

ሰኔ 17 በዓሉ ለአባ ገሪማ ዘመደራ
አባ ገሪማ ቀዳሚ ስማቸው ይስሐቅ ሲሆን አባታቸው ሶፎንያስ ይበላል የሮም ንጉሥ ነበር፡፡ ከልጅነታቸው ጀምረው መንፈሳዊ ትምህርት ሲማሩ በዲቁና ቤተክርስቲያንን ሲያገለግሉ አድገዋል በኋላም የአባታቸውን መንግሥት ወርሰው ሰባት ዓመት ገዝተዋል፡፡
ከዚህ በኋላ አባ ጰንጠሌዎን ዘጾማዕት ምድራዊ መንግሥት ያልፍ ይጠፋ የለምን?
የማያልፈውን ሰማያዊ መንግስት ትወርስ ዘንድ ፈጥነህ ወደ እኔ ና ብለው ላኩባቸው ቅዱስ ገብርኤል በክንፉ ነጥቆ አክሱም አድርሷቸው ተገናኙ መዓርገ ምንኩስና ተቀብለው በጾም በጸሎት ተወስነው ይኖሩ ጀመር ጾማቸውም ስጋቸው አልቆ አጥንታቸው እስኪቆጠር ድረስ ነበር፡፡
በመስከረም 30 ቀን በደብረ ሰሎዳ በቅ.ሚካኤል ቤተክርስቲያን እንዲህ ሆነ፡፡ የክርስትና ቅዳሴ ነበር ልዑካኑ አንድ ቀዳሽ ስለጎደለባቸው የቤተክርስቲያኑ ገበዝ ወደ 9ኙ ቅዱሳን ሄዶ ቅዳሴ የሚቀድስ አባት ያገኝ እንደሆነ በአፅንኦት ይጠይቃል፡፡
ቅዱሳኑ እንደልማዳቸው ቋርፍ ምግባቸውን ሲመገቡ ከመካከላቸው ትልቅ በሆኑት አባት ተባርኮና ተከፋፍሎ ነበር ያንጊዜም እንደልማዳቸው ሲመገቡ ፃድቁ አቡነ ይስሐቅ የተሰጣቸውን ሳይበሉ አስቀምጠው ሲፀልዮ ሳለ ቄሰ ገበዙ መጥቶ አዋያቸው ወዲያውም ከቄሱ ጋር ሄደው ወደ መቅደስ ገብተው ቀደሱላቸው፡፡
የቀሩት ቅዱሳን ግን አቡነ ይስሐቅ የተሰጣቸውን ድርሻ (መቅኑን)ሳይበሉ ማስቀመጣቸውን ባለመረዳታቸው በልተው ቀደሱ ብለው ሲያሟቸው አቡነ ይስሐቅም ይህን አውቀው ሰው ባይመሰክርልኝ እንጨቱና ድንጋዩ ይመስክር ብለው ሲሄዱ ካላቸው መንፈሳዊ ብቃት የተነሳ ሁለት ምዕራፍ ያህል እጽዋቱ እና
ድንጋዮቹን አስከትለው ተንቀሳቅሰዋል፡፡
ይህንን ታላቅና የሚያስደንቅ ተዓምር እግዚአብሔር በእርሳቸው ላይ ስለሰራ ይህን የተመለከቱ ቅዱሳን "ገሪማ ገረምከነ" ብለው ጠርተዋቸዋል ትርጉሙም ግሩም የሆነ የሚያስገርም ትምህርትና ሥራ የሚሰራ ማለት ነው፡፡ አባ ገሪማ የተባሉት ከዚህ በኋላ ነው፡፡
ከዚህ በኋላ መደራ ገብተው በዓት ሰርተው 23 ዓመት በትኅርምት ኖረዋል፡፡ ከዚህም የበዙ ገቢረ ተዓምራትን ሲያደርጉ ኖረው በዚህ ዕለት እንደ ኤልያስ በሠረገላ ብርሃን ተሰውረዋል፡፡
ቅዱስ ያሬድ በድርሰቱ
"ግሩም ግብርከ
ወመንክር ሥነፅድቅከ
አስኬማከኒ አልባቲ ሙስና
እስመተደለወ ለከ መና"
ብሎ አመስግኗቸዋል፡፡
የጻድቁ አቡነ ገሪማ ረድኤት በረከት ምልጃ ጸሎት ከሁላችን ሕዝበ ክርስቲያን ከሀገራችን ከኢትዮጵያ ጋር ለዘለዓለም ይኑር አሜን፡፡

የሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ሰማዕታት መታሰቢያ በሻሸመኔ መካነ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ይከናወናል !!!
************************************************
በነገው ዕለት የሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ሰማዕታት መታሰቢያ በሻሸመኔ መካነ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ይከናወናል።
ባሳለፍነው ዓመት ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን በግፍ የተሰዉ መሆኑ ይታወሳል። ሆኖም ከኦርቶዶክሳውያኑ ሰማዕት መሆን በኋላ መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ.ም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ ዘምዕራብ አርሲ አማካይነት የሰማዕታቱን መታሰቢያ የማድረግና ቤተሰቦቻቸውን የማፅናናት መርሐግብር በሀገረ ስብከት ደረጃ መከናወኑ ይታወሳል።
በነገው ዕለትም በቀዳም ሥዑር ዕለት የዋለው የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓል በሻሸመኔ መካነ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያኔ ከዝክረ ግፉዓን ሰማዕታት ጋር በድምቀት የሚከበር መሆኑ ተጠቁሟል።
በብፁዕ አቡነ ሄኖክ የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መልካም ፈቃድ በነገው ዕለት ከሚከበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በተጨማሪ የሰማዕታቱ መታሰቢያ ልዩ መርሐግብር የሚደረግ መሆኑ ተገልጿል።
ምንጭ ፦ የምዕራብ-አርሲ-ሀገረ-ስብከት

"ሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ ፤ ደማቸውን ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ ፤ ስለ መንግስተ ሰማያት መራራ ሞትን ታገሱ"
ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ ቁ.6
ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ ቁ.6
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
⛈ #በዓተ_ክረምት (የክረምት መግቢያ)
ክረምት ማለት ከርመ፣ ከረመ፣ ፈሰሰ፣ ተከለ፣ ዘነመ፣ ብዙ ዘመን ኖሮ አለፈ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን የልምላሜ ፣ የዘር፣ የዝናምና የደመና ጊዜ ማለት ነው፡፡ ይህም በስፋት ስለ ሥነ-ፍጥረት መገኛና ግኝት፣ ፍጡርን ከፈጣሪ፣ መጋቢውን ከተመጋቢ ለይቶ በዝርዝር የሚያስረዳ በጸደይና በመፀው መካከል ያለ ክፍለ ዘመን ነው፡፡ በዚህ ወቅት ዘር፣ ዝናም፣ ደመና፣ ጠል፣ መብረቅ፣ ነጎድጓድ፣ ባሕር፣ ዮሐንስ፣ ዘመነ ፍሬ እና መስቀል እየተባሉ የሚጠሩ በንዑስ ክፍል የሚጠሩትን ክፍላተ ዘመንን የያዘ ከወቅቱ ጋራ ለእግዚአብሔር ምስጋና የሚቀርብበት፣ መግቦቱ የሚወሳበት ነው፡፡ በዚህ ወቅት በበጋ ወራት የሚለመልሙ ዕፀዋት (ወይን፣ በለስና የመሳሰሉት) የሚደርቁበት በበጋ የሚደርቁ ዕፀዋት ደግሞ የሚለመልሙበት የልምላሜ ወራት ነው፡፡ ይህም በየዓመቱ ከሰኔ 26 ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 25 ቀን ያለው 91 ቀን ዘመነ ክረምት ተብሎ ይጠራል፡፡ በዚህ ወቅት (በክረምት) ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ አንዱ ውኃ ይሰለጥናል፤ አፈርን የሚያጥብ፣ እሳትን የሚያጠፋ በብሩህነቱ ከእሳት በቆሪርነቱ ከነፋስ በርጡብነቱ ከመሬት ተስማምቶ ይኖራል፡፡
#የውኃ_ክፍላት
ሀ. ከምድር በታች ያለ ውኃ፦ ከእሳትና ከነፋስ ጋራ ተነባብሮ ምድርን ተሸክሞ የሚኖር ነው፡፡ ይህ ውኃ በዓለም ላይ በምንጭነትና በወንዝነት እንዲሁም በከርሠ ምድር ውስጥ ሆኖ ለአትክልት ፣ ለአዝርዕት፣ ለመጠጥና ለሰው ልጅ ፍላጎት በመሆን የሚያገለግል ውኃ ነው፡፡
ለ. በናጌብና በአድማስ መካከል ያለ ውኃ፦ በብሄሞትና በሌዋታን ተከቦ በዓለም ዙሪያ ውቅያኖስ ተብሎ የሚጠራው ሦስት እጅ የሚሸፍን ውኃ ነው፡፡ ይህ ውኃ ፀሐይ ስትወጣና ስትገባ ብርሃኗ ስለሚወድቅበት የማታና የጠዋት ነፀብራቁ በዓለም መልቶ ይታያል፡፡ በፀሐይ ሙቀትም ወደ ላይ ተኖ ተመልሶ ወደ ከርሠ ምድር ይገባል፡፡
ሐ. በጠፈር ያለ ውኃ፦ ይህ ውኃ የብርሃናት መመላለሻ ሲሆን ጠፈር የተሠራውም ከውኃ በመሆኑ በፀሐይ ሙቀት እንዳይፈራርስ እግዚአብሔር በአየር ላይ ሐኖስ የሚባል ውኃ ከበላዩ አስቀምጦለታል፡፡
ክረምት ሦስት ክፍሎች አሉት፡፡ እነዚህም፡-
🌦 #መግቢያ፦ ከሰኔ 26 እስከ ሐምሌ 19 ቀን ያለው 23 ቀን ሲሆን ከመሬት ብነት ከውኃ ትነት የሚገኙ ጉምና ደመና በብዛት ይመላለሱበታል፤ ዘር ተዘርቶ ይበቅላል፤ ዕፀዋትም ይለመልማሉ፡፡
⛈ #መካከለኛ፦ ከሐምሌ 20 እስከ ነሐሴ 22 ቀን ያለው 33 ቀን ሲሆን በዚህ ወቅት መብረቅ፣ ነጎድጓድ፣ ባሕርና አፍላግ ይሰለጥናሉ፡፡
ሀ. #መብረቅ፦ በረቀ፣ ብልጭ አለ ካለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ብልጭታ፣ ነፀብራቅ ማለት ነው፡፡
ለ. #ነጎድጓድ፦ አንጎደጎደ፣ ተነዋወጠ፣ አነዋወጠ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ከመብረቅ ኃይል የሚወጣ አስፈሪና አስደንጋጭ ስሜትን ይፈጥራል፡፡ የሚፈጠረውም ከመሬትና ከውኃ ከሚገኙ ደመናዎች ግጭት ነው፡፡
ሐ. #ባሕርና_አፍላግ፦ በዚህ ወቅት ምንጮች ይመነጫሉ፤ ወንዞች እስከ ወሰናቸው ይሞላሉ፡፡ ባሕር ጥልቅ የውኃ ክምችት ሲሆን አፍላግ ደግሞ የፈለግ (ምንጭ) ብዜት ምንጮች ማለት ነው፡፡
🌤 #ፍጻሜ_ክረምት፦ ይህ ሦስተኛው የክረምት ክፍል ሲሆን ከነሐሴ 23 እስከ መስከረም 25 ድረስ ያለው 39 ቀን ነው፡፡
በአጠቃላይ ዘመነ ክረምት ዝናም፣ ዘርዕ፣ ጊሜ፣ ደመና፣ ባሕር፣ አፍላግ፣ ጠል፣ ሐመልማል፣ መብረቅ፣ ነጎድጓድና የመሳሰሉት የሚታወሱበት ወቅት ነው፡፡
የዘመናት ባለቤት እግዚአብሔር ዘመነ ክረምቱን በሰላም ይፈጽምልን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

መዝሙር ደምፀ እገሪሁ ከሰኔ ፳፮ እስከ ሐምሌ ፪
(በ፪/ኒ) ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ሶበ ይዘንም ዝናም ይትፌሥሑ ነዳያን (ደ) ሶበ ይዘንም ዝናም ይጸግቡ ርኁባን (ደ) ወሠርዐ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ደምፀ እገሪሁ ለዝናም።
ትርጕም፦
የዝናም እግሩ ተሰማ ዝናም በሚዘንም ጊዜ ነዳያን ደስ ይሰኛሉ ዝናም በሚዘንም ጊዜ የተራቡ ይጠግባሉ ለሰው ዕረፍት ሰንበትን ሠራ የዝናም እግሩ ተሰማ።
የዕለቱ ምንባባት፦
፩ቆሮ ፲፭፥፴፫ - ፶፩፤
ያዕ ፭፥፲፮ - ፍ፤
ግብ ፳፯፥፲፩ - ፳፩፤
የዕለቱ ወንጌል፦ ሉቃ ፰፥፩ - ፳፪
ቅዳሴ፦ ዘኤጲፋንዮስ፤
የዕለቱ ምስባክ፦
ዘይገለብቦ ለሰማይ በደመና፤
ወያስተዴሉ ክረምተ ለምድር፤
ዘያበቊል ሣዕረ ውስተ አድባር። መዝ ፻፵፮፥፰
ትርጕም፦
ሰማዩን በደመና የሚሸፍን፤
ለምድር ክረምትን የሚያዘጋጅ፤
በተራሮች ላይ ሣርን የሚያበቅል እግዚአብሔር ነው።

[እንኳን ለሠኔ 30 የመጥምቁ ዮሐንስ ልደት አደረሳችሁ]
✍በመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
[መጥምቁ ዮሐንስ በእናቱ ማሕፀን ስላቀረበው ስግደት ያዕቆብ ዘሥሩግ ያቀረበው ቅኔያዊ ውዳሴ]
♥ የእነዚኽ ዘመዳሞች (የኤልሳቤጥና የእመቤታችንን) መልካም ገጠመኝ አኹንም ያስደንቀኛል፤ ውበቱን እገልጥ ዘንድም አንድ ዐሳብ ይጎነትለኛል፡፡ ብላቴናዪቱ (እመቤታችን) እና አረጋዪቱ (ኤልሳቤጥ) አንድ አስደናቂ ታሪክ አስተምረውኛል፤ እየተደነቅኊ ስለ ርሱ እናገር ዘንድም ፍቅር ይወተውተኛል፡፡
♥ ድንግሊቱ በፍቅርዋ መካኒቱም በደስታዋ፤ ስለ ኹለታቸውም እሰብክ ዘንድ ፈልገውብኛል፡፡ ርስ በርስ የተያዩት አጽናፋት በተከሥቷቸው እንደሚተያዩት ነበር፣ የየራሳቸው የጊዜ ኹኔታ ቁልጭ ብሎ እንደሚታይባቸው እንደ ምሥራቅ እና እንደ ምዕራብ ናቸው፡፡
♥ አረጋዪቱ (ኤልሳቤጥ) ምሽት የሚታይበትን፤ በዕድሜው ብዛት (በርጅናው) ብርሃንን የሚሸፍነውንና የሚቀብረውን አጽናፍ ትመስላለች (ዮሐ ፭፥፴፭)፡፡ ብላቴናዪቱም (እመቤታችን) ቀኑን በዕቅፏ ተሸክማ ወደ ምድር የምታመጣውንና፤ የንጋት እናት የኾነችውን ምሥራቅን ትመስላለች (ሕዝ ፵፬፥፪)፡፡
♥ በወጣትነት እና በእርጅና ጊዜ የመደነቅ ስሜት ይበዛ ዘንድ ንጋት እና ምሽት የሚተያዩት በፍቅር ነው፡፡ ታላቁን የጽድቅ ፀሓይ (ጌታን) የምትሸከመው ንጋት (እመቤታችን) (ሚልክ ፬፥፪)፣ እና ብርሃንን (ጌታን) የሚያበሥረው ኮከብ (ዮሐንስ) የሚወጣባት ምሽት፡፡፡
♥ ታላቁ ንጉሥ በብላቴናዪቱ (በእመቤታችን) ዐድሮ ዘውዶችን ያበጃል፣ አረጋዪቱ (ኤልሳቤጥ) መንግሥቱን የሚያውጀውን አገልጋይ ትሸከማለች፡፡ በድንግልና የፍጥረታት ጌታ ይከበራል፤ በመካንነት የሌዋውያን (ወንድ) ልጅ ከፍ ይደረጋል፡፡
♥ ብላቴናዪቱ (እመቤታችን) አዳምን የፈጠረው ቀዳማዊዉን ሕፃን ትሸከማለች፤ አረጋዪቱ (ኤልሳቤጥ) ዛሬ በጋብቻ ውስጥ የተፈጠረውን ሕፃን ትሸከማለች (ሉቃ ፩፥፳፬-፳፭)፡፡ የይሁዳ ብላቴና ውስጥ ያዕቆብ ስለ ርሱ የጻፈው ያ የአንበሳ ደቦል አለ (ዘፍ ፵፱፥፱)፤ በሌዋዊቱ ውስጥ ደግሞ ጥምቀትን የመሠረታት ካህን (ሉቃ ፫፥፫)፡፡
♥ ከአረጋዪቱ (ኤልሳቤጥ) ጋር ስለዚኽ ዐዲስ ፅንስ ሐሤት ታደርግ ዘንድ፤ ድንግል በቅድስና ልቃ እና ተመልታ መጣች (ሉቃ ፩፥፴፱)፡፡ በረከትን (ጸጋን) የተመላችው (እመቤታችን) እና የሌዋውያን ሴት ልጅ የኾነችው (ኤልሳቤጥ)፤ እንዲኹም ምድር በመላ የበለጸገበት የከበረ ሀብት የመሉባቸው ኹለቱ ጀልባዎች ርስ በርስ ተገናኙ (ተያዩ)፡፡ ኹለት ወላዶች፡- አንደኛዋ ተበሣሪና አንደኛዋ አብሣሪ ኾና፣ የዚያኑ የአንዱን (ተመሳሳዩን) ለዓለም ኹሉ የኾነ የመዳን መልእክት ይዛ፡፡
♥ ብላቴናዪቱ (እመቤታችን) ጐበኘቻት፣ እና አንጸባራቂ በኾነ ሰላምታ ተናገረቻት፤ ወዲያውም በርሷ (በኤልሳቤጥ) ውስጥ ተሸፍኖ ያለው ሕፃን አውቆ በደስታ መዝለል ዠመረ (ሉቃ ፩፥፵፩)፡፡ ማርያም ሰላምን መናገርዋ ያማረ ነበረ፣ በቅርብ እና በሩቅ ላሉት ሰላምን ዘርታለችና (ሉቃ ፩፥፵)፡፡ ርሷ ለሰው ዘር በሙሉ የኾነ ሰላም እንደመላበት ክቡር ስጦታ ነበረች፣ በጠላትነት ለነበሩት የሚኾን ታላቅ ሰላም (ወሀቤ ሰላም ጌታ) በርሷ ውስጥ ተሰውሮ ነበርና፡፡
♥ ርሷ ራሷ ከላይ ሰላምን እንደተቀበለች፣ እንዲኹ ደግሞ ለዓለም ኹሉ ሰላምን ሰጠች (ሉቃ ፪፥፲፬)፡፡ በርሷ አፍ ሰላም በብዛት ተትረፍርፎ ይነገር ነበር፣ ይኽች ቡርክት የኾነች እንዲኽ ሰላምን ታውጅ ዘንድ የተገባት ነበር፡፡ ሰላም በውስጧ (በማሕፀኗ) ነበረና በከንፈሯ ሰላምን ሰጠች፣ ይኽነን የሰማው ሕፃንም በደስታ ይፈነድቅ ዠመር (ሉቃ ፩፥፵፩)፡፡
♥ ገና ሳያየው በፊት ያውቀው እንደነበር በማሳየቱ፣ ሲያየውና “ይኽ ርሱ ነው” ብሎ ሲናገር ነገሩን የሚጠራጠረው አይኖርም (ዮሐ ፩፥፳፱-፴)፡፡ ገና ሳይወለድ ርሱን (ጌታን) ለዓለም አስተዋወቀው፣ ከተወለደ በኋላ ርሱን ሲያውጀው ማንም ከምስክርነቱ እንዳይሸሽ፡፡ በተፈጥሮ ላይ ጌታ የኾነው በብላቴናዪቱ ማደሩ ይገለጥ ዘንድ፣ ተፈጥሮን በማሸነፍ ከተፈጥሮ ውጪ (ዮሐንስ) ስለ ወልድ መሰከረ፡፡
♥ ስለ ወልድ የኾኑት ነገሮች ኹሉ ለመግለጽ እጅግ ከባድ ናቸው፣ በእምነት ዦሮ ካልኾነም በቀር አይሰሙም፡፡ እነዚኽ ነገሮች ኹሉ ዐዲስ ነበሩና ሰው አልተረዳቸውም ነበር፤ ፍቅር ባለው ሰው በአድናቆት ካልኾነ በቀርም አይታዩም፡፡ለማርያም አድናቆት ለኤልሳቤጥም ታላቅ ሙገሳ ይገባል፣ ማስተዋል ለሚችል ሰው በኹለቱም ውስጥ ዐዳዲስ መገለጦች አሉባቸውና፡፡
♥ ስለኹለቱም ለመናገር ቃላት በቂዎች አይደሉም፣ አንደበትም (ንግግርም) ዝም ይላል፤ ከአድናቆት የተነሣ ዝምታ ንግግርን ይውጠዋል፡፡ ቃላት ስለማንኛዪቱ ለመናገር ይበቃሉ?፣ እነሆ ኹለቱም ከንግግር (ከአንደበት ገለጻ) በላይ ናቸውና፡፡ ማርያምን በቀረብናት ጊዜ አንደበት በዝምታ ይዘጋል፣ ምክንያቱም የድንግልናን ማስረገጫዎች (ምልክቶች) በርሱም ያደረውን ሕፃን ይመለከታልና፡፡ ወደ ኤልሳቤጥም ስንመጣ ትንታኔ ይከዳናል፣ ከርሷ ማሕፀን ውስጥ አስደናቂውን ብሥራት ይሰማልና፡፡
♥ ድንግሊቱ ፀንሳለችና እነሆ የመካኒቱም ልጅ በደስታ ይዘልላል፤ ስለ ታላላቆቹ ሕፃናት ዕጥፍ ድርብ መደነቅ ይይዘናል፤ ኧረ በማንኛቸው እንደመም (እንደነቅ)? አንደኛዪቱ (እመቤታችን) ያላገባች ኾና ሳለች ወንድ ሳያውቃት ፍሬ በውስጧ አለ፤ በሌላኛዪቱም (በኤልሳቤጥ) ማሕፀን ውስጥ ገና ያልተወለደ ሕፃን በደስታ ይዘልላል፡፡
♥ ማንኛዪቱን እናድንቅ፡- ልጅዋ የምሥራች ነጋሪ የኾነውን በዕድሜ የገፋችውን ሴትን፣ ወይንስ ድንግል ኾና ግን ደግሞ ሕፃን በውስጧ የተሸከመችዪቱን ብላቴና? ይኽችኛዪቱ (እመቤታችን) ወንድን ፈጽማ አታውቅም ግን ደግሞ ማሕፀኗ ሙሉ ነው (ማቴ ፩፥፲፰)፣ ያቺኛዪቱም (ኤልሳቤጥ) ልጇ ገና ሳይወለድ በፊት መንገድ ያዘጋጃል (ሉቃ ፩፥፵፬)፡፡ ያለጋብቻ ውሕደት የኾነችው ርሷ (እመቤታችን) ከንፁሕ ፅንሷ የተነሣ እጅግ ታስደንቃለች፣ ያልወለደችዪቱም (ኤልሳቤጥ) ደግሞ ልጇ ብሥራትን ለማብሠር ይላወሳል (ይዘላል)፡፡
[በእናቱ ማሕፀን በደስታ የዘለለው የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱ ይደርብን]
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልናና ወላዲተ አምላክነት በቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ድርሳን በሚል ርዕስ ካሳተምኩት መጽሐፍ በጥቂቱ ከገጽ 96-97 የተወሰደ

✥#ማኅሌት ዘቅዱስ ያሬድ✥:
ሥርዓተ ማኅሌት ዘሐምሌ ጴጥሮስ ወጳውሎስ "ሐምሌ ፭"
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለቃልክሙ መታሬ እሳት ነዳዲ: ሥሉስ ቅዱስ ንዋያተ ዕፁብ ነጋዲ: አመ በንስሐ ተወልዱ እምጸጋክሙ ወላዲ: ተወፈየ መርኆ ሰማይ የማነ #ጴጥሮስ ከሐዲ: ወመምህረ ወንጌል ኮነ #ጳውሎስ ሰዳዲ።
ዚቅ
ጸጋ ዘአብ ኂሩት ዘወልድ: ሱታፌ ዘመንፈስ ቅዱስ: ተውህቦሙ ለሐዋርያት።
ነግሥ
ሰላም ለመልክዕክሙ እመልክዐ አዳም ዘተቶስሐ: እግዚአብሔር መሐሪ ዘኮነክሙ መርሐ: ፲ወ፪ እለ ሰበክሙ ቃለ ንስሐ: ሥረዩ ኃጢአትየ ወጌጋይየ ብዙኀ: በእንተ ማርያም ድንግል በህሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ።
ዚቅ
ሐዋርያተ ሰላም ክቡራነ ስም: ሥረዩ ኃጢአተ ዓለም: በእንተ ኢየሱስ ክርስቶስ ወበእንተ ድንግል እም።
መልክዐ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ: ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ: ዜና መቃብርከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ: ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም ዐጸድ: ወቦ ዘይቤ ሀለወ በከብድ።
ዚቅ
ንግበር ተዝካሮሙ ለእለ ኃረዮሙ ዓጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ።
መልክዐ ጴጥሮስ ወጳውሎስ
ሰላም ለዝክረ ስምክሙ ዘአልባስጥሮስ አፈው: ወለሥዕርትክሙ ጸሊም ዘድላሌሁ ፍትው: ምቱረ ክሣድ #ጳውሎስ #ወጴጥሮስ ቅንው: ተራወጸ ውስተ ልብየ ምስል መዓዛሁ ቅድው: ደመ ስምክሙ ሐዋርያ ዘኅብሩ ከዋው።
ዚቅ
ሃሌ ሉያ: ከዋው እገሪሆሙ: ለእለ ይዜንዉ ዜና ሠናየ: ዘእግዚአብሔር ፈነዎ: ቃለ እግዚአብሔር ይነግር።
አመላለስ
ሃሌ ሉያ/፪/
ከዋው እገሪሆሙ/፪/
ወረብ
ከዋው እገሪሆሙ ለእለ ይዜንዉ ዜና ሠናየ ለእለ ይዜንዉ/፪/
ዘእግዚአብሔር ፈነዎ ይነግር ቃለ እግዚአብሔር/፪/
መልክዐ ጴጥሮስ ወጳውሎስ
ሰላም ለአዕዛኒክሙ ለሰሚዓ ወንጌል ዘተሰብሐ: ወለመላትሒክሙ ቀይሐት እምነ ሮማን ዘቄሃ: መሥዋዕተ አምልኮት ኩኑ ወዘመሃይምናን ምክሐ: ደምከ #ጴጥሮስ ወልደ ዮና በጽዋዓ መስቀል ተቀድሐ: ወደመ #ጳውሎስ ሐዋርያ ሰማያተ ጸርሐ።
ዚቅ
ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም እንተ ትቀትሎሙ ለነቢያቲሃ: ወትዌግሮሙ ለሐዋርያቲሃ: ሚ መጠን ዘተክዕወ ዲቤሃ: እምደመ #ጳውሎስ ሐዋርያ: እስከ ደመ #ጴጥሮስ ወልደ ዮና።
ዓዲ
ዚቅ
በሀኪ ኦ ዓባይ ሀገር ሀገረ ሮሜ: ሀገረ ነጎድጓድ ሀገረ እግዚአብሔር: እንተ ተሰመይኪ ገነተ: ደሞሙ ለሰማዕታትኪ ውኅዘ ከመ ማይ: ድምፀ ነጎድጓዶሙ በጽሐ እስከ ሰማይ።
ወረብ
ሚ መጠን ዘተክዕወ ዲቤሃ ለኢየሩሳሌም/፪/
እምደመ #ጳውሎስ ሐዋርያ እስከ ደመ #ጴጥሮስ ወልደ/፪/
መልክዐ ጴጥሮስ ወጳውሎስ
ሰላም ለዘባናቲክሙ በምኲራባት እለ ተቀሥፋ: ወለእንግድዓክሙ ዘሰፍሐ መልዕልተ ጠበብት ወፈላስፋ: በእንተ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተጸፍአ ቅድመ ቀያፋ: ሀበኒ #ጴጥሮስ መስቀለከ ይኲነኒ ተስፋ: #ወጳውሎስ ዉቅየተከ እንተ ደም ለከፋ።
ዚቅ
እስመ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ: ዘተሠውጠ ላዕለ ኲሎሙ ሐዋርያት: በመንፈስ ቅዱስ ነበቡ በነገረ ኲሉ በሐውርት: ይኲነኒ አክሊለ መዊዕ ወተስፋ: በረከቶሙ ለሳውል ወኬፋ።
ወረብ
እስመ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ዘተሰውጠ ላዕለ ሐዋርያት/፪/
በመንፈስ ቅዱስ ነበቡ በነገረ ኲሉ በሐውርት/፪/
መልክዐ ጴጥሮስ ወጳውሎስ
ሰላም ዕብል ብርሃናተ ፪ኤተ: በዓውደ ንጉሥ ኔሮን እለ ፈጸሙ ሩጸተ: #ጳውሎስ #ወጴጥሮስ ዘያጸንዑ ፀበርተ: አሐዱ በመስቀል ተሰቅለ ቊልቊሊተ: ወካልዑ ተመትረ ክሣዱ ክብርተ።
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: ብርሃናተ ዓለም ሐዋርያተ ሰላም ሱቱፋነ ሕማም: አሥራበ ምሕረት ከዓዉ እምአርያም።
ወረብ
ሐዋርያተ ሰላም "ብርሃናተ ዓለም"/፪/
አሥራበ ምሕረት ከዓዉ ከዓዉ እምአርያም/፪/
መልክዐ ጴጥሮስ ወጳውሎስ
ተዘኪረከ ክርስቶስ ዘሐዋርያት ኲሎሙ: ህየንተ ክቡር ደምከ እለ ከዓዉ ደሞሙ: አክሊለ ስምዕ ሀበኒ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ: ወደምስስ ለአጽራርየ እመጽሐፈ ህይወት ዝክሮሙ: ከመ ለይሁዳ ረሲዕ ተደምሰሰ ስሙ።
ዚቅ
#ስምዖን #ጴጥሮስ ወአኃዊሁ ሱቱፋነ ሕማምከ: እለ ከዓዉ ደሞሙ ህየንተ ደምከ: ከመ ይኩን ተውሳከ ለሴጠ አሕዛብ በስብከተ ወንጌልከ: በከመ ተቶስሐ መዓዛ ክህነትከ በክህነቶሙ: ቶስሕ ስእለተነ በስእለቶሙ: ጸግወነ ሎሙ ከመ ንድኃን ቦሙ።
ወረብ
#ስምዖን #ጴጥሮስ ወአኃዊሁ "ሱቱፋነ ሕማምከ"/፪//፪/
እለ ከዓዉ ደሞሙ ደሞሙ ህየንተ ደምከ/፪/
መልክዐ ኢየሱስ
ሰላም ለእራኅከ መክፈልተ ሕማማት ሱቱፍ: ወቅንዋቲሁ እኤምሕ በአፍ: #ኢየሱስ_ክርስቶስ በላዕለ ቅዱሳን ዕሩፍ: ይፀነስ ውስተ ከርሥየ ዘርአ ቃልከ መጽሐፍ: ጸዳለ እምጸዳል ከመ ትፀንስ ዖፍ።
ዚቅ
እግዚአ ውእቱ ለሰንበት ውእቱ: አቡሃ ለምሕረት ውእቱ: ኃያል ወብዙኅ ሣህል ውእቱ: ዘባሕቲቱ በቅዱሳኒሁ ዕሩፍ።
ምልጣን
ይቤሎ #ጴጥሮስ #ለጳውሎስ ጥባዕኬ እኁየ #ጳውሎስ ወኢትናፍቅ እምዝ ዳግመ ኢንመውት ዳግመ ወእምዝ ዳግመ ኢንመውት።
ወረብ
ይቤሎ ጴጥሮስ ለጳውሎስ ጥባዕኬ እኁየ ጳውሎስ እኁየ/፪/
ወኢትናፍቅ ዳግመ እምዝ ዳግመ ኢንመውት/፪/
እስመ ለዓለም
ሕዝብ ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡራን: አርድዕት ልዑላን አዕማደ ቤተክርስቲያን: ሰመየ ስሞሙ ደቂቀ ብርሃን #ጴጥሮስ #ወጳውሎስ: ወኲሎሙ ሐዋርያት: ፈድፋደ ቦሙ ሞገሰ በኀበ ኲሎሙ ሕዝብ።
አመላለስ
ሕዝብ ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡራን አዕማደ ቤተክርስቲያን/፪/
ሰመየ ስሞሙ ደቂቀ ብርሃን ጴጥሮስ ወጳውሎስ/፪/

መዝሙር ይሰጠዎ ከሐምሌ ፫ እስከ ሐምሌ ፱
(በ፩/ዩ) ይሰጠዎ ወይሰምዖ ጸሎቶ ለኵሉ ለዘሰአሎ እግዚኣ ለሰንበት አምላከ ምሕረት ያርኁ ክረምተ በበዓመት ይሰምዑ ቃሎ ደመናት።
ትርጉም፦
ይመልስለታል የለመነውን ሁሉ ጸሎቱን ይሰማዋል የይቅርታ አምላክ የሰንበት ጌታ በየዓመቱ ክረምትን ይከፍታል (በጋና ክረምትን ያፈራርቃል) ደመናት ቃሉን ይሰማሉ።
የዕለቱ ምንባባት፦
ዕብ ፮፥፯ - ፍ፤
፩ጴጥ ፫፥፰ - ፲፭፤
ግብ ፲፬፥፰ - ፲፱፤
የዕለቱ ወንጌል፦ ማቴ ፲፫፥፩ - ፴፩
ቅዳሴ፦ ዘእግዚእነ፤
የዕለቱ ምስባክ፦
አርውዮ ለትለሚሃ፤
ወአሥምሮ ለማእረራ፤
ወበነጠብጣብከ ትበቊል ተፈሢሓ። መዝ ፷፬፥፲፤
ትርጕም፦
ትልሟን አርካው፤
መከሯንም አብጀው፤
በነጠብጣብህም ደስ ብሏት ትበቅላለች።
ምሥጢር፦
የኢየሩሳሌም ትልሟን አርካው፤
መከሯን የበጀ/የሚጠቅም አድርገው፤
እንዲህ የሆነ እንደሆነ ጠብ ጠብ ብሎ በሚዘንመው ዝናም ደስ ብሏት ተካክላ ትበቅላለች። ብርቱ ዝናም የዘነመ እንደሆነ ከነመሬቱ ድሶት (ጠራርጎት) ይሄዳል፤ ለሰስ ብሎ የወረደ እንደሆነ ደስ ብሏት ተካክላ ትበቅላለችና።
አንድም ልቡናዋን ደስ አሰኘው፤
ሚጠተ ሥጋውን የበጀ አድርግላት፤
በዘሩባቤል ደስ ብሏት ተካክላ ትወጣለች።
አንድም ነፍሷን ደስ አሰኘው፤
ሚጠተ ነፍሷን የበጀ አድርገው፤
ከቀኝ ጎንህ በፈሰሰ ጽሩይ ማይ ተጠምቃ ደስ እያላት ከሲኦል ወደገነት ትወጣለች።