ለአብርኆት ቤተ መጻሕፍት ከ450 ሺሕ በላይ መጽሐፍ ተሰበሰበ
ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) “ሚሊዮን መጻሕፍት ለሚሊኒየሙ ትውልድ” በሚል መሪ ሀሳብ ለአብርኆት ቤተ መጽሕፍ ሲካሄድ በነበረው መጻሕፍት የማሰባሰብ ዘመቻ ከ450 ሺሕ በላይ መጻሕፍት መሰባሰቡ ተገልጿል።
ለአንድ ወር ሲካሄድ የነበረው መጻሕፍት የማሰባሰብ ዘመቻ የመጀመሪያ ዙር ማጠናቀቂያ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመርኃ ግብሩ ላይ መጻሕፍትን የለገሱት ግለሰቦችና ተቋማት መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉና የተለያየ ይዘት ያላቸው እንደሆኑ ተጠቁሟል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በዘመቻው ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉና የተለያዩ ይዘት ያላቸው መጻሕፍት ማሰባሰብ ተችሏል ብለዋል።
ቤተ መጻሕፍቱ ሀሳብን በውይይት የሚፈታ ወጣት ለማፍራት ትልቅ እድል የሚፈጥር መሆኑንም ተናግረዋል።
ወጣቱን አማራጭ ሳይቀርብለት መውቀስ ተገቢ አይደለም ያሉት ዲያቆን ዳንኤል አሁን ላይ የአብርኆት ቤተ መጻሕፍት በቀን እሰከ 10 ሺሕ ሰው እያስተናገደ ነው ብለዋል።
ቤተ መጻሕፍቱ የሚያስፈልገውን ያህል መጻሕፍት እንዲኖሩት አሁንም ዜጎች ልገሳቸውን ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬትን ጨምሮ በመጻሕፍት ማሰባሰብ ዘመቻው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የመገናኛ ብዙኃን እንዲሁም መጻሕፍት ያበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦችም እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በመስከረም ቸርነት
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የለገዳዲ ምዕራፍ ሁለት የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት መርቀው ከፈቱ
ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የለገዳዲ ምዕራፍ ሁለት የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት መርቀው ከፍተዋል።
ከንቲዋ በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ፕሮጀክቱ የከተማዋን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር የሚያቃልል ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት ይነሳ የነበረውን የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ቅሬታን በመፍታት የጋራ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ መሆኑን ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ውሃ ሰጥተው ውሃ የሚጠማቸው የሚያደርግ ሳይሆን የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።
ፕሮጀክቱ የተሳካ እንዲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና ያቀረቡት ከንቲባዋ ፕሮጀክቱ ተባብሮ፣ ተናቦ እና ተሳስቦ በመስራት የተገኘ ውጤት፤ ወደፊትም ሌሎች ፕሮጀክቶች በተመሳሳይ በትብብር ዕውን እንደሚሆኑ አስታውቀዋል።
የከተማዋን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ከመሰረቱ ለመፍታት የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለንም ነው ያሉት።
የውሃ ፕሮጀክቱ በፈተና ውስጥ የተሰራ ፕሮጀክት መሆኑን የገለፁት ከንቲባዋ ፈተና እንደማያስቆመንም ያሳየንበት ነውም ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ በመደበው 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በጀት የተሰራና በቀን 86 ሺሕ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማምረት የሚችል ፕሮጀክት መሆኑ ተገልጿል፡፡
https://www.facebook.com/489211707826282/posts/pfbid025qXv6UsVTtiRqdD4LqS56ceLDoBieTDFYvkEprQjVoUPgWrXkKwx86HAVmSG7M7Nl/?app=fbl

በርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በኢሉ አባቦር ዞን የሥራ ጉብኝት አደረገ
ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ቡድን በኢሉ አባቦር ዞን የሥራ ጉብኝት አድርጓል።
ቡድኑ በኢሉ አባቦር ዞን በክላስተር በመልማት ላይ የሚገኘውን የጉመሮ ሻይ ተክል በመጎብኘት የዘንድሮውን የሻይ ችግኝ ተከላ በአሌ ወረዳ አስጀምሯል።
በቆይታውም የተለያዩ የልማት ሥራዎችን በመመልከት 4ኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ያስቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ኢብኮ ዘግቧል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ቡድን በኢሉ አባቦር ዞን የሥራ ጉብኝት አድርጓል።
ቡድኑ በኢሉ አባቦር ዞን በክላስተር በመልማት ላይ የሚገኘውን የጉመሮ ሻይ ተክል በመጎብኘት የዘንድሮውን የሻይ ችግኝ ተከላ በአሌ ወረዳ አስጀምሯል።
በቆይታውም የተለያዩ የልማት ሥራዎችን በመመልከት 4ኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ያስቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ኢብኮ ዘግቧል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
በክልሉ በሁሉም ዘርፍ ተስፋ ሰጪ ውጤት መመዝገቡ ተገለፀ
ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) በሲዳማ ክልል የሁለት ዓመት ጉዞ በሁሉም ዘርፍ ተስፋ ሰጪ ውጤት መመዝገቡ ተገልጿል።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 2ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በሃዋሳ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የፓናል ውይይት ላይ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ምሁራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የታደሙ ሲሆን ክልሉ በሁለት ዓመታት ውስጥ ያከናወናቸውን አስተዳደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የመሰረት ልማት ሥራዎች ለታዳሚው ቀርቧል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ባደረጉት ንግግር ልማታችንን ለማፋጠን ሕዝብን ያሳተፈ ሥራ መስራት ከፍተኛ ዋጋ እንዳለውና በዚህም ባለፈው ሁለት ዓመት ብዙ ውጤቶችን ያየንበት ነው ብለዋል።
በአገልግሎት ዘርፉ እና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ደካማ አፈፃፀም መታየታቸውንም ገምግመናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይ ሕዝቡ ችግርም መፍትሄም በእጃችን መሆኑን አውቆ በንቁ ተሳትፎ ከጎናችን መቆም አለበት ብለዋል።
የፓናል ውይይቱ ላይ የውይይት መነሻ ሰነድ ያቀረቡት አራርሶ ገረመው (ፒኤችዲ) ውይይቶች በግልፅነት ላይ የተመሰረተ ሥራን ለማከናወን እና በሕዝብ እና በአስተዳደሩ መካከል ያለውን የጋራ መግባባት የሚያጠናክሩ ስለሆነ ፋይዳቸው የጎላ ነው ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም በመንግሥት የተሰሩትን የመሰረተ ልማት ሥራዎች ቦታው ድረስ በመሄድ መጎብኘታቸውን ጠቅሰው ከልማቱ ጎን ለጎን የፀጥታና ደኅንነት ሥራ እንዲጠናከርም ጠይቀዋል።
የክልሉ መንግሥት 2ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል በነገው እለትም በተለያዩ ሁነቶች መከበር እንደሚቀጥል ይጠበቃል።
አንተነህ ደጀኔ (ከሀዋሳ)

በኢትዮጵያ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው አለመኖሩን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ
ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘም ሆነ የተለየ ሰው አለመኖሩን የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ገለጸ።
"የዝንጀሮ ፈንጣጣ" በመባል የሚታወቀው እና በተለያዩ ሀገራት የተከሰተው ተላላፊ በሽታ በሀገራችን ተከስቶ ሁለት ሰዎች ተለይተዋል (ኳረንቲን ገብተዋል) የሚል መረጃ በሪፖርተር ጋዜጣ ወጥቶ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ እንደሚገኝ የገለጸው ሚኒስቴሩ “በሽታው በሌሎች ሀገራት ቢከሰትም በሀገራችን እስከ አሁን በበሽታው የተያዘም ሆነ የተለየ ሰው አለመኖሩን እናሳውቃለን” ብሏል።
ኃላፊነት የሚሰማቸው የሚዲያ ተቋማት ይህን መሰል ያልተረጋገጠ እና በሚመለከተው አካል ያልቀረበ መረጃን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡም አሳስቧል።
ወቅታዊ የጤና መረጃዎችን እንዲሁም የማኅበረሰቡ የጤና ስጋት የሚሆኑ ወረርሽኞችን በተመለከተ ትክክለኛ መረጃ ከጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማግኘት የሚቻል መሆኑን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር አስጀመሩ
ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ‘‘አረንጓዴ አሻራችን ለትውልዳችን’’ በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደውን አራተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በጋምቤላ ወረዳ ቀርሚ ቀበሌ አስጀምረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በመርኃ ግብሩ ላይ እንዳሉት በአራተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ከ9 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል ታቅዷል።
ዕቅዱን እውን ለማድረግ አመራሩ መላውን የክልሉን ነዋሪ በማስተባበር ውጤታማ ሥራ ማከናወን እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
ባለፉት ሦስት የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብሮች በተሰራው ሥራ በርካታ የተራቆቱ አካባቢዎችን በእጽዋት ማልበስ መቻሉን ገልጸዋል።
ዘንድሮም ካለፈው መልካም ተሞክሮ በመውሰድ እንደሚሰራ ጠቅሰው እስከ መስከረም አጋማሽ በሚዘልቀው የችግኝ ተከላ ሁሉም ሰው ቢያንስ 100 ችግኝ በመትከል ለዕቅዱ መሳካት የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል።
የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ አጃክ ኡቻላ በበኩላቸው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ተራቁቶ የነበረ ከ15 ሺሕ ሄክታር መሬት በላይ ወደ ቀድሞ ይዘቱ መመለሱን ተናግረዋል።
በዘንድሮ መርኃ ግብር የአካባቢውን ሥነ-ምህዳር በማሻሻል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሴ ጋጂት በመርኃ ግብሩ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ተማሪዎች በስፋት እንደሚሳተፉ አመልክተዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።
የአኝዋሃ ዞን አስተዳዳሪ ኡቦንግ ኡጁሉ በበኩላቸው የሽብር ቡድኖችን እኩይ ሴራ በመመከት የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስኬታማ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ በክልሉ 4ኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር አስጀመሩ
ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የ4ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር በኢሉ አባቦር ዞን ያዮ ጫካ ውስጥ አስጀምረዋል።
መርኃ ግብሩ "አሻራችን ለትውልዳችን ለትውልድ እንስራ ለኦሮሚያ እንትከል" በሚል መርህ ሃሳብ ነው የተካሄደው።
ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በመርኃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር በዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ አንድ ሰው 300 ችግኝ መትከል እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ባለፉት 3 ዓመታት ከ9 ቢሊየን በላይ ችግኞች መተከሉን የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አበራ ወርቁ ተናግረዋል።
በክልሉ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በአንድ ቀን ከ4 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ለመትከል የታቀደ መሆኑም ተነግሯል።
ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችም በመርኃ ግብሩ ላይ ተገኝተው የችግኝ ተከላ አከናውነዋል።
ያዮ ጫካ በዩኔስኮ የተመዘገበ የተፈጥሮ ሀብት ሲሆን 167 ሺሕ 21 ሄክታር መሬትን ሸፍኗል።
አስቴር ጌታሁን (ከኢሉ አባቦር)