AddisWalta - AW
48.3K subscribers
44K photos
222 videos
20 files
16.9K links
This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Download Telegram
በአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር የሠራናቸው ሥራዎች ተጽዕኗቸው ድንበር ተሻጋሪ ነው - ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

ጥቅምት 25/2017 (አዲስ ዋልታ) በአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር የሠራናቸው ሥራዎች ተጽዕኗቸው ድንበር ተሻጋሪ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው "የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ ኢንሼቲቭ፤ ለቀጣናዊ ዘላቂ የውኃ ሀብት ልማት እመርታ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በተጀመረው ዓለም አቀፍ የሀይድሮ ሜት ጉባኤ ላይ መገኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

መድረኩ ሀገራችን በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ያስመዘገበቻቸውን አመርቂ ድሎች በአህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ዕድል ፈጥሮልናልም ነው ያሉት፡፡

ይሄን ታሳቢ በማድረግ ላለፉት ስድስት ዓመታት ሀገራችን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን በመቅረጽ እስከ ዛሬ ድረስ 40 ቢሊዮን ችግኞች ተክለናል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተተከሉ ችግኞች ከከባቢ የአየር ሁኔታ፣ ምግብ ዋስትና እና የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር ለቀጣናው ዘላቂ የውኃ ሀብት ልማትና አስተዳደር ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከቱ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ጉባኤው በማዘጋጀት ረገድ ቁልፍ ሚና ለተወጡት የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች እና ሠራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፤ ጥረታችሁ የትብብርና የቁርጠኝነት ኃይል ማሳያ ነው ሲሉም አክለዋል።
በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት የተፋጠጡት ሁለቱ ኮርያዎች

ሰሞኑን ሰሜን ኮርያ 10 ሺሕ ያህል ወታደሮቿን ከሩሲያ ጎን ሆነው እንዲዋጉ መላኳን ተከትሎ ደቡብ ኮርያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዩክሬን ቀጥታ ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ ማሰቧን ገልጻለች።

ደቡብ ኮርያ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ለዩክሬን ሰብዓዊ እርዳታ ብቻ ነበር የምትልከው። ይሁን እንጂ ደቡብ ኮርያ ለሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል አገራት በተዘዋዋሪ መንገድ ወታደራዊ ድጋፍ ማድረጓን አላቋረጠችም ነበር።

የሰሞኑ የሰሜን ኮርያ እርምጃ ግን ደቡብ ኮርያን የፖሊሲ ለውጥ እንድታደርግ ሳያስገድዳት አይቀርም።

የደቡብ ኮርያው ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዩኦል ከፖላንድ አቻቸው አንደሬይ ዱዳ ጋር በሰጡት የጋራ መግለጫ “ሰሜን ኮርያ በሩሲያ-ሰሜን ኮርያ ትብብር መሰረት ልዩ ኃይሎችን ወደ ዩክሬን ጦርነት ከላከች እኛም ለዩክሬን ድጋፍ እናደርጋለን፤ እንዲሁም በኮሪያ ፔኒንሱላ ላይ ጸጥታና ደህንነትን ለመጠበቅ አስፈላጊ እርምጃዎችን እየገመገምን ተግባራዊ እናደርጋለን” ብለዋል።

ደቡብ ኮርያ ለዩክሬን በቀጥታ የጦር መሳሪያ እርዳታ ለመስጠት ማሰቧ በሁለቱ አገራት ጦርነት ውስጥ የነበራት ተሳትፎና ስትከተለው በነበረው ፖሊሲ ዙሪያ ከፍተኛ ለውጥ እንደሆነ እየተነገረ ይገኛል።

የአሁኑ ዕቅድ ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ አገሪቱ ማንኛውንም የጦር መሳሪያ ግጭት ወዳለበት አገር መላክ የሚከለክለውን የውጭ ንግድ ህጓን አንድትከልስ ያስገድዳታል ሲል አልጃዚራ ዘግቧል።
👇👇
https://web.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid0266DDoFYNWgzbYechAVE9VGn34yGWD9NypzCzeUaSSYJXLgmAtSSHv8GTjNcBiz2jl
የአሜሪካ ምርጫ ለምን ማክሰኞ ቀን ይካሄዳል?

በ19ኛው ክፍለ ዘመን የነበሩት አብዛኞቹ አሜሪካዊያን ገበሬዎች ነበሩ። የሚኖሩትም ከምርጫ ጣቢያዎቹ ርቀው ነበር። ምርጫ ለማድረግ ቢያንስ አንድ ቀን መጓዝ ነበረባቸው። በዚህም ምክንያት በጊዜው የሀገሪቱ ህግ አውጪዎች ለምርጫ ሁለት ቀናትን ይፈቅዱ ነበር።

ቅዳሜና እሁድ አብዛኞቹ አሜሪካዊያን ወደ የእምነት ቦታቸው የሚሄዱበት ቀን ነበር። በዚህም የሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ለምርጫ አመቺ አልነበሩም። ረቡዕ ደግሞ ለነዚህ ገበሬዎች የገበያ ቀናቸው ነበር። ስለሆነም ማክሰኞ ለአሜሪካዊያን ምርጫ ለማድረግ አመቺ ቀን ሆና ተገኘች።

የአሜሪካ ምርጫ በኅዳር ወር መደረግም እንዲሁ ከእርሻ ጋር የተያያዘ ታሪክ አለው። ከመጋቢት እስከ ግንቦት ያለው ጊዜ የገበሬዎቹ የምርት መዝርያ ጊዜ በመሆኑ በስራ ይጠመዳሉ። ስለዚህ ለመምረጥ ጊዜ አይኖራቸውም። ከሰኔ እስከ ነሐሴ ያለው ጊዜ ደግሞ የዘሯቸው ምርቶች እንክብካቤ የሚፈልጉበት ወቅት በመሆኑ ገበሬዎቹ ለምርጫ ይሄዳሉ ተብሎ አልታሰበም።

መስከረም እና ጥቅምት ከምርት መሰብሰቢያ ጊዜያቸው ጋር ይጋጫል። ስለሆነም በኅዳር ቢደረግ ከነዚህ ኹነቶች ጋር የማይጣረስ እና ጉዟቸውን አስቸጋሪ ሊያደርግባቸው ከሚችለው ከቀዝቃዛው የክረምት ወቅት በፊት ይሆናል።

በነዚህ ምክንያቶች የተነሳ የአሜሪካ ምርጫ እ.ኤ.አ ከ1845 ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ኅዳር በገባ የመጀመርያው ማክሰኞ ላይ ይካሄዳል።
የአቡዳቢ አልጋወራሽ ግርማዊ ሼህ ኻሊድ ቢን መሃመድ ቢን ዛይድ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ መጡ እላለሁ- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን አውሮፕላን ተረከበ

ጥቅምት 25/2017 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤር ባስ A350-1000 አውሮፕላን ተረከበ፡፡

በርክክብ ሥነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው፣ የአየር መንገዱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲ ለሚክ፣ የኤር ባስ ኩባንያ ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የላቀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ቴክኖሎጂ የተገጠመለት አውሮፕላኑ በአየር መንገዱ ምድረ ቀደምት (Ethiopia land of origins) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው A350-1000 አውሮፕላን 400 መቀመጫዎች አሉት፡፡

አየር መንገዱ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2035 በዓመት 67 ሚሊዮን መንገደኞችን በማጓጓዝ 25 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ ገቢ ለማግኘት እየሰራ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአሁኑ ወቅትም ባሉት 147 አውሮፕላኖች 139 ዓለም አቀፍ እና 22 የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎችን እየሸፈነ ይገኛል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ አየር መንገዱ 124 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማዘዙን መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ዛሬ ምሽት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዘጠኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ

ጥቅምት 26/2017 (አዲስ ዋልታ) ዛሬ ምሽት በአራተኛ ዙር የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መርሃ ግብር ዘጠኝ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

በዕለቱ በጉጉት ከሚጠበቁ ጨዋታዎች መካከል ሊቨርፑል ከአምናው የጀርመን ሻምፒዮንስ ሊቨርኩሰን፣ ሪያል ማድሪድ ከኤሲ ሚላንና ሴልቲክ ከላይፕሲንግ ተጠቃሽ ናቸው።

በዕለቱ ፒኤስቪ ከጂሮና፣ ብራቲስላቫ ከጂኤንኬ ዳይናሞ ምሽት 2 ከ45 ላይ፤ ቦሎኛ ከሞናኮ፣ ቦሩሲያ ዶርትመንድ ከስትረም ግራዛ፣ ሊል ከጁቬንቱስ፣ ስፖርቲንግ ከማንችስተር ሲቲ በተመሳሳይ ምሽት 5 ሰዓት ላይ የሚካሄዱ ጨዋታዎች ናቸው።
"የ'World Without Hunger' ጉባኤ ተሳታፊዎችን እንኳን ወደ አፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና በሰለም መጣችሁ እላለሁ።

አለምአቀፍ መሪዎችን፣ ባለሞያዎችን እና የጉዳዩ ተቆርቋሪዎችን በአንድ ላይ በማምጣት እንዲወያዩ በማድረግ የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ።

በኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ዓመታት በግብርና ሽግግር እና ምርታማነት ላይ በማተኮር የሠራነው ሥራ የታረሰ መሬታችን እጥፍ በማድረስ ከፍ ያለ እሴት ባላቸው የኢንደስትሪ አዝርዕት ምርት ላይ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች አስገኝቷል።

በሚቀጥሉት ቀናት የጉባኤው ውይይቶች የጋራ ግቦቻችንን ስኬት የሚያፋጥኑ ታላላቅ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ እተማመናለሁ።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር
ስድስት መራጮች ብቻ የተሳተፉባት የአሜሪካ ከተማ

ስድስት ሰዎች ብቻ ለመምረጥ የተመዘገቡባት የአሜሪካ ሰሜን ሀምፕሸር ከተማ የድምፅ አሰጣጥ ስርዓቱን አጠናቃለች። መጨረስ ብቻም አይደለም ቆጥራ ውጤቱን ይፋ አድርጋለች።

ውጤቱም አንገት ለአንገት የተናነቁትን ሁለቱን ፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች እኩል ድምፅ ተጋርተው እንዲቆዩ አድርጓቸዋል። በዚች ከተማ ዶናልድ ትራምፕ እና ካማላ ሃሪስ እኩል 3 ድምፆች አግኝተዋል።

ዲክስ ቪል ኖች በአሜሪካ በሰሜን ሀምፐሸር ከተማ ውስጥ የሚገኙ ማህበረሰቦች መጠርያ ነው። እነዚህ ማህበረሰቦች እጅግ በጣም ትንሽ የህዝብ ቁጥር አላቸው።

በከተማዋ እኩለ ሌሊት ላይ ምርጫ ጣቢያ በመክፈት እና ቆጠራ በማጠናቀቅ ቀዳሚ በመሆን ይታወቃሉ።
ዚምባብዌ ፖሊሶች በስራ ላይ እያሉ ስልካቸውን እንደይጠቀሙ ከለከለች

ጥቅምት 26/2017 (አዲስ ዋልታ) የዚምባብዌ መንግስት ፖሊሶች በስራ ላይ እያሉ ስልካቸውን እንዳይጠቀሙ ከልክሏል።

መንግስት መመርያው በፍጥነት ተፈጻሚ እንዲሆን አዟል።

እገዳው ማንኛውም የፖሊስ አባል በስራ ላይ ሆኖ የግል የመገናኛ መሳርያዎቹን በሙሉ መጠቀም እንዳይችል የሚከለክል ነው።

ፖሊሶች ወደ ጣቢያቸው ሲገቡ ስልካቸውን ለቅርብ አለቆቻቸው እንዲያሰስረክቡ መመርያው ያስገድዳል። መጠቀም የሚችሉትም በእረፍት ሰዓታቸው ብቻ እንደሆነም ተገልጿል።

በመመርያው ላይ ዕገዳው የተጣለው ለምን እንደሆነ አለልተገለጸም። ነገር ግን በፖሊስ አባለት የሚፈጸሙ የሙስና ተግባራትን ለመከላከል እንደሆነ ታምኗል።

ክልከላው የተደረገው ከጥቂት ቀናት በፊት በሀገሪቱ ዋና ከተማ ሀራሬ ሁለት የትራፊክ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ነው። ምክንያቱ ደግሞ በማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ በተለቀቀ ቪዲዮ ላይ ከህዝብ ትራንስፖርት መኪናዎች የሙስና ገንዘብ ሲቀበሉ በመታየታቸው ነው።

በመመርያው ላይ የፖሊስ አባላት በስራ ላይ ሆነው ስልካቸውን ይዘው ቢገኙ የፖሊስ አባሉ ብቻ ሳይሆን የቅርብ አለቃውም ጭምር ተጠያቂ ይሆናል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።