አየር መንገዱ በዓየር ትራንስፖርት ዘርፍ እያበረከተ ላለው የላቀ አስተዋፅዖ ሽልማት ተበረከተለት
ኅዳር 27/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በናይጄሪያ አቡጃ በተካሄደው የቱሪዝምና ትራንስፖርት ኤክስፖ ለናይጄሪያ የቱሪዝም ኢንደስትሪ ዕድገት በዓየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ እያበረከተ ላለው የላቀ አስተዋፅዖ "Outstanding Onboarding Experience Achievements” ሽልማት ተበረከተለት።
ይህ ዓመታዊ የቱሪዝም ኤክስፖ የትራንስፖርት ትስስር ለቱሪዝም ዕድገት በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን በአፍሪካ ቱሪዝም ዘርፍ ላይ ወሳኝ ሚና ያላቸው የተለያዩ ተቋማት መሳተፋቸውን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል።

የከርሰ ምድር የውሃ ሀብትን ለማልማት በ132 ሚሊየን ብር ወጪ የውል ስምምነት ተፈረመ
ኅዳር 27/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት አካል የሆነው የከርሰ ምድር የውሃ ሀብትን በማልማት ለማስተዳደር የሚያግዙ የ132 ሚሊየን ብር ወጪ የጥናትና የማማከር ስራዎች የውል ስምምነት ተደረገ፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አብርሃ አዱኛ (ዶ/ር) እንዳሉት ለሚኒስትሩ ከተሰጠው ኃላፊነት አንዱ ከውሃ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሀብቶችን መቆጣጠርና መከታተል ነው፡፡
በዚህም የውሃ ሀብታችን ለመጠቀም እና ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ ፖሊሲ በማዘጋጀት እና እስትራቴጂ በመንደፍ እየተተገበረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በሀገራችን ያለውን የከርሰ ምድር ውሃ ሀብት እና የቦታ መረጣን የማስጠናት እና ለማማከር ስራ ከሚሰሩት አኩዋን ኢንጂነሪንግ ፒ.ኤል.ሲ እና ከዲ.ኤች የማማከር ስራ ጋር በጋራ የውል ስምምነት መደረጉን የሚኒሰቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
የአኩዋን ኢንጂነሪንግ ፒ.ኤል.ሲ ስራ አስኪያጅ ዜናው ተሰማ ስራው በድሬድዋና በአካባቢው ያለውን የከርሰ ምድር ውሃ ለማበልጸግ የሚቻልበትን ሁኔታ መፍጠር የሚያስችል ጥናት በማጥናት ቦታ የመምረጥ ስራውን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም በተያዘለት ጊዜ አጠናቀው እንደሚያስረክቡ ገልጸዋል፡፡
ስራውን ሰርቶ ለማጠናቀቅ የአኩዋን ኢንጂነሪንግ 15 ወራት እና የዲኤች የማማከር ስራ ደግሞ 12 ወራት የጊዜ ገደብ ውል መውሰዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
የዲ.ኤች የማማከር ስራ ስራ አስኪያጅ አስቴር ተሰማ በበኩላቸው ስራው እንደ ዜጋ ሀላፊነታቸውም ጭምር መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮ-ፓኪስታን የወንድማማችነት በዓል በእስላማባድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ተከበረ
ኅዳር 27/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእስላማባድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወዳጅነት እና ወንድማማችነት ለማጠናከር በሚል የኢትዮ-ፓኪስታን በዓል አከበረ።
“የኢትዮ-ፓኪስታን ወንድማማችነት ሻምፒዮኖች” በተሰኘው ስነ-ስርዓት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ግለሰቦች እውቅና መሰጠቱን እና የህዝብ-ለህዝብ ዲፕሎማሲ ተከናውኗል።
በፓኪስታን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እድገት ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የኢትዮ-ፓኪስታን ወንድማማችነት ሻምፒዮኖችን እውቅና የሚሠጥ እና በሀገራቱ መካከል ያለውን ዘላቂ ግንኙነት የሚያድስ ነው ያሉ ሲሆን ሚዲያ እና የሲቪል ማህበረሰቦች ይህን ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር ረገድ ያላቸውን ጉልህ ሚና ገልጸዋል።
ሁለቱም ሀገራት የተሳሳተ መረጃ ስርጭት በተመለከተ የሚያደርጉትን ተጋድሎ አንስተው በተለይም ስለ ኢትዮጵያ የተሳሳተ መረጃ የሚያስተላልፉ ዓለም አቀፍ ትርክቶችን አውግዘዋል።
በዲጂታል ዘመን የተሳሳተ መረጃን በመዋጋት እና ትክክለኛ መረጃን ተደራሽ በማድረግ ረገድ የኢትዮጵያ እና የፓኪስታን ሚዲያዎች ላደረጉት ጥረት አድናቆታቸውን በመግለፅ እውነታን በማካፈል አዎንታዊ ዓለም አቀፍ አመለካከት መፍጠር እንችላለን ብለዋል።
ኢትዮጵያ በየዓመቱ ዓለም አቀፍ መሪዎችን የምታስተናግድ እና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መሪነት አረንጓዴ ለውጥ እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን በማራመድ ላይ የምትገኝ ፈጣን እድገት ያላት አገር ናት ብለዋል።

ጋናውያን ነገ ፕሬዘዳንታቸውን ይመርጣሉ
ኅዳር 27/2017 (ኤፍ ኤም ሲ)የምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ጋና ነገ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ታካሂዳለች።
ባለፉት አስርት ዓመታት ጀምሮ በአስከፊ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ እየተንገዳገደች የምትገኘው ጋና በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት የስልጣን ዘመናቸው መጠናቀቁን ተከትሎ ቀጣዩን ፕሬዚዳንታቸውን ለመምረጥ ቅዳሜ ዕለት ምርጫ ይካሄዳሉ።
የወቅቱ ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ-አዶ የሁለት ጊዜ የስልጣን ገደብ ማብቃቱን ተከትሎ 12 እጩዎች ለፕሬዚዳንትነት እየተወዳደሩ ይገኛሉ።
ነገር ግን በምርጫው ገዥው አዲሱ የአርበኞች ፓርቲ እና የተቃዋሚው ብሔራዊዊ ዴሞክራቲክ ኮንግረስ የተባሉት አውራ ፓርቲዎች ግንባር ቀደምትነት ይፎካከራሉ ተብሏል።
አሁን ላይ በምክትል ፕሬዘዳንትነት የሚገኙትን የ61 አመቱ ማሃሙዱ ባውሚያ እና በ66 አመቱ ጆን ማሃማ መካከል ከፍተኛ ፉክክር እንደሚደረግ የቅድመ ምርጫ የህዝብ አስተያዬቶች ይጠቁማሉ።
የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው እና የቀድሞ የአንድ ጊዜ ፕሬዝዳንት ጋናን የመሩት ጆን ማሃማ ልክ እንደአሜሪካው ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምርጫውን ያሸንፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሲኤንኤን ዘግቧል።

የግብርና ሚኒስቴር ለሴት አርሶ አደሮች የውሃ ፓምፖችን አበረከተ
ኅዳር 27/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የግብርና ሚኒስቴር በጉራጌ ዞን ለሚገኙ ሴት አርሶ አደሮች 20 የውሃ ፓምፖች አበረከተ።
ግብርና ሚኒስቴር የሴት አርሶ አደሮችን የማምረት አቅም ለማሳደግ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶችን በማስተባበር የተገዙና በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚሰራጩ 100 የውሃ መሳቢያ ፓምፖችን ለክልሎች እያስረከበ ይገኛል።
በዛሬው ዕለትም በሚኒስቴሩ የግብርና ኢንቨስትመንትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን በመገኘት በዞኑ ከተለያዩ ወረዳዎች ለተውጣጡ ሴት አርሶ አደሮች 20 የውሃ መሳቢያ ፓምፖችን አስረክበዋል።
ሴት አርሶ አደሮችን በማበረታታት እና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ የግብርናውን ዘርፍ ምርታማነት ማሳደግ እንደሚገባ ሚኒስትር ዴኤታዋ ጠቅሰው በቀጣይ የሴት አርሶ አደሮችን አቅም ለማሳደግ የሚደረጉ እገዛዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

1 ሺህ 155 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
ኅዳር 27/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከሳዑዲ ዓረቢያ 1 ሺህ 155 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ከህዳር 4/2017 እስከ ህዳር 27/2017 ወደ ሀገር ከተመለሱት 1ሺህ 155 ዜጎች 446 ወንዶች፣ 631 ሴቶች 78 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 218 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ እንደሚገኝ የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ ዜጎችን የመመለስ ስራ እስካሁን ከ87 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

የታህሳስ ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል ተገለጸ
ኅዳር 27/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ሚኒስቴሩ የነዳጅ ማደያዎች እና ኩባንያዎች ያልተገባ የነዳጅ ክምችት ከመያዝ እና የዋጋ ጭማሪ ከማድረግ ተቆጥበው ውሳኔውን ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን በቅንነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ ማሳሰቡን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡