𝑬𝒏𝒐𝒓 𝒎𝒖𝒔𝒍𝒊𝒎𝐬 𝒎𝒆𝒅𝒊𝒂
439 subscribers
112 photos
10 videos
2 files
123 links
Download Telegram
የጉንችሬ ሰቃዮች‼
=============
✍ እነዚህ የሞኣ አንበሳ ዩኒፎርም እያሠሩ በመልበስና ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም ይሄዱ ይመስል ነጠላ ለብሰው ት/ቤት በመመላለስ ኒቃብስቶች እንዳይማሩ ሴራ በመጠንሰስ እህቶቻችንን ከትምህርት ገበታቸው አፈናቀሉ እንጂ ቀድሞውኑ እየተማሩ አልነበረም።

ለመሆኑ ፈተናው ከ25 ነበር እንደ?
ሰው እንደት ህይዎት እያለው ማትስን ከ100 ዜሮና አንድ ያመጣል?
ምርጫ የሌለው workout ፈተና ነበር እንደ?

እነዚህ ልጆች በዚህ የማትስ ዕውቀታቸው የበፊቱን የሽንኩርት ዋጋ ከአሁኑ ላይ ቀንሱና ውጤቱን ንገሩኝ ብንላቸው ካልኩለስ የሚሆንባቸው ይመስለኛል¡ አሰዳቢ!

እኔን ዓይኔን ጨፍኜ ምንም ሳልሠራ ከ A-D ካሉት ምርጫዎች መካከል ለሁሉም ጥያቄ አንዱን ፊደል ብቻ መርጨ ብሞላ በትንሹ ከ10 በላይ አመጣለሁ¡

ምድረ ደነዝ! ምቀኝነትና ድግምት ብቻ እንጂ ዕውቀት'ማ ባዶ ናቸው።

ኢንሻ አላህ! የጉንችሬዋ እንቁ ግን ተምራ አንድ ቀን ታኮራናለች።

||
t.me/MuradTadesse
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙአለይኩም የእኖር_ሙስሊም ሚዲያ አባላት አብዛኞቻን በእኖር ወረዳ ጉንችሬ ከተማ መስተዳደር ውስጥ እየተገነባ ያለው የአል-አቅሳ መስጂድ ግንባታን በተመለከተ ብዙዎቻችን ችላ ብለነዋል። ከሰሞኑ ከወገናችን መላኩ ቢረዳ/አርቲስት ከአካባቢ ተወላጅነት በመነጨ ሞራል ስለዚህ መስጂድ መልእክቱን አስተላልፏል። ከመልእክቱም እንደሰማችሁት ለሙስሊሙ አንገት በሚሰብር ሁኔታ ግንባታው ከተጀመረ 3 አመታትን አስቆጥሮዋል!! እኛስ ወዴት ነው ያለነው!? ለመሆኑ ለዚህ መስጂድ ግንባታ የበኩላችንን አስተዋፆ አርገን ይሆን?! ካላደረግንም አሁኑኑ ለአኺራ ሚተርፍን ሰደቀተል ጃሪያ ተካፋዮች እንሁን እያሉ መልዕክቱን ያስተላልፋሉ የመስጂዱ ኮሚቴዎች።

የመስጂዱ ባንክ አካውንቶች
ዳሽንባንክ =2960044778611
ንግድ ባንክ👉  1000363997825
አቢሲኒያ ባንክ   👉 46766008
የጉንችሬ አል-አቅቅሳ መስጂድና መድረሳ

የመስጂዱን ኮሚቴዎች ለማግኘት
ሳኒ በድር +251912241897
አቡበከር ብዛ +251923575655
ኡሥማን ኡመር +251911046347
@voice_of_enor_Muslims
ሰላሙአለይኩም እቺ በፎቶ እምትመለከቷት እናታችን የ6ልጆች እናት ስትሆን በጅማ ዞን አሰንዳቦ በሚባል አካባቢ የምትገኝ ሲሆን አካባቢው ላይ ያሉ ወንድሞች ምን ገጥሞሽ ነው ኬትስ ነው የመጣሽው የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡላት ከእኖር ወረዳ ጠረደ ከሚባል አካባቢ የሄደች መሆኑዋን ተናግራቸዋለች። እናታችን የአዕምሮ ህመም እንዳለባትም ጥርጣሬያቸውን ነግረውናል ከባለ ቤታቸውም ተጣልተው እንደወጡ የገለፁ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑልንም ብለዋል። በመሆኑም የእኖር ሙስሊም ሚዲያ አባላት እኚህ እናት ከቤተሰቦቻቸው እንዲገናኙ ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። እንረባረብ ጠረደ አካባቢ ያላችሁ ልጆች ምስሉን በማረጋገጥ ደውሉልን🙏
+251923600505
እኛ የዚያ ከረሃብ የተነሳ ሆዳቸው ላይ ድንጋይ
ያሰሩት😥 ነብይ ህዝቦች ነን...


የዛ የመልካም ስነምግባር ቁንጮ መልክተኛ  ህዝቦች !
የዚያ ህዝቦቹ ናፍቀውት  ያነባው  ረሱል ህዝቦች
ያ በመለየቱ የቴምር ዛፍ የተንሰቀሰቀለት ታላቅ ሰው ፣ አይደለም የሰው ደም ዉሃ እንኳን ያለ አግባብ ሲፈስ የሚቆጡት ነቢይ ህዝቦች ነን...ተወዳጅ በሆኑት ነብያች ሰ.ዐ.ወ ላይ በሚቀጥፉት ላይ አላህ ቁጣውን ያውርድ🤲

የልብ እርጋታን ምታገኙበት ጁሙዓ ይሁንላቹ ፣ በዱዓ እንተዋወስ ።❤️🖤
وَقَالَ الْمَلِكُ ائْتُونِي بِهِ أَسْتَخْلِصْهُ لِنَفْسِي ۖ فَلَمَّا كَلَّمَهُ قَالَ إِنَّكَ الْيَوْمَ لَدَيْنَا مَكِينٌ أَمِينٌ
ንጉሡም «እርሱን አምጡልኝ ለራሴ ግለኛ አደርገዋለሁና» አለ፡፡ ባናገረውም ጊዜ «አንተ ዛሬ እኛ ዘንድ ባለሟል ታማኝ ነህ» አለው፡፡

قَالَ اجْعَلْنِي عَلَىٰ خَزَائِنِ الْأَرْضِ ۖ إِنِّي حَفِيظٌ عَلِيمٌ
«በምድር ግምጃ ቤቶች ላይ (ሹም) አድርገኝ፡፡ እኔ ጠባቂ አዋቂ ነኝና» አለ፡፡

وَكَذَٰلِكَ مَكَّنَّا لِيُوسُفَ فِي الْأَرْضِ يَتَبَوَّأُ مِنْهَا حَيْثُ يَشَاءُ ۚ نُصِيبُ بِرَحْمَتِنَا مَن نَّشَاءُ ۖ وَلَا نُضِيعُ أَجْرَ الْمُحْسِنِينَ
እንደዚሁም ለዩሱፍ በምድር ላይ ከእርሷ በፈለገው ስፍራ የሚሰፍር ሲሆን አስመቸነው፡፡ በችሮታችን የምንሻውን ሰው እንለያለን፡፡ የበጎ ሠሪዎችንም ዋጋ አናጠፋም፡፡
ሱረቱ ዩሱፍ 54-56

ወህኒ ቤት ውስጥ ከዩሱፍ ጋር  ሁለት ወጣቶች እንደነበሩ ታስታውሳለህ አይደል? ስለዩሱፍ የልብ ንፅህናና ፈሪሃ አላህነት ጥያቄ የለብንም። ብርሃናማ ሰው ነበር። ግን ደግሞ እርሱ በእስሩ ለተወሰኑ ዓመታት እንዲቆይ ተደርጎ ሁለቱ ወጣቶች ነፃ ተባሉ። የመጀመሪያው  አገልጋይ ለመሆን ወጣ ሌላኛው ደግሞ ለሞት ፍርድ ከእስር ተለቀቀ። ዩሱፍ ደግሞ ከረጅም ጊዜ በኋላ የግብፅ ንጉስ ለመሆን ከግድግዳው መሀል ተጠራ።

ምን ልልህ ነው? "ስጦታውን ሊያበዛልህ ሲፈልግ አንዳንዴ መንገዱ ሊርቅህ፣ እግርህም ሊጎተት ይችላል። ጌታህ ልክ እንደዩሱፍ ዓለምህን እየሰራው ነው…  አንተ ግን ጥበቡ አልደረሰህም።" እያልኩህ ነው።


اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
በማያልቀው የጌታዬ የሁን ቃሉ መሻታችን የሚሞላበት ፣ የተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን የታመመ መዳንን የሞቱት ሸሂድነትን á‹¨áˆšá‹ˆáˆá‰á‰ á‰ľ á‰ áˆ°áˆˆá‹‹á‰ľ በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ የታጀበ ምርጥየ ጁምዓ ይሁንልን🖤🖤🖤
« በነብዩ ዘመን ላይ ተገኝቶ እሳቸውን መከተል ያልቻለ አለ። ታላቁን የፍጥረታት እንቁን ተመልክቶ በመንገዳቸው ያልተራመደ አለ። እኛስ? አላየናቸውም ግን እንናፍቃቸዋለን። በዘመናቸው አልተገኘንም ግን እንከተላቸዋለን። አንድም ቀን ጋሻ ሆነ መከታ አልሆንናቸውም ግና ብንችል ነፍሳችንን ብንሰዋ ደስተኞች ነን።
ይህ ሁሉ በእኔ፣ ባንተ ወይም ባንቺ የተቻለ ይመስላችኋል? በፍፁም! አላህ ቢወደን ነው። አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ በልባችን ነብዩን  እንድንወድ፣ እንድንናፍቅ ስላስቻለን ብቻ ሌላ ነገር ከመጠየቅ ሀፍረት ሊይዘን በተገባ ነበር። ግና ሰዎች ነን።
ይህንን የአላህ ጸጋ አታቅልሉት በቃላት የማይገለፅ ረቂቅ እና ፍፁም ፍቅር የሆነ በረከት ነውና። መቼም አላህ ሲወድ ማስወደድን ያውቃል። እናሳ ለዚህ ጸጋው አልሀምዱሊላህ አለማለት ንፉግነት አይደለም ወይ? አልሀምዱሊላህ!
አላህ የሚወደውን የሚወድ ማክበርና ማላቅ ከእሱ በቀር አንድም የሚችል የለም። ለዚህ ምስክሩ በሰለዋት የማይዘናጉ ባሮቹ ምስክር ናቸው።
አላህ እሳቸውን መውደድና መናፈቅን አድሎናል። በትክክለኛው በሳቸው መንገድ ላይ የምንፀና ያድርገን!
ለወደደው ባርያው ሙሃባዎን ዘርቶ
እንዳሻው ያደምቃል
መቼም አላህ ሲወድ ማስወደድን ያውቃል። »
[አብዱልሀኪም ሰፋ]

للهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
ለአለማት እዝነት ሆነው በተላኩት የቃሲም አባት💚 ላይ አብዝተን ሰለዋት ምናወርድበት በሱናቸው ምንበረታበት
በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ በተሳኩ ምኞቶች የታጀበ ጁምዐን ተመኘሁ💚
እሁድ → እግሮች ሁሉ ወደ ጉንችሬ ያመራሉ‼
===============================
✍ በአላህ ፈቃድ የፊታችን እሁድ የካቲት 3, 2016 E.C. ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ የጉራጌ ዞኗ ጉንችሬ ከተማ ደምቃ ትውላለች። ላለፉት አመታት በኩፋሩም በጙላቱም ተፅዕኖ ስር ወድቃ የነበረችው ውቢቷ ጉንችሬ፤ ትክክለኛው የዳዕዋ ጮራ ዳግም ይፈነጥቅባታል። በዕለቱ ከአዲስ አበባ በሚሄዱ ታላላቅ ዳዒዎች ከሚዳሰሱ የሙሐደራ ርዕሶች መካከል፦

①) የቢድዓህ አደጋዎች፣
②) የሲሕር መዘዞቹ እና መፍትሄው፣
③) ተውሒድ የነብያት ጥሪ፣
④) በሱንና ላይ መፅናት… እና ሌሎችም ወሳኝ ወሳኝ ርዕሶች ይዳሰሳሉ።



√ የእለቱ ተጋባዥ ዱዐቶች፦

ኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ
ኡስታዝ ኢብራሂም ሙሳ
ኡስታዝ ሱልጧን ኸድር
ዶክተር ዐብዱ ኸይሬ
ኡስታዝ ዐብዱል ካፊ ሙሐመድ
ኡስታዝ ዐብዱ-ር'ረሕማን ዐባስ


√ የፕሮግራሙ ቦታ፦ በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ጉንችሬ ከተማ ከሃይስኩል ጀርባ መነኻሪያ አካባቢ ሰላም መስጅድ ውስጥ


ይህ አጓጊ የሆነ ፕሮግራም ላይ ቤተሰብዎንና ወዳጅ ዘመድዎን በመያዝ በጊዜ ይገኙ።

√ ለሴት እህቶቻችን በቂና ምቹ ቦታ ተዘጋጅቷል።

እናንተም በዚህ ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በክብር የተጋበዛችሁ ስለሆነ፤ ከወዲሁ ቀጠሯችሁን በማስተካከል በሰዓቱ ተገኙ።


✔ ለጉዞው ቅልጥፍና ይመች ዘንድ ለመሄድ ያሰባችሁ ሰዎች ወደ እነዚህ የዳዕዋው አስተባባሪዎች ጋር በመደወል እስከ ነገ ጁሙዓህ ድረስ እንድታሳውቁ አሳስበዋል።

🔹ቤተል፣ ዓለም ባንክ እና ዙሪያው አስተባባሪዎች

ዐብዱልጀሊል ፋሪስ  0937775792
ዐብዱልሀዲ ሙሐመድ  0947540222
አሕመድኑር አይታ  0911106306

🔹ኮካ, አብነት መርካቶ
ሬድዋን  0909113696
መኑር ዲኖ  0911082208
ዐብዱሰላም ኸይሩ 0913842798
ኢብራሂም   0921776328

🔹ፉሪ ኬንተሪ
ሙባረክ ኑሩ  0911921980
ዐብዱልጀባር  0911895313
ሙሐመድ ዑመር 0919411289
ኢብራሂም ኸሊል 0912420191
አብራሂም ዐረብ 0911830951

🔹ወለቴ
መኑር ዐባስ 0920969361
ሬድዋን ዑመር 0919225578

🔹ቦሌ ገርጂ
ሰኢድ ሙሐመድ  0913786613
ሱፊያን ለማ  0922976870
ዐብዱልጘፋር  0910122537

🔹አጠና ተራ
ዐብዱልፈታሕ በህሩ 0961065933
ከማል አወል  0919225568



♠
የላ! ጉዞ ወደ ጉንችሬ!
||
t.me/MuradTadesse
#በ_8ኛው ክፍለ ዘመን የኖሩት ኢማሙ ማሊክ ረህመቱላህ ዐለይህ እጅግ ድንቅ የሆነ ኪታባቸውን "ሙወጠእ"الموطأ አበርክተው ነበር። ይህ ኪታብ በኢስላሚክ ኢምፓየሩ ተሰራጭቶ  ደረሶች እየቀሩት ሙፍቲዎች እየጠቀሱት ዳኞች እየተመረኮዙበት በጣም ታዋቂነቱ ናኘ። ይህንን ያዩ የዛ ዘመን ሸይኾች ከእውቅናው ለመቋደስ አስበው ኪታብ እየጻፉ ርእሱን "ሙወጠእ" ይሉት ጀመር (plagiarism)። እናም በርካታ  ሙወጠኦች ታትመው ወጡ። ይህንን የታዘበው ልጃቸው አባቱ ጋር ሄዶ "የእርሶን ኪታብ እያስመሰሉ ብዙ ሰዎች እያሳተሙ ነው ምን ይሻላል? አላቸው። እሳቸውም አብሽር አታስብ ለአላህ ተብሎ የተሰራው ብቻ ምድር ላይ ይቀራል فقال ما كان لله يبقى  አሉት።
ታድያ ዛሬ ላይ በዚህ ስም የሚታወቅ ኪታብ የእርሳቸው ብቻ ሆኖ ቀሪው ሁሉ ጠፍቷል።
ስራንም ሆነ ንግግር፣ ፍቅርንም  ይሁን ወቀሳ ለአላህ ብለን ካደረግነው ግቡን ይመታል። ከዛ ውጭ ለእውቅና ለገጽታ ግንባታ ቀብድ ከሆነ በዱንያም በአኼራም ያዋርደናል።


اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
ስራችን ከይሉኝታ እና ከይስሙላ የፀዳ ኢኽላስ ላይ የፀና የሚሆንበትና ከንትርኮችና ከመጠላለፍ ወጥተን በጋራ ዲናችንን የምንረዳበት: ለአለማት እዝነት ሆነው በተላኩት የቃሲም አባት ላይ አብዝተን ሰለዋት ምናወርድበት በሱናቸው ምንበረታበት በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ በተሳኩ ምኞቶች የታጀበ ምርጥየ ጁምዐን ተመኘሁ💚

™𝑎𝑏𝑑..
Forwarded from áŠ˘á‰ĽáŠ‘ ቃሲም ኢስላማዊ ትምሕርቶች መስጫ እና ኢስላማዊ ተርቢያ ማእከል(Official Channel)☪️🇪🇹
አሰላሙ አለይኩም ወራሕመቱሏሂ ወበረካትሁ
የተከበራችሁ የዚህ ቻናል አባላት ሁላችሁም ባላችሁበት ሰላማችሁ አላህ ያብዛው
ይህ ቻናል የተከፈተበት አላማ ከዚህ በፊት online ላይ በኢሞ ግሩፓችን የጀመርነው የቁርአን ቲላዋ ሒፍዝ እና አዲስ ለቁርአን ጀማሪዎች ቃኢዳ አኑራኒያ እንደዚሁም ለጀማሪዎች የሚሆኑ የአጫጭር ኪታቦች ደርስ ፕሮግራም ማሕደሩ በማስፋት ለሑሉም ተደራሽ ለማድረግ ነዉ ስለዚሕ ቁርአን ያልጀመረ በቁርአን ፕሮግራማችን ላይ ተገኝቶ መጀመርና እንደዚሁ ኪታብ መጀመር የሚፈልግ በኪታብ ፕሮግራማችን ላይ ተገኝቶ መሣተፍ ይችላል
Forwarded from áŠ˘á‰ĽáŠ‘ ቃሲም ኢስላማዊ ትምሕርቶች መስጫ እና ኢስላማዊ ተርቢያ ማእከል(Official Channel)☪️🇪🇹
ቻናሉ ላይ በመጀመሪያ የተለቀቁ ኦዲዮዎች እስካሁን የተቀሩ የኪታብ ደርሶችና አሑን እየተቀሩ ያሉ ናቸው ቂርአቱን ለሑሉም ተደራሽ እንዲሆን የግሩፑን ሊንክ Share በማድረግ የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናበርክት
Forwarded from áŠ˘á‰ĽáŠ‘ ቃሲም ኢስላማዊ ትምሕርቶች መስጫ እና ኢስላማዊ ተርቢያ ማእከል(Official Channel)☪️🇪🇹
የምንቀራቸው ኪታቦች
1–ሰኞናሃሙስ አዱሩሱል ሙሒመህ
2–ማክሰኞ ነሕውሙምቲእ አጅሩሚያናአርበኢንሓዲስ
3–እሮብናአርብ ሙምቲአጅሩሚያ እናተጅዊድ ሒዳየቱልሙስተፊድ
4–ቅዳሜናእሁድ አርበኢን ሐዲስ
Click the link to join us!https://s.imoim.net/aJsqUc?from=copy_link

https://t.me/+l1T0ZqZkHUBiZGE0
📢{ ۞ قُلۡ یَـٰعِبَادِیَ ٱلَّذِینَ أَسۡرَفُوا۟ عَلَىٰۤ أَنفُسِهِمۡ لَا تَقۡنَطُوا۟ مِن رَّحۡمَةِ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ یَغۡفِرُ ٱلذُّنُوبَ جَمِیعًاۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِیمُ }
በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡(ሱረቱ ዙመር 53)

አላህ ወደ ወንጀል በሄድክበት እርቀት ልክ እሚቀጣህ ቢሆን ኖሮ…አላህ እያንዳንዱ ንግግርሽን ባላየ ሆኖ ባያልፍልሽ ኖሮ… አላህን መገዛት ባለብን ልክ ባለመገዛታችን ቢተሳሰበን ኖሮ የሚከተለንን የአላህን ቁጣ አስበነው እናውቃለን?
አላህ ሁሉን ማድረግ ከመቻሉ ጋር አብዛኞቹን ስህተቶቻችንን ፣ እሱን ማመፃችንን ፣ ትእዛዙን መጣሳችንን እና ብዙ ብዙ ወንጀሎቻችንን በይቅርታ አልፎ ልክ ምንም ወንጀል እንደሌለብን በሰላም ወጥተን እንድንገባ ማድረጉ ሳያንስ ጥራት የተገባው ነውና አንድ ስንዝር ወደእርሱ ስንጠጋ እሱ አንድ ክንድ ወደ እኛ የሚጠጋ ፣ እኛ የባህር አረፋ የሚያህል ወንጀል ተሸክመን ስንቀርበው እሱ ግን የባህር አረፋን እሚያህል ምህረት የሚያላብሰን ፣ በለመንነው…ይቅርታውን…እዝነቱን…ምህረቱን በጠየቅነው ቅፅበት የሚያሟላ ሆኖ የሚቀርበን አላህ ምስጋና የተገባው ነው።

✅اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
ወዶ በላካቸው እዝነቱን በእርሳቸው ባሳየን ወዱ ነብያችን የበዛ ሰለዋት ምናወርድበት እንደ ሀገር ከገባንበት ዝቅጠት የምንወጣበት በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ በተሳኩ ምኞቶች በጀሊሉ ራህመት የታጀበ የተዋበ ምርጥየ ጁምዐን ተመኘሁ🤎
ነሲሓ ኮንፈረንስ የሚታደሙበትን የመግቢያ ትኬት online በመመዝገብ በነፃ ይውሰዱ

ታላላቅ ኡለማዎች የሚሳተፉበት ልዩ የነሲሓ ኮንፈረንስ በአላህ ፈቃድ በሚሊኒየም አዳራሽ መጋቢት 1/2016 ይካሄዳል። በተከታዩ ሊንክ ከዌብሳይታቸን በስምዎ ነፃ የመግቢያ ቲኬት ማግኘት ይችላሉ።

https://conference.nesiha.tv

ለፕሮግራሙ ድጎማ በማድረግ አጋራችን ለመሆን Cbe 444 የሂሳብ ቁጥራችንን ይጠቀሙ።

እናመሰግናለን


____
🕌 ibnu Masoud islamic Center
@merkezuna
የ ም ስ ራ ች! ለሰለፊያ ዳዕዋ ናፋቂዎች!!
=
እነሆ የፊታችን እሁድ ቀን 24/06/2016 ከጥዋቱ 2:30 ጀምሮ ደማቅ የዳዕዋ ፕሮግራም በሙሳ ራማሽ (ቆዳና ሌጦ) መስጂድ ተሰናድቶ ይጠብቆታል። ፕሮግራሙ ለየት የሚያደርገው ከሌላጋ የሚመጡ እንግዶችን የሚያሳትፍ መሆኑ ነው።

እነርሱም፦
☞ ኡስታዝ ሙሐመድ አሕመድ (ኢብኑ ሙነወር) > «አል ዑሉው እና ወቅታዊ ጉዳይ ዳሰሳ»
☞ ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ> «የፆም ህግጋት»
☞ ኡስታዝ ሳዳት ከማል> መንዙማና ረመዷን


እርሶም ለዚህ ፕሮግራም ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር ደምቀው ይታደሙ ዘንድ ከወዲሁ ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው።

ኡስታዞቹ በአሏህ ፍቃድ ቅዳሜ ወደ ከተማችን ብቅ እንደሚሉ ይጠበቃል። ምናልባትም ተጨማሪ ፕሮግራም በእለተ ቅዳሜ መያዝ ከቻሉ በጊዜውም ተከታትለን የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

«ጥሪን ማክበር ኢስላማዊ ግዴታ ነው!!»

https://t.me/butajira_Qirat_daewa_group
የመን ሀገር በዒባዳዋ የታወቀች አንዲት ሴት ነበረች። ሲመሽ «ነፍሴ ሆይ! ዛሬ ሌሊት ያንቺ ነው። ሌላ ለሊት የለሽም።» ትላለች። ሌሊቱን ስትታገል ታድራለች።
ሲነጋም «ነፍሴ ሆይ! ዛሬ ቀን ቀንሽ ነው። ሌላ ቀን የለሽም።» ትላለች። ቀኑን በብርታት ስትታገል ትውላለች።»
መልካም እንሰንቅ!
ያለፍነውን አላህ ይማረን! መጪው ላይ ተውፊቅ ይስጠን! አሚን!🤲


اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
ወዶ በላካቸው እዝነቱን በእርሳቸው ባሳየን ወዱ ነብያችን የበዛ ሰለዋት ምናወርድበት በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ በተሳኩ ምኞቶች በጀሊሉ ራህመት የታጀበ የተዋበ ምርጥየ ጁምዐን ተመኘሁ🤎