✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
አንተ አሁን ድነኃል ወይስ አልዳንክም? ለሚሉን
ለጠያቂዎቻችን መልስ አዘል ጥያቄ እናቀርብላቸዋለን
● እስራኤል ከፈርኦን ባርነት ተላቀው ከግብጽ በወጡበት ቅጽበት ከነዓን ገብተዋል ወይስ አልገቡም?
● ከግብጽ ባርነትስ ድነዋል ወይስ አልዳኑም?
● ከግብጽ መውጣታቸው ከነዓን ለመግባታቸው ማረጋገጫ ነውን?
● ከነዓን ለመግባት ከግብጽ መውጣት ብቻውን በቂ ነውን?
✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
ይህን ደግሞ ምን አመጣው? ምንስ ያገናኘዋል? የሚለን ካለ "ይህም ለአሁኑ ጊዜ ምሳሌ ነው" የሚለውን አላነበብክምን? እንለዋለን። [ዕብ ፱፥፱]
የብሉይ ታሪክ ለሐዲስ ምሳሌ መሆኑን እንዲረዳ የተወሰኑ የመጽሐፍ ጥቅሶችን አስቀምጠን ንግባዕኬ ኀበ ጥንተ ነርገር እንዲል ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ ወደ ነገረ ድኀኅነትነ!!!
📖"... ይህ ምሳሌ ሆነልን. . . እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገሥጸን ተጻፈ " ፩ቆሮ ፲፥፮-፲፩
📖 ".. . ይህም ነገር ምሳሌ ነው.. . " ገላ፬፥፳፬
📖 ማቴ ፲፪፥፵፤ ዮሐ ፫፥፲፬ ፤ ፩ኛ ጴጥ፫፥፳፩ ፤ ...
✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
እስራኤል እናቱ አገልጋዩ አገልጋዩ እናቱ በሆነችለት በሙሴ መሪነት ከአባቶቻቸው ጀምሮ ከኖሩበት ከፈርኦን አገዛዝ ከግብጽ ባርነት እንደዳኑ እኛም እናቱ እናትም አገልጋይም በሆነችለት በክርስቶስ ኢየሱስ መሪነት ከአዳም ጀምሮ አዳም ገብሩ ለዲያብሎስ ሔዋን አመቱ ለዲያብሎስ እየተባልን ጠላት የባሪያዬ ልጅ የላሜ ውላጅ እያለ እኛን ከገዛበት ከዲያብሎስ አገዛዝ ከሲኦል ባርነት ድነናል!
✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
● የእስራኤል ከግብጽ መውጣት የበቅጽበት ከነዓን መግባት እንዳልሆነ ሁሉ ፶፭፻(5500) ዘመን ከኖርንበት ባርነት ድነናል ማለት ገነት መንግስተ ሰማያት ገብተናል ድኅነታችንንም አጠናቀናል ማለት አይደለም!
● ይህ የማይረዳው ካለ የከበረ ሐዋርያ ቅ/ጳውሎስን ይጠይቅ እርሱ "በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ" ይላልና [ፊልጵ ፪፥፲፪]
◎ ክርስቶስ አድኖን የለምን ስለየትኛው ያልተፈጸመ መዳን ነው የምታወራው እያሉ ይጠይቁት።
◎ እኛኮ ባመንበት ቅጽበት ድነናል የተፈጸመ እንጂ የሚፈጸም ድህነት የለንም ብለውም ይሞግቱት (ቅ/ጳውሎስ መልዕክቱን የጻፈው ላመኑት መሆኑን ልብ እንበል)
✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
➥ የእስራኤል ከግብጽ መውጣት ብቻውን ከነዓን መግባት እንዳልሆነ የእኛም በአዳም በኩል ከመጣብን ዕዳ መዳን መንግስተ ሰማያት መግባት ስላልሆነ...👇👇👇
➥ እስራኤል በእግዚአብሔርና በባሪያውም በሙሴ እንዳመኑ ማመን የግድ ያስፈልጋል[ዘፀ ፲፬፥፴፩]። የማያምን ግን የድኅነት ጎዳና ላይ የለም መንገድ ስቶ ወደ ፍርድ እየሄደ ነው።
📖 "በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል" ዮሐ 3:18
● በሚያምን #አይፈረድበትም ይላል እንጂ አሁን ተፈርዶለታል አለማለቱን እናስተውል እምነት #ብቻውን ደግሞ ለማዳን አይበቃምና
● በማያምን ግን #አሁን_ተፈርዶበታል ይላል ያለእምነት ደግሞ ምንም ምን ለድኅነት የሚያበቃ ሥራ መስራት አይቻልምና
➥ እስራኤል ከነዓን ለመግባት ባሕረ ኤርትራን መሻገር የግድ አስፈላጊያቸው እንደሆነ እኛም ድነን መንግስቱን ለመውረስ የግድ መጠመቅ አለብን[፩ኛ ቆሮ ፲፥፪] ባመንኩበት ቅጽበት ድኛለሁ የግድ ልጠመቅ አይገባኝም ለሚሉን እኛ የክርስቶስ እንጂ የሌላ ደቀ መዛሙርት አይደለንምና ከመምህራችን ከክርስቶስ የተማርነውን እንነግራቸዋለን
📖 "ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል። እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም" ዮሐ 3:5
➥ እስራኤል ከሰማይ የወረደ መና ከዓለት የፈለቀ ውኃ መጠጣት እንደነበረባቸው ሁሉ እኛም
ሰው ከእርሱ በልቶ እንዳይሞት ከሰማይ የወረደ እንጀራ የክርስቶስን ሥጋውን [ዮሐ፮፥፶] ከዓለት ክርስቶስ የተገኘ ክቡር ደሙን[፩ኛ ቆሮ ፲፥፬] የግድ ልንበላና ልንጠጣ ያስፈልገናል ያለ እርሱም መዳን የለም!
📖 "ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም" ዮሐ ፮፥፶፫
ይህ የሚከብዳቸው ካሉ "እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን? " ይባላሉ እንጂ ያለቁርባን ሊድኑ አይችሉም [ዮሐ ፮:፷፯]
➥ እስራኤል ከግብጽ ወጥተው አምነው ባህረ ኤርትራን ተሻግረው ከመናው በልተው ከዓለት ላይ ከፈለቀው ውኃ ጠጥተው በሲና ተራራ የተሰጣቸውን ህግ ካልተቀበሉና በእርሱ መመራት/መኖር/ ካልቻሉ ከነዓን አይገቡም። አታመንዝር የምትለዋን በመተላለፍ ስንቶቹ በበረሃ ቀሩ! [ዘኁ፳፭]
እኛስ በተራራው ስብከት የተሰጡንን ቃላት ካልጠበቅን ከከነዓን የምትልቀዋን በዓይን ያልታየች በልብ ያልታሰበችዋን መንግስት እንዴት እንወርሳለን? [ማቴ፯፥፳፩] መንግስቱን አለመውረስ አለመዳን አይደለምን?
➥ እስራኤል ወደ ምድረ ርስት ሲጓዙ እነርሱን ከመዳረሻቸው እንዳይደርሱ ጦር ከሚገጥሙ የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን[ዘኁ፳፩] የበሳንን ንጉስ ዐግን[ዘኀ፳፩፥፴፫] ከመሳሰሉ ጠላቶች ጋር መፋለም ነበረባቸው
እኛ የአዲስ ኪዳን እስራኤሎችም (እስራኤል ማለት ሕዝበ እግዚአብሔር ማለት ነው) ወደ ርስት መንግስተ ሰማያት በምናደርገው የመዳን ጉዞ ከመንገድ ሊያስቀሩን ውጊያ ከሚገጥሙን አጋንንት ጋር መጋደል አለብን
📖 "መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።" ኤፌ ፮፥፲፪
📖 "... መልካም ጦርነት ትዋጋ ዘንድ ይህችን ትእዛዝ አደራ እሰጥሃለሁ" ፩ኛ ጢሞ ፩፥፲፰
➥ በዚህ ሁሉ መላእክት ሊራዷቸው[ኢያ ፭፥፲፫-፲፭] ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት ሊቆምላቸው(ሊያማልዳቸው) [መዝ፻፮፥፳፫] እነኢያሱ ታቦቱ ሥር ተደፍተው ሊማጸኑላቸው [ኢያ፯፥፮-፲] ያስፈልጋቸዋል።
እኛንም መዳንን ለመውረስ እንድንችል የቅዱሳት መናፍስት (መላእክት) እርዳታ፣ የአማላጆች የቅዱሳን አማላጅነት ዘወትር ያግዘናል
📖 "ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?" ዕብ ፩፥፲፬
📖 "እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል" ማቴ ፲፥፵-፵፩
● የነቢያት የጻድቃን ዋጋቸው ምንድነው? መንግስቱ አይደለችምን?
"ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን #መንግሥት_ውረሱ" እንዲል ማቴ ፳፭፥፴፬
.
.
.
ሌላም ሌላም አለ እያንዳንዱን ለመዘርዘር ቦታውም ጊዜውም አይፈቅድልንም ዕውቀታችንም ይገድበናል።
✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
● ወዳጆች ሆይ መዳን በሂደት እንጂ በቅጽበት አለመሆኑን አስተዋላችሁን? ስለዚህ
" ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ. . . ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ" ዕብ ፬፥፯-፲፩
ከድኅነት የምታራቁት ድነናል የምትል ፉከራ መሳይ ከንቱ ፍልስፍናችሁን ትታችሁ እርሱ ነዋየ ህሩይ እንደመከረን በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ሆናችሁ መዳናችሁን ለመፈጸም ከቤተ ክርስቲያን ጋር አብራችሁ ትጉ!