ትምህርት ሚኒስቴር
231K subscribers
667 photos
2 videos
47 files
657 links
📚 This unique channel is prepared by the community request.

Any comment & Paid Ads @Tmhrt_Ministers_bot

《Buy Ads :- https://telega.io/c/tmhrt_ministers1

#ትምህርት_ሚኒስቴር
Download Telegram
#MOE
የ 2016 የ 12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ  ፈተና በምን መልኩ ይሰጣል


ትምሀርት  ሚንስትር  ሶስት አማራጮችን አስቀምጦ  ውሳን ላይ እዳልተደረስ ገለጹ

1,ከ 9-11 በቀድሞ ስርአት ትምህርት  የተማሩትና በ2016 የሚማሩት በአንድ ላይ ለመፈተን የተያዘ እቅድ

2,12ኛ ክፍሎች ብቻ በ 2016 በቀድሞ የትምህርት  ስርአት   ተምረው ከ9-12 እዲፈተኑ

3,በአዲሱ የትምህርት  ስርአት የ 12 ኛ ክፍል ትምህርት  ብቻውን ፈተና ለመስጠት  የተያዘ እቅድ ።

የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ ‼️

ትምህርት ሚኒስቴር


Share -> @Tmhrt_Ministers
#MOE_For_G12
" የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናው በኦንላይን ይሰጣል (ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ) " - የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን #በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በ #ኦንላይን እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ይህን ያሳወቁት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ናቸው።

ሚኒስትሩ ፤ በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚሆን አሳውቀዋል።

ለዚህም ተግባራዊነት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ፤ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቁመው የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናው በኦንላይን እንደሚሰጥም ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከአዲሱ የትምህርት ስርዓት ጋር በተያያዘ በመጽሐፍት ሕትመትና ስርጭት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ ነው በዋል።

በመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የመጽሐፍት እጥረት ማጋጠሙን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ፤ ችግሩ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ እንዳያጋጥም ቀደም ብሎ ጨረታ በማውጣት መጽሐፍትን በወቅቱ ለማድረስ እየተሠራ ነው ብለዋል።

መጽሐፍት እስከ መስከረም ወር መጨረሻ ድረስ እንደሚቀርቡ የትምህርት ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

Share -> @Tmhrt_Ministers
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኤባ ሚጄና አማካኝነት ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ላይ ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ዝግጅት ለማድረግ እንዲቻል ለፈተናው የሚቀመጡ ተማሪዎች መረጃ በአስቸኳይ እንዲላክለት ጠይቋል።

ሚኒስቴሩ ፤ ተቋማት መረጃው እጅግ ቢዘገይ እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲልኩ ያሳሰበ ሲሆን የማያሳውቅ ዩኒቨርሲቲ " ተፈታኝ ተማሪ የለውም " በሚል ተይዞ የሚታቀድ መሆኑን በጥብቅ አስገንዝቧል።

በ2015 ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው የመውጫ ፈተና በመንግስት ተቋማት ለፈተናው ከተቀመጡት 77,981 ተማሪዎች ውስጥ 50 እና ከዚያ በላይ በማምጣት ያለፉት 48,632 ተማሪዎች ወይም 62.37 በመቶ መሆናቸው አይዘነጋም።

በግል ተቋማት ደግሞ ለፈተና ከተቀመጡት 72,203 ተማሪዎች ውስጥ 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተው ያለፉት 12,422 ተማሪዎች ወይም 17.2 በመቶ ብቻ ነበሩ።

በድምሩ ከአጠቃላይ 150,184 የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን ያለፉት 61,054 ብቻ ወይም 40.65 በመቶ ናቸው።

የትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና አስተዳደር መመሪያ እንደሚያሳየው ከሆነ ፈተናው በዓመት ሁለት ጊዜ ይሰጣል። የመጀመሪያው በአመቱ መጨረሻ ሲሆን ሁለተኛ በአመቱ አጋማሽ ነው።

የመጀመሪያውን የመውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች በዚህ አመት አጋማሽ ላይ በሚዘጋጀው ሌላ ፈተና መፈተን የሚችሉ ሲሆን ከዚህ ቀደም ትምህርት ሚኒስቴር  ተፈታኞች ዳግም ፈተና ለመውሰድ መጀመሪያ ሲማሩበት ወደነበረበት ተቋም መሄድ ሳይጠበቅባቸው ባሉበት አካባቢ ባሉ ተቋማት ፈተናውን እንደሚወስዱ የሚደረግበት ስርዓት እንደሚዘረጋ መግለፁ አይዘነጋም (በዚህ ጉዳይ ወደፊት የሚወጣ መረጃ ካለ ተከታትለን እናሳውቃለን)።


🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች #የዩኒቨርሲቲ_ምደባን አስመልክቶ በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ ማብራሪያ

የተማሪ ምደባ መስፈርቶች፡-

1. በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች 1,000 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በመጀመሪያ የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸው ምደባ የሚካሄድ ይሆናል።

2. የምደባ ስርዓቱ እያንዳንዱ ተማሪ ያስመዘገበውን አጠቃላይ ውጤት በምደባ ስርዓት ሂደት ውስጥ መለያ አድርጎ ይጠቀማል፡፡ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሌሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ህግና ደንቦችን ባልጣሰ መልኩ ምርጫቸውን በመጠበቅ ረገድ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡

3. የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የቅበላ አቅም ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ተማሪዎች 46 ዩኒቨርሲቲዎች ለምርጫ ቀርበውላቸዋል፡፡

4. የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ የትምህርት ፕሮግራሞችና የተመረጡት ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የትምህርት ፕሮግራም መሰረት ያደረገ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

5. በተቋማት የጾታ ተዋፅኦን ለመጠበቅ በሚኖረው የምደባ ስርዓት የጾታ ተዋፅኦና ሚዛን እንዲጠበቅ ተደርጓል።

6. የምደባ ስርዓቱ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚመደቡ ተማሪዎችን ተዋጽኦ በጠበቀ መልኩ እንዲሆን ያግዛል፡፡

7. የምደባ ስርዓቱ ተማሪዎች ያስመዘገቡትን ውጤት ታሳቢ ያረገ ሲሆን ይህም ተመሳሳይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች አንድ ላይ እንዳይመደቡ በማድረግ የተለያየ ችሎታና ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎችን ቀላቅሎ ለማስተማር ያግዛል፡፡

8. የምደባ ስርዓቱ እንደ ወሊድ ያሉ ልዩ ሁኔታዎችን ያማከለ ነው፡፡ በመሆኑም በመሰል ሁኔታ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመቀጠል የሚቸገሩ ከሆነ ትክክለኛ ለውጥና ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል፡፡

9. በምደባ ወቅት የጤና ችግር ኖሮባቸው ትክክለኛ የሕክምና ማስረጃ ላላቸው ተማሪዎች ምደባው በተለየ መልኩ ሊታይ ይችላል፡፡

10. ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትዮች ካሉ የምደባ ስርዓቱ ከፍተኛ ነጥብ ያገኘው/ችው ተማሪ ከተመደበበት/ችበት የትምህርት ተቋም ቀሪው መንትያ ደግሞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በቀጥታ ይመድባል።

11. የምደባ ሲስተሙ የአካል ችግር ላለባቸው ተማሪዎች እኩል ዕድሎችን የሚሰጥ ሲሆን ልዩ ፍላጎቶቻቸውን እና ለምደባ መስፈርቶቻቸውን ግምትውስጥ በማስገባት የሚሰራ ይሆናል።

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም በሁለቱም የትምህርት መስኮች እያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች ፈተናው እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡

የተፈጥሮ ሣይንስ፦
እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

የማኅበራዊ ሣይንስ፦
እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተፃፈው ሰርኩላር፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅትንም ያብራራል።

በዚህም የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ዓ.ም ከ12ኛ ክፍል ብቻ ፈተናው የሚዘጋጅ ሲሆን ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9-11ኛ ክፍሎች በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንደሚሆን ያትታል።

ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ወደፊት ጥናት ተጠንቶ እስከሚለይ ድረስ በነበረው አሠራር መሠረት ውጤት ተደምሮ የሚገለጽ መሆኑንም ገልጿል።

የፈተና አሰጣጡን በተመለከተ ለተማሪዎች፣ ለወላጆች፣ ለመምህራን እና ለትምህርት ማህበረሰቡ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከወዲሁ እንዲያውቁት እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE

በ2016 አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ለሚወስዱ ተፈታኞች የሞዴል ፈተና ከዛሬ ጥር 28/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 05/2016 ዓ.ም እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አዟል።

ሚኒስቴሩ የመውጫ ሞዴል ፈተናን በማስመልከት ለሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ሰርኩላር፤ ፈተናው በተመረጡ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ አስታውሷል፡፡

ፈተናውን የተሳካ ለማድረግ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የጠቆመው ሚኒስቴሩ፤ ከዛሬ ጥር 28/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 05/2016 ዓ.ም የሚሰጠው ሞዴል ፈተና አንዱ የዝግጅት አካል መሆኑን ጠቁሟል።

የመውጫ ፈተናው ከየካቲት 06 እስከ 09/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።


🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ሽግግር የሚያሳልጡ ፍኖተ ካርታ እና መመሪያ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

የዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ መሆን ተቋማቱ በአስተዳደራዊ፣ አካዳሚያዊ እንዲሁም በሰው ሃብትና ፋይናንስ አስተዳደር ጉዳዮች ነፃነትን ከተጠያቂነት ጋር የሚያገኙበት የአሰራር ስርዓት እንደሆነ በሚኒስቴሩ የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ሽግግር ለማሳለጥ የሚያስችሉ የፍኖተ ካርታ እና የመመሪያ ዝግጅት በቅርቡ ተጠናቀው ወደ ሥራ እንደሚገቡ ጠቁመዋል።

ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ እየተሠራ ሲሆን ተቋማቱ ከአደረጃጀት ጀምሮ ለሽግግሩ የሚያግዟቸውን ተግባራት እያከናወኑ እንደሆነ ኃላፊው አስረድተዋል።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ራስ ገዝ ለመሆን የሰው ኃይል፣ ሃብት የማመንጨት አቅም፣ የመሰረተ ልማትና የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓታቸው እንዲሁም ዓለም አቀፍ ትስስራቸው እንደሚታይ ገልፀዋል። #ENA

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል።

በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ ሲሉም አሳውቀዋል።

ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎትም ፈተና በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው ብሏል።

ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጿል።

የአሰልጣኞች ስልጠና በመሥጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሠጣቸው ተገልጿል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ተብሏል።

#MoE

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ይፋ አድርጓል።

በንቅናቄው ተፈታኝ ተማሪዎችን ለፈተና ለማዘጋጀት ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት መርሐግብር በትምህርት ቤቶች ይሰጣል።

በማጠናከሪያ ትምህርቱ የተማሪዎችን የመማር ብቃትና የሥነ-ልቦና ዝግጅት ለማሳደግ እንደሚሠራ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገልፀዋል።

ይህን ሥራ አንዳንድ ክልሎች ቀደም ብለው መጀመራቸው የሚያበረታታ ተግባር መሆኑን ጠቅሰዋል።

ንቅናቄው ውጤታማ እንዲሆን የክልል ትምህርት ቢሮዎች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በጎ ፈቃደኞች፣ የተቋማት ባለሙያዎች፣ ወዘተ በማሳተፉ እንዲሠሩ ጥሪ አድርገዋል።


🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በመጪው ሰኔ ወር የሚሰጠው የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ን በድጋሜ ለሚወስዱ ተፈታኞች መልዕክት አስተላልፏል።

1ኛ. በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የነበረና አሁን በድጋሜ ለመፈተን ማመልከት ለሚፈልጉ፤

2ኛ. ከሰኔ 2015 ዓ.ም በፊት #የሕግ_መውጫ_ፈተና ወስደው የማለፍያ ነጥብ ያለገኙ አሁን በድጋሚ ለመውሰድ ለሚፈልጉ ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርስቲያቸው ለትምህርት ሚኒስቴር የተላከላቸው አመልካቾች፤

ምዝገባው እስከ ግንቦት 25/ 2016 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ገልጿል።

ተፈታኞች በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ብቻ ምዝገባውን እንዲያጠናቅቁ ተብሏል።

ሚኒስቴሩ ፦

➡️ ከላይ ከተገለጸው ጊዜ ውጭ የሚቀርቡ የምዝገባ ጥያቄዎች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው አሳስቧል።

➡️ በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የማለፊያ ውጤት ያልመጡ አሁን በድጋሜ መፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች የሚጠበቅባቸውን የአገልግሎት ክፍያ በቴሌ ብር ብቻ መፈጸም አለባቸው ተብሏል።

➡️ ከሰኔ 2015 ዓ/ም በፊት ለሕግ መውጫ ፈተና ተቀምጠው በድጋሜ ለመፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርሲቲያቸው መላኩን በማረጋጥ የሚጠበቅባቸውን #የአገልግሎት_ክፍያ ለዚሁ ጉዳይ ብቻ በተከፈተው የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር ➡️1000553176097 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን በግልፅ በሚታይ #ስካን_ኮፒ በማድረግ በ seneexit2016@gmail.com ኢሜል አድራሻ እንዲልኩ ጥሪ ቀርቧል።

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MOE

ሬሜዲያል ተፈታኞች በሙሉ
የትምህርት ሚኒስቴር የሬሚዲያል (የማካካሻ) ትምህርት የማጠቃለያ ፈተናን ከሰኔ 3-10/ 2016 ዓ.ም ድረስ ለመስጠት የፈተና ፕሮግራም ማዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጅ ሰኔ 9/ 2016 ዓ.ም የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ስለሆነ በዕለቱ ይሰጥ የነበረው ፈተና ሰኔ 11/2016 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡


🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MOE_Exam
የ2016 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ተጠናቀቀ
**

የከፍተኛ ትምህርት
የ2016 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ተጠናቅቋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት የጥራትና ብቃት ማሻሻል ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰይድ መሐመድ፤ በ244 የቅድመ ምረቃ መርሐ ግብሮች ከሰኔ 14 እስከ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና መጠናቀቁን ገልጸዋል።

57 የመንግስትና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ያስፈተኑ ሲሆን ፈተናውም በ51 የፈተና ማዕከላት ተሰጥቷል።

ለፈተናው ከተመዘገቡት 169ሺህ 790 ተማሪዎች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ 117ሺህ 192 ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን መውሰዳቸው ተጠቅሷል፡፡

እንዲሁም 52ሺህ 598 ተማሪዎች ደግሞ ፈተናውን በድጋሚ ለመውሰድ የተመዘገቡ መሆናቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሪሚዲያል ተማሪዎች የፕሮግራም ድልድል የሚሰሩበትን መስፈርት አሳውቋል።


የሪሚዲያል ተማሪዎቹን ወደ ፕሮግራም ለመመደብ በሚደረግ ድልድላ ተመሳሳይ መሰፈርት መጠቀም እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

በዚህም ሁሉም ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 20%፣ በአንደኛ ሴሚስተር አማካይ ውጤት 50% እና ወደ መስክ መግቢያ ፈተና 30% ብቻ የሚደለደሉ መሆኑን ደብዳቤው ያስረዳል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጥ የሆነ የአካዳሚክ ካላንደር መተግባር ይጀምራል።

ደብዳቤው ወጥ የሆነ የአካዳሚክ ካላንደር ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መተግባር እንደሚጀምር ይገልፃል።

በዚህም፦

★ የ1ኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ፦ መስከረም 7 እና 8/2017 ዓ.ም

★ የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሁሉም መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ፦ መስከረም 9 እና 10/2017 ዓ.ም

★ የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሁሉም መርሐግብር የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት መስከረም 13/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

(ሙሉው የ2017 ትምህርት ዘመን የአካዳሚክ ካላንደር ከላይ ተያይዟል።)

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በክረምት መርሀግብር ከዲፕሎማ ወደ ድግሪ የትምህርት ደረጃ የሚሰለጥኑ መምህራን የመውጫ ፈተና እና PGDT

በክረምት መርሃግብር የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና እየወሰዱ ያሉ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች PGDT የመውሰድ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ስልጠናቸውን እንዳጠናቀቁ በቀጣይ በሚገለፀው የመውጫ ፈተና ፕሮግራም መሰረት ተፈታኞች በአቅራቢያቸው በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የመውጫ ፈተናውን የሚወስዱ ይሆናል። #MoE

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የNGAT ፈተና መቼ ይሰጣል ?

ትምህርት ሚኒስቴር ፥ የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ እና የፈተና ቀንን አሳውቋል።

በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ያላቸው እና በተለያዩ ምክንያቶች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ያመለጣቸው አመልካቾች እስከ ነሐሴ 26/2016 ዓ.ም ድረሰ በ https://ngat.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ ይችላሉ ብሏል።

ለፈተናው የተመዘገቡ በየተመደቡበት የፈተና ማዕከላት እና የመፈተኛ ፕሮግራም መሰረት ከነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ፈተናው እንደሚሰጣቸው ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ተፈታኞች በፈተና ወቅት የተሰጣቸውን User Name and Password፣ እና ማንነታቸውን የሚገልጽ መታዋቂያ ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል።

#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE

" ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች የመላው ኢትዮጵያውያን እንጂ የተቋቋሙበት መንደር አይደሉም " - ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

የ33ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ " ፍትሃዊ እና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ! " በሚል ጭብት ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ተካሒዷል።

ጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ፥ በትምህርት ዘርፍ ላይ ያሉ አመራሮች የትምህርት ሥራን ከፖለቲካ መለየት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

" ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች የመላው ኢትዮጵያውያን እንጂ የተቋቋሙበት መንደር አይደሉም " ብለዋል ሚኒስትሩ።

" ከዚህ በኋላ በምንም ዓይነት ሁኔታ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በአካባቢ የሚመደብበት ሁኔታ እንደማይኖር " ገልፀዋል።

" የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ምደባ በውድድር እና በብቃት ላይ ብቻ የተመሠረተ እንዲሆን ይሠራል " ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰኞ ይፋ ይደረጋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ሰኞ ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ/ም እንደሚገለጽ አሳውቋል።

የዘንድሮው ብሔራዊ ፈተና በቅይጥ ማለትም በወረቀት እና በኦንላይን መሰጠቱ ይታወሳል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE
#Placement

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት እንደምትችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንድትልኩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።


ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM