ትምህርት ሚኒስቴር
231K subscribers
667 photos
2 videos
47 files
657 links
📚 This unique channel is prepared by the community request.

Any comment & Paid Ads @Tmhrt_Ministers_bot

《Buy Ads :- https://telega.io/c/tmhrt_ministers1

#ትምህርት_ሚኒስቴር
Download Telegram
ከ18 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና ይሰጣል።

በፀጥታና በሌሎች ምክንያቶች ፈተና ላልወሰዱ ከ18 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በጎንደር፣ በጋምቤላ፣ በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች 17,753 ተማሪዎች እንዲሁም 300 በውጭ ሀገራት ለሚገኙ ተማሪዎች ፈተናው እንደሚሰጥ የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ለኢዜአ ተናግረዋል።

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሦስት መፈተኛ ጣቢያዎች ሲፈተኑ ከነበሩ ተማሪዎች መካከል ከ16 ሺህ በላይ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሁለት እስከ ሦስት የትምህርት ዓይነቶች ሳይፈተኑ መቅረታቸውን አስታውሰዋል።

በጋምቤላ ደግሞ ከ100 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን በከፊል እና ሙሉ ለሙሉ አልወሰዱም ብለዋል።

በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ 982 ተማሪዎችን ጨምሮ በድምሩ ከ18 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናው ይሰጣል ብለዋል።

በውጭ ሀገራት በኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርት የሚማሩ 300 ተማሪዎች ከዛሬ ነሐሴ 28/2015 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 02/2015 ዓ.ም ፈተናው ይሰጣል።

ለዚህም የፈተና ጣቢያ አስተባባሪዎች ከኢትዮጵያ ፈተናው ወደሚሰጥባቸው ሀገራት መጓዛቸውን ም/ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
#ENA

የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ
‼️‼️

Share -> @Tmhrt_ministers
#MoE

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ሽግግር የሚያሳልጡ ፍኖተ ካርታ እና መመሪያ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

የዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ መሆን ተቋማቱ በአስተዳደራዊ፣ አካዳሚያዊ እንዲሁም በሰው ሃብትና ፋይናንስ አስተዳደር ጉዳዮች ነፃነትን ከተጠያቂነት ጋር የሚያገኙበት የአሰራር ስርዓት እንደሆነ በሚኒስቴሩ የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ሽግግር ለማሳለጥ የሚያስችሉ የፍኖተ ካርታ እና የመመሪያ ዝግጅት በቅርቡ ተጠናቀው ወደ ሥራ እንደሚገቡ ጠቁመዋል።

ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ እየተሠራ ሲሆን ተቋማቱ ከአደረጃጀት ጀምሮ ለሽግግሩ የሚያግዟቸውን ተግባራት እያከናወኑ እንደሆነ ኃላፊው አስረድተዋል።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ራስ ገዝ ለመሆን የሰው ኃይል፣ ሃብት የማመንጨት አቅም፣ የመሰረተ ልማትና የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓታቸው እንዲሁም ዓለም አቀፍ ትስስራቸው እንደሚታይ ገልፀዋል። #ENA

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ አመራሮች ካውንስል ተመሠረተ።

ካውንስሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ዘርፉን ማስተሳሰር የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

የአመራር ካውንስሉ ጥናትና ምርምር በማድረግ ልዩነት መፍጠር የሚችል የሰው ኃይል ማፍራት ኃላፊነት እንደተጣለበት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከ2,000 በላይ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት በመንግሥት እና በግል ባለቤትነት ስራ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ ከ100 በላይ የሚሆኑት የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች መሆናቸውን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ጠቅሰዋል፡፡ #ENA

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM