Tikvah-University
250K subscribers
9.11K photos
16 videos
54 files
730 links
Download Telegram
#Exit_Exam

የመውጫ ፈተና በመጪው ሐምሌ ወር በኦንላይን ለሁሉም የመንግስት እና የግል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይሰጣል።

ለመውጫ ፈተናው ብቁ ለመሆን ተማሪዎች የመጨረሻ ሴሚስተር ፈተና መውሰድ እና ኮርሶቻቸውን ማጠናቀቅ እንደሚጠበቅባቸው የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የፈተና ንድፈ ማሳያ / Blueprint / እንዲሁም የፈተና ዝግጅት ሥራ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በመውጫ ፈተናው ዙሪያ ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተማሪዎች ሕብረት ተወካዮች ጋር የተወያዩት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ተማሪዎች በቀሪዎቹ አምስት ወራት ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

@tikvahuniversity
#Exit_Exam

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ባለፈው ወር የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው ተማሪዎች መካከል 13 በመቶ ብቻ ማሳለፋቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ ላይ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ተገኝተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውስጥ 87 በመቶዎቹ መውደቃቸውን ጠቁመዋል። 22 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ  አለማሳለፋቸውን ገልፀዋል።

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ካስፈተኗቸው ተማሪዎች 58 በመቶ ማሳለፋቸውን  ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ ሊያደርግ መሆኑ ተሰምቷል።

ዳግም ምዝገባው ያስፈለገው እንደ  ሀገር ወጥነት ያለው የፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ እና በመንግሥት እና በግል ተቋማት መካከል ያለውን የፈቃድ አሰጣጥ የአሰራር ስርዓት ልዩነት ለማስቀረት መሆኑን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሽፈራው ሽጉጤ ገልፀዋል። #ETA

@tikvahuniversity