Tikvah-University
235K subscribers
8.76K photos
15 videos
50 files
671 links
Download Telegram
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የገጠር እና የከተማ ቀበሌዎች የግብርና ናሙና ቆጠራ ያከናውናል።

አገልግሎቱ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ የሚያሟሉ #መረጃ_ሰብሳቢዎችን አወዳድሮ በኮንትራት መቅጠር ይፈልጋል።

በዚህም በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በኩል በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (ሌበር ማርኬት ፖርታል - E-LMIS) በመጠቀም ከመላ የሀገሪቱ ክፍሎች 43,500 ሰራተኞች ይፈልጋል።

በዚህ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን lmis.gov.et ላይ በመግባት በመመዝገብና አቅራቢያችሁ ወደሚገኝ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመሔድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር ይዛችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

የሥራ መደብ፡-
የስታቲስቲክስ መረጃ ሰብሳቢ 1
ብዛት፡- 43,500
ፆታ፡- አይለይም
ሊንኩን በመጫን ይመዝገቡ፦
https://lmis.gov.et

@tikvahuniversity
#National_GAT

ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) በዚህ ወር መጨረሻ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተፈታኞችን ለ3ኛው ዙር አገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና ለማዘጋጀት ቲቶሪያል እየሰጡ ይገኛሉ።

የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ለመቀጠል "ወጥ የሆነ" ፈተና በትምህርት ሚኒስቴር እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ተማሪዎቹ ለመማር የሚያመለክቱበት የትምህርት ክፍል የተለያዩ በመሆናቸው ወጥ ፈተና መሰጠቱ አግባብነት የለውም የሚሉ ባለሙያዎች አሉ፡፡

ተፈታኞች "የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተናው ከባድ ነው፣ የማለፊያ ነጥቡም በጣም ተሰቅሏል" ሲሉ ይደመጣሉ።

ምሁራን በበኩላቸው "ፈተናውን ማቅለል ይቻላል፣ ይህ ግን መፍትሔ አይደለም" ይላሉ። ይልቁንም "ሌሎች አገራት እንደሚያደርጉት የመግቢያ ነጥቡን ቀነስ ማድረግ የተሻለ አማራጭ እንደሆነ" ምሁራኑ ይመክራሉ፡፡

የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና ወስደዋል? በፈተናው ላይ ያለዎትን አስተያየት ለቲክቫህ ያድርሱ። ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከብሔራዊ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ያደርሳችኋል።

@tikvahuniversity
የክረምት ልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና ዛሬ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም ይጀምራል።

እስከ ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም በተመረጡ 28 የስልጠና ማዕከላት የሚሰጠውን የአቅም ግንባታ ስልጠና የሚወስዱ ሰልጣኞቹ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡

60 ሺህ የሚሆኑ ሰልጣኞች የሚከታተሉት ስልጠናው፤ ለትምህርት ቤት አመራሮች ለ10 ቀናት እንዲሁም ለመምህራን ለ20 ቀናት እንደሚሰጥ መርሐግብር ተይዞለታል፡፡

ስልጠናውን የተከታተሉ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ከ100% ፈተና የሚፈተኑ ሲሆን፤ 75% እና ከዚያ በላይ የሚያመጡ የምስክር ወረቀት በሙያቸው ይሰጣቸዋል።

ምስል፦ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
የክረምት ልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና የመክፈቻ ስነ-ስርዓት በበይነመረብ ተካሒዷል፡፡

ስልጠናውን በሚሰጡ 28 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የመክፈቻ መርሐግብሩን ታድመዋል፡፡

ስልጠናው ለትምህርት ቤት አመራሮች ለአስር ቀናት እንዲሁም ለመምህራን ለሃያ ቀናት ይሰጣል፡፡

@tikvahuniversity
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ከግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ጋር በፈቃድ እና ፈቃድ ዕድሳት አሰጣጥ መመሪያ፣ ስታንዳርዶች እና ዳግም ምዝገባ መምሪያ ላይ ውይይት አካሒዷል፡፡

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባለቤቶች/አንድ ተወካይ በውይይቱ ተሳትፈዋል፡፡

@tikvahuniversity
#Exit_Exam

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ባለፈው ወር የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው ተማሪዎች መካከል 13 በመቶ ብቻ ማሳለፋቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ ላይ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ተገኝተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውስጥ 87 በመቶዎቹ መውደቃቸውን ጠቁመዋል። 22 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ  አለማሳለፋቸውን ገልፀዋል።

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ካስፈተኗቸው ተማሪዎች 58 በመቶ ማሳለፋቸውን  ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ ሊያደርግ መሆኑ ተሰምቷል።

ዳግም ምዝገባው ያስፈለገው እንደ  ሀገር ወጥነት ያለው የፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ እና በመንግሥት እና በግል ተቋማት መካከል ያለውን የፈቃድ አሰጣጥ የአሰራር ስርዓት ልዩነት ለማስቀረት መሆኑን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሽፈራው ሽጉጤ ገልፀዋል። #ETA

@tikvahuniversity
3ኛ ዙር የፋይናንስ እና ካፒታል ማርኬት ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!

የካፒታል ማርኬት ገበያ በኢትዮጵያ ሊጀመር ነው። እርስዎም ኢንስቲትዩታችን ውስጥ የሚሰጠውን የፋይናንስና ካፒታል ማርኬት ስልጠና በመውሰድ ራስዎን ለትግበራው ያዘጋጁ።

ብቁ በሆኑ መምህራን የሚሰጠው ስልጠናው፤ ከመሰረታዊ የካፒታል ገበያ ምንነት አንስቶ እንዴት አንድ ግለሰብ ወይም ተቋም ከስጋት ነፃ በሆነ መንገድ በገበያው ላይ መሳተፍ እንደሚችል ግልፅ ያደርጋል።

☎️    0906777799 / 0906777755

አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 3ኛ ፎቅ

Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
🎯 ትክክለኞቹን የሳፋሪኮም ገጾች እንከተል! ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት! ⚡️

🔗 የM-PESAን ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉 https://t.me/Safaricom_Ethiopia_PLC

የፌስቡክ ገጻችንን እዚህ እንቀላቀል 👉 https://www.facebook.com/SafaricomET

የኢንስታግራም አካውንታችንን እዚህ እንቀላቀል 👉 https://www.instagram.com/safaricomet/

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether
ተመዝግበዋል?

አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ለሚያሳትፈው የኮዲንግ ስልጠና የኦንላይን ምዝገባ ተጀምሯል።

ከክፍያ ነፃ የሚሰጠውን ስልጠና ለመከታተል ይመዝገቡ 👇
www.ethiocoders.et/

(ምዝገባውን ለማድረግ መፈፀም ያለበዎት steps ከላይ በምስሎቹ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የክረምት አዲስ የ "PGDT" ሰልጣኖች የማመልከቻ ጊዜን እስከ ሐምሌ 25/2016 ዓ.ም አራዝሟል፡፡

በሌላ በኩል የዩኒቨርሲቲው የማታ መርሐግብር ነባር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የክረምት ሴሚስተር ምዝገባ ከሐምሌ 24-26/2016 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡ ትምህርት ሐምሌ 27/2016 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
Tikvah-University
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች እንዲሁም ዳግም ተፈታኞች ሰኔ 24/2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና መውሰዳቸው ይታወቃል። በርካታ ተፈታኞች የመውጫ ፈተና ውጤት ሳይገለፅ ዘገየ ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ አድርሰዋል። በጉዳዩ ላይ የኢንስቲትዩቱን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ጠይቀናል። "ኢንስቲትዩቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመውጫ ፈተናው ላይ እየተወያየ መሆኑን"…
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ያደርጋል።

የኢንስቲትዩቱ የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች እንዲሁም ዳግም ተፈታኞች የዛሬ ወር የመውጫ ፈተና መውሰዳቸው ይታወቃል።

"ኢንስቲትዩቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመውጫ ፈተናው ላይ እየተወያየ መሆኑንና ውይይቱ ሲጠናቀቅ የተፈታኞች ውጤት እንደሚገለፅ" ነግረናችሁ ነበር።

ተቋሙ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የነበረው ውይይት ትናንት ተጠናቋል። በመሆኑም የተፈታኞች ውጤት ዛሬ ወይም ነገ ይፋ እንደሚደረግ ከኢንስቲትዩቱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ሰምተናል።

@tikvahuniversity