Tikvah-University
294K subscribers
9.85K photos
15 videos
62 files
861 links
Download Telegram
#ጥቆማ

በሁዋዌ የተማሪዎች ICT ውድድር 2024-2025 ይሳተፉ!

በሁዋዌ የተማሪዎች ICT ውድድር (Huawei ICT Competition 2024-2025 for Northern Africa) ለመሳተፍ በቅድሚያ የሁዋዌ ICT አካዳሚ አባል ይሁኑ።

የአካዳሚው አባል ለመሆን 👇
https://e.huawei.com/en/talent/portal/#/

በሁዋዌ ICT ውድድር 2024-2025 ለመመዝገብ 👇
https://e.huawei.com/en/talent/#/ict-academy/ict-competition/regional-competition?zoneCode=026902&zoneId=98269642&compId=85131998&divisionName=North%20Africa&type=C001&isCollectGender=N&enrollmentDeadline=undefined&compTotalApplicantCount=209

የምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው፦
ኅዳር 1/2017 ዓ.ም

የማጣሪያ ፈተና የሚሰጠው፦
ኅዳር 6/2017 ዓ.ም

የፍፃሜ ውድድር፦
ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በ2017 ዓ.ም በደረጃ እና በመጀመሪያ ዲግሪ በማታ እና ቅዳሜና እሑድ ፕሮግራም ከዚህ በታች በተዘረዘሩ ሙያዎች ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ይፈልጋል።

በመጀመሪያ ዲግሪ
► Hotel Management
► Tourism Management

መስፈርቶች፦
► የትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርስቲ መግቢያ ያወጣውን መስፈርት ያምታሟሉ፣
► በቴክኒክና ሙያ በደረጃ 4 የሰለጠናችሁና የአንድ ዓመት የሥራ ልምድ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፣
► በማንኛውም ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላችሁ፣
► የ8ኛ እና የ12 ከፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒውን ማቅረብ የምትችሉ፣
► ኢንስቲትዩቱ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆናችሁ፣
► ሁለት ጉርድ ፎቶ እና የመመዝገቢያ 200 ብር።

የምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው 👇
ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም

በደረጃ
► Culinary art
► Food & Beverage Service
► Food & Beverage Control
► Bakery & Pastry production
► Front office Service
► Housekeeping & Laundry Service
► Tour Guide Service
► Tour Operation Service

መስፈርቶች፦
► የ12ኛ ከፍል ትምህርት ያጠናቀቃችሁ፣
► የ8ኛ እና የ12ኛ ከፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒውን ማቅረብ የምትችሉ፣
► ኢንስቲትዩቱ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆናችሁ፣
► ሁለት ጉርድ ፎቶ እና የመመዝገቢያ 200 ብር።

የምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው 👇
ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የፌዴራል የማናቸውም ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ የመግቢያ ፈተና ይውሰዱ!

ለመመዝገብ ማሟላት ያሉባችሁ መስፈርቶች፦

➢ የኢትዮጵያ ዜግነት ያለው ወይም ትውልደ ኢትዮያዊ/ዊት/የሆነ/የሆነች/፣
➢ በሕግ ዕውቅና ካለው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም በሕግ በዲግሪ የተመረቀ/ች እና የመውጫ ፈተና የማለፊያ ውጤት ተግባራዊ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ የማለፊያ ውጤት ያመጣ/ያመጣች፣
➢ የትምህርት ማስረጃ ዲግሪ ከኢትዮጵያ ውጪ የተሰተጠ ከሆነ የዲግሪውን አቻ ግምት ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
➢ የትምህርት እና የሥራ ልምድ ማስረጃ እንዲሁም ማንነቱን የሚገልፅ የታደስ መታወቂያ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ የሚያቀርብ/የምታቀርብ፣

የምዝገባ ጊዜ፡-
ከጥቅምት 18 እስከ 29/2017 ዓ.ም

የምዝገባ ቦታ፡
በፍትህ ሚኒስቴር በጥብቅና ፈቃድ እና ነፃ የህግ ድጋፍ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ 2ኛ ፎቅ

የፈተና ቀን፡-
ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ሰዓት

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በ2017 ዓ.ም በተለያዩ የሙያ መስኮች በቀን፣ በማታ እንዲሁም በቅዳሜና እሑድ መርሐግብር ሰልጣኞችን በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡

► በዲግሪ
► በደረጃ አምስት
► በደረጃ አራት
► በደረጃ ሦስት

የምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው፦
ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115308121 ይደውሉ፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ Children's Surgery International (CSI) ከተባለ አሜሪካን ሀገር ከሚገኝ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በተፈጥሮ የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ላለባቸው ህፃናት ነፃ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ሊሰጥ ነው፡፡

ህክምናው ከጥቅምት 9 እስከ 15/2017 ዓ.ም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እንደሚሰጥ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡ ችግሩ ያለባቸው ህጻናት ህክምናውን እንዲያገኙ ያድርጉ፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም በቀን መደበኛ እንዲሁም በቅዳሜ እና እሁድ መርሐግብሮች የማስተርስ ትምህርታችሁን መከታተል የምትፈልጉ እስከ ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም ድረስ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡

የትምህርት መስኮች፦

✍️ General Public Health
✍️ Health Care Quality
✍️ Reproductive Health
✍️ Epidemiology

የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች፡-

► ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ ወይም ኮሌጅ በጤና ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ
► 400 ብር የመመዝገቢያ በንግድ ባንክ ቁጥር 1000010795218
► የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) የማለፊያ ውጤት ማቅረብ

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከሲስኮ አካዳሚ ጋር በመተባበር የቴክኖሎጂ ስልጠና አዘጋጅቷል፡፡

አካዳሚው ቀጣሪ ተቋማት በሚፈልጓቸው የኔትወርኪንግ፣ የሳይበር ሰኪዩሪቲ እና የአይቲ መሰረታዊያን ላይ ስልጠናን ይሰጣል፡፡

ስልጠናው በአካል ወይም በኦንላይን የሚሰጥ ሲሆን፤ ስልጠናውን ለሚያጠናቅቁ ሰልጣኞች ሰርተፊኬት እንደሚሰጥ ዩኒቨርሲቲው ያወጣው ማስታወቂያ ያሳያል፡፡

የስልጠና ቀን፦
ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡00

የስልጠና ቦታ፦
መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከሲስኮ አካዳሚ

ለበለጠ መረጃ፦
0935838316 / 0921970076

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይውሰዱ፡፡

ብሪቲሽ ካውንስል ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ IELTS ፈተና ኅዳር 21/2017 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ፈተናውን መውሰድ የሚፈልጉ አመልካቾች ምዝገባ ማድረግ ጀምሯል።

የፈተና ቦታ፦ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ

ሁለት አይነት የ IELTS ፈተናዎች (IELTS Academic and IELTS General Training) ይሰጣሉ፡፡

ኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://ethiopia.britishcouncil.org/exam/ielts

በአካል ለመመዝገብ፦ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ህንፃ ቁ. 130፣ ቢሮ ቁ. 408

ለበለጠ መረጃ፦ 0925629589

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለ2017 ትምህርት ዘመን በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ሰልጣኞችን መመዝገብ ጀምሯል፡፡

መስፈርቶች
▪️የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆነ/የሆነች፣
▪️በ2015/16 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የማለፊያ ውጤት (50%) ያለው/ያላት፣
▪️በ2014/15 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትለው ያጠናቀቁ

ስልጠናው በአዲስ አበባ ላምበረት መናኸሪያ አካባቢ በሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ግቢ የሚሰጥ ሲሆን፤ በተጨማሪም የቻይንኛ እና ኮሪያኛ ስልጠናዎች ይሰጣሉ፡፡ ኢንስቲትዩቱ የምግብ እና የዶርም አገልግሎቶች ያቀርባል፡፡

የምዝገባ ጊዜ፦
ጥቅምት 11-15/2017 ዓ.ም
የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ፦
ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም
ትምህርት የሚጀምረው፦
ኅዳር 2/2017 ዓ.ም

አስፈላጊ ሰነዶች
▪️ የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
▪️ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሰርተፊኬት
▪️ የሪሚዲያል ፕሮግራም ሰርተፊኬት

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ጥቅምት 13 እስከ 19/2017 ዓ.ም ያከናውናል፡፡

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት የመግቢያ ፈተና (NGAT) ወስደው የማለፊያ ነጥብ በማምጣት ካመለከቱ መካከል፣ በቂ አመልካች ቁጥር የተገኘባቸውና በ2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ የሚከፈቱ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች፦
▪️ Nutrition (መደበኛ)
▪️ Reproductive Health (መደበኛ)
▪️ MBA (መደበኛ እና ኤክስቴንሽን)

በሌሎች የትምህርት ክፍሎች ያመለከታቸሁ፣ በቂ የአመልካች ቁጥር ባለመገኘቱ የትምህርት ዝግጅታችሁ በሚያሳትፋችሁ በተከፈቱ ትምህርት ክፍሎች ላይ እንድትመዘገቡ ዩኒቨርሲቲው ጠቁሟል፡፡

በኦንላይን የተመዘገባችሁ ለምዝገባ ስትሔዱ ለማመልከት የተጠየቁትን መረጃዎች ይዛችሁ መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የፕሮግራሚንግ ክህሎትንና የዲጂታል ዕውቀትን የሚያጎለብት የፕሮግራሚንግ መፅሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በአማርኛ ለህትመት በቅቷል።

C++ Programming in Amharic የተሰኘው መፅሐፉ፥ በዘርፉና በሶፍትዌር ማበልፀግ የበርካታ ዓመታት ልምድ ባላቸው ዮሐንስ እዘዘው የተፃፈ ነው።

346 ገፆች ያሉት መፅሐፉ፤ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን፣ መምህራንን እና የዘርፉ ተመራማሪዎችን በፕሮግራሚንግ ቋንቋ ዙሪያ እንደሚጠቅም ፀሐፊው ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

መፅሐፉ በነፃ የቀረበ ሲሆን፤ በኦንላይን https://t.me/eteldigital ሊያገኙት ይችላሉ ብለዋል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አመልካቾችን በመቀበል ላይ ነው።

ኢንስቲትዩቱ (BDU-EITEX) በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ ተማሪዎችን ይቀበላል።

የትምህርት መስኮች
- Textile Engineering
- Garment Engineering
- Leather Product Engineering
- Fashion Design
- Textile & Apparel Merchandising
- Visual Art
- Textile Chemical Process Engineering

የማመልከቻ ጊዜ፦
ከጥቅምት 18-27/2017 ዓ.ም

ለበለጠ መረጃ፦ 0938882020

ለ2017 ዓ.ም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደባችሁ ተማሪዎች በዝውውር ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።

ኦንላይን ለማመልከት 👇
https://forms.gle/gSypn17ttmm8k4746

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በፖስት ቤዚክ ነርሲንግ በመደበኛ መርሐግብር ለመማር የምትፈልጉ አመልካቾች ምዝገባ እስከ ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም እንደሚካሔድ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና በኮምፕሬሄንሲቭ ሰፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአካል በመገኘት ምዝገባ ማድረግ ትችላላችሁ ተብሏል።

የትምህርት መስኮች፦
- Surgical Nursing
- Neonatal Nursing
- Pediatric & Child Health Nursing
- Emergency & Critical Care Nursing

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ጥበባት ትምህርት ቤት በ2016 ዓ.ም እና በ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁና በሙዚቃ እና በትያትር ጥበባት የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር ፍላጎት ያላችሁን በመደበኛ ፕሮግራም ማሰልጠን ይፈልጋል።

መስፈርቱን የምታሟሉና ፍላጎቱ ያላችሁ አመልካቾች ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ሁለት ኮፒ ይዛችሁ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት በመቅረብ መመዝገብ ትችላላችሁ።

የምዝገባ ጊዜ፦
ከጥቅምት 21 እስከ ህዳር 6/2017 ዓ.ም

የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪ የነበራችሁና ለፍሬሽማን ፕሮግራም የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁፋችሁ የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ ነፃ ስልጠናን ለመከታተል ይመዝገቡ።

ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችልዎትን ስልጠና ይውሰዱ።

የስልጠና ዘርፎች፦

► ዌብ ፕሮግራሚንግ
► አንድሮይድ ማበልፀግ
► ዳታ ሳይንስ

ስልጠናውን በስምንት ሳምንት ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይሰጣቸዋል።

ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢውን ማኅበረሰብ፣ የዩኒቨርሲቲውን ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሰራተኞች ተጠቃሚ የሚያደርግ #ነጻ የኮሪያ ቋንቋ ስልጠና አዘጋጅቷል፡፡

ስልጠናው በዲላ ዩኒቨርሲቲ እና በኮሪያ መንግሥት ትብብር የተዘጋጀ ነው፡፡

ስልጠናውን ተከታትለው ለሚያጠናቅቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ይሰጣል።

የምዝገባ ጊዜ፦
ከጥቅምት 25 እስከ ኅዳር 3/2017 ዓ.ም

የምዝገባ ቦታ፦ ኦዳያኣ ግቢ

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አመልካቾችን በመቀበል ላይ ነው።

ኢንስቲትዩቱ (BDU-EITEX) በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ ተማሪዎችን ይቀበላል።

የትምህርት መስኮች
- Textile Engineering
- Garment Engineering
- Leather Product Engineering
- Fashion Design
- Textile & Apparel Merchandising
- Visual Art
- Textile Chemical Process Engineering

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም

ለበለጠ መረጃ፦ 0938882020

ለ2017 ዓ.ም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደባችሁ ተማሪዎች በዝውውር ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።

ኦንላይን ለማመልከት 👇
https://forms.gle/gSypn17ttmm8k4746

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይውሰዱ፡፡

ብሪቲሽ ካውንስል ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ IELTS ፈተና ኅዳር 21/2017 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ፈተናውን መውሰድ የሚፈልጉ አመልካቾች ምዝገባ ማድረግ ጀምሯል።

የፈተና ቦታ፦ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ

ሁለት አይነት የ IELTS ፈተናዎች (IELTS Academic and IELTS General Training) ይሰጣሉ፡፡

ኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://ethiopia.britishcouncil.org/exam/ielts

በአካል ለመመዝገብ፦ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ህንፃ ቁ. 130፣ ቢሮ ቁ. 408

ለበለጠ መረጃ፦ 0925629589

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በደረጃ ስድስት በቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በማታ ፕሮግራም ለመሰልጠን ፍላጎት ያላችሁ እንድትመዘገቡ ተጋብዛችኋል።

የምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው 👇
ህዳር 5/2017 ዓ.ም

በኦንላይን ለመመዝገብ 👇 http://196.188.248.35

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን 👇
ህዳር 6/2017 ዓ.ም

የመግቢያ ፈተናውን ያለፉ አመልካቾች የምዝገባ ጊዜ 👉 ከህዳር 12-15/2017 ዓ.ም

(የኢንስቲትዩቱ መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#ጥቆማ #የኢትዮጵያአየርመንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ Trainee Cabin Crew, Senior Accountant I እንዲሁም በሌሎች የሙያ ዘርፎች አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ማስታወቂያ አውጥቷል።

ለ Trainee Cabin Crew ለማመልከት ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ቢያንስ (ዝቅተኛው) 200 ነጥብ ያስመዘገበ/ች መሆን አለባቸው።

አመልካቾች ዕድሜያቸው ከ19 እስከ 30 ዓመት፣ ቁመት ቢያንስ 1.58 ሜትር እና 212 ሴ.ሜ የሆነ ክንድ ለሴት እንዲሁም ለወንድ ቢያንስ 1.70 ሜትር ቁመት መሆን አለበት።

የምዝገባ ጊዜ፦
ከህዳር 8 እስከ 12/2017 ዓ.ም

ምዝገባው የሚከናወንባቸው ዩኒቨርሲቲዎች፦

- አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (አዳማ)
- አዲስ አበባ (በኦንላይን - ማመልከቻው ሲከፈት ይፋ ይደረጋል)
- አምቦ ዩኒቨርሲቲ (አምቦ)
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ (አርባ ምንጭ)
- አሶሳ ዩኒቨርሲቲ (አሶሳ)
- ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (ባህር ዳር)
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ (ደሴ)
- ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ (ድሬዳዋ)
- ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ( ጋምቤላ)
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (ጎንደር)
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ (ሀዋሳ)
- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ (ጅግጅጋ)
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ (ጅማ)
- መቐለ ዩኒቨርሲቲ (መቐለ)
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ)
- መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ (ሮቤ)
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ (ሰመራ)
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ (ወልቂጤ)

ተጨማሪ መረጃዎች፣ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፣ ዝርዝር ጉዳዮች እንዲሁም ሌሎች የወጡ ማስታወቂያዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረ-ገጽ ላይ ሰፍሮ ይገኛል ይመልከቱ 👇
https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies

@tikvahethiopia