TIKVAH-SPORT
247K subscribers
47K photos
1.48K videos
5 files
2.99K links
Download Telegram
#EURO2024

የአልባንያ ብሔራዊ ቡድን ከደቂቃዎች በኋላ ከክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ጋር በሚያደርገው ጨዋታ በጣልያን ከተሸነፈበት የመጀመሪያ ጨዋታ የሁለት ተጨዋቾች ለውጥ አድርጓል።

ብሔራዊ ቡድኑ አርማንዶ ብሮሀን በሬይ ማናህ እንዲሁም ቃዚም ላቺን በታውላንት ሴፌሪን ተክቶ ወደ ሜዳ ይገባል።

የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ ሽንፈት ካስተናገደበት የስፔን ጨዋታ ውስጥ ሶስት ተጨዋቾችን ተጠባባቂ አድርጎ ጨዋታውን የሚጀምር ይሆናል።

ክሮሽያ ሁለቱን ተከላካዮች ጆሲፕ ስታንሲች እና ማሪን ፖንግራቺች በጁራኖቪች እና ኢቫን ፔርሲች ስትተካ አጥቂው አንቴ ቡዲሚር በበኩሉ ብሩኖ ፔትኮቪችን ተክቷል።

ኢቫን ፔሪሲች በቋሚ አሰላለፍ መካተቱን ተከትሎ የማንችስተር ሲቲው የመስመር ተጨዋች ጆስኮ ግቫርዲዮል የግራ መሐል ተከላካይ ሆኖ እንደሚጫወት ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ከአልባንያ አቻቸው ጋር ያደረጉትን የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ለክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ግቦችን አንድሬ ክራማሪቾ እና ጋሱላ በራሱ ግብ ላይ ከመረብ ሲያሳርፉ ለአልባንያ ቃዚም ላቺ እና ጋሱላ አስቆጥረዋል።

ክሮሽያ በአንድ ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጣ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ ስትይዝ አልባንያ በተመሳሳይ አንድ ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ቀጣይ ሳምንት ሰኞ ክሮሽያ ከጣልያን እንዲሁም አልባንያ ከስፔን ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የስኮትላንድ ብሔራዊ ቡድን ከስዊዘርላንድ አቻቸው ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የስኮትላንድ ብሔራዊ ቡድን ግብ ስኮት ማክ ቶሚናይ ከመረብ ሲያሳርፍ ጆርዳን ሻኪሪ ስዊዘርላንድን አቻ ማድረግ ችሏል።

የስዊዘርላንዱ ተጨዋች ጆርዳን ሻኪሪ በሶስት የአውሮፓ ዋንጫ ውድድሮች ላይ ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

ስዊዘርላንድ ጥሎ ማለፉን ለመቀላቀል ስትቃረብ ስኮትላንድ በበኩሏ የመጨረሻ ጨዋታዋን ማሸነፍ ቀጣዩን ዙር የመቀላቀል እድልን እንድታገኝ ያደርጋታል።

የምድብ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ ጀርመን :- 6 ነጥብ

2️⃣ ስዊዘርላንድ :- 4 ነጥብ

3️⃣ ስኮትላንድ :- 1 ነጥብ

4️⃣ ሀንጋሪ :- ምንም ነጥብ

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ እሁድ ስዊዘርላንድ ከጀርመን እንዲሁም ስኮትላንድ ከሀንጋሪ ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

በአሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት የሚመራው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በምሽቱ የዴንማርክ ጨዋታ በመጀመሪያ ጨዋታው የተጠቀመውን አሰላለፍ ይዞ ወደ ሜዳ ይገባል።

በጨዋታው አሌክሳንደር አርኖልድ በተለመደው መልኩ የመሐል ሜዳውን የዴላን ራይስ ጋር ተጣምሮ የሚመራው ይሆናል።

የማንችስተር ሲቲው ተጨዋች ፊል ፎደን በበኩሉ በጨዋታው በግራ መስመር ተጨዋችነት ብሔራዊ ቡድኑን ያገለግላል።

ኬራን ትሪፔር ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ሀምሳኛ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ በመጀመሪያው አሰላለፍ ከተጠቀመበት ስብስብ የአንድ ተጨዋች ለውጥ አድርጎ ወደ ሜዳ ይገባል።

ክርስቲያን ኤሪክሰን በተመሳሳይ ከሁለቱ የፊት መስመር አጥቂዎች ጀርባ የአስር ቁጥር ሚናን በመያዝ ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

በአሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ የሚመራው የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት ከስፔን ጋር በሚያደርገው ጨዋታ በመጀመሪያው የአልባኒያ ጨዋታ የተጠቀመውን አሰላለፍ ይዞ ይገባል።

የስፔን ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ ክሮሽያን ከረታበት የመጀመሪያ ጨዋታው የአንድ ተጨዋች ለውጥ አድርጎ ጣልያንን የሚገጥም ይሆናል።

የስፔን ብሔራዊ ቡድን በሳውዲ አረቢያ ሊግ ለአል ናስር የሚጫወተውን ተከላካዩ አይመሪክ ላፖርቴ በቋሚ አሰላለፍ አካቷል።

የመጀመሪያ ጨዋታውን በቋሚነት የጀመረው ናቾ ፈርናንዴዝ መጠነኛ ጉዳት እንዳጋጠመው ሲገለፅ ጨዋታውን በተጠባባቂነት ይጀመራል።

ከሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የሚያሸንፈው ቡድን ከወዲሁ ምድቡን በበላይነት በማጠናቀቅ ጥሎ ማለፉን መቀላቀሉን ያረጋግጣል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የፖላንድ ብሔራዊ ቡድን በኔዘርላንድ ከተሸነፈበት የመጀመሪያ ጨዋታ የአራት ተጨዋቾች ለውጥ በማድረግ ወደ ሜዳ የሚገቡ ይሆናል።

የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ በፈረንሳይ ከደረሰበት ሽንፈት የሶስት ተጨዋቾች ለውጥ አድርገው ወደ ሜዳ ይገባሉ።

የኦስትሪያ አሰልጣኝ ራልፍ ራኚክ በራሱ ላይ ግብ ያስቆጠረውን ዎበር ጨምሮ በፈረንሳይ ጨዋታ በመሐል ተከላካይነት የተጠቀሟቸውን ሁለት ተከላካዮች ተጠባባቂ አድርገዋል።

የፊት መስመር ተጨዋቹ ማርኮ አርናቶቪች በበኩሉ ሚሼል ግሪጎራሽን በመተካት በቋሚ አሰላለፍ ተካቷል።

የፖላንድ ወሳኝ ተጨዋች ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በምሽቱ ጨዋታም በጉዳቱ ምክንያት ለብሔራዊ ቡድኑ በቋሚ አሰላለፍ ገብቶ ግልጋሎት አይሰጥም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ፈረንሳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ንጎሎ ካንቴ በመጀመሪያዎቹ ሁለት የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች የጨዋታው ኮከብ ተብሎ መመረጥ ችሏል።

ውጤቱን ተከትሎ የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎችን የተሸነፈው የፖላንድ ብሔራዊ ቡድን ከውድድሩ የተሰናበተ የመጀመሪያው ቡድን መሆኑ ተረጋግጧል።

የምድብ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ ኔዘርላንድ :- 4 ነጥብ

2️⃣ ፈረንሳይ :- 4 ነጥብ

3️⃣ ኦስትሪያ :- 3 ነጥብ

4️⃣ ፖላንድ :- ምንም ነጥብ

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ሐሙስ ፈረንሳይ ከፖላንድ እንዲሁም ኔዘርላንድ ከኦስትሪያ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የጆርጂያ ብሔራዊ ቡድን ከቼክ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የጆርጂያን ግብ ሚካውታድዝ ከመረብ ሲያሳርፍ ፓትሪክ ሺክ ቼክ ሪፐብሊክን አቻ ማድረግ ችሏል።

የምድብ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ ቱርክ :- 3 ነጥብ

2️⃣ ፖርቹጋል :- 3 ነጥብ

3️⃣ ቼክ ሪፐብሊክ :- 1 ነጥብ

4️⃣ ጆርጂያ :- 1 ነጥብ

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ እሮብ ጆርጂያ ከፖርቹጋል እንዲሁም ቼክ ሪፐብሊክ ከቱርክ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አምበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግርኳስ ህይወቱ የቱርክ ብሔራዊ ቡድን ላይ ግብ አላስቆጠረም።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከቱርክ ብሔራዊ ቡድን ጋር ሶስት ጊዜ የተጫወተ ሲሆን እ.ኤ.አ 2012 ያገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ማስቆጠር ሳይችል ቀርቷል።

ሮናልዶ በምሽቱ ጨዋታ ሁለት መቶ ዘጠኝ ኢንተርናሽናል ጨዋታውን ከፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን በምሽቱ የስዊዘርላንድ ጨዋታ በመጀመሪያ ሁለት የምድብ ጨዋታዎች የተጠቀሙትን የቡድን ስብስብ ይዘው ይገባሉ።

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ማኑኤል ኑዌር በአስራ ስምንት ጨዋታዎች በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ታሪክ ለብሔራዊ ቡድኑ ብዙ ጨዋታዎች ያደረገ ግብ ጠባቂ ይሆናል።

የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ከደቂቃዎች በኋላ በሚጀምረው ጨዋታ ተመሳሳይ አማካይ ፣ ተከላካዮች እና ግብ ጠባቂ ይዘው ወደ ሜዳ ይገባሉ።

በምሽቱ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ስዊዘርላንድ ሁለት የፊት መስመር ተጨዋቾች ለውጥ አድርገው ሲገቡ ጆርዳን ሻኪሪ ተጠባባቂ ሆኖ ይጀመራል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

በምሽቱ የጣልያን እና ክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ 38,000 ተመልካች በሚይዘው የሌፕዚግ ስታዲየም 25,000 ገደማ የክሮሽያ ደጋፊዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።

የፊት መስመር ተጨዋቹ ኢቫን ፔርሲችን ተጠባባቂ ያደረገችው ክሮሽያ የአጥቂ አማካዩ ክራማሪችን በፊት መስመር ቦታ ላይ አሰልፋለች።

የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን በጨዋታው ያለ ተፈጥሯዊ አጥቂ ሲገቡ 4-6-0 የሆነ የጨዋታ አሰላለፍ ሊጠቀሙ ይችላሉ።

የጣልያን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ በምሽቱ የክሮሽያ ጨዋታ የሶስት ተጨዋቾች ለውጥ አድርገው ወደ ሜዳ ይገባሉ።

የጣልያን ብሔራዊ ቡድን በጨዋታው የ3-5-2 የጨዋታ አሰላለፍ ይዘው እንደሚገቡ ይጠበቃል።

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
#EURO2024

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ሶስት የመጨረሻ ጨዋታዎች ሲደረጉ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ከስሎቬኒያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

በሌላኛው የምድብ ጨዋታ የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን ከሰርቢያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

የምድቡ ደረጃ ምን ይመስላል ?

1️⃣ እንግሊዝ :- 5 ነጥብ

2️⃣ ዴንማርክ :- 3 ነጥብ

3️⃣ ስሎቬኒያ :- 3 ነጥብ

4️⃣ ሰርቢያ :- 2 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ አምስት የመጨረሻ ጨዋታዎች ሲደረጉ የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ከዩክሬን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

በምድቡ ሌላኛው ጨዋታ የሮማንያ ብሔራዊ ቡድን ከስሎቫኪያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

የስሎቫኪያን ግብ ኦንድሬ ዱዳ ማስቆጠር ሲችል ራዝቫን ማሪን ሮማንያን አቻ ማድረግ ችሏል።

የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ምድቡን በሁለተኝነት ማጠናቀቁን ተከትሎ በጥሎ ማለፉ ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የሚገናኝ ይሆናል።

የምድቡ ደረጃ ምን ይመስላል ?

1️⃣ ሮማንያ :- 4 ነጥብ

2️⃣ ቤልጂየም :- 4 ነጥብ

3️⃣ ስሎቫኪያ :- 4 ነጥብ

4️⃣ ዩክሬን :- 4 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የጨዋታ አሰላለፍ ! 1:00 እንግሊዝ ከ ስሎቫኪያ @tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ የተጠቀሙትን ኮነር ጋላገር ተጠባባቂ በማድረግ ኮቢ ማይኖን በቋሚ አሰላለፍ አካተዋል።

የማንችስተር ዩናይትዱ አማካይ ኮቢ ማይኖ በትልቅ ውድድር የመጀመሪያ ጨዋታውን ለእንግሊዝ በቋሚ አሰላለፍ ገብቶ የሚያደርግ ይሆናል።

በምድብ ጨዋታዎች ትችት ሲሰነዘርባቸው የነበሩት ሶስቱ አናብስት በምሽቱ ጨዋታ የመሐል ክፍላቸው  በዴክላን ራይስ ፣ ኮቢ ማይኖ እና ቤሊንግሀም የወጣቶች ጥምረት ይመራል።

የስሎቫኪያ ብሔራዊ ቡድን አንድ አቻ በተለያዩበት የሮማንያ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ የተጠቀሙትን ቋሚ አስራ አንድ ይዘው እንግሊዝን የሚገጥሙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ ጆርዳን ፒክፎርድ ለምሽቱ የስሎቫኪያ ጨዋታ በሟሟቅ ላይ እያለ ጣቶቹን መጉዳቱ ተገልጿል።

ፒክፎርድ በአሁን ሰዓት የግራ እጁን ህመም እተሰማው እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በጨዋታው መሰለፍ ካልቻለ አሮን ራምስዴል የሚተካው ይሆናል።

ጆርዳን ፒክፎርድ ከቀናት በፊትም በተመሳሳይ ከጨዋታ በፊት ሲያሟሙቅ ጣቶቹ ላይ ጉዳት አድርሶ ለህመም ተጋልጦ እንደነበር ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን በኦስትሪያ ከተሸነፈበት በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ የሶስት ተጨዋቾች ለውጥ አድርጎ ሮማንያን የሚገጥሙ ይሆናል።

የፒኤስጂው አማካይ ዣቪ ሲሞንስ ወደ ቋሚ አሰላለፍ ሲመለስ አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን በፊት መስመር እና ተከላካይም ለውጥ አድርገዋል።

የሮማንያ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ ከሴሎቫኪያ ጋር አቻ ከተለያየበት የምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ የሁለት ተጨዋቾች ለውጥ አድርጓል።

በምሽቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን የአሸናፊነት ግምቱን አግኝቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የአውሮፓ ዋንጫው ውድድር ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ሲጠናቀቁ ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀሉ ስምንት ብሔራዊ ቡድኖች ተለይተው ታውቀዋል።

የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ምን ይመስላሉ ?

አርብ 1:00 - ስፔን ከ ጀርመን

አርብ 4:00 - ፖርቹጋል ከ ፈረንሳይ

ቅዳሜ 1:00 - ስዊዘርላንድ ከ እንግሊዝ

ቅዳሜ 4:00 - ቱርክ ከ ኔዘርላንድ

እነማን ግማሽ ፍፃሜ ይደርሳሉ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎችን እነማን ይመሩታል ? ማክሰኞ እና እሮብ የሚደረጉ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎችን የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል። ማክሰኞ ምሽት 4:00 በፈረንሳይ እና ስፔን መካከል የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ስሎቬኒያዊው የ 42ዓመት ዳኛ ስላቭኮ ቪንቺክ በመሐል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል። እንዲሁም እሮብ ምሽት 4:00 ሰዓት የሚደረገውን የእንግሊዝ እና ኔዘርላንድ ጨዋታ ጀርመናዊው…
#EURO2024

እንግሊዝ ከ ኔዘርላንድ ጋር የሚያደርጉትን የአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ጀርመናዊው ዳኛ ፌሊክስ ዝዋየር በመሀል ዳኝነት እንዲመሩት ተመርጠዋል።

ዋና ዳኛው ፌሊክስ ዝዋየር ከዚህ በፊት በጨዋታ ማጭበርበር ተከሰው ለስድስት ወራት ከዳኝነት ታግደውም እንደነበር ተገልጿል።

ዳኛው በወቅቱ ጉቦ መቀበላቸው ተረጋግጦ እንደነበር ሲገለፅ እንግሊዛዊው ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም በበኩሉ ጀርመን እያለ " ጨዋታ አጭበርባሪ " ሲል ጠርቷቸው እንደነበር ተዘግቧል።

በዚህ ምክንያት ዋና ዳኛው ለጨዋታው መመደብ ከእንግሊዝ መገናኛ ብዙሃን ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ማስነሳቱ እየተነገረ ይገኛል።

@tikvahethsport    @kidusyoftahe
#EURO2024

ስፔናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የሚሳተፍ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ይፅፋል።

የ 16ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል በታላላቅ ኢንተርናሽናል ውድድሮች የተሳተፈ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች በመሆንም የፔሌን ሪከርድ ይሰብራል።

ፔሌ እ.ኤ.አ 1958 በ17 አመቱ በአለም ዋንጫ ውድድር ግማሽ ፍፃሜ በመሳተፍ ባለታሪክ ተጨዋች ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

እንግሊዝ ውስጥ በርካታ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸው በመጪው ሰኞ ጠዋት ከተለመደው የመግቢያ ሰዓት ዘግይተው እንዲገቡ ፍቃድ እንደሚሰጡ ተገልጿል።

ትምህርት ቤቶቹ ይህንን የሚያደርጉት ተማሪዎቹ እሁድ ምሽት እንግሊዝ ከስፔን ጋር የምታደርገውን የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ አምሽተው እንዲመለከቱ መሆኑ ተነግሯል።

አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ዛሬ ተማሪዎቻቸው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ማልያን ለብሰው እንዲገቡ መፍቀዳቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe