TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.4K photos
1.39K videos
199 files
3.72K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዶላር በቀናት ውስጥ ምን ያህል ጨመረ ?

የውጭ ምንዛሬው በገበያ ይመራል ወይም floating exchange rate ተግባራዊ ይደረጋል ከመባሉ 3 ቀን በፊት የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 57 ብር ከ4838 ሳንቲም ፤ መሸጫ ዋጋው 58 ብር ከ6335 ሳንቲም ነበር።

ሰኞ መግዣ 74 ብር ከ7364 ሳንቲም ፤ መሸጫ 76 ብር ከ2311 ሳንቲም

ማክሰኞ መግዣው 74 ብር ከ7364 ሳንቲም ፤ መሸጫ 76 ብር ከ2311 ሳንቲም

ረቡዕ
#ጥዋት መግዣ 77 ብር ከ1280 ሳንቲም ፤ መሸጫ 78 ብር ከ6706 ሳንቲም // #ከሰዓት ፦ መግዣ 80 ብር ከ0203 ሳንቲም ፤ መሸጫ 81 ብር ከ6207 ሳንቲም

ሐሙስ መግዣው 80 ብር ከ0203 ሳንቲም ፤ መሸጫ 81 ብር ከ6207 ሳንቲም

አርብ መግዣ 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ፤ መሸጫ 85 ብር ከ6201 ሳንቲም

ይህ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሲሆን ዛሬ ላይ በግል ባንኮች አንዱ የአሜሪካ ዶላር መግዣ ዋጋው ከ90 ብር አልፏል ፤ መሸጫውም ከ94 ብር ተሻግሯል።

አጠቃላይ ዶላር ከብር ጋር ያለው ልዩነት እጅግ እየሰፋ ሲሆን አንዱ ዶላር ወደ መቶ እየተጠጋ ነው።

የሌሎች ምንዛሬ ዋጋም እጅግ በፍጥነት እየተተኮሰ ነው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ለነገ አርብ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጨምሯል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ አርብ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል። በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ፤ መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል። ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 101 ብር ከ9101 ሳንቲም ፤ መሸጫው 103 ብር ከ9483 ሆኖ ይውላል ብሏል። ዩሮም ጨምሯል።…
#Update

ዶላር መሸጫው ከ100 ብር አለፈ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ ቅዳሜ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል።

በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 95 ብር ከ6931 ሳንቲም ፤ መሸጫው 101 ብር ከ4347 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል።

ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 116 ብር ከ6881 ሳንቲም ፤ መሸጫው 123 ብር ከ6894 ሆኖ ይውላል ብሏል።

ዩሮም እጅግ በጣም ጨምሯል። መግዣው 104 ብር ከ4107 ሳንቲም መሸጫው 110 ብር ከ6754 ሳንቲም እንደሚሆን አሳውቋል።

የUAE ድርሃም በተመሳሳይ ጨምሯል። አንዱ ድርሃም ነገ በ23 ብር ከ3201 ሳንቲም እየተገዛ ፤ በ24 ብር ከ7194 ሳንቲም ይሸጣል ብሏል።

#TikvahEthiopia #CBE #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዶላር መሸጫው ከ100 ብር አለፈ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ ቅዳሜ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል። በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 95 ብር ከ6931 ሳንቲም ፤ መሸጫው 101 ብር ከ4347 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል። ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 116 ብር ከ6881 ሳንቲም ፤ መሸጫው 123 ብር ከ6894 ሆኖ ይውላል ብሏል። ዩሮም እጅግ በጣም…
#Ethiopia : በዛሬውና ነገ በሚውለው በዶላር ምዛሬ ዋጋ መግዣው ላይ የ12 ብር ልዩነት ፤ በመሸጫው ላይ የ15 ብር ልዩነት ታይቷል።

ዛሬ የነበረው መግዣ 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ሲሆን መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም ነበር።

ነገ ማለትም
#ቅዳሜ ሐምሌ 27 የሚውለው የምንዛሬ ዋጋ መግዣው 95 ብር ከ6931 ሳንቲም ፤ መሸጫው ደግሞ 101 ብር ከ4347 ሳንቲም ነው።

ሌላው በጣም ልዩነት የታየበት ዩሮ ነው ዛሬ 90 ብር ከ5307 ሳንቲም መግዣ ፤ መሸጫው 92 ብር ከ3413 ሳንቲም ሆነ ነበር የዋለው።

በነገው ምንዛሬ ግን የአንዱ ዩሮ መግዣው 104 ብር ከ4107 ሳንቲም ፤ መሸጫው 110 ብር ከ6754 ሳንቲም ሆኖ ይውላል።

ብዙም የምይነገርለት
#የኩዌይት_ዳናር ደግሞ የአንዱ መሸጫ ከ315 ብር አልፏል።

በነገ ምንዛሬ አንዱ ዲናር በ298 ብር ከ8463 ሳንቲም እየተገዛ በ316 ብር ከ7771 ሳንቲም ይሸጣል ተብሏል።

ይህ መረጃ በ ' ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ' ያለውን ምንዛሬ የሚያሳይ ሲሆን የግል ባንኮች ደግሞ ምን ይዘው እንደሚመጡ ጥዋት ይታያል።

#TikvahEthiopia #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia : በዛሬውና ነገ በሚውለው በዶላር ምዛሬ ዋጋ መግዣው ላይ የ12 ብር ልዩነት ፤ በመሸጫው ላይ የ15 ብር ልዩነት ታይቷል። ዛሬ የነበረው መግዣ 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ሲሆን መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም ነበር። ነገ ማለትም #ቅዳሜ ሐምሌ 27 የሚውለው የምንዛሬ ዋጋ መግዣው 95 ብር ከ6931 ሳንቲም ፤ መሸጫው ደግሞ 101 ብር ከ4347 ሳንቲም ነው። ሌላው በጣም ልዩነት የታየበት…
#DailyExchangeRate

ዛሬግል ባንኮች ያለው የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ከላይ ተያይዟል።

ከላይ የ7 የግል ባንኮች ዕለታዊ ምዛሬ ቀርቧል።

ከነዚህ ባንኮች 3ቱ ማለትም ኦሮሚያ፣ አባይ ፣ ዳሽን የዶላር መግዣቸውን በ90 ብር አድርገው በሳንቲም ይለያያሉ መሸጫቸው ግን ልዩነት አለው።

ኦሮሚያ የዶላር መግዣው 102 ብር ከ3848 ሳንቲም ነው ፤ ሲሆን በአባይ 102 ብር ከ9560 ሳንቲም ፤ በዳሽን ደግሞ 100 ብር ከ7768 መሸጫው ነው።

ሌሎቹ ባንኮች አቢሲንያ፣ አዋሽ ፣ ሲዳማና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንኮች መሸጫቸውም መግዣቸውም ይለያያል።

አቢሲንያ ዛሬ ሁለት (ጥዋት እና ከሰዓት) የዶላር ምንዛሬ ነው የተጠቀመው ።

ጥዋት ላይ በ90 ብር ከ0690 ሳንቲም መግዣ መሸጫ ደግሞ 106 ብር ከ7318 ሳንቲም ነበር ፤ አሁን ይፋ ባደረገው የከሰዓት ምንዛሬ ግን መግዣውን ወደ 96 ብር ከ3738 ሳንቲም መሸጫውን 107 ብር ከ9387 ሳንቲም አሳድጎታል።

አዋሽ ዶላር መግዣው 96 ብር ከ3011 ሳንቲም ሲሆን መሸጫው 106 ብር ከ8941  ሳንቲም ነው። ሲዳማ በ96 ብር ከ6500 ገዝቶ በ106 ብር ከ3110 ሳንቲም እንደሚሸጥ ገልጿል። ኦሮሚያ ህብረት ስራ በበኩሉ መፍዣው 97 ብር ከ7329 ሳንቲም ሲሆን መሸጫው 107 ብር ከ5062 ሳንቲም ነው።

ከዶላር ውጭ ያሉ ምንዛሬዎችም በግል ባንኮች ዋጋቸው ጨምሯል። ዝርዝሩን ከላይ ይመልከቱ።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#Ethiopia

° " በርካታ መሰረታዊ ሸቀጥ የያዙ ተሽከርካሪዎች ከጉምሩክ ጣቢያዎች ተንቀሳቅሰዋል " - መንግሥት

° " የዋጋ ጭማሪ ቁጥጥር የአንድ ሰሞን ወሬና ወከና ሆኖ በዛው ጨምሮ እንዳይቀር ተከታተሉልን ፤ከዚህ ቀደም በዘይት የሆነውን አይተናል። ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም " - የ4 ልጆች እናት ሰራተኛ
(ከአ/አ)

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ ተደረገ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ መሰረታዊ በሚባሉ ሸቀጦች ላይ ጭማሪ፣ እንዲሁም " የለም " የማለት ነገር እያጋጠማቸው እንደሆነ ዜጎች ተናግረዋል።

ይህም ሁኔታ እያማረራቸው እንደሆነ ያመለክታሉ።

በተለይም አንዳንድ ምርቶችን ለመግዛት ሲሄዱ ከፍ ያለ ብር ተጨምሮ እንደሚነገራቸው ፤ ከዚህ ባልፈ ደግሞ " አሁን ምርት የለም " እየተባሉ እንደሚጉላሉ በምሬት ይናገራሉ።

መንግሥት በበኩሉ ገበያው እንዳይናጋ የቁጥጥር ስራ እየሰራ እንደሆነ እየገለጸ ነው።

ዋጋ ጨምረው የተገኙ በርካታ ሱቆችን ከማሸግ በተጨማሪ የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠረ ሸቀጥ በገፍ እንዲገባ እየሰራ መሆኑን በተደጋጋሚ እያሳወቀ ይገኛል።

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በማሻሻያው ምክንያት የገበያ መናጋት እንዳይፈጠር እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነ ገልጿል።

ለአብነት በጉምሩክ ጣቢያዎች መሰረታዊ ሸቀጥ ጭነው የቆሙ ተሽከርካሪዎች እንዲወጡ መፍትሄ እየተሰጠ እንደሆነ አመልክቷል።

በተለይ ገንዘብ ሚኒስቴር አዲስ ባወጣው የቫት ክፍያ ምክንያት ቆመው የሚገኙትን እንዲንቀሳቀሱ የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በዛሬው ዕለት ፦
➡️ 101 ከባድ ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢያቸው 44,000 ሌትር ዘይት የያዙ ፤
➡️ 80 ከባድ ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢያቸው 32,000 ኩንታል ስኳር የጫኑ
➡️ 23 ከባድ ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢያቸው 9,200 ኩንታል ሩዝ የጫኑ
➡️ 69 ከባድ ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢያቸው 27,600 ኩንታል የስንዴ ዱቄት የጫኑ በጥቅሉ 273 ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢያቸው የጉምሩክ ስነስርዓት ጨርሰው ወደ መዳረሻቸው እንደተንቀሳቀሱ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በነገው እለትም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው መሰረታዊ ሸቀጥ ከጉምሩክ ጣቢያዎች ወደ መላው ሀገሪቱ አከባቢዎች እንደሚጓጓዝም አሳውቀዋል።

በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች " ዶላር ጨምሯል " በሚል በተለይ መሰረታዊ ምርቶች ላይ የሚታየው ጭማሪ ዜጎችን እያማረረ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረዳት ችሏል።

በተለይ እንደ ዘይት፣ ስኳር፣ ያሉት ምርቶችን አንዳንድ ቦታ ማግኘት እንደማይቻል ሲገኝ ደግሞ ዋጋው ጨምሮ ነው ለሸማች የሚነገረው።

ቃላቸውን የሰጡን የ4 ልጆች እናት ሰራተኛ ፥ " እኔ ደመወዜ አንድም ጊዜ ሳይጨምር ይኸው ዘይት ጨምሮ ጨምሮ በሺህ ቤት ገብቷል። እንዴት መኖር እንዳለብኝ አልገባኝም። ደመወዘኔ ምኑን ከምኑ እንደማደረገውም ጠፍቶብኛል " ሲሉ በሀዘን ተናግረዋል።

" የሆነ ነገር በተፈጠረ ቁጥር የሚጨምረው ዋጋ ቁጥጥሩ የአንድ ሰሞን ወሬና ወከባ ይሆንና ዋጋው በዛው ጨምሮ ጣራ ነክቶ ይቀራል ፤ ይህ ከዚህ በፊት በዘይት አይተነዋል " ብለዋል።

" ነጋዴው አያዝንልን፣ የመንግስት ሰዎች ተገቢና ዘላቂ ቁጥጥር አያደርጉልን፣ መፍትሄ አይሰጡን፣ የሚመጣው ሁሉ ግን እኛ ላይ ያርፋል። እንደ ከዚህ ቀደሙ ዋጋ ጨመረ ተብሎ ቁጥጥሩ የአንድ ሰሞን ግርግር ሆኖ በዛው ዋጋው ተሰቅሎ እንዳይቀር መደረግ ያለበት ይደረግ፤ ኑሮው በጣም ከብዶናል። " ሲሉ አክለዋል።

#Tikvahethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የዛሬው ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ምን ይመስላል ?

(ሐምሌ 29/2016 ዓ/ም)

በኢትዮያ ንግድ ባንክ የዛሬ ምንዛሬ ከቅዳሜው ምንዛሬ ዋጋ የተለየ ነገር የለም።

የአሜሪካ ዶላር መግዣው 95.6931 ፤ መሸጫው 101.4347 ሆኖ ዛሬ ቀጥሏል።

የሌሎች ውጭ ምንዛሬዎች ላይም በቅዳሜው ነው የቀጠለው።

በግል ባንኮች ግን ፉክክሩ ደርቷል።

ለአብነት (
#CASH)፦

አቢሲንያ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 100.2288 ፤ መሸጫው 113.2585
💷 ፓውንድ መግዣው 122.2153 ፤ መሸጫው 138.1033
💶 ዩሮ መግዣው 109.3596 ፤ መሸጫው 123.5763

➡️ ወጋገን ባንክ

💵 ዶላር 101.6434 መግዣ ፤ መሸጫው 113.8406
💷 ፓውንድ መግዣ 130.1137 ፤  መሸጫ 145.7273
💶 ዩሮ መግዣ 110.9031 ፤ መሸጫው 124. 2115

➡️ ዳሸን ባንክ

💵 ዶለር መግዣው 100.9253 ፤ መሸጫው 112.0271
💷 ፓውንድ መግዣ 124.0748 ፤ መሸጫ 137.7230
💶ዩሮ መግዣው 109.4334 ፤ መሸጫው 121.4711
🇸🇦የሳውዲ ሪያል 24.3462 መግዣው ፤ መሸጫው 27.0243
🇦🇪የUAE ድርሃም መግዣው በ24.8666፤ መሸጫው 27.6019

➡️ ንብ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 101.0959 ፤ መሸጫው 111.2055
💷 ፓውንድ መግዣው 129.3521 ፤ መሸጫው 142.2874
💶ዩሮ መግዣው 110.3056 ፤ መሸጫው 121.3362
🇦🇪የUAE ድርሃም መግዣው 27.5263 ፤ መሸጫው 30.2789
🇸🇦የሳዑዲ ሪያል መግዣው 26.9446 ፤ መሸጫው 29.6390

➡️ ኦሮሚያ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 100.8445 ፤ መሸጫው 113.9543
💷 ፓውንድ መግዣው 128.5263 ፤ መሸጫው 145.2347
💶 ዩሮ መግዣው 108.8012 ፤ መሸጫው 122.9453
🇰🇼 የኩዌት ዲናር መግዣው 329.8724 ፤ መሸጫው 372.7558

ፀደይ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 101.0348 ፤ መሸጫው 111.1383
💷 ፓውንድ መግዣው 123.2017 ፤ መሸጫው 135.5219
💶 ዩሮ መግዣው 110.2390 ፤ መሸጫው 121.2629

ብርሃን ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 96.1716 ፤ መሸጫው 110.5973
💷 ፓውንድ መግዣው 118.2188 ፤ መሸጫው 135.9516
💶 ዩሮ መግዣው 104.2746 ፤ መሸጫው 119.9158

ቡና ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 101.0000 ፤ መሸጫው 113.6250
💷 ፓውንድ መግዣው 125.8698 ፤ መሸጫው 138.4568
💶 ዩሮ መግዣው 106.5545 ፤ መሸጫው 117.2100

ፀሐይ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 100.9253 ፤ መሸጫው 115.0548
💷 ፓውንድ መግዣው 130.1137 ፤ መሸጫው 146.3779
💶 ዩሮ መግዣው 112.5666 ፤ መሸጫው 126.6375

#Floatingexchangerate #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ብር ለኢትዮጵያ የ800ሜትር ሴቶች ውድድር ፍፃሜውን ሲያገኝ አትሌት ፅጌ ድጉማ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለሀገራችን ሁለተኛውን የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች። @tikvahethiopia
#TsigeDuguma

ፈረንሳይ ፓሪስ ላይ በ800 ሜትር የሴቶች ፍጻሜ ለሀገሯ ኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኘችው ፅጌ ዱጉማ ከውድድሩ በኃላ " JESUS IS LORD ! " የሚል ጽሁፍ አሳይታለች።

ፅጌ ስሟ ተጽፎ ደረቷ ላይ ከተለጠፈበት ወረቀት የጀርባ ክፍል ላይ ነው ይህን መልዕክት ፅፋ ገብታ ያስተላለፈችው።

የዘንድሮ የፓሪስ ኦሎምፒክ የመክፈቻ ስነስርዓት በክርስቲያኖች ዘንድ ቁጣ ቀስቅሶ እንደነበር ይታወሳል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia @tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ አሶሳ ከተማና ወምበራ ወረዳ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ ችግር ላይ መውደቃቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። በተለይም በወምበራ ወረዳ አገልግሎቱ ከተቋረጠ አራት ወራት እንዳስቆጠረ ገልጸው፣ እስካሁን (ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ) መፍትሄ እንዳልተገኙ ተናግረዋል። ሞባይል በጀነሬተር ቻርጅ ለማድረግ እንኳ በየቀኑ 20 ብር እንደሚያወጡ…
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ የተለያዩ ቦታዎች ኤሌክትሪክ እንደተቋረጠ፤ በተለይም በአንዳንዶቹ አካባቢዎች ከተቋረጠ ከ3 ወራት በላይ እንዳስቆጠረ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቤት ማለታቸው ይታወሳል፡፡

አሁንም ድረስ ችግሩ መቀጠሉን መብራት እንደሌለ ክረምቱን እጅግ እንዳከበደባቸው፣ ህይወታቸውንም ማመሰቃቀሉን እንደቀጠለ ተናግረዋል።

እኛም የወገኖቻችንን ጥያቄ ይዘን ' ይመለከታቸዋል ' የሚባሉትን አነጋግረናል።

ለምን ኃይል ተቋረጠ ? ችግሩን ለመፍታት ምን እየተሰራ ነው ?

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮሚኒኬሽን " እኛ እኮ ኃይል ማቅረብ ነው ከዚያ የዘለለ የስርጭት ሥራ አንሰራም፡፡ ስለዚህም የሥርጭት ሥራን የሚሰሩትን ብትጠይቁ ነው የተሻለ የሚሆነው " አለን።

እሺ ብለን፣  የኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮሚኒኬሽን ጠየቅን ፥ " እኛ አይደለንም የምንሰራው፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ነው፤ ከተማ ውስጥ አይደለም የተቋረጠው የከፍተኛ መስመር ላይ ነው " ሲል መለሰልን።

" ከፍተኛ መስመር ላይ ጉዳት ደርሶ ኃይል እየደረሰን አይደለም ለኛም፡፡ ኃይል ከእነርሱ ነው የምንገዛው። ስለዚህ እነርሱ ኃይል እያደረሱን አይደለም፡፡ ችግሩ ምን እንደሆነ እነርሱ ናቸው ባለቤቶቹ የሚያውቁት " ሲል አክለልን።

እሺ የኤሌክትሪክ ኃይልን እንጠይቅ ብለን ደወልን " ከኛ ጋር የሚገናኝ ነገር ስለሌለው ነው " ተባልን።

ቆይ ታዲያ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥን ማንን ነው የሚመለከተው ? የት ብለን እንጠይቅ አልን ፥  " ኃይል በተለያዬ ምክንያት ሊቆራረጥ ይችላል፡፡ መቋረጥ ሁሉ ወደ እኛ አይመጣም ። አጠቃላይ ክልሉ ላይ አይደለም ችግሩ አለ ያላችሁት የተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ነው፡፡ የተወሰኑ አካባቢዎች ደግሞ ችግር ካለ ከስርጭት ሊሆን እንደሚችል ነው እኛ የምንገምተው። " ብሎናል።

እስከዛሬ ድረስ ችግሩን አልዳሰሳችሁትም ? ወንበራ ላይ ለምሳሌ አራት ወራት ሊሆነው ነው፤ የመተከል ደግሞ አመታት አስቆጥሯል፤ ብለን ጠየቅን ፥ " መተከል ወደ 2 ዓመት ይስለኛል፡፡ እርሱ ላይ እርግጠኛ አይደለሁም " ብሏል።

አጣርታችሁ ምላሽ እስከምትሰጡን እንጠብቅ ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ " ይሄ እኛን የሚመለከት ስላልሆነ ምንም የተለዬ የማጣራው ነገር የለም " የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Ethiopia

" አዲስ የጨዋታ ሕግ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ እየመጣ ያለው " - ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

መንግሥት አሁን ላይ በኢኮኖሚው ውስጥ ካለው እንቅስቃሴ አንጻር " ገቢ ገና አልሰበሰብኩም ፤ ገና አልጀመርኩ " ብሎ ያስባል።

ይህንን ለማስተካከል እና ሀገራዊ ገቢን ለማሳደግ በአዲሱ ሪፎርም ብዙ ስራዎች ይሰራሉ ብሏል።

ገቢ ለማሳደግ በሚሰራው ስራ ግን ተጨማሪ ታክስ አይጣልም፣ የታክስ መጥናኔም አይጨምርም ሲል ገልጿል።

ታዲያ በምን መንገድ ገቢውን ለማሳደግ ነው ያሰበው ?

የገንዝብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ፦

" በየዓመቱ የገቢ መሰብሰብ አቅማችን እየተሻሻለ መምጣቱ የሚታይ ነው። ግን ኢኮኖሚ ውስጥ ካለው አቅም አንጻር ገቢ ገና አልሰበሰብንም / አልጀመርንም የሚል ድምዳሜ ላይ ነው መንግሥት የደረሰው።

ጎረቤት ሀገር አማካይ 15% እና 14% በመሆነበት ሁኔታ እኛ 7% አካባቢ ከሀገራዊ ምርት አንጻር እየሰበሰብን ገቢ እየሰበሰብን አይደለም።

ይህ ሪፎርም አንዱ አንጓ በፊሲካል ፖሊሲው ስር የተቀመጠው ሀገራዊ ገቢ ማሳደግ ነው።

4% GDP በሚቀጥለው ሶስት ዓመት እንጨምራለን ማለት ቀላል ስራ አይደለም ከባድ ነው። በዚህ ዓመት ሰኔ 30 ላይ 527 ቢሊዮን አካባቢ ገቢ አውጀን ከወር በኋላ 851 ቢሊዮን ማወጅ በጣም ከባድ ነው።

ይህንን ስናደርግ ግን ሌሎች ሀገራት እንዳደረጉት ተጨማሪ ታክስ በመጣል፣ ወይም የታክስ ምንጣኔ በመጨመር አይደለም። ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን distortion በማስተካከል ነው ለመጨመር ያሰብነው።

አንድ ምሳሌ ላንሳ፦ የመኪና አስመጪዎች ጋር ገበያ ተኪዶ መኪና ሲገዛ የመኪና ዋጋው 10 ሚሊዮን ከሆነ ገቢዎች ሄደው ደረሰኝ የሚሰጡት ወይ የ1 ሚሊዮን ወይ 2 ሚሊዮን ነው። ስንት እንደሚሸጥ እየታየ ማንም ሰው ገበያው ላይ የሚያውቀውን። ይሄ መስተካከል አለበት።

ከዚህ በፊት በነበረ ሁኔታ እነሱም ችግር ነበረባቸው (መኪና አስመጭዎች) LC የሚሰጣቸው 1000 ዶላር ይሆናል ፤ ሌላው ብር ከኤክስፖርተር ገዝተው ወይ ከጥቁር ገበያ አሰባስበው መኪና ገዝተው ፣ ጅቡቲ አምጥተው ነው የሚሸጡት ይሄን ችግር በመሰረታዊነት ነው ሪፎርሙ የሚቀይረው።

ሁሉ ነገር ግልጽ ይሆናል። ዋጋ እንዲታወቅ እና ግልጽ በሆነ መንገድ እንዲሆን ይደረጋል ሪፎርሙ።

ይህንን መሰል እና በተለያየ ቦታ ያልሰበሰብናቸው ፦

- መርካቶ አካባቢ ያለው የንግድ እንቅስቃሴ ይታወቃል፣

- የንግድ ሂደት ላይ ደረሰኝ መቁረጥ አለመቁረጥ ችግር ይታወቃል

- ጉምሩክ ላይ የ1 ሚሊዮን አይተም አስገብቶ እዛ ቀረጥ ከፍሎም አስገብቶ ገቢዎች ሄዶ ሪፖርት የሚያደርገው ምናልባት የ100 ሺህ እቃ ይሆናል ... ያንን የሚያስታርቅ ዳታውን reconcile የሚያደርግ ሲስተም እየዘረጋን ነው።

እስካሁን ታክስ ሳይከፍል ይከብር የነበረው ባለሃብት አሁን ቶሎ ወደ መስመር መግባት አለበት። ይሄን የሚፈቅድ ነገር አይኖርም።

ጠንካራ የሆነ የ enforcement ስራ ይካሄዳል። እነዚህ የዳታ ጉዳዮችም አሉ። ታክስ ሳይከፍል ሃብት የሚያፈራውን ደግሞ even ያፈራውን ሃብት መውረስ የሚያስችል ለህግ ድጋፍ ተቀምጧል።

ስለዚህ አዲስ የጨዋታ ሕግ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ የመጣ ያለው። ይሄ የታክስ መሰብሰብ አቅማችንን እንድናሳድግ ትልቅ አቅም ይሆነናል። የልማት ትልማችንን ለማሳካት፣ የራሳችንን ወጪ በራሳችን ገቢ ለመሻፈን ያስቀመጥነውን ራዕይ እንድናሳካ እድል ይፈጥርልናል። "

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬም ሜዳሊያ ውስጥ አልገባንም። @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Ethiopia

በ3000 ሜትር መሰናክል ፍጻሜ ወደ ማጠናቀቂያው በጥሩ ኃይል ወደፊት እየመጣ የነበረው እና ለኢትዮጵያ ሜዳሊያ ሊያስገኝ ይችላል ተብሎ የተጠበቀው ለሜቻ ግርማ ወድቆ ውድድሩን ማጠናቀቅ አልቻለም።

ጉዳቱ የከፋ እንዳይሆንበትና ጤናው  ደህና እንዲሆን እንመኛለን።

ሳሙኤል ፍሬው 6ኛ ፤ ጌትነት ዋለ ደግሞ 9ኛ ሆነው ነው የጨረሱት።

ሞሮኮ፣ አሜሪካ እና ኬንያ ሜዳሊያዎቹን ወስደዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia

" በእግሩ እና በጭንቅላቱ ላይ ጉዳት አልደረሰበትም " - የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ ራሱን ከሳተበት በመንቃት መናገር መጀመሩን ሌኪፕ የተሰኘው ታቃዊው የፈረንሳይ ጋዜጣ አስነብቧል።

በአሁን ሰዓት ተጨማሪ የህክምና ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝም ጋዜጣው ገልጿል።

የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ቃል አቀባይ በበኩላቸው ፤ " አትሌት ለሜቻ ግርማ አስፈላጊ የሆነ አፋጣኝ ህክምና ተደርጎለታል " ብለዋል።

ስለ ጉዳቱ ዝርዝርና የህክምና ውጤቱን በተመለከተ ግን በይፋ ምንም የተባለ ነገር የለም።

በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፥ " አትሌት ለሜቻ ግርማ በውድድሩ ላይ በደረሰበት የመውደቅ አደጋ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ በተደረገለት የሲቲ ስካን ምርመራ በእግሩና በጭንቅላቱ ላይ ጉዳት እንዳልደረሰት ከሆስፒታል የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች አረጋግጠዋል " ሲል በይፋ አሳውቋል።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችን ለመክፈት የሥራ ፈቃድ ማመልከቻዎችን መቀበል ጀመረ።

ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ጀምሮ ሥራ ላይ በዋለው የውጭ ምንዛሪ መመሪያ ቁ.01/2016 መሠረት የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮ ለመከፈት የሚፈልጉ የሥራ ፈቃድ ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ብሔራዊ ባንክ ጥሪ አቅርቧል።

በገበያ ላይ ተመሥርተው የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ መሸጥና መግዛት የሚፈልጉ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች እንዲቋቋሙ በተፈቀደው መሠረት የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸው በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚኖሩ እንዲሁም የሌላ ሀገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ምንዛሪ ቢሮ መስፈርቱን አሟልተው ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ሲያገኙ መክፈት ይችላሉ፡፡

የውጭ ምንዛሪ ቢሮ ለመክፈት የሚያስፈልገው የካፒታል መጠን እንዲሁም ሌሎች ለሥራው የሚያስፈልጉ መስፈርቶች ከላይ ተያይዟል።

ካፒታልን በተመለከተ በመመሪያው ላይ የሰፈረው ይህ ነው ፦

Fulfills the minimum capital requirement of Birr 15 million and is able to provide a Security Deposit of Birr 30 million to be placed in a blocked account (which can be interest-earning) at any bank:


ዝቅተኛ 15 ሚሊዮን ብር ካፒታል እና በዝግ በየትኛውም ባንክ የተቀመጠ 30 ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል።

ባንኩ " የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች መቋቋም የውጭ ምንዛሪ ገበያን መሠረት ለማስፋትና ለማጠናከር እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ ለመሸጥም ሆነ ለመግዛት የሚሹ ደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት እንደሚረዳ እሙን ነው " ብሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ፣ " የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች እንዲከፈቱ የሥራ ፈቃድ መስጠታችን የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ለመክፈትና ዘርፉን በቀጣይ ዓመታት ከዓለም ምርጥ ተሞክሮዎችና አሠራሮች ጋር የተመጣጣነ እና ተወዳዳሪ የሆነ ለማድረግ የጀመርነውን አዲስ ምዕራፍ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የጀመረውን ስትራቴጂካዊ የሆነ ለውጥ ከግብ ለማድረስ በቁርጠኝነት መነሣሣቱን የሚያመለከት ነው " ብለውታል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
የደመወዝ ማሻሻያ / ጭማሪ ይፋ ተደርጓል ?

አጭር መልስ ፦ ሀሰት ነው ! ምንም ይፋ የተደረገ ነገር የለም።

እስካሁን የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ / ጭማሪ ዝርዝር መረጃ ይፋ አልተደረገም።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በቴሌግራም ፣ በፌስቡክ እየተዘዋወረ ያለው " የፌዴራል መንግሥት ሲቪል ሰርቫንት ደመወዝ ማሻሻያ " የሚለው መረጃ ምንም ምንጩ የማይታወቅ ነው።

የተሰራጨው የደመወዝ ማሻሻያ ሰንጠረዥ ፤ የፅሁፍ ስህተቶች ጎልተው የሚታዩበት፣ የአጻጻፉ ግድፈት ያለበት፣ የድምር ጭምር ግልጽ እና ቀላል ስህተት ያለበት ነው።

ሌላው ማን ይፋ እንዳደረገው አይታወቀም።

ማህተም አላፈረበትም ፤ መረጃውንም ያወጣው መ/ቤትም አይታወቅም።

እስካሁን በይፋ ለህዝብ የተሰራጨ የደመወዝ ጭማሪ ዝርዝር መረጃ የለም።

በመሆኑንም እየተዘዋወረ ያለው የደመወዝ ጭማሪ ሰንጠረዥም ሆነ የደመወዝ ጭማሪ መረጃ ሀሰተኛ ነው።

መንግሥት በቅርቡ የደመወዝ ጭማሪ እንደሚደረግ ማሳወቁ ይታወሳል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#Ethiopia

በማራቶን ውድድር ላይ " ተጠባባቂ ነህ " ተብሎ የተያዘውና ለውድድሩ የተመረጠ ሌላ አትሌት መጎዳቱን ተከትሎ ሀገሩን ወክሎ የተሳተፈው ጀግናው አትሌት ታምራት ቶላ ለሀገሩ ኢትዮጵያ ወርቅ ማምጣት ብቻ ሳይሆን በሚደንቅ ብቃት የኦሎምፒክ ሪከርድም ጭምር ነው የሰበረው።

ጀግናው አትሌት ታምራት ከአትሌት ገዛኸኝ አበራ በኋላ (ከ24 ዓመታት በኃላ) ነው የመጀመሪያውን የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ለሀገራችን ያስገኘው።

ሌላው አንጋፋው ኢትዮጵያ ሁል ጊዜ በስራው የምታመሰግነው የ42 ዓመቱ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 39ኛ ደረጃ ይዞ እጅግ ከባድ የነበረውን የፓሪስ ማራቶን አጠናቋል።

አትሌት ደሬሳ ገለታም 5ተኛ ደረጃ በመውጣት እጅግ በጣም አበረታችና ተስፋ ሰጪ ውጤት አስመዝግቧል።

ምንም እንኳን ዛሬ በወንዶች ማራቶን የተገኘው ውጤት አስደሳችንና የሚያኮራ ቢሆንም በፓሪስ እየተመዘገበ ያለው ውጤት ኢትዮጵያን የሚመጥናት አይደለም።

በጭቅጭቅና ንትርክ በተሞላው በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ ያገኘችው እስካሁን 3 ሜዳሊያ ብቻ ነው። 1 ወርቅ እና 2 ብር ብቻ።

የአትሌቲክሱ ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶ ያሉ ችግሮች እና ኢትዮጵያን ዝቅ ያደረጉ ነገሮች ሁሉ ተፈትሸው መለወጥ እንዳለባቸው የፓሪስ ኦሎምፒክ በግልጽ አመላክቷል።

ከሚዲያ በዘለለ ስለዚህ ሀገር አትሌቲክስ ሁሉም " የሀገር ክብር ያሳስበኛል " የሚል ቁጭ ብሎ ተነጋግሮ በአስቸኳይ ለውጥ ማምጣት አለበት። እንዲህ ከቀጠለ በዓለም ደረጃ የነበረን ክብር የማናጣበት ምክንያት የለም።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በዚህም ምንም ሜዳሊያ አላገኘንም። የኬንያዋ ኪፕዬጎን ወርቁን ወስዳዋለች። አውስትራሊያ ብር እንዲሁም እንግሊዝ ነሐስ አግኝተዋል። ድርቤ ወልተጂ 4ኛ እንዲሁም ጉዳፍ ፀጋይ 12ኛ በመሆን አጠናቀዋል። @tikvahethiopia
#Kipyegon : የኬንያዋ አትሌት ፌዝ ኪፕዬጎን በሶስት (3) ተከታታይ ኦሎምፒክ በ1500 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ለሀገሯ ገቢ በማድረግ ታሪክ ሰርታለች።

ዛሬ በ 3:51.29 በመግባት የኦሎምፒክ ሪከርድ ሰብራለች።

አትሌቷ የ1500 ሜትር የዓለም ሪከርድ ባለቤትም ናት።

#TikvahEthiopia #WA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

ህወሓት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ፤ " ጥያቄው ሌላ መልሱ ሌላ " ሲል ውድቅ አድርጎታል።

ህወሓት ባወጣው መግለጫ ፥ " የስራ ኃላፊዎቼ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከሚመለከታቸው የፌደራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማካሄድ ሕጋዊ ሰውነታችን እንዲመለስ መግባባት ላይ ተደርሷል " ብሏል።

" በአፍሪካ ህብረት ፓናል ውይይትም ይህ ጉዳይ ተነስቶ ህጋዊ ሰውነቱ መመለስ እንዳለበት ስምምነት ተደርሶበታል " ሲል ገልጿል።

ይህን ተከትሎ " ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ ሰውነታችን ወደነበረበት እንዲመለስልን ብቻ በሀምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጥያቄ አቅርበናል " ብሏል።

ሆኖም " ቦርዱ የፕሪቶሪያውን ስምምነት፣ ከዚህ በፊት በሌሎች የፌደራል ተቋማት የተሰጡትን ውሳኔዎች፣ ሌሎች ህጎችና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተደረሱ መግባባቶች ወደጎን በመተው ጥያቄውን ' በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ' መልሷል " ሲል ገልጿል።

ይህን ተከትሎ ህወሓት " ጥያቄው ሌላ መልሱ ሌላ ሆኗል " በማለት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ " አልቀበልም " ሲል አሳውቋል።

" በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ላይ የተካተቱት ዝርዝር ይዘቶች አዲስ በወጣው ማሻሻያ ህግ መሰረት የተቀመጡና ካቀረብነው ጥያቄ ጋር የማይገናኙ ናቸው " ሲልም አክሏል።

" የቦርዱ ውሳኔ ህጋዊ ሰውነቴን ወደነበረበት እንዲመለስ የቀረበውን ጥያቄ የማይመልስ ፤ የነበሩ ውይይቶችን የሚቃረኑ ዝርዝር ይዘቶች የሚጭንብን በመሆኑ አልተቀበልኩትም " ያለው ህወሓት " ጥያቄያችን እስኪመለስ ድረስ የፓርቲው ሕገ ደንብ በሚፈቅድልን መልኩ ተያያዥ ስራዎችን እናከናውናለን " ብሏል።

የፌደራል መንግስቱም የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመከሩበት ወቅት ፦

- TPLF እና መሰል ፓርቲዎች በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው ሕጋዊ ፓርቲ እንዲሆኑ አዋጅ መሻሻሉ፤
- አቃቤ ህግ ለምርጫ ቦርድ መጻፍ የነበረበትን ማለትም ስራውን ሰርቶ የሚያጣራውን አጣርቶ በሕጋዊ መንገድ እንዲፈቅድላቸው፤
- የአስፈጻሚውን ስራ 100% መሰራቱን፤
- ፓርቲ ለፓርቲ ፤ የመንግሥት ለመንግሥት ውይይቶች ላይ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ እንደተሰጠ፤
- TPLF ምርጫ ቦርድ ሄዶ የሚጠበቅበትን ዶክመንት አሟልቶ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ጉባኤ ማድረግ እንዳለበት ፤ ይህን ባያደርግ ምርጫ ቦርድም ካልተቀበለው፤ TPLFን ሕጋዊ ፓርቲ ካላለው ፦
በምርጫ ሊሳተፍ እንደማይችል ፤
መንግሥትም ሊሆን እንደማይችል ይህ ደግሞ ተመልሶ ጦርነት ውስጥ የሚያስገባ እንደሆነ፤
- ተመልሶ ጦርነት ውስጥ ከመግባት በተበጀው ሕግ ፤ በተደረሰው ስምምነት ህወሓት የቀረውን ጉዳይ አሟልቶ በሕጋዊ መንገድ ጉባኤ አካሂዶ ፓርቲውን መልሶ ወደ ፖለቲካ ስርዓት መመለስ እንዳለበት መግለጻቸው ይታወሳል።

#Ethiopia #TPLF #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የተስፋ አለመቁረጥ ምሳሌ👏

የጀመርኩትን አላቋርጥም ያለችው አትሌት መነጋገሪያ ሆናለች።

ሀገሯ ቡታንን በመወከል የሮጠችው ኪንዛንግ ላሃሞ የተባለች አትሌት በሴቶች የማራቶን ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ካገኘችው አትሌት ሲፋን ሀሰን ከ1 ከሰዓት ከ30 ደቂቃ በኃላ በመግባት ውድድሯን አጠናቃለች።

አትሌቷ ውድድሯን ስትጨርስ በቦታው የነበረው ታዳሚ እጅግ በጋለ ሞራል ተቀብሏታል።

የመጨረሻ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀችው አትሌቷ በፍጹም የጀመርኩትን ውድድር አላቋርጥም ብላ የውድድሩ የወርቅ አሸናፊ ከታወቀ ከ1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ በኃላ ገብታለች።

80ኛ ደረጃ የወጣችው አትሌቷ ውድድሯን ለመጨረስ 3 ሰዓት ከ52 ደቂቃ / 4 ሰዓት ደገማ ወስዶበታል።

በዚህ ሁሉ ፥ የቴሌቪዥን ስርጭት ያልተቋረጠ ሲሆን እያንዳንዷ እንቅስቃሴዋን ሲያሳይ ነበር ፤ በስፍራው የነበረው ተመልካችም የትም ሳይሄድ በክብርና በትልቅ ሞራል ተቀብሏታል።

የቡታኗ አትሌት የጀመረችውን ውድድር እስከመጨረሻ ድረስ ያለ ማቋረጥ ተፋልማ በመጨረሷ በበርካቶች " የተስፋ አለመቁረጥ ምሳሌ " ተደርጋ ተወስዳለች።

ሁላችንም በምንም አይነት ሁኔታ ቢሆን የጀመርነውን መጨረስ፣ ለቆምንለት ዓላማ እስከመጨረሻው መሄድ እንዳለብን ያስተማረ ነው።

" እኔ አልችልም " ብሎ ፣ ተስፋም ቆርጦ አለመቆም እንጂ በተንቀሳቀስን ቁጥር ግባችን ጋር መድረሳችን የማይቀር ነው።

#TikvahEthiopia

ቪድዮ፦ ከሱፐር ስፖርት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Bangladesh : ለ15 ዓመታት ያህል ባንግላዴሽን የመሩት ሺህክ ሀሲና የተነሳባቸውን ጠንካራ ተቃውሞ ተከትሎ ሀገር ጥለው  ጠፍተዋል። የተቆጡ ተቃዋሚዎችም ወደ ሚኖሩበት ቤተመንግስት በኃይል ሰብረው በመግባት ወረው በመኖሪያ ቤታቸው እንዳሻቸው እየፈነጩበት ነው። ግማሹ አልጋ ላይ ፣ ግማሹ በየክፍሉ እየዞረ እቃቸውን ይፈትሻል፣ ግማሹ ይጨፍራል። ከመንግሥት የስራ ኮታ ስርዓት ጋር በተያያዘ ተማሪዎች…
#Bangladesh

ተማሪዎች በቀሰቀሱትና በኃላም ሌላውም ዜጋ በተቀላቀለው የመንግሥት የስራ ኮታ ተቃውሞ ምክንያት ስልጣናቸውን ለቀው ከሀገር ወጥተው የሄዱት የቀድሞ የባንግላዴሽ ጠ/ሚኒስትር ሼኪህ ሀሲና ከስልጣን እንዲወርዱ " የአሜሪካም እጅ አለበት " ማለታቸውን ' ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ' አስነብቧል።

ልጃቸው ግን " ውሸት ነው " ሲል አጣጥሏል።

ሀሲና አሁን ላይ ሀገራቸውን ጥለው ህንድ ነው ያሉት።

እሳቸው ናቸው የተናገሩት ብሎ ' ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ' እንዳስነበበው ሀሲና ፤ " የደም መፋሰስ እንዳይፈጠርና እሱን ላለማየት ስልንነው ስልጣን የለቀቅኩት " ብለዋል።

" በተማሪዎች እሬሳ ላይ ተረማምደው ስልጣን መያዝ ፈልገው ነበር ግን እኔ ያንን አልፈቀድኩም፤ በዚህም የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣኔን ለቅቂያለሁ " ሲሉ መግለጻቸውን አስነብቧል።

ሀሲና " የሴንት ማርቲን ደሴትን ሉዓላዊነት አሳልፌ ብሰጥና ፤ አሜሪካ የቤይ ኦፍ ቤንጋልን እድትቆጣጠር ብፈቅድ ኖሮ በስልጣን ላይ እቆይ ነበር " ማለታቸውን ገልጿል።

አሜሪካ ተቃውሞ ማቀናበሯንና ይህን ያደረገችው የአገዛዝ ለውጥ አድርጋ ፍላጎቷን ለማሟላት እንደሆነ እንደጠቆሙ ነው ' ታይም ኦፍ ኢንዲያ ' ያስነብበው።

አሁን ላይ አሜሪካ የሚኖረው ልጃቸው ሳጂብ ዋዜድ ፤ " እናቴ ከስልጣን መልቀቋን በተመለከተ የሰጠችው መግለጫ ተብሎ በጋዜጣ ታትሞ የወጣው ሙሉ በሙሉ ውሸትና የተቀናበረ ነው፤ ከራሷ እንዳረጋገጥኩት ዳካን ከመልቀቋ በፊትና በኃላ ምንም መግለጫ እንዳልሰጠች ነው " ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ሀሲና ባንግላዴሽ ፓርላማ " አሜሪካ በሀገሪቱ የአገዛዝ ለውጥ ለማድረግ እየሞከረች ነው " በማለት አሜሪካንን ወንጅለው ነበር።

ሴንት ማርቲን ደሴት ከ1971 (እ.አ.አ) አንስቶ በባንግላዴሽን ፖለቲካ ትልቅ ተጽእኖ ያላት ትንሽዬ ግን በጣም ወሳኝ ደሴት ናት።

ቦታው ከቤይ ኦፍ ቤንጋል ያለው ርቀት እንዲሁም ከማይናማር ጋር ያለው የባህር ወሰን በስፍራው ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ፍላጎት እንዲኖር አድርጓል።

' ቤይ ኦፍ ቤንጋል ' ን ለመቆጣጠር እንዲሁም የህንድ ውቂያኖስ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ጭምር ለመከታተል ፤ ስትራቴጂክ የሆነ ስፍራ ነው።

በዚህም በቀጠናው ኃይሏን ለማጠናከር የተሟላ ቁጥጥር እንዲኖራትና በቻይና ላይም የበላይነት ለመውሰድ አሜሪካ ወታደራዊ ቤዟን ለማቋቋም እንደምትፈልግ ይናገራል።

አሜሪካ ግን ከበርካታ ዓመታት በፊት ይህንን ቦታ እንደማትፈልገው እና በስፍራው ወታደራዊ ቤዝ እንዲኖርት እቅድ እንደሌላት አሳውቃ ነበር።

#TikvahEthiopia #TimesofIndia

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

" ከዛሬ ጀምሮ ከአያት አደባባይ ወደ መገናኛ ፤ ከመገናኛ ወደ አያት አደባባይ የተቃራኒ ጉዞ ተከልክሏል " - የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ

በአዲስ አበባ፣ ከአያት አደባባይ ወደ መገናኛ ፤ ከመገናኛ ወደ አያት አደባባይ ድረስ በስራ የመውጫ እና የመግቢያ ሰዓቶች ላይ ይፈጠር የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ በሚል በጊዜያዊ መፍትሄነት ከአያት አደባባይ እስከ ሴንቸሪ ሞል በሁለቱም መስመሮች የተቃራኒ ጉዞ ተፈቅዶ ነበር።

ነገር ግን መጨናነቁን ይፈጥር የነበረው የሳዕሊተ ምህረት አደባባይ በመቀየሩ ከዛሬ ነሐሴ 6 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በሁለቱም መስመሮች የተቃራኒ ጉዞ መከልከሉን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳውቋል።

አሽከርካሪዎች ይሄን ተገንዝበው የመደበኛ የጉዞ መስመሮችን ብቻ እንዲጠቀሙ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

#AddisAbaba #TMA

#TikvahEthiopia
@TikvahEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ድርጅቱ ጉባኤውን እንዳያካሂድ እንቅፋት የሚሆን ከድርጅቱ የተፈለፈለ ከፍተኛ አመራር አለ " - ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችን ለሁለት የከፈለውና በብሔራዊ ምርጫ ቦርድም እውቅና የተነፈገው የህወሓት 14ኛ ጉባኤ መክፈቻ ዛሬ ተደርጓል። የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በመክፈቻው ባሰሙት ንግግር ምን አሉ ? ሊቀመንበሩ " ድርጅቱ ህጋዊ…
#TPLF

' ህወሓት ' ውስጥ እየሆነ ያለው ምንድነው ?

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከትግራዩ ጦርነት በፊት እንደ ህጋዊ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ስር ተመዝግቦ ይንቀሳቀስ ነበር።

ነገር ግን  ቦርዱ ፓርቲው " ኃይልን መሰረተ ያደረገ የአመጽ ተግባር ላይ ተሰማርቷል " በሚል ሰርዞታል።

የተወካዮች ምክር ቤትም ፓርቲውን " ሽብርተኛ ድርጅት " ሲልም ፈርጆት ነበር።

ደም አፋሳሹና አስከፊው ጦርነት እንዲያበቃ ፕሪቶሪያ ላይ ስምምነት ሲፈረም አንዱ ፈራሚ ይኸው ህወሓት ነበር።

በስምምነቱ ላይ ፓርቲው የተለጠፈበት የሽብርተኝነት ፍረጃ እንደሚፋቅ በግልጽ ሰፍሯል።

በዚህ መሰረት ከወራት በፊት ድርጅቱ ከሽብርተኛነት ተሰርዟል።

ነገር ግን የምዝገባው ጉዳይ ሌላ ነው።

ክፍፍሉ እና ' የቀደመ ህጋዊ ሰውነት ይመለስልኝ ' ጥያቄ ምንድነው ?

ህወሓት የፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኃላ በውስጥ የኃይል ሽኩቻ ላይ ነበር።

አመራሮቹም ቀስ በቀሰ በሂደት የለየለት መከፋፈል ውስጥ ገብተዋል።

ምንም እንኳን በይፋ ባይወጣም ግልጽ ክፍፍል ይታይ ነበር።

ይህም በአቶ ጌታቸው ረዳ እና በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ቡድኖች መካከል ነው።

ባለፉት ወራት እጅግ በርከታ ስብሰባዎች ተደርገው የነበረ ቢሆንም ልዩነቶች ግን እየሰፉ እንጂ እየጠበቡ ሲሄዱ አልታዩም።

ከአንድነት ይልቅ መከፋፈሉ እና ሽኩቻው ጨምሮ ታይቷል።

በዚህ ሂደት ላይ ግን ህወሓት ፥ " ህጋዊ ሰውነታችን ወደነበረበት እንዲመለስ " የሚል ጥያቄ ለምርጫ ቦርድ ይቀርባል (ሚያዚያ ወር ላይ)።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግን አንድ በአመጽ ተግባር ላይ ተሳትፎ የሰረዘውን ፓርቲ የቀደመው ህልውና መመለስ የሚያስችልበት የሕግ ድንጋጌ የለውም። በዚህም ጥያቄውን ሳይቀበለው ይቀራል።

ህወሓትንና ሌሎችንም ለመመዝገብ በሚል አዋጅ እስኪሻሻል ተደርጓል።

ህወሓትም ዳግም " ህጋዊው ሰውነቴ ወደነበረበት ይመለስ " ሲል በሊቀመንበሩ ዶ/ር ደብረጽዮን በኩል ጥያቄ ያቀርባል።

በእርግጥ ሁሉም አመራሮች " የነበረው ህልውና ይመለስ " የሚለው ላይ ልዩነት የላቸውም።

የተሻሻለው አዋጅም ግን በአመጽ ተሳትፎ ለተሰረዘ ፓርቲ የቀደመ ህልውናውን መመለስ የሚያስችል የህግ ድንጋጌ አልያዘም።

ይህን ተከትሎም ቦርዱ " #በልዩ_ሁኔታ " በሚል ፓርቲውን መዝግቦታል።

ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልም ወደ አዲስ አበባ ሄደው ከምርጫ ቦርድ የተሰጠውን " በልዩ ሁኔታ " መመዝገቡን የሚገልጽ ህጋዊ የሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ፈርመው ወስደው መቐለ ሄደዋል።

ከዚህ በኃላ መቐለ ሄደው በሰጡት መግለጫ " እኛ ይሄን አንቀበልም ፤ የጠየቅነው ሌላ የተሰጠን ሌላ ነው " ሲሉ መግለጫ ሰጥተዋል።

" እኛ እንደዛ አልነበረም የተነጋገርነው ፤ የተባልነውም እንደዛ አልነበረም " የሚል ነገር አንስተዋል።

የእውቅና ምስክር ወረቀቱን ፈርመው ከወሰዱ በኃላ  " ከምቀደው ብዬ ነው ይዤው የመጣሁት " ብለዋል። ምዝገበውን እንደማይቀበሉት እና እንደተመዘገቡም እንደማይቆጠር ነው የገለጹት።

እነ አቶ ጌታቸው ረዳ በምስክር ወረቀቱ ጉዳይ ምንድነው አቋማቸው ?

- በምዝገባ ጉዳይ ለምርጫ ቦርድ የተላከው ደብዳቤ ማእከላዊ ኮሚቴ የማያውቀው በግለሰቦች የተላከ ነው።

- የተወሰኑ ግለሰቦች ናቸው ከድርጅቱ አሰራር ውጪ በቡድን በመሆን የፈረሙት እንጂ እኛ ለምዝገባ ብለን የፈረምነው ማንኛውም ሰነድ የለም።

- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ' ህወሓት ' ን አስመልክቶ ለተወሰኑ ግለሰቦች የሰጠው እውቅና #የተጭበረበረ በመሆኑ ዳግም ሊያጤነው ይገባል ... የሚል ነው።

ጉባኤው ?

የህወሓት ፅህፈ ቤት እና ማህተምን የተቆጣጠረው የነ ዶ/ር ደብረጾን ገ/ሚካኤል ቡድን ክፍፍሉ እና ከምርጫ ቦርድ ጋር ያለው ልዩነት ሳይፈታ ለጉባኤ ዝግጅት ሲያደርግ ነበር።

በጣም አጭር ጊዜ ውስጥም የጉባኤ ተሳታፊ ለይቶ ጉባኤ ማካሄድ ጀምሯል።

ይህ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከተው አንዱ የህወሓት ቁጥጥር ኮሚሽን " አካሄዱን የጠበቀ አይደለም " በማለት ራሱን አግልሏል።

አቶ ጌታቸው ያሉበት 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት " እኛ የለንበትም " ብለው ራሳቸውን አግልለዋል።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ደግሞ ባለው አሰራር አንድ ህጋዊ ፓርቲ ጠቅላላይ ጉባኤ ከማድረጉ ከ21 ቀናት በፊት ለቦርዱ ማሳወቅ እንዳለበት ይገልጻል።

በመሆኑንም ፤ የቦርዱን አሰራር ያልተከተለ ፣ ቦርዱ ባልተገኘበት የሚደረግ ጉባኤ ላይ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን እውቅና እንደማይሰጥ አሳውቋል።

ህወሓት ግን መቐለ ላይ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና በርካታ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በሌሉበት ጉባኤ እያካሄደ ነው።

ጉባኤ ማድረግ ምድነው ጥቅሙ ?

አንድን ጉባኤ ህጋዊ የሚያደርገው በሚመለከተው አካል እውቅና አግኝቶ አሰራሩን ተከትሎ ሲካሄድ ነው።

የፓርቲዎችን ጉዳይ የሚመለከተው ምርጫ ቦርድ በመሆኑ " አካሄዱ ትክክል አይደለም። እውቅናም አልሰጥም " ባለበት ሁኔታ ጉባኤ ቢደረግ ተሰብስቦ ከመበተን ውጭ ውጤት የለውም የሚሉ አሉ።

ዶ/ር ደብረጽዮን ግን ፥ " ህወሓትን አድኖ ህዝብ ከጥፋት መታደግ የጉባኤው ዋነኛ አላማ ነው " ብለዋል።

" የድርጅቱና የህዝቡ የተሟላ ድህንነት ማረጋገጥ በሚችል መልኩ በዴሞክራሲያዊ ውይይትና ክርክር ብቃት ያላቸው አመራሮች መምረጥ ይገባል "ም ብለዋል።

" የአሁኑ ጉባኤ ለድርጅቱ የሞት የሽረት ጉዳይ ነው " እንደሆነ ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው ፍጹም መግባባት ሳይሰረግበት እየተካሄደ ያለ መሆኑን ያነሳሉ።

የጉባኤው ውጤት ምን ሊሆን ይችላል ?

ጉባኤ ማድረግ ምን ችግር ላይፈጥር ይችላል።

ጉባኤውን ተከትሎ የሚተላለፉ ውሳኔዎች እውቅና ስለማያገኙ ሌላ ጭቅጭቅ እና ልዩነት መፍጠሩ ይጠበቃል።

ጉባኤው ላይ በእነ አቶ ጌታቸው እና ቡድናቸው ምትክ ሌሎች የመምረጥ ነገር ካለ ይበልጥ ነገሩ ይከራል።

አቶ ጌታቸውም " #ይቃወሙናል " የሚሏቸውን አመራሮች ለማስወገድ የሚደረግ ጉባኤ እንደሆነ ተናግረዋል።

ጉባኤው የሚያመጣው የግጭት ስጋት አለ ?

በትግራይ ፖለቲካውን የሚከታተሉ አካላት አሁን ላይ በተጨባጭ የሚታይ የግጭት ስጋት የለም ባይ ናቸው።

ጉባኤውን ተከትሎ ምርጫ ተደርጎ ፤ አመራሮችን የማስወገድ ነገር ከመጣ ግን በሂደት ጭቅጭቁና ንትርኩ መጨመሩ እንደማይቀር ያነሳሉ።

በፓርቲው ጉዳይ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ያለው ልዩነት የመስፋት እድል ሊኖረው እንደሚችል ይገልጻሉ።

በፓርቲው ያሉት አንጃዎች የራሳቸው ደጋፊ ስላላቸው ልዩነታቸው በሰፋ ቁጥጥር በሂደት ወደ ኃይል እርምጃ እንዳይሄዱ ያሰጋል።

አሁን ላይ ግን በተጨባጭ የሚታይ የግጭት ስጋት ግን የለም።

#ትግራይ : ትግራይ ከአስከፊው ጦርነቱ በቅጡ ሳታገግም ፣ ብዙ ተጎጂ ባለበት ፣ ገና ተጠያቂነት ባልተረጋገጠበት ፣ ብዙ እገዛ የሚፈልግ ባለባት ፣ ተፈናቃይ ተሟልቶ ባልተመለሰበት ... ሌሎችም ብዙ ስራዎች ባልተሰሩበት ይህ የጉባኤ እና ምዝገባ ጉዳይ የህዝብ አጀንዳ እንዲሆን መደረጉ በርካቶችን ያስቆጣ ሆኗል። ይህ ጉዳይ ቀስ በቀስ በሂደት መሄድ እንደሚችልና መቅደም ያለባቸው ህዝባዊ ጉዳዮች መቅደም እንደነበረባቸው የሚያነሱ ብዙዎች ናቸው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia