TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ደላሎችም ይሁኑ ' ወደ ውጭ ሀገር እንልካችሏለን ' የሚሉ ኤጀንሲዎች የት እና ለምን ስራ እንደሚልኳቹ በደንብ አጣሩ !! ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ወጣቶችን " ለብሩህ ተስፋ፣ ለጥሩ ህይወት ጠቀም ያለ ገንዘብ የሚያስገኝ ስራ በታይላንድ አለ " በማለት ወጣቶቻችንን ለከፋ የስቃይ ህይወት የሚዳርጉ ሰዎች አሉ። አንዳንዶቹ ጭራሽ ወደ አሜሪካ ፣ ካንዳ እና አውሮፓ ሀገራት ነው የምንልካችሁ…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#Myanmar

ይህ የ ' DW ዶክመንተሪ ' #በማይናማርና #ታይላንድ ድንበር ባሉ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ሰዎችን ከተለያዩ የዓለም ሀገራት በማዘዋወር ስለሚሰሩ ዓለም አቀፍ የኦንላይን ማጭበርበር (scam) ስራዎችን በግልጽ የሚያሳይ ነው።

የሰው አዘዋዋሪዎች ሰዎችን የሚያዘዋውሩት በቅድሚያ ታይላንድ / የአውሮፓ ሀገራት እንደሆነ በመግለጽ እና ጠቀም ያለ ገቢ እንደሚገኝ በመንገር ጭምር ነው በኋላ የሚሰራው ማጭበርበር (Online Scam) ነው።

ቦታዎቹ ብዙ ናቸው።

ልክ እንደ ካምፕ አይነት ሲሆኑ ከነዛም ውስጥ ብዙ እንግልት እና ስቃይ የሚደርስባቸው አሉ።

ገና እንደሄዱ ስልካቸውን የሚቀሙ ፣ ፍጹም ኢሰብዓዊ አያይዝ የሚያዙ፣ ካልሰሩ የሚደበደቡ ፣ ስቃይ የሚፈጸምባቸው አሉ።

ከነዚህ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ይገኙበታል።

አንድ ለቲክቫህ መልዕክቱን የላከ ወጣት በደረሰበት ድብደባ ለወራት ያህል በክራንች ለመሄድ መገደዱን ጠቁሟል።

በሌላ በኩል በዛው በማይናማር በስልክ ያነጋገርናቸው አንዳንድ ወጣቶች በማይናማርና ታይላንድ ድንበር የሚፈጸሙ ጉዳዮች ከአንድ ቦታ ሌላ ቦታ እንደሚለያዩ አስረድተው እነሱ በሚኖሩበት ምንም አይነት ስቃይ ይሁን ችግር ደርሶባቸው እንደማያውቅ ተናግረዋል።

ስልክም ሆነ ሌሎች አይነት ኤሌክትሮኒክስ ነገሮችን ተከልክለው እንደማያውቁ አስረድተዋል።

አሁንም የውጭ ፕሮሰስ ላይ ያላችሁ የት ሀገር ፣ በምን ስራ ዘርፍ እንደምትሄዱ በደንብ ጠይቁ።

በደላሎች ወደ ካናዳ ፣ አሜሪካ ፣ አውሮፓ ፣ ታይላንድ ጠቀም ያለ ገንዘብ ለሚያስገኝ ስራ እየተባሉ ብዙ ወጣቶች ዓለም አቀፍ የሆነ የኦንላይን የማጭበርበር (online scam) ስራ ወደ ሚሰራባቸው የማይናማር የተለያዩ አካባቢዎች ነው የሚወሰዱት።

ስቃይ ላይ ነን ስላሉት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ጉዳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ለማነጋገር ጥረት ያደርጋል።

ተጨማሪ ዶክመንተሪዎች እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች ፦
Al Jazeera - Rebels uncover scam centers in Myanmar
DW Shift - Scam Factories in Myanmar
Sea Today - Indonesian Scam Victims
WION - 900 scam factory Chinese Victims rescued near Myanmar
CNN News18 - Mynamar Cyber Crimes
CCTV - Major Criminal Suspects Transferred to China from Myanamar

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Myanmar ይህ የ ' DW ዶክመንተሪ ' #በማይናማርና #ታይላንድ ድንበር ባሉ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ሰዎችን ከተለያዩ የዓለም ሀገራት በማዘዋወር ስለሚሰሩ ዓለም አቀፍ የኦንላይን ማጭበርበር (scam) ስራዎችን በግልጽ የሚያሳይ ነው። የሰው አዘዋዋሪዎች ሰዎችን የሚያዘዋውሩት በቅድሚያ ታይላንድ / የአውሮፓ ሀገራት እንደሆነ በመግለጽ እና ጠቀም ያለ ገቢ እንደሚገኝ በመንገር ጭምር ነው በኋላ የሚሰራው…
" እንደ ባሪያ ነው የምንታየው ፤ እባካችሁ ጭሁልን !! " - በማይናማር የሚገኙ ወጣቶች

ማይናማር እና ታይላንድ ድንበር ላይ ከሚገኙ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የበየነ መረብ ማጭበርበር (Online Scam) ተግባራት ከሚፈጸምባቸው አንዳንድ ቦታዎች ቲክቫህ ኢትዮጵያ መልዕክቶችን በቴሌግራም እየተቀበለ ይገኛል።

እነዚህ ቦታዎች ላይ በርካታ የሀገራችን ወጣቶች ያሉ ሲሆን " ታይላንድ እንልካችኋለን " በሚል የደላሎች ማታለያ ተታለው ነው በማይናማር የበየነመረብ ማጭበርበር (Online Scam) ላይ ተሰማርተው የሚገኙት።

ስሜን አይገለጽ ያለ በስፍራው ያለ ወጣት ፦

" ለምን ስራ አላመጣችሁም ? ለምን አልሰራችሁም (የኦንላይን ማጭበርበር) ተብሎ ሰው ይታሰራል።

እስር ቤት ይጣላል።

እኔ ለምሳሌ 5 ቀን ሙሉ እስር ቤት አድሪያለሁ። ያለ ምንም ምክንያት ።

ሽንት ቤት መሄድ የለም፤ ራስህ ላይ ነው የምትሸናው ፣ውሃ በግድ ያስጠጣሉ እምቢ ማለት አይቻልም ፣ የቁም እስር ነው ፣ መጮህ አይቻልም አፋችን ውስጥ ጨርቅ ይከታሉ በስነ ልቦና ሊጎዱን ነው ይህን ሁሉ የሚያደርጉት።

እንደ ሰው አንታይም። በስነልቦና በጣም እየተጎዳን ነው። በሰንሰለት ይገርፋሉ፣ በኤሌክትሪክ ሾክ ያደርጋሉ፣ መሬት ውስጥ በሚቅበር ሽቦ ይገርፋሉ እራቁት።

ለዚህ ችግር አንደኛው መጠየቅ ያለበት የታይላንድ መንግስት ነው። የሱን ቪዛ መተን ነው ወደዚህ የመጣነው። አሳልፈው የሚሰጡን ከታይላንድ ነው።

ከባንኮክ ከኤርፖርት መጥተው በመኪና ሲወስዱን ያውቃል መንግስት ። የምንሰራበት ሲም ካርድ የታይላንድ ነው። ዓለም ሁሉ እየተጭበረበረ ያለበትን ስራ በታይላንድ ሲም ነው የሚሰራው።

እዚህ በካምፕ ላይ ያለው ቁሳቁስ ከታይላንድ ነው የሚመጣው ፣ ህንጻ የሚሰራበት እቃ ከታይላንድ ነው፣ መብራት እና ውሃም ከታይላንድ ነው፣ አልጋው ምኑ የታይላንድ ነው።

ቻይናም ስለ ሁኔታው የምታውቅ ሀገር ስለሆነች ማናገር ይገባል። በቻይናውያን ድጋፍ የተሰመረተ ኩባንያ ነው ያለው።

መጠየቅ ያለባቸው ታይላንድ እና ቻይና ናቸው።

ማይናማር ለራሷ ላለፉት በርካታ ዓመታት እስካሁን ድረስ በእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ናት።

የኢትዮጵያ መንግስት ታይላንድን እና ቻይናን ይጠይቅልን።

የኢትዮጵያን ዜጎች ነው እንደ እቃ ነው የሚጠቀሙት። ቁሳቁስ ሲመጣ እንኳን የሚያሸክሙን እኛን ነው። እንደ አህያ ነው የሚጠቀሙን። ክትባት ሲመጣ ለኛ አይሰጥም። ጥቅም የለንም። እንደባሪያ ነው የምንታየው። እየኖርን አይደለም። ተስፋም የለንም።

እባካችሁ ጭሁልን ! " ብሏል።

ሪፖርት፦ አንድ የተመለከትነው ሪፖርት በማይናማር ፣ ካምቦዲያ፣ ላኦስ እስከ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ የኦንላይን ማጭበርበር (Scam) ላይ የተሰማሩ ሰዎች አሉ። ማፊያዎች በሚመሯቸው በነዚህ አካላት በየአመቱ እስከ 43.8 ቢሊዮን ዶላር ድረስ ይሰርቃሉ። በማጨበርበር ስራው ላይ የተሰማሩት ሰዎች እራሳቸውም የችግሩ የመጀመሪያ ሰለባዎች ናቸው።

#ጥንቃቄ፦ " እጅግ ጠቀም ላለ ስራ ነው " እየተባለ ወደ ታይላንድ የምትሄዱ ጥንቃቄ አድርጉ። ስራው ምንድነው በሉ ፣ ከታይላንድ ውጭ እንደማትወሰዱ እርግጠኛ ሁኑ ፣ ዶክመንት ተፈራረሙ የሚልኳቹን ሰዎች ማንነት አጣሩ፣ ኤጀንሲ ይሁን ደለላ ማስረጃቸውን ሁሉ ያዙ።

ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይደረስ !

#TikvahEthiopia
#Myanmar

@tikvahethiopia