TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጾመ_ፍልሰታ

የ2014 ዓ.ም ጾመ ፍልሰታን በተመለከተ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትከዋሽንግተን ዲሲ፤ ሰሜን አሜሪካ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው የተወሰደ ፦

" ሁላችንም እንደምንገነዘበው በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት ፍጹም ሰላም ያላት ሀገር እንድትኖረው ነው፤ ይህ ትክክለኛ ፍላጎት ነው፡፡ ይሁንና ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉም ነገር ስለማይሆን ፍጹም ሰላም በሀገር ሰፍኖ ሕዝባችን እግዚአብሔር በሰጠው ምድር በፍቅር፣ በአንድነት በነጻነትና በእኩልነት እንዲኖር ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ በዚህ ወቅት የቅድስት ድንግል ማርያምን ጸሎትና ስእለት ተማኅፅኖና አስተበቊዖት አጋዥ አድርገን በልዩ ሱባዔ ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ በንሥሐ፣ በጾም፣ በጸሎት፣ ነዳያንን በመርዳትና ቅዱስ ቊርባንን በመቀበል እሱን መማፀን ይኖርብናል፡፡

... በሀገራችን የተከሠቱት ያላስፈላጊ ግጭቶችን በድርድር ለመፍታት እየተሞከሩ ያሉ አንዳንድ የሰላምና የውይይት ድምፆች ተስፋ ሰጪ ስለሆኑ ሥር ሰደው፣ በተግባር ተተርጉመው፣ ለተጐዳው ሕዝባችን መጠገኛ ይሆኑ ዘንድ፣ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ በዚህ ዙርያ በሱባዔው ወቅት ወደ እግዚአብሔር አቤት በማለትና ሂደቱን በመደገፍ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ፣ መንግሥትም ሆነ የዓለም አቀፉ ማኅበረ ሰብ በዚህ በጎ ሐሳብ እንዲገፉበትና ሕዝባችንንና ሀገራችንን ከጥፋት እንዲታደጉ አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ጾሙን የሰላም፣ የሥርየት፣የፍቅር፣ የአንድነት ጾም ያድርግልን።

ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ጾመ_ፍልሰታ

ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶለካውያን የ2014 ዓ.ም የፍልሰታ ፆም መግቢያን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው የተወሰደ ፦

" ይህንን የፍልሠታ ጾም ስንጾም እና ሱባኤ ስንገባ ምንም እንኳን ዛሬም ቢሆን በብዙ ጨለማ ተከብበን የዲያብሎስን ውጊያ እየተጋፈጥንም ቢሆን እንደ ክርስቲያንነታችን በጽኑ እምነት እና ተስፋ ተሞልተን ነው። ምክንያቱም ምንም ያኽል ቢጨላልም ንጋት አይቀርምና። ሞት የመጨረሻ ቃል የለውምና። ትንሣኤ መሆኑ አይቀርምና።

ስለሆነም እያንዳንዳችን በልባችን በዚህ በጾም ወቅት ከእኔ በላይ የተቸገረ የሚሰቃይ፣ የተፈናቀለ፣ የተሰደድ፣ በጦርነት አውድ ዘወትር በስጋት እና ጭንቀት የሚኖር አለ በማለት የወንድማዊ የርህራሄ ፣ የአለኝታነት እና የቅርበት መንፈስ እየተሰማን ሊሆን ይገባል።

እነዚህንም የጾምና የሱባኤ ቀናት በተጋድሎም በማሳለፍ ለበዓለ ፍልሰታዋ በሰላም ለመድረስ ያብቃን። አምላክ የተቀደሰ የተባረከ ጾመ ፍልሰታ ለመላው ካቶሊካውያን እና በጎ ፈቃድ ላላቸው ሁሉ ያድርግልን እያልኩ የደስታ ምንጭ የሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለእኛ ለልጆቿ እና ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ትለምንልን፡፡ አሜን!

ቸሩ አምላካችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ኢትዮጵያን ይባርካት፡፡ "

ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባኤ ፕረዝደንት

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia