TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ታህሳስ 7 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት አዲስ አበባ ቦሌ ኤድና ሞል አካባቢ አንድ ሰው በጥይት ተመቶ ተገድሏል። ድርጊቱ የተፈፀመው ቦሌ ከኤድናሞል ወረድ ብሎ በሚገኝ አንድ የመዝናኛ ስፍራ አካባቢ ነው። ምሽት አራት ሰዓት ገደማ ሟች #አባተ_አበበ በአንድ #መሳሪያ_በታጠቀ ግለሰብ በጥይት ተመቶ መገደሉ ታውቋል። አባተ አበበ ተወልዶ ባደገበት ፣ በሚኖርበት  አካባቢ እንዲሁም ደግሞ በስራ…
#ግድያ #የፖሊስ_ምላሽ

" ፖሊስ ሥራውን እየሰራ ነው። ግልጽ ማድረግ በሚገባን ሰዓት ላይ ግልጽ እናደርጋለን " - ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ

አቶ አባተ አበበ የተባሉ ግለሰብ ታህሳስ 7 ቀን 2016 ዓ/ም አዲስ አበባ ቦሌ ኤድናሞል አካባቢ ዝቅ ብሎ በሚገኝ መዝናኛ 'በጥይት ተመትቶ ተገደለ' መባሉን በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጠይቋል።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " ፖሊስ ሥራ እየሰራ ነው። ግልጽ ማድረግ በሚገባን ሰዓት ላይ ግልጽ እናደርጋለን " ብለዋል።

ኮማንደሩ በሰጡት ማብራሪያ፣ " ሰው ወዲያው እንደሞተ ወደ ሚዲያ መውጣት አለበት ? " ሲሉ ጠይቀው፣ " በጣም አሁን እኮ አንዳንድ ፀሐፊዎች እንዳውም ፎቶ ግራፉን ሁሉ ' ተጠርጣሪ ይሄ ነው ' እያሉ እየለጠፉ ነው። ይሄ ኢቲካል እኮ አይደለም " ብለዋል።

አክለውም፣ " ይሄን ሰውየ እኮ ፍርድ ቤት ነው 'ጥፋተኛ ነህ' ብሎ ጥፋተኛ መሆኑን የሚገልጽለት እንጂ ግለሰብ እየተነሳ 'ጥፋተኛ ነው' ብሎ ፎቶ እየለጠፉ ትክክል እኮ አይደለም " ብለዋል።

ምክትል ኮማንደር ማርቆስ የጉዳዩን አሳሳቢነት ሲያስረዱም ፦

- " ፍርድ ቤት እኮ ጥፋተኛ እስከሚለው እኮ ነፃ ሆኖ የመቆጠር መብት አለው። "

- " ከሕግ አንጻር እኮ ማዬት መቻል አለብን። ይሄ ነገር #የሚያስከትለውን ነገር ማየት መቻል አለበት። "

- " ቤተሰቦቹን ማሰብ መቻል አለበት። አሁን እነዚህ ሰዎች #ጎረቤታሞች ቢሆኑ እኮ የዛ ቤተሰብ መጥቶ እዚህ ልጅ ላይ እርምጃ ሊወስድ ነው። እንዴት እንደዚህ አይታሰብም ? ብቻ በአጠቃላይ በጣም ቀውሷል ሚዲያው ፤ ከባድ ቀውስ ላይ ነው ያለነው " ሲሉ አስረድተዋል።

የሟቹን ጉዳይ በተመለከተ ፖሊስ ያገኘው መረጃ እና የጀመረው ምርመራ እንዳለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው ኮማንደር ማርቆስ፣ " ፖሊስ ሥራ እየሰራ ነው። ግልጽ ማድረግ በሚገባን ሰዓት ላይ ግልጽ እናደርጋለን። አሁን ሥራ እየተሰራ ነው " ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

የአባተ አበበን ጉዳይ በተመለከተ እየተከታተልን የምናቀርብ ይሆናል።

ይህን መረጃ አዘጋጅቶ የላከው የአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia