TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.4K photos
1.39K videos
199 files
3.72K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጅብ

የስልጤ ዞን ጦራ አስተዳደር ከሰሞኑን ጅብ በሰው ላይ ጥቃት እያደረሰ ስለሆነ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰቢያ አስተላለፈ።

በስልጤ ዞን ላንፉሮ ወረዳ ሶስተሮ ቀበሌ ላይ አንድ በግምት አስር አመት የሚሆነው ህፃን ወደ ትምህርት ቤት እየሄደ በጅብ ጥቃት ደርሶበታል።

ይኸው ጥቃት ከሰሞኑን የተፈፀመ 3ኛው መሆኑ ተነግሯል።

ህፃኑ ወደ ትምህርት ቤት በመሄድ ላይ ሳለ ጅብ ይዞት ከፍተኛ ጉዳት አድርሶበት ወደ ወራቤ ሆስፒታል ሪፈር መደረጉ ተመላክቷል።

ከሰሞኑን በስልጤ ዞን ጦራ ከተማ አስተዳደር ጦራ መልታሜና ጦራ ሚሊኒዬም ቀበሌዎች ላይ በሁለት ህፃናት ላይ ጅብ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶ ነበር።

በጦራ መልታሜ ቀበሌ ልዩ ስሙ " መናፈሻ መንደር " አካባቢ በመኖሪያ ቤቷ በር ላይ የቆመች አንዲት የሶስት አመት ህፃን ጀቡ ወደ ጫካ ይዟት ሊገባ ሲል በህብረተሰቡ ትግል ማትረፍ ተችሏል። በሚሊኒዬም ቀበሌ ደግሞ የ10 አንድ ህፃን ወደ መስጂድ እየተጓዘ እያለ በጅብ ተበልቶ በህይወት ሊተርፍ ችሏል።

የጦራ አስተዳደር ሰሞኑን ከወትሮው በተለየ መልኩ ጅብ በሰው ላይ የተለያዩ ጥቃቶችን እያደረሰ በመሆኑ ልዩ ጥንቃቄ ይሻል ብሏል።

ህፃናት ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱ ወላጆች ማድረስ ከትምህርት ቤት ሲመለሱም ወላጆች በጥንቃቄ ወደቤታቸው መመለስ ይኖርባቸዋል ብሏል።

ህፃናትን ብቻቸውን ጥሎ መሄድ አይገባም ያለው አስተዳደሩ፤" ማነኛውንም እንቅስቃሴ ስናደርግ ከወትሮው በተለየ ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል " ሲል አሳስቧል።

@tikvahethiopia