TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ናዲያ ሙራድ🕊 በፈረንጆቹ 2014 በሃገሯ #ኢራቅ በጽንፈኛው ታጣቂ ቡድን #አይ_ኤስ ታግታ የቆየችና #የወሲብ ጥቃት ሰለባ የሆነች ወጣት ናት። ከቡድኑ እገታ ከወጣች በኋላም ይህን መሰሉ #ጥቃት እንዲቆምና በጦርነት ቀጠና ውስጥ የሚገኙ #ሴቶችን ለመታደግ ጥረት ስታደርግ ቆይታለች። ናዲያ ላደረገችው ጥረት የዘንድሮው የኖቤል #የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆናለች።
.
.
እኔ ግሌ እስካሁን ድረስ በህይወቴ ውስጥ ካየኋቸው እና ታሪካቸውን ከሰማሁ ድንቅ ሰዎች አንዷ ናት። ከእርሷ ጥንካሬን፣ ተስፋ አለመቁረጥን፣ ሰላም ወዳድ መሆንን፣ ለሰው ልጅ መኖርን ተምሪያለሁ! ዛሬ ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ ለናዲያ ያለኝን ትልቅ ክብር ለመገልፀ እወዳለሁ!
.
.
🕊🕊🕊ናዲያ ሙራድ🕊🕊🕊
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር ዴኒስ🕊ኮንጓዊው የማህጸን ስፔሻሊስት ዶክተር #ዴኒስ_ሙክዌጊ የዘንድሮው የኖቤል #የሰላም ሽልማት አሸናፊ ነው። በጦርነት ወቅት የሚደርስ #የወሲብ ጥቃትን ለማስቆም ባደረጉት አስተዋጽኦ ሽልማቱን ያገኙት። ኮንጓዊው ዶክተር የዚህ ሰለባ ለሆኑ ሴቶች ህክምና በሚሰጥ ክሊኒክ ውስጥ ህክምና በመስጠት የሚፈጸመው የወሲብ ጥቃት እንዲቆም ሲታገሉ መቆየታቸው ተገልጿል።

ዶክተር ዴኒስ ለሰላም ላደረጉት ትልቅ ስራ በቻናላችን ስም እናመሰግናቸዋለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ 55 ፐርሰንቱ ስራ አገናኝ ኤጀንሲ ህገወጥ ስራ ላይ የሚሳተፍ ነው ተብሏል። አረብ ሀገር እንወሰዳለን እያሉ #የወሲብ ትንኮሳም የሚያደርጉም ተበራክተዋል።

Via Tesfaye Getnet
@tsegabwolde @tikvahethiopia