TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወንጀል ነክ መረጃ‼️

ከባድ #የሰው_መግደል_ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በዘጠኝ ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።

የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ መለስ ግርማ ሀብተማሪያም የተባለው ግለሰብ በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1/ሀ/ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ነው ክስ የተመሰረተበት።

በክሱ ዝርዝር ላይም ተከሳሹ ከሟች ጋር የጎዳና ተዳዳሪዎች ሆነው ሲኖሩ የምተኛበትን ማዳበሪያ ወሰድክብኝ በሚል ይጣላሉ።

ገዳይ ጥር 17 ቀን 2009 ዓ.ም ቀን ላይ ሟችን ገድዬ አገሬ እገባለሁ እያለ ሲዝት እንደዋለ፣ ከምሽቱ በ3፡00 ሠዓት ከሟች ርቆ በመሄድና አረቄ ገዝቶ በመጠጣት ሟች መተኛቱን አረጋግጦ በተኛበት በትልቅ ድንጋይ ጭንቅላቱ ላይ በኃይል በመምታት ተሰውሯል።

ሟችም በደረሰበት ከፍተኛ የጭንቅላት መሰበርና መሰርጎድ ምክንያት ህይወቱ ወዲያውኑ ማለፉን ያስረዳል።

የፌዴራል ዐቃቤ ህግም በተከሳሹ ላይ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የአስከሬን ምርመራ ውጤትና ሌሎች የሰነድና የሰው ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።

ግራ ቀኙን ክርክር ያየው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ኅዳር 14 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ወንጀሉ በሌሊት መፈጸሙን በቅጣት ማክበጃነት፣ የተከሳሽን የቀድሞ መልካም ባህሪና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆን በማቅለያነት ወስዷል።

በዚሁ መሰረትም #በዘጠኝ_ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አግልግሎት
@tsegabwolde @tikcahethiopia
ከመቀለ...

"የሐገር መሠረት ቤተሰብ ነው፡፡ አያትና ቅድመ አያቶቻችን በአንድነት ና በፍቅር ሆነው የኢትዮጵያን እና የጥቁር ህዝቦችን #ነፃነት ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው አቀዳጁን፤ እኛ ታዲያ ልጆቻችንን እሕት ወንድሞቻችንን ከቤት እስከ ጎረቤት ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን ድሮም #አንድ አድርጎ ያስተሳሰረን ውድ ፍቅራችንን ፣ #እሴቶቻችን መንገርና በተግባር ማሳየት ያቅተናል? እኛ የተሳሳተ አስተሳሰብ እንጂ #የሰው_ጠላት_የለንም፤ ሰው በሰውነቱ እኩል ነው ፤ የሃሳብ ልዩነቶቻችንን በሰከነና ሰላማዊ በሆነ መንገድ መፍታት እየቻልን ጥላቻንና በቀልን በመዝራት ሞትን፣ ውድመትንና መከራን ስለምን እናጭዳለን?? እኛኮ ውድ የአፍሪካ የቁርጥ ቀን ልጆች ነን፤ እኛኮ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት አርማ ኩራታቸው ነን፤ አባቶቻችን በታላቅ መስዋዕትነት የገነቡትንና ያወረሱንን ድንቅ ታሪካችንን በመገዳደልና በመዘራረፍ ለአለም ሕዝብ #መሳለቂያ መሆን #ያሳፍራል፤ ተው ወገን ይህም ያልፍና ቀጣይ ትውልድ ይታዘበናል...የአገራችን ሰላም በእጃችን ነው አንድም ለማፍረስ አንድም ሰላማችንን ለማስቀጠል፡፡ አሸናፊ ግርማ ከመቖለ ዩኒቨርሲቲ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እኔ በእውነቱ ከተማው ፈርሶ እየተሰራ ነው እየተባለ #ዐይናማዎቹ ሲያወሩም ሲያስወሩም እሰማለው። ፈርሶ መሰራት ያለበት ግን የሰው #አስተሳሰብ ነው። #የሰው አስተሳሰብ ፈርሶ ካልተሰራ፤ የተሰራ ከተማ #ይፈርሳል። ጃፓን እና ቻይና ሀገራቸውን ያለሙት መጀመሪያ አስተሳሰባቸውን #አልምተው ነው"-- መጋቤ ሀዲስ አሸቱ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሸዋሮቢት

የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን መገደላቸውን የከተማው አስተዳደር አሳወቀ።

የከተማ አስታዳደሩ ፤ አቶ አብዱ የተገደሉት " ድንገት ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች ነው " ብሏል።

ግድያው የተፈፀመባቸው የመንግስት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ሲሰሩ መፈፀሙን የገለፀው አስተዳደሩ ግድያውን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይፋ አላደረገም።

በሌላ በኩል ፤ የከተማው ጊዜያዊ የጸጥታ ኮማንድ ፓስት ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ የሰዓት ገደብ ጥሏል።

ኮማንድ ፖስቱ የከተማውን የሰላምና የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ እንዲሆን እና  ዜጎች ያለ ስጋት ወጥተው የሚገቡበት ለማድረግ ብዙ ጥረት የተደረገ ቢሆንም አሁንም ከተማዋን ሰው አልባ እንድትሆንና ከፍተኛ የጸጥታ ችግር እንዲከሰት ጥረቶች እየተደረጉ ነው ብሏል።

በዚህም ሳቢያ ፤ ከነገ ከሰኔ 28/2015 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ #ከምሽቱ_12_ሰዓት_ጀምሮ  ፦

- ማንኛውም #ተሽከርካሪ ይሁን #የሰው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ #እንዲገደብ

- አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የምሽት ክለቦችን ጨምሮ ከምሽቱ 12 ስዓት  በኃላ  ምንም አይነት አገልግሎት እንዳይሰጡ ውሳኔ ተላልፏል።

የከተማው ጊዜያዊ የጸጥታ ኮማንድ ፓስት ፤ የከተማው ነዋሪ ለጸጥታ መዋቅሩ እገዛና ድጋፍ በማድረግ ከተማዋን ካለባት ከፍተኛ የጸጥታ ችግር እንዲታደጋት ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ፦ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

የፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አመራሮች በአዲስ አበባ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ውይይት ማካሄዳቸው ተሰምቷል።

ውይይት ሲካሄድ የነበረው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ሲሆን ሰዓታትን የወሰደ ሰፊ ውይይት መካሄዱ ተጠቁሟል።

ከፍተኛ አመራሮቹ ከውይይቱ በኃላ ባወጡት መግለጫ ሰሞኑን በአዲስ አበባ በተካሄደ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ፦
- በእገታ ወንጀል፣
- በሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ፣
- በተደራጀ ከባድ የዝርፊያ ወንጀል
- ሞተር ሳይክል፣ ባጃጅ፣ የሜትር ታክሲዎችን ተጠቅመው #የሰው_ግድያ፣ የሞባይል ንጥቂያ እና ሌሎች ወንጀሎችን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራ ነው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፦
- በርካታ የሺሻ ማስጨሻ፣
- #የጭፈራ_ቤቶች እንዲሁም ሕገ-ወጥ የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ ተወስዶ እንዲዘጉ መደረጉን አስረድተዋል።

የፌዴራል ፖሊስ እና አዲስ አበባ ፖሊስ የስፖርት ውርርድ ቤቶችን " የቁማር ቤቶች (betting) " ሲሉ የጠሯቸው ሲሆን በእነዚህም ላይ እርምጃ ተወስዶ እንዲዘጉ መደረጉን ገልጸዋል።

እነዚህ ወንጀሎች ለኅብረተሰቡ የፀጥታ ሥጋት በማይሆኑበት ደረጃ ላይ ለማድረስ ተከታታይ ኦፕሬሽን እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።

በየጊዜው ውጤቱ እየተገመገመ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግም ገልጸዋል።

* የሜትር ታክሲ፣
* የሞተር ሳይክል
* የባጃጅ አጠቃቀም ሥርዓት እንዲይዝ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ይሰራልም ያሉ ሲሆን በወንጀል ተሳትፈው ከተገኙ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል።

በቀጣይ ለሚካሄድ ኦፕሬሽን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለፖሊስ መረጃ በመስጠት ድጋፍ እንዲያደርጉ ባወጡት መግለጫ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
#ኩሽ #ሴራሊዮን

የሴራሊዮን መንግሥት በአገሪቷ በተንሰራፋው ‘ #ኩሽ / Kush ’ እየተባለ በሚጠራው የአደንዛዥ እፅ ምክንያት ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ።

' ኩሽ ' የተለያዩ ሱስ የሚያስይዙ ግብዓቶችን በመደባለቅ የሚሰራ አደገኛ እፅ ሲሆን ለዓመታት በአገሪቷ ተንሰራፍቶ ይገኛል።

በአደንዛዥ እጹ ውስጥ ከሚጨመሩ ግብዓቶች መካከል አንዱ የተፈጨ #የሰው_አጥንት ነው።

በዚህም ምክንያት #ከመቃብር ውስጥ አፅም ለማውጣት የሚቆፍሩ #ሱሰኞችን ለማስቆም የጸጥታ አካላት በመካነ መቃብር ሥፍራዎች የሚያደርጉትን ጥበቃዎች አጠክረው ቆይተዋል።

የሴራሊዮን ፕሬዚደንት የሆኑት ጁሊየን ማዳ ባዮ አስተዳደራቸው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያውጅ ያስገደደውን ይህንን እፅ / ኩሽ “ የሞት ወጥመድ ” ሲሉ የገለጹት ሲሆን በአገሪቷ ላይም የህልውና ቀውስና ስጋት ፈጥሯል ብለዋል።

ፕሬዚደንት ባዮ ፤ በእፁ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርም እንዳሻቀበ ተናግረዋል።

በመሆኑም በ ' ኩሽ ' እፅ ምክንያት የሚደርሰውን ቀውስ ለመከላከል በሀገሪቱ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል ፤ ብሔራዊ ግብረ ኃይል እንዲቋቋምም መደረጉን ቢቢሲ አስነብቧል።

ፎቶ/ቪድዮ ፦ ቻናል 4 እና አፍሪካ ኒውስ (ፋይል)

@tikvahethiopia