TIKVAH-ETHIOPIA
1.42M subscribers
55.2K photos
1.38K videos
199 files
3.7K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የተሻለ ህይወት ፍለጋ አህጉሩን ጥለው የተሰደዱ አፍሪካውያን የጤና ባለሞያዎች ቁጥር የሚስደነግጥ ነው " - ካሉምቢ ሻንጉላ

አፍሪካ የጤና ባለሙያዎች እጥረት እንዳለባት የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

ድርጅቱ በናሚቢያ ዋና ከተማ ፤ #ዊንድሆክ በዚህ ሳምንት እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ የጤና ባለሞያዎች ፎረም ላይ ነው ይህን ያሳወቀው።

ፎረሙ ላይ የናሚቢያ የጤናና የማህበራዊ አገልግሎት ሚኒስትር ካሉምቢ ሻንጉላ ፥ " #አፍሪካ ያጋጠማት የጤና ባለሙያዎች እጥረት አህጉሪቱ እ.አ.አ በ2030 ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ለማግኘት የያዘችውን እቅድ እንዳታሳካ እንቅፋት ይሆናል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

" የተሻለ ህይወት ፍለጋ አህጉሩን ጥለው የተሰደዱ አፍሪካውያን ቁጥር #የሚስደነግጥ_ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ይህን ጉዳይ የአፍሪካ መንግስታትም ሆኑ ታሪካዊ እና ወቅታዊ ሁኔታዎች ተለውጠው ማየት የሚሹ በሙሉ ቅድሚያ ሰጥተው ሊፈቱት የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ አስረድተዋል።

የአፍሪካ በሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ዳይሬክተር ጀነራል ጂን ካሳያ እንዳስታወቁት፣ እ.አ.አ በ2030 ለመድረስ የታቀደውን ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ለማሳካት አፍሪካ ተጨማሪ 1.8 ሚሊየን የጤና ሰራተኞች ያስፈልጓታል።

በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ 1.55 የጤና ባለሙያዎች ለአንድ ሺህ ሰዎች አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን ፣ ይህም ለ1 ሺህ ሰዎች 4.55 የጤና ባለሙያዎች እንደሚያስፈልግ የዓለም ጤና ድርጅት ካስቀመጠው ገደብ በታች ነው።

እ.አ.አ በ2023 ብቻ አፍሪካ " 166 ወረርሽኞች "ን መመዝገቧን ያመለከቱት ካሳያ ፤ የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት እ.አ.አ በ2030 ሁለት ሚሊየን የቋማዊ የማህበረሰብ የጤና ሠራተኞችን እንዲመለምሉ እንዲያሰለጥኑና ወደ ስራ እንዲያሰማሩ የተወሰነውን ውሳኔ ለማሳካት በጣም ወደኃላ መቅረታቸውንም አመልክተዋል። #ቪኦኤ

@tikvahethiopia