TIKVAH-ETHIOPIA
1.41M subscribers
55K photos
1.37K videos
199 files
3.67K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ?

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሲፈጸም እንደቆየ የተነገረለት እጅግ በጣም የለየለት የህዝብ ገንዘብ እና ሀብት ምዝበራን የሚያሳይ የ " ፋና ቴሌቪዥን " የምርመራ ዘገባ ከሰሞኑን ለህዝብ ተሰራጭቶ ነበር።

👉 በአበል መልክ የሚመዘበረው ገንዘብ ፦

የተቋሙ ገንዘብ በአበል መልክ ይመዘበራል።

ለአብነት ሁለት የፋይናንስ ቡድን መሪዎች ከፍተኛ አበል ለራሳቸው ከፍለዋል።

አቶ መሰረት ለማ የተባሉት ግለሰብ በ6 ወራት ብቻ የ1 ሺህ 496 ቀን ይህ ማለት 1 ሚሊዮን 56 ሺህ 854 ብር አበል ተከፏላቸዋል።

አቶ ደስታ ደቦጭ የሚባሉት ደግሞ የ940 ቀን አበል ወስደዋል።

➡️አቶ ደስታ የስንት ቀን አበል ወሰዱ ? ሲባሉ " የ790 ቀን ነው የወሰድኩት " ብለዋል።

ወስደዋል እንዴ ? ተብለው በመርማሪ ጋዜጠኛው ሲጠየቁ " #አልወሰድኩም " ሲሉ ቃላቸውን አጥፈው ተናግረዋል።

➡️አቶ መሰረት የ1 ሺህ 496 ቀን አበል ወደ አካውንቶ ገብቷል ? ተብለው ሲጠየቁ " ይሄ ስህተት ነው የተሰሳሳተ ነው " ሲሉ መልሰዋል።

የተቋሙ ፋይናስ ዳይሬክተር አቶ ማርቆስ ዮሐንስ ፥ " እኔ ለረጅም ወራት ፍቃድ ላይ ነበርኩኝ የህመም ፍቃድ ላይ ከመጣሁ በኃላ ነው እንደዚህ አይነት ነገር እሰማ ነበር " ብለዋል።

አቶ ደስታ ግን በዚህ አይስማሙም፤ አቶ ማርቆስ ታመው ቤት የተቀመጡት 2 ወር ብቻ እንደነበር የወጣው ደግሞ የ5 ወር መረጃ እንደሆነ ገልጸዋል። 3 ወር የሰራው እራሱ ነው ሲሉ አጋልጠዋል።

ቀደም ሲል " እኔ አበል አልወሰድኩም " ያሉት አቶ ደስታ 3 ወር የሰራው እራሱ ነው ሲሉ እሱ እያለ ነው የተከፈሎት ? ተብለው ሲጠየቁ " ምኑን ? እንደ ስራ ባህሪ የተከፈለኝ ነገር ሊኖር ይችላል " ሲሉ መልሰዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ሀብቶሙ አበበ (ዶ/ር) ፥ " በሰነድ የተረጋገጠ ነው ብሎ የውጭ ኦዲት ያመጣውን ያክል አስመልሰናል ሰራተኞቹ ከስራ እንዲታገዱ ተደርጓል፤ በዲስፒሊም እየተጠየቁ ናቸው የኛ ኦዲት ያመጣውን የትራዛክሽኑን ቼክአፕ በህግ እንዲጣራ ክትትል እየተደረገ ነው " ብለዋል።

የፋይናስ ስርአታቹ ክፍተት ያሉት ይመስላል ሲባሉ " በፍጹም በፍጹም !! " ሲሉ መልሰዋል።

👉 ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ስለወጣበት ፕሮጀክት ፦

ለኦክስጅን ማምረቻ በሚል ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ግልጽነት በጎደለው መልኩ ተፈጽሟል።

በዚህ ጉዳይ ፕሬዜዳንቱ እና የፋይናንስ ዳይሬክተሩ እርስ በእርስ የሚያወዛግብ ምላሽ ነው የሰጡት።

የፋይናንስ ዳይሬክተሩ ያለ ሰነድ ከእውቅናቸው ውጭ ገንዘቡ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ይገልጻሉ።

ክፍያ ሲፈጸም ሰነድ እጃቸው ላይ እንደሌለ እና እሳቸውም እንዳልተሳተፉ ተናግረዋል።

የፋይናንስ ዳይሬክተሩ " እኔ እኮ ዝርዝር መረጃ አልተሰጠኝም ፤ እንደሚንቀሳቀስ አያለሁ እሰማለሁ " ብለዋል።

ገንዘቡን እኔ አላንቀሳቅስም ነበር ብለዋል።

ፕሬዜዳንቱ ግን የኦክስጂን ፕሮጀክት በጀቱ ሲመራ የነበረው በፋይናንስ ነው ሲሉ መልሰዋል።

የፋይናንስ ዳይሬክተሩ እኔ ሳላውቅ ነው ክፍያው የተፈጸመው ሲሉ ተናግረዋል።

የቀድሞ ም/ፕሬዜዳንት ፀደቀ ላምቦሬ (ዶክተር) ፤  የአካውንቱ ጉዳይ በዋነኝነት የሚመለከተው ፕሬዜዳንቱን እንደሆነ ገልጸዋል።

▪️ለኦክስጅን ማምረቻው መሳሪያውን ያቀረበው ያለጨረታ ያለፍቃድ ያለውድድር 240 ሚሊዮን 988 ሺህ ብር ተሰጥቶታል። ለድርጁ ሙሉ ክፍያ ቢከፈልም ዝርጋታው ግን አላለቀም ስራውም አልተሰራም። ከተጀመረ 2 ዓመት አልፎታል።

የምርመራ ዘገባውን ይመልከቱ👇
https://youtu.be/wREkP5S8zNM?feature=shared (አዘጋጅ ፦ ጋዜጠኛ አፈወርቅ እያዩ)

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM