TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.4K photos
1.39K videos
199 files
3.72K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ነገ የሚጀምረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በውጭ ሀገር ባሉ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ት/ቤቶች አይሰጥም !

በኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ምክንያት ለዘንድሮ የተሸጋገረው የ2012 ዓ.ም ፈተና ከነገ የካቲት 29 ጀምሮ እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በሀገር ውስጥ ይሰጣል።

ይህ ፈተና በመጨረሻ ሰዓት ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት #በውጭ ሀገር ባሉ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች እንደማይሰጥ ታውቋል።

ይህ ከአቅም በላይ ነው የተባለው ችግር በግልፅ አልተገለፀም።

ፈተናው በሌላ ተለዋጭ ፕሮግራም እንደሚሰጥ የተገለፀ ሲሆን ፕሮግራሙ በቅርቡ ይገለፃል ተብሏል።

መረጃው ከኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት ሳዑዲ አረቢያ፣ ጅዳ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ20/80 እና 40/60 ባለዕድለኞች ውል እንዲፈፅሙ ጥሪ ቀረበ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የ14ኛ ዙር 20/80 እና 3ኛ ዙር 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቤት እድለኞች ማሟላት የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ከጥር 1ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ባሉት 60 የሥራ ቀናት ውስጥ ባለእድለኛው ወይም ወኪሉ ቀርበው ውል መዋዋል…
20/80 እና 40/60 ውል ፦

የቤት እድለኞች #ውል_ለመዋዋል_ሲመጡ ማሟላት የሚጠበቅባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ምንድናቸው ?

- እጣው የደረሰው ግለሰብ ውል ለመፈፀም በአካል መቅረብ፤

- በውጭ የሚኖሩ ጉዳያቸውን በውክልና ለማስጨረስ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ (አውታንቲኬት) ሆኖ የመጣ ውክልና ማቅረብ፤

- የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤

- የጋብቻ የምስክር ወረቀት ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤

- ያላገባ/ች ከሆነ/ች 6 ወር ያላለፈው የምስክር ወረቀት፤

- ያገባ/ች ከሆነ/ች የትዳር አጋር የታደሰ መታወቂያ ዋና እና ፎቶ 2 ኮፒ፤

- የምዝገባ ማረጋገጫ (print out) ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤

- የምዝገባ የምስክር ወረቀት ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤

- የባንክ ምዝገባ ማረጋገጫ ከተመዘገቡበት ባንክ የሚቀርብ ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤

- የባንክ የቁጠባ ደብተር ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ (ፎቶ ባለው በኩል)፤

- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤

- ቅጽ -09 (ከወረዳ ተሞልቶ ታሽጎ የሚላክ) ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤

- የጠፋ ሰነድ ካለ የፖሊስ ማስረጃ ዋና እና 1 ፎቶ ኮፒ፤

- 4×4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ 4፤

- ፍቺ ካለ በፍ/ቤት የፀደቀ ፍቺ ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤

- የንብረት ክፍፍል ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤

- ባለ ዕድለኛው በሞት ከተለየ የውርስ አጣሪ ሪፖርት ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤

- የወራሽነት ማስረጃ ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ ባለ እድለኛው ወይም ወኪሉ ይዞ መቅረብ አለባቸው።

የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎችን ሳያሟላ የሚመጣ ማንኛውም ባለጉዳይ #እንደማይስተናገድ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በጥብቅ አሳስቧል።

#በውጭ_ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያዊ ከላይ የተጠቀሱትን ማሟላት #የግድ_ሆኖ

• የታደሰ ፓስፖርት ወይም ቢጫ ካርድ (yellow card) የታደሰ፤

• በውክልና ከሆነ የውክልና ወረቀቱ በጀርባው በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህተም የተረጋገጠ እና የተወካይ የታደሰ መታወቂያ ይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል ተብሏል።

ባለዕድለኞች / ወኪላቸው በ60 የስራ ቀናት ውስጥ ካልተዋዋሉ ምን ይፈጠራል ?

ባለእድለኞች ወይም ወኪላቸው ምዝገባ ከተጀመረበት ቀን አንስቶ ባሉት 60 የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርበው ካልተዋዋሉ #ቤቱን_እንዳልፈለጉት_ተቆጥሮ ተመላሽ እንደሚደረግ የከተማው ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአጽንኦት አሳስቧል።

Credit : አዲስ ዘመን ጋዜጣ

@tikvahethiopia