TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56K photos
1.4K videos
202 files
3.79K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፦

" ከዓለም ህዝብ ሩብ ያህሉ (2 ቢሊዮን ህዝብ) በጦርነት ቀጠና ውስጥ እየኖረ ነው።

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ሁከትን የፈጠሩ ከፍተኛ ግጭቶች አሁን ላይ ተስተውለዋል።

በየመን፣ በሶሪያ፣ በሚያንማር፣ በሱዳን፣ ሄይቲና ሳህል ቀጠና ያሉ ጦርነቶች እንዲሁም የቅርብ ጊዜው የዩክሬኑ ጦርነት ዓለም የተገነባበትን ስርዓት የሚሸረሽሩ ናቸው።

እነዚህ ጦርነቶች #በምግብ#በነዳጅ እና #በማዳበሪያ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ እንዲኖር ምክንያት ሆነዋል።

ባለፈው ዓመት ብቻ 84 ሚሊየን ሰዎች ጦርነት በፈጠረው ሁከትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት ቤታቸውን ለቀው ተሰደዋል።

በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል የተደረገው ጦርነትም 4 ሚሊዮን ዜጎችን ከዩክሬን ሲያስወጣ በሀገሪቱ ውስጥ ደግሞ 6 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚሆኑት እንዲፈናቀሉ አድርጓል።

በዚህ ዓመት ብቻ 274 ሚሊየን ሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍ የሚፈልጉ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ 17 በመቶ ጨምሯል "

#AlAIN

@tikvahethiopia
#UN

" ሚሊዮኖች በምግብ እና ነዳጅ ዋጋ ንረት እየተሰቃዩ ነው " - ተመድ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) በዩክሬን ጦርነቱ በመባባሱ ምክንያት ሚሊየኖች #በምግብ እና #በነዳጅ ዋጋ ንረት ምክንያት እየተሰቃዩ ነው አለ።

- በፋይናንስ፣
- በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ
- በአየር ንብረት ለውጥ እየተባባሰ በመጣው ቀውስ ላይ ጦርነቱ ሲጨመርበት በዓለም የኑሮ ውድነት መባባሱን ተመድ ገልጿል።

የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ያስከተለውን ጫና እንዲያጠና በተመድ የተሰየመው ቡድን ይፋ ባደረገው መረጃ ጦርነቱ ፦
- የምግብ ዋስትና፣
- የኃይል አቅርቦት እና
- በፋይናንስ ላይ ከባድ እና ፈጣን ተጽዕኖው እየታየ ነው ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ ዛሬ ጀርመን እና ፖላንድ የምግብ አቅርቦትን ለመደገፍ በዩክሬን ወደቦች ላይ ተከማችቷል የተባለን እህል ወደተለያዩ አካባቢዎች ለማጓጓዝ የሚደረገውን ጥረት ለመርዳት ዝግጁ ነን ብለዋል።

ከዩክሬን እህል ማውጣት እንዲቻል ለማደራደር ቱርክ ከፍተኛ ሚና እንድትጫወት ይጠበቃል። ሆኖም ቱርክ በጥቁር ባሕር ላይ እህል እንድታጓጉዝ ስምምነት ተደርሷል የሚባለውን ሩሲያ የተሳሳተ መረጃ ነው ብላለች።

ሞስኮ በዩክሬን ወደቦች ላይ ተከማችቷል የሚባለው እህል መጓጓዝ እንዲችል የበኩሏን ኃላፊነት እንድትወጣ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥባለች።

ሌሎች ሃገራት በነዳጅ እና የምግብ እህል እጥረት እንዲቸገሩ ምክንያት ሆናለች በሚል የሚቀርቡ ክሶችንም ውድቅ ማድረጓን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አፍሪካ ቀንድ 🇸🇴🇪🇹🇰🇪

እንደ ዓለም ምግብ ፕሮግራም መረጃ በአፍሪካ ቀንድ ከ20 ሚሊዮን በላይ ሰዎች #በድርቅ#በግጭት እና #በምግብ_ውድነት ምክንያት አስከፊ ለሆነ ረሃብ ተጋልጠዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ ላሉ ቤተሰቦች እገዛ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።

#ShareTheMeal (በUN | WFP ስር ያለ) በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ቤተሰቦች የድንገተኛ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን ለዚሁ ስራ የሚውልን ገንዘብ ከለጋሾች በመተግበሪያው እንዲሁም በድረገፁ በኩል እያሰባሰበ ይገኛል። https://t.co/rjY1JlrJTl

@tikvahethiopia
በጎመን ተጠቅልሎ የተያዘው የጥይት ካዝና !

በሀገራችን በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ከተሞች እና ቦታዎች ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች፣ ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር ሲውሉ ይሰማል።

ህገወጥ የጦር መሳሪያ ለጥፋት ዓላማ የሚውል ሲሆን በተለይ በዚህ ድርጊት ውስጥ ያሉ አካላት መሳሪያውን ለማዘዋወር የተለያዩ መንገዶችን ሲጠቀሙ ይስተዋላል።

ከዚህ በፊት በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ከተሰሙት መካከል #በምግብ_እህል_ውስጥ ጥይት በመቅላቀል ለማዘዋወር ሲሞከር፣ በመኪና በሮች ላይ ሻግ በማድረግ ለማሳለፍ ሲሞከር፣ በኩርሲ ወንበር ውስጥ በመደበቅ ለማሳለፍ ሲሞከር ... ብዙ ብዙ ነው ተይዘው ታይተዋል።

ትላንትና ደግሞ ከኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ በሰማነው መረጃ በከተማው ማናኸሪያ 60 የጥይት ካዝና በጎመን ተጠቅልሎ ለጥፋት ዓለማ በህገወጥ መንገድ ለማዘዋወር ሲሞከር በህበረተሰብ ጥቆማ ተይዟል።

ከጠዋቱ 5 ሰዓት አከባቢ ከሲዳማ ክልል ፤ ጩኮ አከባቢ የተነሳ አንድ ግለሰብ #በ3_እስር_ጎመን ውስጥ በመደበቅ ለጥፋት አካላት ሊደርሰው የነበረ 60 የጥይት ካርታ በቁጥጥር ስር መዋል መቻሉን ፤ መዳረሻውም ያቤሎ እንደነበር ያገኘነውም መረጃ ያሳያል።

የህገወጥ ጦር መሳሪያ ዝውውር በተለያየ መንገድ እየተፈፀመ የሚገኝ በመሆኑ የደህንነት አካላት የተጠናከረ ፍተሻ እንዲሁም ህብረተሰቡ መሰል ድርጊቶችን በመጠቆም ተባባሪ መሆን ሲችል የህገወጥ መሳሪያ አዘዋዋሪዎችን ድርጊት በእጅጉ መቀነስ ፤ የሁሉንም ዜጋ ደህንነት ማረጋገጥ ይቻላል።

ፎቶ ፦ አስቹ (ከቡሌሆራ Tikvah Family) እና የቡሌ ሆራ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia