TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የዛሬው የምንዛሬ ዋጋ ስንት ነው ? 💵 US Dollar #CASH Buying ➡️ 74.7364 Selling ➡️ 76.2311 #TRANSACTION Buying ➡️ 74.7364 Selling ➡️ 76.2311 💷 Pound Sterling #CASH Buying ➡️ 91.8787 Selling ➡️ 93.7162 #TRANSACTION Buying ➡️ 96.2081 Selling ➡️ 98.1322 💶 Euro #CASH…
በባንክ የምዛሬ ዋጋ በስንት ጨመረ ?

የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ላይ ማሻሻያ ከመደረጉ ከ3 ቀናት በፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር መግዣ ዋጋ 57 ብር ከ4895 ሳንቲም ነበር ፤ መሸጫው 58 ብር ከ6393 ሳንቲም ነበር።

አሁን ማሻሻያውን ተከትሎ በዛሬው የምናዛሬው ተመን አንድ የአሜሪካ ዶላር መግዣ 74 ብር ከ7364 ሳንቲም ሲሆን መሸጫው 76 ብር ከ2311 ሳንቲም ሆኗል።

የአንድ ፓውንድ መግዣ ዋጋ 70 ብር ከ6759 ሳንቲም ፤ መሸጫው 72 ብር ከ0894 ሳንቲም የነበረ ሲሆን በዛሬው የባንክ ምንዛሬ መግዣው 91 ብር 8787 ሳንቲም ፤ መሸጫው 93 ብር ከ7162 ሳንቲም ሆኗል።

አንድ ዩሮ በ62 ከ3359 ሳንቲም ይገዛ ፤ በ63 ብር ከ5856 ሳንቲም ይሸጥ የነበረ ሲሆን በዛሬው የባንክ ምንዛሬ መግዣው 81 ብር ከ0367 ሳንቲም ፤ መሸጫው 82 ብር ከ6574 ሳንቲም ሆኗል።

#ETHIOPIA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia : የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አሳውቋል። (ሙሉ መግላጫው ከላይ ተያይዟል) @tikvahethiopia
" 10.7 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ተገኝቷል " - ብሔራዊ ባንክ

ብሔራዊ ባንክ ፥ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ አጋሮች መገኘቱን አሳውቋል።

ባንኩ " የሽግግር ወቅት ወጪዎችንና የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ የሚያስከትላቸውን ጫናዎችን ለመቀነስ የሚረዳ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ትልቅ የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ አጋሮች ተገኝቷል " ብሏል።

የገንዘብ ድጋፉ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት (#IMF) ፣ ከዓለም ባንክ (WB) እና ከአበዳሪዎች የሚገኘውን እንደሚጨምር አመልክቷል።

ነገር ግን፣ በሁለትዮሽ የማዕከላዊ ባንክ ተቀማጭ (central bank deposits) እና በከረንሲ ልውውጥ (currency swap) መልክ የሚመጣውን 2.8 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንዲሁም ከዓለም ባንክ፣ ከዓለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) እና ከሌሎች ባለብዙ ወገኖች (multilaterals) ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀውንና በሃደት ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት ይፋ የሚደረገውን ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ አያካትትም ብሏል።

ብሔራዊ ባንክ " በዓለም የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ የሚለገሰው ልዩ የገንዘብ እርዳታ የመንግሥትን የሪፎርም ሥራዎችን ጥንካሬ ያገናዘበና በአፍሪካ አህጉር ትልቁ ከሚባሉት የገንዘብ እርዳታዎች አንዱ ነው " ብሎታል።

#NBE #Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" 10.7 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ተገኝቷል " - ብሔራዊ ባንክ ብሔራዊ ባንክ ፥ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ አጋሮች መገኘቱን አሳውቋል። ባንኩ " የሽግግር ወቅት ወጪዎችንና የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ የሚያስከትላቸውን ጫናዎችን ለመቀነስ የሚረዳ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ትልቅ የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ አጋሮች ተገኝቷል " ብሏል። የገንዘብ ድጋፉ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት (#IMF) ፣ ከዓለም…
#Ethiopia : ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ ምን ለውጦችን አካቷል ?

1ኛ. የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወሰንበት የገበያ ሥርዓት ተሸጋግሯል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሚና፣ ገበያውን በማረጋጋት ላይ ያተኩራል።

2ኛ. የውጭ ምንዛሪን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማስተላለፍ ግዴታ ቀሪ ሆኗል፡፡ ላኪዎች እና ንግድ ባንኮች ያፈሩትን የውጭ ምንዛሪ ለራሳቸው ማስቀረት ይችላሉ። ይህ ለግሉ ዘርፍ የሚሰጠውን የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በእጅጉ እንደሚያሻሽል ይጠበቃል።

3ኛ. ቀደም ሲል በ38 የገቢ ንግድ ሸቀጦች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሥቷል፡፡ ወደ ውጭ የሚደረግ የካፒታል ሂሳብ ፍስት እንደ በፊቱ የተገደበ ቢሆንም፣ የውጭ ምንዛሪ ገበያው ለገቢ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ነጻ ሆኗል፡፡

4ኛ. ምርቶችን ወደ ውጭ የሚልኩ ነጋዴዎች ካፈሩት የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለራሳቸው ያስቀሩት የነበረው 40 በመቶ ወደ 50 በመቶ ብሏል፡፡ በሂደት የውጭ ምንዛሬ ገቢያቸውን ሙሉ በሙሉ ለራሳቸው የሚያስቀሩበት አሰራር ይዘረጋል።

5ኛ. ቀደም ሲል ባንኮች ለተለያዩ ገቢ ሸቀጦች የሚጠቀሙበት የውጭ ምንዛሪ አሠራርና አደላደል ደንቦች ቀሪ ሆነዋል፡፡

6ኛ. አሁን በሥራ ካሉና በባንኮች ከተቋቋሙ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች (Forex Bureaus) በተጨማሪ ባንክ ያልሆኑ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ይቋቋማሉ፡፡ ለእነዚህ ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችም በገበያ ዋጋ የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ እንዲገዙና እንዲሸጡ የሥራ ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡

7ኛ. ሸቀጦችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ረገድ የተጣሉ ክልከላዎች ተነስተዋል።

8ኛ. በውጭ ተቋማት፣ በውጭ ኢንቨስተሮች እና በትውልደ ኢትዮጵያውያን (በዳያስፖራዎች) የተከፈቱ የውጭ ምንዛሪ ሂሳቦችን አስተዳደር የሚመለከቱ በርካታ ሕጎች እንዲላሉ ተደርጓል፡፡

9ኛ. በኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ስዎች ከውጭ የሚላክላቸውን ሐዋላ፣ በውጭ ምንዛሪ የሚከፈል ደሞዝን/የኪራይ ገቢን እና ሌሎች ገቢዎችን የሚያስቀምጡባቸውን የውጭ ምንዛሪ ሃሳቦች እንዲከፍቱ፣ እንዲሁም እነዚህን የውጭ ምንዛሪ ሂሳቦች ተጠቅመው የውጭ አገልግሎት ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ ተፈቅዷል፡፡

10ኛ. ቀደም ሲል የግል ኩባንያዎች ወይም ባንኮች በሚወስዷቸው የውጭ ብድሮች ላይ ይከፍሉት የነበረው የወለድ ተመን ጣሪያ ተነሥቷል።

11ኛ. መመዘኛውን የሚያሟሉ የውጭ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ (Ethiopian Securities Exchange) እንዲሳተፉ ተፈቅዷል፡፡

12ኛ. በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የሚሠሩ ኩባንያዎች የውጭ ምንዛሪ ገቢያቸውን ሙሉ በሙሉ ለራሳቸው መያዝን ጨምሮ ልዩ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀም መብት ተሰጥቷቸዋል፡፡

13ኛ. ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገራት የሚጓዙ ወይም ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች ሊይዙ በሚገባ የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ መጠን ላይ ተጥለው የነበሩ የተለያዩ ጥብቅ ደንቦች እንዲላሉ ተደርጓል፡፡

#NationalBankofEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia : ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ ምን ለውጦችን አካቷል ? 1ኛ. የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወሰንበት የገበያ ሥርዓት ተሸጋግሯል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሚና፣ ገበያውን በማረጋጋት ላይ ያተኩራል። 2ኛ. የውጭ ምንዛሪን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማስተላለፍ ግዴታ ቀሪ ሆኗል፡፡ ላኪዎች እና ንግድ…
#Ethiopia

በአዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ባንኮች እና ፍቃድ የሚሰጣቸው የውጭ ምንዛሪ ላይ የሚሰሩ አካላት በራሳቸው መካከል እና ከደንበኞቻቸው ጋር በዋጋው ላይ ነጻ ድርድር በማድረግ የውጭ ምንዛሪ መግዛት እና መሸጥ እንዲችሉ ተፈቅዶላቸዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሚና ገበያውን በማረጋጋት ላይ ያተኮረ እንሰሚሆን ተነግሯል።

ባንኮች በየዕለቱ ለሚያደርጉት የውጭ ምንዛሪ ግብይት የሚያውሉትን የምንዛሪ ዋጋ በቀኑ መጨረሻ ለብሔራዊ ባንክ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል።

በኢትዮጵያ ከዛሬ ጀምሮ " በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት ወይም Floating exchange rate " ወደ ስራ ገብቷል።

ማሻሻያውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ74 ብር ከ7364 ሳንቲም እየገዛ በ76 ብር ከ2311 ሳንቲም በመሸጥ ላይ ነው።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

" 7.02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ (Revenue) ተገኝቷል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

በመግለጫው ባለፈው በጀት ዓመት በአጠቃላይ 7.02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ (Revenue) ማግኘቱንና ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 14 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ ገልጿል።

ይህ ገቢ በኢትዮጵያ ብር ሲቀመጥ 402 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ምን አሉ ?

አየር መንገድ 577,746 የበረራ ሰዓቶችን እንደበረረና ይህም ቀደም ሲል ካለው 19 በመቶ እድገት እንዳሳየ ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ አየር መንገዱ 17.1 ሚሊየን ተጓዧችን እንዳስተናገደ ተናግረዋል።

ከዚህ ውስጥ 13.4 ሚሊዮን የሚሆነው አለም አቀፍ ተጓዦች እንደሆኑ 3.7 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ የሀገር ውስጥ መንገደኞች እንደሆኑ ጠቁመዋል።

" የሀገር ውስጥ በረራ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል " ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ " ያለፈው በጀት ዓመት ማስተናገድ የተቻለው 2.7 ሚሊዮን የሀገር ተጓዦች ነበር " ብለዋል።

ከካርጎ ጋር ተያይዞ በዚህ ዓመት ካለፉት ተመሳሳይ ወቅቶች ጋር ሲነጻጸር ቅናሽ እንዳሳየ ተሰምቷል።

በዚህ በጀት ዓመት አየር መንገዱ ያጓጓዘው ጭነት መጠን ከ754, 681 ቶን ጭነት እንደሆነ ተናግረዋል።

" አየር መንገዱ ከካርጎ ያገኘው ገቢ 1.65 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 8 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ " ቀደም ተብለው ከታዘዙ 20 የሚሆኑ አውሮፕላኖች ጋር ተደምሮ 125 የሚሆን አውሮፕላኖች እንደታዘዙ " ዋና ስራ አስኪያጁ ጠቁመዋል።

ከቦይንግ የታዘዙ አውሮፕላኖች አለመገኘታቸውን ተከትሎ የአውሮፕላን እጥረት እንዳጋጠመ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia " 7.02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ (Revenue) ተገኝቷል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። በመግለጫው ባለፈው በጀት ዓመት በአጠቃላይ 7.02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ (Revenue) ማግኘቱንና ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 14 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ ገልጿል። ይህ ገቢ በኢትዮጵያ ብር ሲቀመጥ 402 ቢሊዮን…
#EthiopianAirlines🇪🇹

" የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ውሳኔውን መልሶ እንዲያጤነው እንጠይቃለን ፤ ይህ የማይሆን ከሆነ የሚጎዱት ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ናቸው " - " አቶ መስፍን ጣሰው

የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚያደርገው በረራ ከመስከረም 30 / 2024 ጀምሮ እንዲቆም የሚያሳውቅ ደብዳቤ መላኩን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ምን አሉ?

" ከቅርብ ወራት በፊት ከኤርትራ ሲቪል አቬሽን ቅሬታ ቀርቦልን ነበር፤ ይህም ከተሳፉሪዎች ሻንጣ ተያይዞ ወደኋላ እየቀረ ነው በሚልየቀረበ ነበር።

የተነሳውም የትራንስፖርቴሽን መዘግየትና የሻንጣ ዘግይቶ መድረስ ጋር የተያያዘ ነው። ይህ የተፈጠረው ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ብዙ ሻንጣ ይሸከማሉ፤ ሁሉንም ማስተናገድ ባለመቻላችን በሚቀጥለው በረራ ሻንጣዎችን እንልክ ነበር።

ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ በፊት የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከ737 አውሮፕላን ውጪ ከፍ ያለ የመንገደኞች ማመላለሻ እንዳንጠቀም እግድ ጥሎብን ነበር። በተጨማሪም በሳምንት ከ10 በረራ ውጪ እንዳናደርግ ተደርጎ ነበር።

መጋቢት ላይ ነው ይኼ የሆነው። ይህን ተከትሎ የኤርትራ ተጓዦች ከሻንጣቸው ጋር እንዲጓዙ ለማስቻል የተሳፋሪዎችን ቁጥር በመቀነስ ተጓዦች ከሻንጣዎቻቸው ጋር እንዲጓዙ አድርገናል። ከዚያ በኋላ ይህ ነው የሚባል ቅሬታ አልሰማንም ነበር።

ይህን ተከትሎ ሰኔ መጀመሪያ ላይ ሌላ ደብዳቤ ተቀብለናል። ይህም የነበሩ በረራዎችን ወደ 15 እንድናሳድግና የምንጠቀመው አውሮፕላን ላይ ነበረው ገደብም መነሳቱን ተገልጾልን ነበር።

ይህንን ግን ወዲያው ተግባራዊ ማድረግ አልቻልንም፤ የአውርፕላን እጥረቶች አሉብን። በዚህ ምክንያት ይኽን ደብዳቤ ከተቀበልን በኋላ በነበረው አሰራር ቀጥለናል።

አሁን ላይ የወጣው ደብዳቤ ግን ከመስከረም 30/2024 በኋላ በረራ እንዳይደረግ የሚገልጽ ነው። ይህን ተከትሎም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ክስ ቀርቦብናል፤ በዚህ በጣም አዝነናል።

ይህ ሁሉ ሲሆን እንደ ዓለም አቀፍ አሰራር ቅሬታዎቹ ላይ እንወያይ ተብሎ ጥያቄ አልቀረበልንም፤ የነበሩ ችግሮች ላይ ቀደም ብለን መፍትሔ ሰጥተናል።

አሁንም የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ውሳኔውን እንዲያጤነው እንጠይቃለን፤ ይህን የማይሆን ከሆነ የሚጎዱት ግን ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ናቸው። "


#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia በአዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ባንኮች እና ፍቃድ የሚሰጣቸው የውጭ ምንዛሪ ላይ የሚሰሩ አካላት በራሳቸው መካከል እና ከደንበኞቻቸው ጋር በዋጋው ላይ ነጻ ድርድር በማድረግ የውጭ ምንዛሪ መግዛት እና መሸጥ እንዲችሉ ተፈቅዶላቸዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሚና ገበያውን በማረጋጋት ላይ ያተኮረ እንሰሚሆን ተነግሯል። ባንኮች በየዕለቱ ለሚያደርጉት የውጭ ምንዛሪ ግብይት የሚያውሉትን…
#ያንብቡ

የኢኮኖሚ ባለሙያው ዋሲሁን በላይ ምን አሉ ?

- የማይጠበቅ ነው ብዬ መናገር አልችልም። ግን በዚህ ፍጥነት መሆኑ ለእኔ አስደጋጭ ነው።

- በእርግጥ አሁን የተደረገው devaluate /ገንዘብ ማዳከም/  አይደለም። devaluation ማድረግ እና floating ይለያያል።

- devaluate የገንዘቡን የመግዛት አቅም በተወሰነ መልኩ በመንግስት ውሳኔ ማዳከም ማለት ነው። አሁን ግን እንደዛ አይደለም የተደረገው። አሁን የተደረገው በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ስርዓት / floating / ነው።

- የውጭ ምንዛሪ ተመን በ3 መልኩ ይመራል።

1. fixed exchange rate / 👉 በመንግስት ውሳኔ / መንግስት አንድ ዶላር በዚህ ያህል ብር ነው የሚወሰነው ብሎ ድርቅ ሲያደርግ በዛ ብር ብቻ ነው የሚወሰነው ሲል።

2. floating managing 👉 ኢትዮጵያ እስከ ዛሬ ስትመራበት የነበረው ነው። በመንግስት ውሳኔ አለው ግን በየቀኑ መንሸራተት ያለው ነው። በየቀኑ የሚምሸራተት ነው። በምዛሬው ላይ በየዕለቱ ለውጥ የሚታይበት ነው። መንግስት መነሻውን እያስቀመጠ ገበያው እየወሰነ ሲቆይ ነው።

3. floating 👉 በገበያው ላይ ባለው ፍላጎት እና አቅርቦት ገንዘብ ከዶላር አንጻር ሲመራ ነው። አሁን መንግስት የወሰነው በገበያው ላይ ባለው ፍላጎት እና አቅርቦት ገንዘብ ከዶላር አንጻር እንዲመራ ነው (floating exchange rate)።

- ብዙ floating እያደረጉ የሚመሩ ሀገራት አሉ ያደጉ ሀገራትን ጭምር።

- floating የሚመራው እንዴት ነው ? ብሔራዊ ባንክ 1 ዶላር በዚህ ብር ይመንዘር ማለት አይችልም። ለኢትዮጵያ ብር ያላቸው ፍላጎት ኢትዮጵያ ለውጭ ምንዛሬ ያላት ፍላጎት ዓለም አቀፍ ገበያው ላይ ያለው እንቅስቃሴ ከግምት ይገባል። ገበያው የዕለቱን ፍላጎት ይወስናል። በዕለቱ ዶላር በጣም ከተፈለገ ከፍ ይላል። ካልተፈለገ ዝቅ ይላል።

-  floating ለገበያ በጣም መጥፎ ላይሆን ይችላል ግን በቂ የዶላር reserve ኢኮኖሚው መያዝ አለበት። floating በተጀመረ በጀንበር ውስጥ ገበያው ብዙ ሊለዋወጥ ይችላል። ፍላጎት ካለ ዶላር አሁን ካለው በእጥፍ ሆኖ ሊያድር ይችላል።  ይህ ደግሞ ገበያውን ያናጋዋል። ስለዚህ ይሄን የሚያመጣጥን ብቂ የዶላር reserve በባንክ ቤቶች በብሄራዊ ባንክ ይዞ መገኘት ይገባል።

- floating ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ብቻ ነው ብሎ መናገር አይቻልም። የውጭ ጫና፣ ብድር ፣እርዳታ ፍለጋም ስላለበት ኢኮኖሚው ስለሚጠቀም ብቻ ሳይሆን የIMF ዓለም አቅፍ ተቋማትም ጫና ስላለ እሱን ለመቋቋምና በቀጣይ ትብብራቸውን ለማግኘት ሲባል ሊወሰን ይችላል።

- ገበያው በጣም shock / መናጋት የሚጠብቀው እንደሆነ ምንም ክርክር የሚያስፈልገው አይደለም። መጀመሪያ የሚሆነው import በጣም ውድ ያደርገዋል። floating ሲደረግ ገንዘብ devaluate መሆኑ / መዳከሙ አይቀርም። ይህ ማለት ወደ ጥቁር ገበያው ወዳለው ተመንና ከዛም ከፍ እያለ ነው የሚሄደው።

- ከባንክ ላይ 58 ብር ገዝተው / በጥቁር ገበያው ተመን ገዝተው ወደ ገበያው import ያደርጉ የነበሩ አሁን floating ከሆነ በጣም በከፍተኛ ገንዘብ 1 ዶላርን መግዛታቸው አይቀርም። በዚህም ከውጭ የገዙት ቁሳቁስ ሀገር ውስጥ ሲገባ ውድ መሆኑ አይቀርም። ይሄን መንግስትም የሚያምነው ነው።

-  ኢትዮጵያ ውስጥ ሸቀጣሸቀጥ ብቻ ሳይሆን ለProduction የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች import ይደረጋሉ፤ ስለዚህ ውድ መሆናቸው አይቀርም።

- ' በፍጹም ደመወዝ አልጨምርም ' የሚለው ዜና አሁን ደመወዝ እጨምራለሁ እደጉማለሁ እያለ ነው። ' ከነዳጅ ድጎማ እራሴን አወጣለሁ ' ይል የነበረው ዜና አሁን መደጎሜን እቀጥላለሁ እያለ ነው። ስለዚህ import ቁሳቁስ ውድ እንደሚሆን ያሳያል።

- floating የተወሰኑ አካላትን ተጠቃሚ ሊያደርግ ይችላል። ሌሎችን ተጎጂ ሊያደርግ ይችላል። ለምሳሌ ፦  በ58 ብር ተመን ጊዜ ዶላር ይዘው የነበሩ ሰዎች ምንዛሬ ሲጨምር የሆኑ አካላት ተጠቃሚ መሆናቸው አይቀርም በግልባጩም እንደዛው ነው።

- ብዙ ነገሮች import ስለሚድሩግ ገበያው ላይ ተፅእኖ ማሳደሩም አይቀርም።

- የውጭ ቀጥተኛ investment ላይ ማሻሻያው ጥሩ ጎን ሊኖረው ይችላል። አንድ ዶላር ይዞ የመጣ የውጭ ባለሃብት በ58 ብር ይገዛ ነበር አሁን floating ከሆነ devaluate ከተደረገ ይዞት የሚመጣው ከፍ ያለ ይሆናል ምንዛሬው።

- በቀጣይ ጊዜ የውጭ ባላሃብቶች ወደ ገበያ ብስፋት እንዲገቡ ሊያደርጋቸው ይችላል።

- በዚህ ወቅት floating መደረጉ ግን በግሌ በጣም አስደንጋጭ ነው። በዚህ ፍጥነት ይሆናል ብዬ አልገምትኩም። "

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-29-2

@tikvahethiopia
የሀገር ውስጥ በረራዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ ይኖር ይሆን ?

በኢትዮጵያ ከዛሬ ጀምሮ " በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት ወይም Floating exchange rate " ወደ ስራ መግባቱን ተከትሎ የሀገር ውስጥ በረራዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ ይኖር ይሆን ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጠይቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና የንግድ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ያዴቻ ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ በረራ አገልግሎት የሚሰጠው "በአብዛኛው የዜግነት አገልግሎት የመስጠት ግዴታ ስላለብን ነው "  ሲሉ ገልጸዋል።

አሁን ያለው ክፍያም የተወሰነ ወጪን ለመሸፈን የሚሆን እንደሆነ ገልጸዋል።

" እኛ ምንም የምንሰራው ነገር በውጪ ምንዛሬ ነው የምናመጣው ፤ እንደምታውቁት ነዳጅ ዋነኛው ነው። አሁን መንግስት ነዳጅ ላይ የሚያወጣውን ትዕዛዝ እንጠብቃለን። " ብለዋል።

ከዋጋ ጭማሪው ጋር ተያይዞ " የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ይኖራል የሚል እምነት የለኝም " ሲሉ ገልጸዋል።

ፖሊሲዎችንና አሰራሮችን በጥልቀት በመመልከትም በቀጣይ ግብረ-መልስ እንደሚሰጡም ጠቁመዋል።

" ትጨምራላችሁ ወይስ አትጨምሩም የሚለውም የሚወሰነው መንግስት ያወጣው ፖሊሲ አፈጻጸም መሬት ላይ ያለውን መመልከት ይኖርብናል። ነዳጅ ላይ ድጎማ ሊኖር እንደሚችል ጥቆማዎች አሉ ያ ከሆነ አብዛኛው ወጪያችንን እሱ ይወስዳል ስለዚህ ብዙ አይፈትነንም ማለት ነው " ሲሉ ገልጸውልናል።

ዋጋ ለመጨመር ገፊ ምክንያቶች ምን ምን ሊሆኑ ይችላሉ በሚል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርቧል።

እሳቸውም ፤ " መለዋወጫ እቃው በዶላር ነው፤ የአውሮፕላን ግዢ በዶላር ነው። በብር ደግሞ ብዙ የአገልግሎት ወጪዎች ይሸፈናሉ"  ሲሉ አንስተው "ወጪያችን ምን ያህሉ የዶላር ምን ያህሉ የብር ነው የሚለውን ካየን በኋላ ነው ተጽዕኖውን የምናየው " ሲሉ መልሰዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዛሬው የምንዛሬ ዋጋ ስንት ነው ? 💵 US Dollar #CASH Buying ➡️ 74.7364 Selling ➡️ 76.2311 #TRANSACTION Buying ➡️ 74.7364 Selling ➡️ 76.2311 💷 Pound Sterling #CASH Buying ➡️ 91.8787 Selling ➡️ 93.7162 #TRANSACTION Buying ➡️ 96.2081 Selling ➡️ 98.1322 💶 Euro #CASH…
#Ethiopia የግል ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ተመን ምን ይመስላል ?

እካሁን በርካታ የግል ባንኮች የዕለቱን የምንዛሪ ተመን ይፋ አልደረጉም።

ከግል ባንኮች መካከል የሆኑት አዋሽ ባንክና የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ ግን ተግባራዊ በተደረገው የፖሊሲ ማሻሻያ መሰረት ዕለታዊ የውጪ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ አድርገዋል።

ባንኮቹ ጥዋት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይፋ ካደረገው የምንዛሪ ተመን ጋር ተመሳሳይ አይነት ነው።

በዚህም ፤ ባንኮቹ አንዱን የአሜሪካ ዶላር በ74 ብር ከ7394 ሳንቲም እየገዙ በ76 ብር 2342 እየሸጡ ነው።

ፓውንድ በ91 ብር ከ8824 ሳንቲም እየገዙ በ93 ብር ከ7201 ሳንቲም እየሸጡ ይገኛል።

ዩሮ በ81 ብር ከ0401 ሳንቲም እየገዙ በ82 ብር 6608 ሳንቲም እየሸጡ ነው።

#Ethiopia #Dollar #EUR #GBP

@tikvahethiopia
#Jasiri

" We are convinced that the biggest challenge facing the continent is youth unemployment, and that focused support of entrepreneurship will have the greatest leverage for ensuring meaningful employment. We intend to pursue a long-term strategy of developing exceptional and responsible entrepreneurs," Anthony Farr, Group CEO of Allan & Gill Gray Philanthropies in Africa.

Apply now for Cohort 7 at jasiri.org/application!

#Jasiri4Africa
#SafaricomEthiopia

* 400,000 ብር?? * በዛ ላይ ደግሞ አስቡት የእናንተ ሙዚቃ በመላው ኢትዮጵያ ሲደመጥ...እናንተ ችሎታው ይኑራችሁ የቀረውን በእኛ ጣሉት! አሁኑኑ የአንድ ደቂቃ ቪዲዮአችንን እንላክ!

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፡
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበትከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳንረሳ
📲የTikTok ደረገጽ @Safaricomet ታግ እናድርግ

እንዝፈን! ፖስት እናድርግ! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!
እንዳያመልጣችሁ!

#SafaricomEthiopia #1Wedefit
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirlines🇪🇹 " የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ውሳኔውን መልሶ እንዲያጤነው እንጠይቃለን ፤ ይህ የማይሆን ከሆነ የሚጎዱት ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ናቸው " - " አቶ መስፍን ጣሰው የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚያደርገው በረራ ከመስከረም 30 / 2024 ጀምሮ እንዲቆም የሚያሳውቅ ደብዳቤ መላኩን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው…
#Ethiopia : የኢትዮጵያ አየር መንገድ በህይወት ያሉ እንሰሳትን በማጓጓዝ ላይ ስለሚቀርበው ቅሬታ ምን ምላሽ ሰጠ ?

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፦

" ይህ ጉዳይ ዓለም አቀፍ አሰራር ስለሆነ መስፈርቱን ጠብቀን አገልግሎቱን እንሰጣለን።

ጫጩት እናጓጉዛለን፤ በጎች የምናጓጉዝበት ጊዜ ነበረ፤ ፍየሎች እናጓጉዛለን። በአንድ ወቅት አሁን እንኳን አይደለም ላሞችና በሬዎች በህይወት እያሉ እናጓጉዝ ነበረ።  አሁን ዝንጀሮዎች አጓጓዛችሁ ነው የሚሉን።

ህጋዊ ፈቃድ የተሰጠው ከአሜሪካም ከሌላም ሀገር ህጋዊ ፈቃድ የተሰጠው ድርጅት እስከመጣ ድረስ ያንን የዓለም አቀፍ ህጉን ተከትለን እናጓጉዛለን።

ጥያቄ የእንስሳት ተቆርቋሪ ነን የሚሉ አካላት ናቸው የሚያነሱት መነሻቸው ' ዝንጀሮዎቹ  ወደ እዛ ሄደው ለላብራቶሪ አገልግሎት ነው የሚውሉት ' የሚል ነው። ይሄ ግን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ኃላፊነት አይደለም።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ተቋም ነው እንደ ንግድ ተቋም ነው የሚሰራው። "


#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia : የኢትዮጵያ አየር መንገድ በህይወት ያሉ እንሰሳትን በማጓጓዝ ላይ ስለሚቀርበው ቅሬታ ምን ምላሽ ሰጠ ? የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፦ " ይህ ጉዳይ ዓለም አቀፍ አሰራር ስለሆነ መስፈርቱን ጠብቀን አገልግሎቱን እንሰጣለን። ጫጩት እናጓጉዛለን፤ በጎች የምናጓጉዝበት ጊዜ ነበረ፤ ፍየሎች እናጓጉዛለን። በአንድ ወቅት አሁን እንኳን አይደለም ላሞችና በሬዎች በህይወት…
#Ethiopia : የኢትዮጵያ አየር መንገድ " #ወታደሮችን ያጓጉዛል " በሚል ለሚነሳትበት ቅሬታ ምን ምላሽ ሰጠ ?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሀገር ውስጥ ባሉ ግጭቶች ላይ ' ወታደር በማጓጓዝ ይሳተፋል ' የሚል ቅሬታዎች ይነሱበታል።

ይሄ ጉዳይ ከዓለም አቀፍ የበረራ ህጎች ጋር አይጻረርም ወይ ? በሚል የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ መስፍን ጣሰው ምን አሉ ?

" ወታደሮች በአውሮፕላኖች የሚሄዱበት አሰራር አለ።

በዚህ ረገድ አየር መንገዱ ዓለሞ አቀፍ አሰራሮችን ጠብቆ ነው የሚሰራው።

ለማሳያነት አየር መንገዱ ሁለት አውሮፕላኖችን መድቦ ለUN ወታደር ብቻ የሚያጓጉዝበት አሰራር አለ።

በተለይ አንደኛው አውሮፕላን ለዚሁ ግልጋሎት ብቻ የተመደበ ነው።

ሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ከሀገር አገር አጓጉዘናል ፣ የአፍሪካ ጸጥታ አስከባሪ ወታደሮችን ስናጓጉዝ ነው የኖርነው፤ እናጓጉዛለን፥ ያ ማለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጦርነት ላይ ተሳተፈ ማለት አይደለም።

ይሄን ሁሉ ስናደርግ ገንዘብ እያስከፈልን እኮ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወታደሮችን ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ ወታደር አንዲያጓጉዝ ጥያቄ ቀርቦለት ያውቃል።

ውሰዱልን ተብለን ተጠይቀን ነበር በዛ መሰረት ገንዘብ አስከፍለን ወታደሮችን ልክ ለUN እንደምናደርገው አድርገናል።

ወታደሩ ምን ያደርጋል ያ የእኛ ኃላፊነት አይደለም። ነገር ግን ወታደር በአውሮፕላን ሲጓዝ መደረግ ያለባቸው መስፈርቶች አሉ እነዛን አድርገን እንሰራለን።

ከዚህ በፊት ' ወታደሮች ስለምታጓጉዙ አውሮፕላኖችን ፋይናንስ አናደርግላችሁም ' ተብለን እናውቃለን እኛ አሰራራችንን አስረድተን፤ አሰራራችን ከዓለም አቀፉ አሰራር ጋር አብሮ የሚሄድ መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ አውሮፕላኖቻችንን እንድናመጣ አድርገውናል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ተቋም ነው እንደ ንግድ ተቋም ነው የሚሰራው። "

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ 87 በመቶ የሚሆኑት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የዘንድሮውን የመውጫ ፈተና ማለፍ እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

22 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ገልጸዋል።

የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው አጠቃላይ ተማሪዎች መካከል ማሳለፍ የቻሉት 13 በመቶ ብቻ ነው ብለዋል።

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ካስፈተኗቸው ተማሪዎች 58 በመቶ ማሳለፋቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎች ይኖሩናል።

#ETA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የግል ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ተመን ምን ይመስላል ? እካሁን በርካታ የግል ባንኮች የዕለቱን የምንዛሪ ተመን ይፋ አልደረጉም። ከግል ባንኮች መካከል የሆኑት አዋሽ ባንክና የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ ግን ተግባራዊ በተደረገው የፖሊሲ ማሻሻያ መሰረት ዕለታዊ የውጪ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ አድርገዋል። ባንኮቹ ጥዋት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይፋ ካደረገው የምንዛሪ ተመን ጋር ተመሳሳይ አይነት…
#Ethiopia

ተግባራዊ በተደረገው የፖሊሲ ማሻሻያ መሰረት የግል ባንኮች ዕለታዊ የውጪ ምንዛሬ ተመናቸውን ይፋ እያደረጉ ይገኛሉ።

ከላይ የተወሰኑ ባንኮች የዛሬ ዕለታዊ ምንዛሬ ተያይዟል።

ከላይ ከተያያዙት የአብዛኞቹ ቀደም ብሎ ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የምንዛሬ ተመን ጋር ተመሳሳይ ነው።

በአንጻሩ ሲዳማ ባንክ የውጭ ምንዛሬው ከሌላው ከፍ ያለ ነው።

ሲዳማ ባንክ አንዱን የአሜሪካ ዶላር በ76 ብር ከ2311 ሳንቲም እየገዛ በ77 ብር ከ7557 ሳንቲም እየሸጠ ነው።

ፓውንድ ስተርሊንግ በ93 ብር ከ7163 ሳንቲም እየገዛ በ95 ብር ከ5906 እየሸጠ ይገኛል።

ዩሮ በ82 ብር ከ6574 ሳንቲም እየገዛ በ84 ብር ከ3105 ሳንቲም እየሸጠ ይገኛል።

ዛሬ ተግባራዊ በተደረገው በገበያ ላይ የተስመረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን / Floating exchange rate ባንኮች ከደንበኞቻቸው ጋር በሚያደርጉ ነጻ ድርድር የውጭ ምንዛሬ መግዛት እና መሸጥ እንዲችሉ ይፈቅዳል።

በመሆኑም በዕለቱ ፍላጎት ገበያው ይወሰናል።

ብሔራዊ ባንክ ከአሁን በኋላ ለባንኮች አንድ ዶላር በዚህ ብር መንዝሩ አይልም ፤ ስራው ገበያውን በማረጋጋት ላይ ያተኮረ ነው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia