TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ በተገነቡት መሰረተ ልማቶች ላይ ቆሻሻ የጣሉ ፣ ከተፈቀደላቸው መንገድ ውጪ የሄዱ እንዲሁም በመንገድ አካፋዮች ላይ የተተከሉ ዛፎችን ' በግዴለሽነት ' በተሽከርካሪ በመግጨት ጉዳት ያደረሱ አካላት መቀጣታቸውን አሳውቋል።

3 ተቋማት ከተፈቀደ ቦታ ውጪ ቆሻሻ በመጣል እንደየጥፋት ደረጃቸው 100 ሺሕ ፣ 50 ሺ እና 20 ሺሕ ብር ተቀጥተዋል።

5 አሽከርካሪዎች በመንገድ አካፋይ ላይ የተተከሉ ዘንባባ ዛፎችን ገጭተው በመጣላቸው እንደየጥፋት ደረጃቸው ከ150 እስከ 300 ሺሕ ብር መቀጣታቸውን አሳውቋል።

11 ሰዎች ደግሞ ከተፈቀደው የእግረኞች መንገድ ውጪ በመሄዳቸው ከ150 እስከ 1000 ብር እንደተቀጡ ገልጿል።

ነዋሪዎች የተገነቡትን መሰረተ ልማቶች እንዲጠብቁ እና እንዲንከባከቡ ራሳቸውንም ከቅጣት እና ከትራፊክ አደጋ እንዲከላከሉ ጥሪ አቅርቧል።

(የቅጣት ደረሰኞቹ ከላይ ተያይዘዋል)

#AddisAbaba #MayorOffice

@tikvahethiopia
#EthioTelecom

ኢትዮ ቴሌኮም የ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርትን በዛሬው እለት አቅርቧል።

የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ሪፖርቱን በማቅረብ ገለፃ አድርገዋል።

በዚህም ተቋሙ አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢውን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት በ21.7% ወይም በ16.7 ቢሊዮን ብር በማሳደግ 93.7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል።

21.79 ቢሊዮን የተጣራ ትርፍ ነው።

የእቅዱን 103.6% ማሳካቱንም አሳውቋል።

ተቋሙ የቴሌኮም ደንበኞቹንቁጥር ከአምና ተመሳሳይ ወቅት በ8.9% በማሳደግ 78.3 ሚሊዮን አድርሶ የእቅዱን 100.4% ማሳካቱን ገልጿል።

ቴሌኮሙ በበጀት አመቱ የቴሌኮም እና የዲጂታል መሰረተልማት አቅምን ለማሳደግ ምን ሰራ ?

- የ4G ኔትወርክ አገልግሎትን ወደ 124 ተጨማሪ ከተሞች እና ወረዳዎች በማስፋፋት በአጠቃላይ 4G ተደራሽ የሆነባቸውን ከተሞች ቁጥር ከ300 ወደ 424 ማሳደጉን ገልጿል።

- በተጨማሪም በ79 የሞባይል ጣቢያዎች ላይ የ5G የኔትወርክ ማስፋፊያ ስራ በማከናወን የ5ጂ ጣቢያዎችን ቁጥር ወደ 189 ማድረስ እንደቻለ ጠቁሟል።

- አዲስ አበባን ጨምሮ 5 የከልል ዋና ከተሞችን የ5G ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ተጨማሪ 4 ከተሞችን የ5G ተጠቃሚ ለማድረግ የትግበራ ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ተብሏል።

የዲጂታል ገንዘብ ዝውውር እና የተቋሙ የሞባይል ገንዘብ ቴሌብር አፈፃፀም ምን ይመስላል ?

- ቴሌኮሙ የቴሌብር ደንበኞቹን ብዛት 47.55 ሚሊዮን በማድረስ የእቅዱን 107.8% ማሳካቱን አሳውቋል።

- የገንዘብ ዝውውርን በቴሌብር ዲጂታላይዝ በማድረግ በበጀት አመቱ 1.81 ትሪሊዮን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ዝውውር በቴሌብር
ተከናውኗል።

- አገልግሎቱ ከተጀመረ (May 11, 2021) ጀምሮ አጠቃላይ በኢኮኖሚው ላይ 2.55 ትሪሊየን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ማንቀሳቀስ ተችሏል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ልጆቻችን ... በማይናማር !

በርካታ የሀገራችን ልጆች ፦
- የወጣትነት እድሜያቸው ሳያልፍ ህይወታቸውን ለመቀየር፣
- ደክመው ያሳደጓቸውን ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ እንዲሁም፣
- እድሜያቸው ሳይገፋ ቤተሰብ መስርተው ጥሩ ኑሮ ለመኖር ሲሉ ወደ ተለያዩ ሀገራት ይሰደዳሉ።

አንዳንዶቹ እጅግ አደገኛ ነው የተባለውን የህገወጥ ስደት በእግር ፣ በበረሃ ፣ በባህር አድርገው ይጓዛሉ።

አንዳንዶች ደግሞ እዚሁ ሀገር ውስጥ በየከተማው በተቀመጡ ደላሎች ማካኝነት ተታለው ምንም እንኳ በኤርፖርት በኩል ከሀገር ቢወጡም የሚሄዱት ግን መጀመሪያ ወደ ተባለው ቦታ ሳይሆን ሌላ እጅግ አደገኛ ቦታ ነው።

ለአብነት ማይናማር ይጠቀሳል።

የሀገራችንን ልጆች ' ታይላንድ ነው ለስራ የምትሄዱት ' ተብለው በደላሎች ተታለው ከሀገር የሚወጡ ሲሆን የሚወሰዱት ግን ወደ ማይናማር (ማያዋዲ) ነው።

ማይናማር ከደረሱ በኋላ የሚወሰዱት የቻናይና ማፊያ ቡድኖች ወደያዟቸው ቦታዎች እጅግ ደህንነት ወደ ሌለባቸው ስፍራዎች ነው።

በዛም የተለያዩ ህገወጥ ስራዎችን እንዲሰሩ በኃይል ያስገድዷቸዋል።

ከኢትዮጵያ ሲወሰዱ 1200 ዶላር እንደሚከፈላቸው ቢነገራቸውም እዛ ከደረሱ በኋላ ግን ለወራት ጉልበታቸውን ይበዘብዙታል። ስቃይና መከራ ይደርስባቸዋል።

ልጆቹ ድብደባ ፣ በኤሌክትሪክ ሾክ፣ በሰንሰለት መገፈ ጭምር ነው የሚደርስባቸው።

ያለ ምግብ መጠጥ እስርም ይፈጽምባቸዋል።

ህይወታችንን እንቀይራለን ብለው የሄዱት ወጣቶች በስቃይ እና መከራ ውስጥ ያልፋሉ። ለወራት ያህል ስራ እያሉ እያሰሯቸው በኪሳቸው አንድም ብር የላቸውም።

በነገራችን ላይ በስፍራው የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የሌሎች በርካታ ሀገር ዜጎችም አሉ።

አንዳንድ ሀገራትም ልጆቻቸውን ያስወጣሉ።

በታይላንድ ጎረቤት፣ ማይናማር (በርማ፣ ማይዋዲ) የሚገኙ ' ድረሱልን ፍትህ እንሻለል ' ሲሉ ቃላቸውን የሰጡ የሀገራችን ልጆች፦

- ለስራ ተብለው ወደ ታይላንድ የሄዱ ከ1500 በላይ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ፤

- በአሁን ሰዓት ላይ የሚገኙት ማይናማር (በርማ) ፤ ማያዋዲ (Myanmar-Myawaddy) በሚባል ቦታ እንደሆነ፤

- በህገወጥ የቻይና ጋንጎች ተይዘው በአሰሪዎች ከፍተኛ ግፍ እየተፈጸመ እንዳለ፤

- በግዴታ ህገወጥ ስራ (ሰዎችን በማጭበርበር ገንዘብ መቀበል / Online Scamming) ስራ የሚያሰሯቸው እንደሆነ፤

- ከፍተኛ ድብደባ፣ የኤሌክትሪክ ቶርቸር፣ ሴቶችን መድፈር ፣ ምግብ መከልከል እንዲሁም እስከ መግደል የሚደርስ ግፍ እየተፈጸመ እንደሆነ፤

- እስከ አሁን በርካታ ሰዎች በድብደባና ቶርቸር ብዛት ህይወታቸው እንዳለፈ፤

- ካሉበት የስቃይ ቦታ ነጻ ወጥተው ወደ ሀገራቸው መመለስ እንዲችሉ የህዝብንና የመንግስትን እገዛ እንደሚያስፈልጋቸው፤

- በኤጀንሲዎች በኩል ወደ ታይላንድ ለስራ ለመሄድ ፕሮሰስ ላይ ያሉ ወገኖችም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ

... ድምጻቸው አሰምተዋል።

በዚህ ጉዳይ ተጨማሪ መልዕክቶች በተከታታይ እናጋራለን።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

🎉 የምስራች!  🎁 ተወዳጆቹ ሜጋ ጥቅሎች ተመልሰው መጥተዋል! ለ90 እና ለ180 ቀን የሚቆዩትን ልዩ የኢንተርኔት ጥቅሎች በM-PESA በመግዛት እስከ 500 ብር የሚደርስ ቅናሽ አግኝተን ፏ እንበል! 🌐🤳
  
🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://t.me/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት ከነገ ግንቦት 28 /2016 ዓ/ም ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በስራ ላይ በነበረበት ዋጋ እንዲቀጥል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል። ስራ ላይ ያለው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ስንት ነው ? - ቤንዚን ➡️ ብር 78.67 በሊትር - ነጭ ናፍጣ ብር 79.75 በሊትር - ኬሮሲን ብር 79.75 በሊትር - የአውሮፕላን ነዳጅ ብር 70.83 በሊትር …
የነዳጅ  ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

ቤንዚን በሊትር 82 ብር ከ60 ሳንቲም ሲገባ ነጭ ናፍጣ 83 ብር ከ74 ሳንቲም ሆኗል።

ከዛሬ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ከአይሮፕላን ነዳጅ በስተቀር በቤንዚን፣ በኬሮሲን፣ በነጭ ናፍጣ፣ በቀላል ጥቁር ናፍጣ እና በከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተሰምቷል።

በዚህ መሰረት ፦

ቤንዚን - ብር 82.60 በሊትር
ነጭ ናፍጣ - ብር 83.74 በሊትር
ኬሮሲን - ብር 83.74 በሊትር
ቀላል ጥቁር ናፍጣ - ብር 65.48 በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ - ብር 64.22 በሊትር  ሆኗል


የአውሮፕላን ነዳጅ በሊት 70 ብር ከ83 ሳንቲም ሆኖ ባለበት ይቀጥላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update (ቅዳሜ ሰኔ 29/2016 ዓ/ም) ስለ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ታጋች ተማሪዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ ? በታጣቂዎች ስለታገቱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ፣ የግቢው የወንጌላውያን ተማሪዎች ህብረት እና የታጋች ቤተሰብን ምን አዲስ አለ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬም ጥያቄ አቅርቧል። የታጋች ቤተሰቦች አጋቾቹ ወደ 20 የሚሆኑ ታጋቾችን ከትላንት ጀምሮ ወደ ማያውቁትና ጫካ በበዛበት…
#Update (No. 5)

የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ቤተሰብ እየተመለሱ በነበሩበት በታጣቂዎች ስለታገቱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተደጋጋሚ መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።

ዛሬስ ምን አዲስ ነገር አለ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለታጋቾቹ ምን አዲስ አለ ? ሲል የተማሪ ወላጆችን የወንጌላውያን ተማሪዎች ህብረት፣ ደርባርቅ ዩኒቨርሲቲ እና ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።

ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ወቅት ድረስ ከእገታው ያልተለቀቁ ተማሪዎች እንዳሉ ወላጆች ቃላቸውን ሰጥተዋል።

አጋቾቹ አሁንም ለአንድ ተማሪ ግማሽ ሚሊዮን ብር እንደጠየቋቸው፣ ያሰባሰቡትን የተወሰነ ገንዘብ ልከው ታጋቾቹን እንዲለቁላቸው ቢማጸኑም ገንዘቡ ካልተሟላ እንደማይለቋቸው ገልጸዋል።

በርካታ ተማሪዎች አሁንም እንደታገቱ መሆናቸውን እንዳረጋገጡ የገለጹት ሁለት የታጋች ቤተሰቦች፣ ጉዳዩ በሚዲያ እየተንሸራሸረ ስለሆነ መንግስት ሰምቷል ፤ ታዲያ ለምን መፍትሄ አይሰጠንም ? ሲሉ ጠይቀዋል።

የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው አንድ ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ አካል፣ ትንሽ ታጋቾች ቢለቀቁም አብዛኛዎቹ ገና እንደሆኑ መስማታቸውን ተናግረዋል።

ከዚህ የተለዬ መረጃ ግን እንዳልተገኘ አስረድተዋል።

ከትምህርት ሚኒስቴር ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረበላቸው ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉ አቶ አብዱ ናሲር፣ ስለጉዳዩ ከፍተኛ አመራሮች እንዲጠየቁ ከመናገር ውጪ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

በዩኒቨርሲቲው የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት በሰጠው ቃል፣ ታጋቾቹ ወደ ወለጋ መስመር እንደተወሰዱ መስማቱን ገልጿል።

በሌላ በኩል ፥ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) 138 ታጋቾች እንደተለቀቁ መግለጹን ሪፓርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ደግሞ በሸኔ ታግተው የነበሩት 167 ተማሪዎች ናቸው ከነዚህ ውስጥ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ባካሄዱት ኦፕሬሽን 160ዎቹ ከእገታ ተለቀዋል ብሏል።

ይህንን የመረጃና በየሚዲያው " አብዛኛው ተለቀዋል " እየተባለ የሚሰራጨውን መረጃ ተመልክተው ከደቂቃዎች በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መልዕክት የላኩ የተማሪ ወላጆች በጣም እንደተበሳጩ ገልጸው " ውሸት ባይዘገብስ " ሲሉ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ልጆቻችን ... በማይናማር ! በርካታ የሀገራችን ልጆች ፦ - የወጣትነት እድሜያቸው ሳያልፍ ህይወታቸውን ለመቀየር፣ - ደክመው ያሳደጓቸውን ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ እንዲሁም፣ - እድሜያቸው ሳይገፋ ቤተሰብ መስርተው ጥሩ ኑሮ ለመኖር ሲሉ ወደ ተለያዩ ሀገራት ይሰደዳሉ። አንዳንዶቹ እጅግ አደገኛ ነው የተባለውን የህገወጥ ስደት በእግር ፣ በበረሃ ፣ በባህር አድርገው ይጓዛሉ። አንዳንዶች ደግሞ እዚሁ ሀገር…
ደላሎችም ይሁኑ ' ወደ ውጭ ሀገር እንልካችሏለን ' የሚሉ ኤጀንሲዎች የት እና ለምን ስራ እንደሚልኳቹ በደንብ አጣሩ !!

ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ወጣቶችን " ለብሩህ ተስፋ፣ ለጥሩ ህይወት ጠቀም ያለ ገንዘብ የሚያስገኝ ስራ በታይላንድ አለ " በማለት ወጣቶቻችንን ለከፋ የስቃይ ህይወት የሚዳርጉ ሰዎች አሉ።

አንዳንዶቹ ጭራሽ ወደ አሜሪካ ፣ ካንዳ እና አውሮፓ ሀገራት ነው የምንልካችሁ በማለት የሚያጭበረብሩ ናቸው።

በእነዚህ ደላሎች እና ኤጀንሲዎችም ጭምር ተታለው ታይላንድ ተብለው የሚሄዱ ሰዎች እጅግ አስከፊ ስቃይ እና ዓለም አቀፍ የማጭበርበር ወንጀል ወደ ሚሰራበት በታይላንድ አቅራቢ ወዳለችው ማይናማር (ድንበር ላይ) ወዳለ ካምፕ ያስገቧቸዋል።

ይህ ሁሉ የሚሆነው በኃይል ነው።

ታይላንድ የደረሱ ወጣቶች ገና ኤርፖርት ላይ ሲደርሱ ተቀባይ አላቸው።

" እፎይ አሁን ህይወታችን ሊቀየር ነው ወደ ሆቴል / ወደምንሰራበት ስፍራ ሊወስዱን ነው " ብለው ሲጠብቁ ከከተማ ውጭ በተቃራኒ መንገድ በመኪና ረጅም ጉዞ ያስጉዟቸውና ወደ አደገኛው የማፍያዎች ስፍራ ያስገቧቸዋል።

እነዚህ ቦታዎች የደህንነት ካሜራ ገና ከበር ጀምሮ ያላቸው፣ መሳሪያ በታጠቁ ሰዎችም የሚጠበቁ ሲሆኑ ማፍያዎቹ ወጣቶቹን በማስገባት ህገወጥ ስራ እንዲሰሩ ያስገድዷቸዋል።

ይኸው ህገወጥ ስራ ዓለም አቀፍ የሆነ የኦንላይን የማጭበርበር ስራ ነው።

ወጣቶቹ በይቆታቸው ፦
- አሰቃቂ ድብደባ ይደርስባቸዋል፣
- ምግብ ይከለከላሉ፣
- ሴቶች ይደፈራሉ፣
- ማሰቃየት (በኤሌክትሪክ ሾክ) ይፈጸምባቸዋል፣
- በሰንሰለት ይታሰራሉ፣
- በኤሌክትሪክ ሽቦ ይገረፋሉ።

እስከ ግድያም ሊደርስ ይችላል።

ህይወታችን ይቀየራል ብለው ከፍተኛ ዋጋ ከፍለው የሄዱ ወጣቶች ለወራት አንድም ብር ሳያገኙ ጭራሽ ህይወታቸው በስቃይ ይሞላል።

እድለኞች ከብዙ ስቃይ በኋላ ይወጣሉ።

አሁንም የውጭ ሀገር ፕሮሰስ እያደረጋችሁ ያላችሁ የሀገራችን ልጆች የት ? ለምን ? ስራ እንደምትሄዱ ጠይቁ መርምሩ።

አሁን ላይ በማይናማር እና ታይላንድ ድንበር በሚገኝ ስፍራ እንደ ባርነት የተያዙ የበርካታ ሀገራት ወጣቶች አሉ።

ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የሚመለከተው አካል ይህን ጉዳይ ተከታትሎ እንዲደርስላቸው ተማጽነዋል።

ታይላንድም ይሁን አሜሪካ ፣ ካናዳም ይሁን አውሮፓ ደህንነቱ የተጠበቀ ህጋዊ ስራ ካልሆነ ባትሄዱ ይመከራል።

የሚልኳችሁን ሰዎች በትክክል የት ነው የምንሄደው ? የምናርፈው የት ነው ? የድርጅቱ ስም ምንድነው ? የመስሪያ ፍቃዱ የታለ ? አድራሻው የታለ ? ከዚህ በፊትም የሄዱ ልጆችን አገናኙን ብላችሁ ጠይቁ።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Africa #Kenya

" በሙስና የተዘፈቀውን ካቢኔዎትን ይበትኑ ! " - የኬንያ አብያተ ክርስቲያናት ብሔራዊ ምክር ቤት

ምንም እንኳን ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ የፋይናንስ ረቂቅ አዋጁን ቢሰርዙም ተቃውሞው ቀጥሏል።

የኬንያ አብያተ ክርስትያናት ፕሬዜዳንቱ ካቢያናቸውን እንዲበትኑ ጠይቀዋል።

የቤተክርስቲያን መሪዎች እና በርከታ ኬንያውያን ሩቶ በሀገሪቱ የተንሰራፋውን ሙስና እንዲያጸዱ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

የኬንያ አብያተ ክርስቲያናት ብሔራዊ ምክር ቤት ፥ " የሩቶ አስተዳደር በመጥፎ አመራር እና የሙስና ክሶች ተጨማልቋል " በማለት የታቅውሞውን ድምጽ ተቀላቅሏል።

ምክር ቤቱ ፥ ሩቶ ሚኒስትሮቻቸውን እንዲያባርሯቸው ጠይቋል።

" ፕሬዚዳንቱ በራሳቸው አንደበት ካቢኔያቸው ብቃት እንደሌለው ተናግረዋል። ኬንያውያንም የፕሬዜዳንቱ ካቢኔ ምንም ብቃት የለውም እያሉ ነው። በተጨማሪ አብዛኛዎቹ የካቢኔ አባላቶች ሙስና ውስጥ የተዘፈቁ ናቸው። ኬንያውያን ካቢኔውን የመበተኛ ጊዜ አሁን ነው እያሉ ነው " ሲል ገልጿል።

በኬንያ የፋይናንስ ረቂቁ ባስነሳው ተቃውሞ ቢያንስ 40 ሰዎች መገደላቸው፤ 380 ሰዎች መጎዳታቸው ፣ ታቃዋሚዎችም ፓርላማውን በመውረር የምክር ቤት አባላት እንዲሸሹ ከሆኑ በኃሏ ሩቶ ረቂቁን ውድቅ አድርገው ነበር።

ሩቶ ከቀናት በፊት ፦
- ቁልፍ ሚኒስትሮችን እና የመንግስት ተቋማትን ማዋሃድ
- የመንግስት መኪናዎች ለ12 ወራት እንዳይገዙ መከልከል
- የመንግስት ባለስልጣናትን አላስፈላጊ የውጭ ጉዞ ማገድን ጨምሮ የተለያዩ የወጪ ቅነሳ እርምጃዎችን ይፋ አድርገው ነበር።

ነገር ግን ተቃውሞው ቀጥሎ ፕሬዜዳንቱ በመስና ተዘፍቋል የተባለውን ካቢኔ እንዲባትኑ ግፊት እየተደረገ ነው።

የኬንያ ፖለቲካ ተንታኝ ዲስማስ ሙአኮ " ፍርድ ቤት አንዳቸውንም በምንም ነገር ጥፋተኛ እስካላላቸው ድረስ ፕሬዜዳንት ሩቶ ሰዎች እንዲባረሩ ስለጠየቁ ብቻ የካቢኔ አባሎቻቸውን የማባረራቸው እድል ዜሮ ነው " ብለዋል።

" ነገር ግን፣ በጣም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የኑሮ ውድነቱ ነው። የኢኮኖሚውን ሁኔታ በማሻሻል እና ለኑሮ ውድነቱ መፍትሄ በማምጣት የመንግስት እዳ በአብዛኛው ኬንያውያን ዜጎች ላይ የማይወድቅ መሆኑን ማረጋገጥ ከቻሉ ህዝቡም ተረጋግቶ እስከ 2027 ድረስ (የፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ) መጠበቅ ይችላል " ሲሉ አክለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከቪኦኤ ነው ያገኘው።

#Kenya

@tikvahethiopia
" ሚዲያዎች የመንግስት፣ በተለይም የኔ ደጋፊ መሆን አይጠበቅባችሁም !! " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ

ትላንትና ሐምሌ 3 /2016 ዓ/ም በኢትዮጵያ በሕጋዊ መንገድ በ ' ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ' ስር ተመዝግበው ለሚንቀሳቀሱ የመንግስት እና የግል ሚዲያ ተቋማት በኮሚኒኬሽን አገልግሎት በኩል የእውቅና እና ሽልማት መርሀግብር ተዘጋጅቶ ነበር።

በስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው የነበሩት ጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ (ዶክተር) መልዕክት አስተላልፈው ነበር።

ከጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) መልዕክት ፦

➡️ " ሚዲያዎች
የመንግስታት ደጋፊ መሆን አይጠበቅባችሁም ፤ በተለይም የኔ ደጋፊ መሆን አይጠበቅባችሁም። የሚጠበቅባችሁ እውነትን ብቻ መግለጥ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምን በማስቀደም እውነትን መግለጥ እና ማሳየት ከቻላችሁ ሚናችሁን በደምብ ተወጣችሁ ማለት ነው። "

➡️ " በሚዲያዎች የሚተላለፉ መረጃዎች የብሔራዊ ጥቅምን ታሳቢ ማድረግ አለባቸው ፤ የሀገሪቱን ህልውና አደጋ ውስጥ የማይከቱ መሆን አለባቸው። "

➡️ " ያደገ ሀገር ሲኖር ነው ያደገ ሚዲያ የሚኖረው በሀገር ጉዳይና እድገት ላይ በጋራ ፣ በትብብርና እና በስምምነት መስራት ይገባናል። "

➡️ " የእውቅና መርሀግብሩ ሙሉ ላይሆን ይችላል። ለሚዲያ እውቅና ሰጥተን ስለማናውቅ ባልተገባ መንገድ እውቅና ሰጥተን ሊሆን ይችላል። የቀራችሁ ሚዲያዎች መጀመራችን በራሱ ትልቅ እርምጃ እንደሆነ ተገንዘቡልን። በቀጣይ እየታረመ ይሄዳል። "


ከሽልማቱ በኋላ በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሽልማቱ ተመሳሳይ አይነት አቋም ያላቸው እና የመንግስትን አቋም ብቻ የሚያንጸባርቁ ሚዲያዎች ተመርጠው ነው የተሸለሙት በማለት ሲኮንኑ ታይተዋል።

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-11-3

#Ethiopia #GoECommunication

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ደላሎችም ይሁኑ ' ወደ ውጭ ሀገር እንልካችሏለን ' የሚሉ ኤጀንሲዎች የት እና ለምን ስራ እንደሚልኳቹ በደንብ አጣሩ !! ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ወጣቶችን " ለብሩህ ተስፋ፣ ለጥሩ ህይወት ጠቀም ያለ ገንዘብ የሚያስገኝ ስራ በታይላንድ አለ " በማለት ወጣቶቻችንን ለከፋ የስቃይ ህይወት የሚዳርጉ ሰዎች አሉ። አንዳንዶቹ ጭራሽ ወደ አሜሪካ ፣ ካንዳ እና አውሮፓ ሀገራት ነው የምንልካችሁ…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#Myanmar

ይህ የ ' DW ዶክመንተሪ ' #በማይናማርና #ታይላንድ ድንበር ባሉ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ሰዎችን ከተለያዩ የዓለም ሀገራት በማዘዋወር ስለሚሰሩ ዓለም አቀፍ የኦንላይን ማጭበርበር (scam) ስራዎችን በግልጽ የሚያሳይ ነው።

የሰው አዘዋዋሪዎች ሰዎችን የሚያዘዋውሩት በቅድሚያ ታይላንድ / የአውሮፓ ሀገራት እንደሆነ በመግለጽ እና ጠቀም ያለ ገቢ እንደሚገኝ በመንገር ጭምር ነው በኋላ የሚሰራው ማጭበርበር (Online Scam) ነው።

ቦታዎቹ ብዙ ናቸው።

ልክ እንደ ካምፕ አይነት ሲሆኑ ከነዛም ውስጥ ብዙ እንግልት እና ስቃይ የሚደርስባቸው አሉ።

ገና እንደሄዱ ስልካቸውን የሚቀሙ ፣ ፍጹም ኢሰብዓዊ አያይዝ የሚያዙ፣ ካልሰሩ የሚደበደቡ ፣ ስቃይ የሚፈጸምባቸው አሉ።

ከነዚህ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ይገኙበታል።

አንድ ለቲክቫህ መልዕክቱን የላከ ወጣት በደረሰበት ድብደባ ለወራት ያህል በክራንች ለመሄድ መገደዱን ጠቁሟል።

በሌላ በኩል በዛው በማይናማር በስልክ ያነጋገርናቸው አንዳንድ ወጣቶች በማይናማርና ታይላንድ ድንበር የሚፈጸሙ ጉዳዮች ከአንድ ቦታ ሌላ ቦታ እንደሚለያዩ አስረድተው እነሱ በሚኖሩበት ምንም አይነት ስቃይ ይሁን ችግር ደርሶባቸው እንደማያውቅ ተናግረዋል።

ስልክም ሆነ ሌሎች አይነት ኤሌክትሮኒክስ ነገሮችን ተከልክለው እንደማያውቁ አስረድተዋል።

አሁንም የውጭ ፕሮሰስ ላይ ያላችሁ የት ሀገር ፣ በምን ስራ ዘርፍ እንደምትሄዱ በደንብ ጠይቁ።

በደላሎች ወደ ካናዳ ፣ አሜሪካ ፣ አውሮፓ ፣ ታይላንድ ጠቀም ያለ ገንዘብ ለሚያስገኝ ስራ እየተባሉ ብዙ ወጣቶች ዓለም አቀፍ የሆነ የኦንላይን የማጭበርበር (online scam) ስራ ወደ ሚሰራባቸው የማይናማር የተለያዩ አካባቢዎች ነው የሚወሰዱት።

ስቃይ ላይ ነን ስላሉት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ጉዳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ለማነጋገር ጥረት ያደርጋል።

ተጨማሪ ዶክመንተሪዎች እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች ፦
Al Jazeera - Rebels uncover scam centers in Myanmar
DW Shift - Scam Factories in Myanmar
Sea Today - Indonesian Scam Victims
WION - 900 scam factory Chinese Victims rescued near Myanmar
CNN News18 - Mynamar Cyber Crimes
CCTV - Major Criminal Suspects Transferred to China from Myanamar

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 “ ... ያለፉትን ዘመናት እኮ #እንደ_ቅንጦት እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው ” - ጎጎት ፓርቲ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ' #የፖለቲካ_ፓርቲዎች_ምን_ይላሉ ? ' በሚል በህጋዊ መንገድ ተመዝገበው ለሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች እያቀረበ ያለውን ወቅታዊ ሀገራዊ ጥያቄዎች በመቀጠል ጎጎት ፓርቲን አነጋግሯል። የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ጀሚል ሳኒ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ…
#OLF

🇪🇹 የፓለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

“ መንግስት በተለዬ መልኩ ጫና እያደረሰብን ነው ” ሲል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ፓርቲ ወቀሰ።

ፓርቲው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርጓል።

በዚህም በወቅታዊ እና በአገራዊ ጉዳዮች እንደ ፓርቲ ያለውን ግምገማና የመፍትሄ ሀሳብ አጋርቷል።

Q. ስለ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የፓርቲው ግምገማ ምንድን ነው ?

ኦነግ ፦

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በገዢው ብልጽግና ፓርቲ ብቻ የሚዘወር ከመሆኑም ባሻገር ፓርቲዎችን ያገለለ ነው። ገና ከጅምሩ ብዙ መንገራገጮች አሉበት።

በአዲስ አበባ ደረጃ በተካሄደው አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ፓርቲያችን አልተሳተፈም። 

በምክክሩ መፍትሄ አዘል ውጤት ለማምጣት ሂደቱ አሳታፊ ሊሆን ይገባል። ካልሆነ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ተካሂዷል እንዲባል ብቻ የይስሙላ ይሆናል።

Q. እንደ ፓርቲ ከመንግሥት የሚደርስባችሁ ጫና አለ ? ካለ ምንድን ነው?

ኦነግ ፦

መንግስት ከሌሎች በተለዬ መልኩ ጫና እያደረሰብን ነው።

በፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ አመራሮች ደጋፊዎች በእስራትና እንግልት ከፍተኛ ጫና ይደርስባቸዋል።

የፓርቲያችን ተሽከርካሪዎች እና ሌሎችም ንብረቶች ተዘርፈዋል። ለጉዳዩ የተለያዩ የሚመለከታቸውን ተቋማትን እያነጋገርን ነው።

ይህ ብቻ ሳይሆን እንደ ህጋዊ ፓርቲ ተንቀሳቅሰን ለመስራት እና የፓርቲውን አባላት ፣ ደጋፊዎቻችን ለማግኘት ሁኔታዎች እየፈቀዱልን አይደለም። 

ቢሯችን ገብተን መስራት አልቻልንም። በጥቅሉ ከፍተኛ ጫና ነው የሚደርስብን።

Q. የኦነግ ከፍተኛ አመራር አቶ በቴ ኡርጌሳ በትውልድ ቦታቸው መገደላቸው የቅርብ ጊዜ ክስተት ነው። ፓርቲው ስለጉዳዩ ምን እየሰራ ነው ?

ኦነግ ፦

የጃል በቴን ግድያ በተመለከተ በወቅቱ መግለጫ ከማውጣት ጀምሮ የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራን ነው።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን (ኢሰመኮ) ጨምሮ ከሌሎች የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ምርምራው እንዲቀጥል እየተነጋገር ነው።

Q. በአማራም ሆነ በኦሮሚያ ክልል የፍጥ ያነገቡ ኃይሎች አሉ። የሰው ልጅ ህይወት እየተቀጠፈ ነው። መፍትሄው ምንድን ነው ?

ኦነግ፦

ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ ለሀገሪቱ ሰላም ይበጃሉ ያልናቸውን የመፍትሄ ሀሳቦች እያቀረብን ቆይተናል።

መንግስት ግን የመፍትሄ ሀሳቦቹን ወደ ጎን መተውን መርጧል።

በዚህም በአማራ፣ በኦሮሚያ ክልሎች የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር አሁን ካለበት አስከፊ ደረጃ ደርሷል።

ግጭቶቹን ለማስቆም ነፍጥ ያነሱ ኃይሎች እገዛ ማስፈለጉ እንደተጠበቀ ሆኖ መንግስት ግን ግጭቱን የሚፈልገው ይመስላል። 

የኦሮሚያም ሆነ የአማራ ህዝብ በመካከል ከፍተኛ ጉዳት እየተደረሰበት፣ መጥፎ የሚባል ጊዜ እያሳለፈ ነው።

Q. በቀጣዩ ምርጫ ተመራጭ ሆኖ ለመቅረብ የምታደርጉት ዝግጅት ምን ይመስላል ?

ኦነግ ፦

ለቀጣዩ ምርጫ እንዲካሄድ በመጀመሪያ ሰላም መስፈን አለበት። ሰላም ሲሰፍን ነው ሁሉም ነገር ሁሉም ነገር በሰላም የሚካሄደው።

የምናደርጋቸው ዝግጅቶች ይኖራሉ። ግን የምርጫ ጊዜ ሲደርስ ጊዜው ራሱ ቢነግረን ይሻላል። ያለንን የዝግጅት ሂደት ወደ በቀጣይ እንገልጻለን።

---

የፓለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? የሌሎች ፓርቲዎች ምልከታም ይቀጥላል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ፦
- እናት
- ነእፓ
- ኢዜማ
- ጎጎት
- ሕብር
- ኦፌኮ ፓርቲዎችን በወቅታዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ምልከታቸውን እንዲያጋሩ ማድረጉ ይታወሳል።

#TikvahErhiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ፍትህን እስከምናገኝ ድረስ የሚከፈለውን መስዋዕትነት እንከፍላለን " - ካውንስሉ

በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ከርስቲያን ኩሪፍቱ ማዕከል ላይ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ኢ-ህገ መንግስታዊ ጥሰት እየፈጸመ እንደሆነ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስትያናት ካውንስል አሳወቀ።

ድርጊቱን በመቃወምም መግለጫ አውጥቷል።

ካውንስሉ ፤ የኩሪፍቱ ማዕከል በህጋዊ መንገድ ለቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ ሰነድ ያለው ይዞታ መሆኑን ገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ ግን ከቤተ ክርስቲያኒቱን ቦታ ላይ 40 ሺህ ካሬ ሜትር የሚሆነውን በኃይል ለሁለት ለግለሰቦች በመስጠት ኢ ህገመንግስታዊ በደል እንደፈጸመ ጠቁሟል።

ይህንን ጉዳይ አስመልከቶ ከዚህ ቀደም ቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዩን ለፍርድ ቤት አቅርባ ፍርድ ቤት ቦታው የቃለ ሕይወት ይዞታ መሆኑን ውሳኔ አስተላልፎ ነበር።

የከተማ አስተዳደሩ የግንባታን ሂደት ሆን ብሎ እያስተጓጎለ ስለነበረ ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና ለፌደራል መንግስት ቀርቦ በከፍተኛ አመራር ደረጃ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየታየ ባለበት ሁኔታ ትላንት ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም የከተማ አስተዳደሩ የቤተ ከርስቲያቱ ይዞታ ውስጥ ወታደሮችን እና የመሬት አስተዳደር ባለሙያዎችን ይዞ በመግባት ችካል በማስቀመጥ የቤተ ከርስቲያኒቱን ይዞታ ለግለሰብ በማስተላለፍ ህገ ወጥ ተግባር እንደፈጸመ ካውንስሉ በይፋ አሳውቋል።

ሁኔታው ከባድ እና በወንጌላውያን አምነት ተከታዮች ላይ የተቃጣ ሐይማኖታዊ ጥላቻ ባላቸው ግለሰቦች የተቀነባበረ እንደሆነ ካውንስሉ አመልክቷል።

ጥያቄው ልማት ከሆነ ለምን ቤተ ክርስቲያኒቱ እንድታለማ ቅድሚያ አይሰጣትም ? የሚለው ሐሳብ ላይ መግባባት ኖሮ ቤተ ከርስቲያኒቱ ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ ሙሉ በሙሉ ጊቢውን ወደ ልማት በመቀየር እየሰራች እንደነበር ተጠቁሟል።

ይህ በሆነት ሁኔታ ነው ለአመታት በይዞታነት የያዘችውን ንብረት በሐይል በመቀማት የተወሰደው።

ካውንስሉ ፤ " የወንጌል አማኞች በዚህ የህልውናችን ጉዳይ ህግ መንግስታዊ መብታችን እስከሚከበር ድረስ ለሚመለከታቸው ለክልሉ እና ለፌደራል መንግስት አካላት ጥያቄያችንን ከማቅረብ ባሻገር ፍትህን እስከምናገኝ ድረስ የሚከፈለውን መስዋዕትነት እንከፍላለን " ሲል አሳውቋል።

#Bishoftu

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update (No. 5) የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ቤተሰብ እየተመለሱ በነበሩበት በታጣቂዎች ስለታገቱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተደጋጋሚ መረጃ አድርሰናችሁ ነበር። ዛሬስ ምን አዲስ ነገር አለ ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለታጋቾቹ ምን አዲስ አለ ? ሲል የተማሪ ወላጆችን የወንጌላውያን ተማሪዎች ህብረት፣ ደርባርቅ ዩኒቨርሲቲ እና ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል። ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት…
#Update

እህታቸው የታገተችባቸው የአዲስ አበባ ነዋሪ ለዶቼ ቬለ ከሰጡት ቃል ፦

" በጣም ይገርማል በእውነት፤ እኔ እኮ በእራሳቸው ስልክ (በአጋቾቹ ማለታቸው ነው) ትናንት ጠዋትም ከሰአት በኋላም እራሴ አግኝቻታለሁ በድምፅ፣ ሰዎቹንም አግኝቻቸዋለሁ። ልጆቹ አሁንም እዚያው ነው ያሉት፤ ተፈተዋል ምናም የሚባለው ነገር ውሸት ነው። ማታ ዜና ስንሰማ ነበር። እንዴት እንዲዚህ ያለ ነገር ይሰራል እስኪ ? " ብለዋል።

ከቀናት በፊት እጅግ በርካታ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጨርሰው ወደ ቤት ሲመለሱ በታጣቂዎች መታገታቸው ይታወቃል።

ትላንትና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ አንድ የዩኒቨርሲቲው አካል እስከ ትላንት ድረስ አብዛኛዎቹ ታጋቾች እንዳልተለቀቁ ፤ ትንሽ ታጋቾች ግን እንደተለቀቁ አሳውቀዋል።

በተለያዩ ሚዲያዎች " በርካታ ታጋቾች ተለቀዋል " የሚለውን ዜና የሰሙ የታጋች ቤተሰቦች በድርጊቱ ተበሳጭተዋል፤ አዝነዋል። ለምን ውሸት ይዘገባል ? ሲሉም ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሩዋንዳ እቅድ (ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ) ገና ከጅምሩ ሞቶ የተቀበረ ነው " - አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሰሞኑን ዩናይትድ ኪንግደም (UK) አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር አግኝታለች። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሌበር ፓርቲ መሪ ሰር ኪር ስታርመር ናቸው። ፓርቲው የሪሹ ሱናክን የወግ አጥባቂ (ኮንሰርቫቲቭ) ፓርቲ በከፍተኛ ብልጫ ነው ዘርሮ ያሸነፈው። በከፍተኛ ብልጫ የተሸነፉት ሱናክ ፥ "…
" 310 ሚሊዮን ዶላሩን መመለስ የስምምነቱ አካል አልነበረም " - ሩዋንዳ

ሩዋንዳ የዩናይትድ ኪንግደም ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለመቀበል የገባችው ስምምነት መሰረዝ ተከትሎ የተቀበለችውን 310 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ መመለስ እንደማይጠበቅባት አስታውቃለች።

በቀድሞ ጠ/ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ይመራ የነበረው የወግ አጥባቂው መንግሥት ስደተኞችን ሩዋንዳ ለመላክ ዕቅዱን ይፋ ካደረገበት ከእ.ኤ.አ. 2022 ጀምሮ ለሩዋንዳ 310 ሚሊዮን ዶላር ከፍሏል።

ምንም እንኳን በተሟላ ሁኔታ እቅዱ ወደ ተግባር ባይገባም አሁን ላይ ዩናይትድ ኪንግደም የተወሰነ ገንዘብ ይመለስልኛል የሚል ተስፋ አድርጋ ነበር።

ሩዋንዳ ግን " ገንዘቡ አይመለሰም " ብላለች።

የሩዋንዳ መንግሥት ቃለ አቀባይ የሆኑት አሌይን ሙኩራሊንዳ  ፥ "  ግልጽ መሆን ያለበት ጉዳይ ገንዘቡን መመለስ የስምምነቱ አካል አልነበረም። " ብለዋል።

" ስምምነቱ ገንዘቡ ተመላሽ እንዲሆን አይደነግግም እንዲሁም ዩናይትድ ኪንግደም ከሩዋንዳ ጋር በጥልቀት ስትነጋገር የነበረው በአጋርነት መንፈስ ነው " ሲሉ አክለዋል። #BBC

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

እናሸንፋለን ድሉን እናያለን ! ጉዞ ወደ ወርቅ፣ ጉዞ ወደ ፓሪስ ኦሎምፒክስ! ብርቅዬ አትሌቶቻችንን በፓሪሱ ኦሎምፒክስ ለመቀላቀል ጊዜው አሁን ነው!

የፓሪስ ኦሎምፒክስን በ350 ብር በጎጆ ፓኬጅ ይከታተሉ! ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/dg1

#ParisOlympics #2024Olympics #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Myanmar ይህ የ ' DW ዶክመንተሪ ' #በማይናማርና #ታይላንድ ድንበር ባሉ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ሰዎችን ከተለያዩ የዓለም ሀገራት በማዘዋወር ስለሚሰሩ ዓለም አቀፍ የኦንላይን ማጭበርበር (scam) ስራዎችን በግልጽ የሚያሳይ ነው። የሰው አዘዋዋሪዎች ሰዎችን የሚያዘዋውሩት በቅድሚያ ታይላንድ / የአውሮፓ ሀገራት እንደሆነ በመግለጽ እና ጠቀም ያለ ገቢ እንደሚገኝ በመንገር ጭምር ነው በኋላ የሚሰራው…
" እንደ ባሪያ ነው የምንታየው ፤ እባካችሁ ጭሁልን !! " - በማይናማር የሚገኙ ወጣቶች

ማይናማር እና ታይላንድ ድንበር ላይ ከሚገኙ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የበየነ መረብ ማጭበርበር (Online Scam) ተግባራት ከሚፈጸምባቸው አንዳንድ ቦታዎች ቲክቫህ ኢትዮጵያ መልዕክቶችን በቴሌግራም እየተቀበለ ይገኛል።

እነዚህ ቦታዎች ላይ በርካታ የሀገራችን ወጣቶች ያሉ ሲሆን " ታይላንድ እንልካችኋለን " በሚል የደላሎች ማታለያ ተታለው ነው በማይናማር የበየነመረብ ማጭበርበር (Online Scam) ላይ ተሰማርተው የሚገኙት።

ስሜን አይገለጽ ያለ በስፍራው ያለ ወጣት ፦

" ለምን ስራ አላመጣችሁም ? ለምን አልሰራችሁም (የኦንላይን ማጭበርበር) ተብሎ ሰው ይታሰራል።

እስር ቤት ይጣላል።

እኔ ለምሳሌ 5 ቀን ሙሉ እስር ቤት አድሪያለሁ። ያለ ምንም ምክንያት ።

ሽንት ቤት መሄድ የለም፤ ራስህ ላይ ነው የምትሸናው ፣ውሃ በግድ ያስጠጣሉ እምቢ ማለት አይቻልም ፣ የቁም እስር ነው ፣ መጮህ አይቻልም አፋችን ውስጥ ጨርቅ ይከታሉ በስነ ልቦና ሊጎዱን ነው ይህን ሁሉ የሚያደርጉት።

እንደ ሰው አንታይም። በስነልቦና በጣም እየተጎዳን ነው። በሰንሰለት ይገርፋሉ፣ በኤሌክትሪክ ሾክ ያደርጋሉ፣ መሬት ውስጥ በሚቅበር ሽቦ ይገርፋሉ እራቁት።

ለዚህ ችግር አንደኛው መጠየቅ ያለበት የታይላንድ መንግስት ነው። የሱን ቪዛ መተን ነው ወደዚህ የመጣነው። አሳልፈው የሚሰጡን ከታይላንድ ነው።

ከባንኮክ ከኤርፖርት መጥተው በመኪና ሲወስዱን ያውቃል መንግስት ። የምንሰራበት ሲም ካርድ የታይላንድ ነው። ዓለም ሁሉ እየተጭበረበረ ያለበትን ስራ በታይላንድ ሲም ነው የሚሰራው።

እዚህ በካምፕ ላይ ያለው ቁሳቁስ ከታይላንድ ነው የሚመጣው ፣ ህንጻ የሚሰራበት እቃ ከታይላንድ ነው፣ መብራት እና ውሃም ከታይላንድ ነው፣ አልጋው ምኑ የታይላንድ ነው።

ቻይናም ስለ ሁኔታው የምታውቅ ሀገር ስለሆነች ማናገር ይገባል። በቻይናውያን ድጋፍ የተሰመረተ ኩባንያ ነው ያለው።

መጠየቅ ያለባቸው ታይላንድ እና ቻይና ናቸው።

ማይናማር ለራሷ ላለፉት በርካታ ዓመታት እስካሁን ድረስ በእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ናት።

የኢትዮጵያ መንግስት ታይላንድን እና ቻይናን ይጠይቅልን።

የኢትዮጵያን ዜጎች ነው እንደ እቃ ነው የሚጠቀሙት። ቁሳቁስ ሲመጣ እንኳን የሚያሸክሙን እኛን ነው። እንደ አህያ ነው የሚጠቀሙን። ክትባት ሲመጣ ለኛ አይሰጥም። ጥቅም የለንም። እንደባሪያ ነው የምንታየው። እየኖርን አይደለም። ተስፋም የለንም።

እባካችሁ ጭሁልን ! " ብሏል።

ሪፖርት፦ አንድ የተመለከትነው ሪፖርት በማይናማር ፣ ካምቦዲያ፣ ላኦስ እስከ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ የኦንላይን ማጭበርበር (Scam) ላይ የተሰማሩ ሰዎች አሉ። ማፊያዎች በሚመሯቸው በነዚህ አካላት በየአመቱ እስከ 43.8 ቢሊዮን ዶላር ድረስ ይሰርቃሉ። በማጨበርበር ስራው ላይ የተሰማሩት ሰዎች እራሳቸውም የችግሩ የመጀመሪያ ሰለባዎች ናቸው።

#ጥንቃቄ፦ " እጅግ ጠቀም ላለ ስራ ነው " እየተባለ ወደ ታይላንድ የምትሄዱ ጥንቃቄ አድርጉ። ስራው ምንድነው በሉ ፣ ከታይላንድ ውጭ እንደማትወሰዱ እርግጠኛ ሁኑ ፣ ዶክመንት ተፈራረሙ የሚልኳቹን ሰዎች ማንነት አጣሩ፣ ኤጀንሲ ይሁን ደለላ ማስረጃቸውን ሁሉ ያዙ።

ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይደረስ !

#TikvahEthiopia
#Myanmar

@tikvahethiopia