TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SouthEthiopiaRegion

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች ለወራት ያልተከፈለ ውዝፍ ደሞዛቸዉ እንዲሰጣቸዉ በአደባባይ ሠልፍ ጠይቀዋል።

በዎላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኘው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የግቢ በሮች ላይ የተሰበሰቡት ሠራተኞች እንደገለጹት እስከ 3 ወራት የሚደርስ ደሞዝ አልተከፈላቸዉም።

ሠራተኞቹ ደሞዝ ሥላልተከፈላቸዉ እራሳቸዉንና ቤተሰቦቻቸዉን ለመመገብም ሆነ ልጆቻቸዉን ለማስተማር መቸገራቸዉን አስታዉቀዋል።

የገዢዉ ፓርቲና የክልሉ ባለሥልጣናት ሠራተኞቹን " በትዕግሥት ጠብቁን " የሚል ምላሽ ቢሰጡም ሠራተኞቹ ግን " ረሐብ እንዴት ቀን ይሰጣል ? " በማለት ጠይቀዋል።

ሠራተኞቹ በወረዳው በተለያዩ ጽ/ቤቶች ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ መሆናቸውን የሠራተኞቹ ተወካዮች መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#USA #Ethiopia

አሜሪካ በአማራ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ያለቻቸው የፋኖ ኃይሎች " ውይይትን አልቀበልም " ማለታቸውን በመግለጽ ይህ " ለራሳቸውም አይጠቅማቸውም " አለች።

ሀገሪቱ ይህን ያለችው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በሆኑት ኢርቪን ማሲንጋ አማካኝነት ነው።

አምባሳደሩ ፤ " በአማራ ክልል ውስጥ ውጊያ እያደረጉ የሚገኙት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ኃይሎች ' ውይይትን አንቀበልም ' ማለታቸው ለራሳቸውም አይጠቅማቸውም " ብለዋል።

ከመንግስት ጋር በታንዛንያ የሰላም ንግግር ሲያደርጉ የቆዩት የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (OLA) ተዋጊዎችን " በድርድር ተስፋ ሳትቆርጡ ፤ መተማመንን ለመገንባት ጥረት አድርጉ " ብለዋቸዋል።

አሜሪካ ይህን ያለችው ዛሬ ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ/ም ኢትዮጵያን በተመለከተ የምትከተለውን ፖሊሲ አስመልክቶ በአምባሳደሯ በኩል ባስተላለፈችው መልዕክት ነው።

በአዲስ አበባ ፤ መርካቶ አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ የአሜሪካን ግቢ በነበረ መርሀ ግብር የአሜሪካ አፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመርን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ነበር።

Video Credit : US Embassy Addis Ababa / Ethiopia Insider

@tikvahethiopia
#ቡሬ

➡️ “ 15 ተፈናቃዮች ናቸው በሚሊሻ የተወሰዱት ” - በአማራ ክልል የሚገኙ የወለጋ ተፈናቃዮች

➡️“ በቡሬ በኩል ስላለው መረጃ የለኝም ” - አቶ ኃይሉ አዱኛ

በ2013 ዓ/ም ከኦሮማያ ክልል #ተፈናቅለው በአማራ ክልል ቡሬ ፣ ቻግኒ ፣ ፍኖተ ሰላም ፣ ባሕር ዳር የነበሩ ተፈናቃዮች ሰሞኑን ወደ ወለጋ ለመመለስ እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ሰንቶም ቀበሌና ጣቦ የገጠር ከተማ ላይ ድንገተኛ ችግር እንደገጠማቸው አሳውቀዋል።

ተፈናቃዮቹ ለቲክቫህ በሰጡት ቃል ፣ “ እየሄድን እያለ ሶንቶምና ጣቦ ላይ አደጋ አጋጠመን። የሕዝብ ማዕበል መጣብን። ኬላ ላይ ተይዘን በ1ዐ ተሽከርካሪዎች የተሳፈርን ተፈናቃዮች አወረዱን እና ተሰቃየን በጣም ” ብለዋል።

“ ወጣቶች ድንጋይ፣ መሳሪያ ይዘው (ያልያዙት መሳሪያ የለም) ወጡ፣ ልክ አሸባሪ እንደሄደ እንጂ ተፈናቃይ አልመሰልናቸውም። ‘ከዚህ ቀደም በጦርነት ሲሳተፉ የነበሩ ናቸው’ እየተባለ ተፈናቃዮቹ እየተመረጡ ተያዙ ” ነው ያሉት።

“ 15 ተፈናቃዮች በሚሊሻ ተወስደዋል ፤ ሊገድሏቸው ሲሉ መከላከያ ወደ ካምፕ ወስዷቸዋል። ቀሪዎቹ ጫካ አድረን ወደ #ቡሬ_ተመልሰናል። በድንጋይ የተመቱ አሉ። ሰዎቹ ' እንደምትመጡ ማወቅ ነበረብን ጠብ እንዳንፈጥር ' ነው ያሉት ” ሲሉ ተናግረዋል።

ተፈናቃዮቹን ወደ ምሥራቅ እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ሀገር መከላከያ አጅቦ ሊመልሳቸው ፣ የወለጋ ኃላፊዎች ደግሞ ሊቀበሏቸው ቅድሚያ ቢነገራቸውም የሸኟቸው ሚሊሻዎች መሆናቸውን ተፈናቃዮቹ አስረድተዋል።

ሚሊሻዎቹ ከዓባይ ወደዛ ለመሻገር ስላልቻሉ፣ የወለጋ ዞኖች ኃላፊዎችም ‘ ትዕዛዝ አልተሰጠንም ’ በማለት ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ከሞት አምልጠው ወደ ቡሬ ለመመለስ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጥ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ለምን ጥበቃ እንዳልተደረገላቸው ጥያቄ የቀረበላቸው የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛም፣ “ በቡሬ በኩል ስላለው መረጃ የለኝም ” ነው ያሉት።

“ ደብረ ብርሃን፣ ወሎ ካምፕ ያሉትን ቅድሚያ ተሰጥቶ በ1ኛው ዙር 1,600፣ በ2ኛው ከ400 በላይ ሰዎች ተመልሰዋል” ሲሉ አስታውሰው ፣ “ በሶስተኛው ዙር ለመመለስ ደግሞ ከአማራ ክልል መንግስት ጋር በቅንጅት እየሰራን ነው ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #Ethiopia አሜሪካ በአማራ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ያለቻቸው የፋኖ ኃይሎች " ውይይትን አልቀበልም " ማለታቸውን በመግለጽ ይህ " ለራሳቸውም አይጠቅማቸውም " አለች። ሀገሪቱ ይህን ያለችው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በሆኑት ኢርቪን ማሲንጋ አማካኝነት ነው። አምባሳደሩ ፤ " በአማራ ክልል ውስጥ ውጊያ እያደረጉ የሚገኙት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ኃይሎች ' ውይይትን አንቀበልም…
#የአሜሪካ_አቋም!

" ግጭት የኢትዮጵያውያንን #ስቃይ_ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የለውም " - አሜሪካ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ አሜሪካ ስለ ኢትዮጵያ ያላትን ፖሊሲ በተመለከተ ምን አሉ ?

- በትጥቅ ግጭት ውስጥ የገቡ አካላት፣ ግጭት አቁመው በንግግር ሰላምን ሊያሰፍኑና የሰብአዊ መብቶችን ማክበር አለባቸው።

- የታጠቁ ቡድኖች ፖለቲካዊ ዓላማዎቻቸውን በአመፅ ለማሳካት እየገፉ ናቸው ፤ መንግስትም ይህን ለመከላከል የሚወስዳቸው ርምጃዎች፣ በፖለቲካ ምኅዳሩ ላይ የማይካድ ተጽእኖ አለው። ውይይትን ወደ ጎን ያለው ይህ አካሔድ የመብት ጥሰቶች እንዲቀጥሉ አድርጓል።

- ሰላማዊ ዜጎች፣ በተለያዩ ኀይሎች ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የዘፈቀደ እስራት፣ አስገዳጅ ስወራ፣ ከግጭት ጋራ የተያያዘ ጾታዊ ጥቃት እና ሌሎችም ጥቃቶች እየተፈጸሙባቸው መሆኑን የሚገልጹ ዘገባዎችን ማየቱ እጅግ ያሳዝናል።

- የተፈጸሙ ጥፋቶች እውነተኛና ግልጽ የሽግግር ፍትሕ ሒደት በተከተለ የተጠያቂነት አሰራር በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል።

- ሽፍታዎች፣ የታጠቁ ቡድኖች፣ አንዳንዴም የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች፤ በህይወት የመኖር፣ የሰብዓዊ ክብርን፣ መከበርን በመሰሉ መብቶች ላይ ያለምንም ተጠያቂነት ጥሰቶች ይፈጽማሉ።

- በጦርነት እና ግጭት ወቅት እንኳ የሰብዓዊ መብቶች ሊረሱ አይገባም።

- ሁሉም ሀገር ራሱን የመከላከል ህጋዊ መብት አለው፤ ሆኖም ሀገራት ራሳቸውን የሚከላከሉበት መንገድ ያለምንም ጥርጥር የወደፊት ግጭቶችን አካሄድ የሚወስን ነው።

- ሀገር የመከላከያ መንገዶቹ በዛሬው እና በወደፊቱ የማህብረሰብ ትስስር ላይ ይበልጡኑ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነው።

- የታጠቁ ወገኖች የፖለቲካ ግባቸውን ከውይይት ይልቅ በግጭት ለማሳካት ሲሞክሩ፤ ለሚፈጸሙ በደሎች ሁኔታዎች የተመቻቹ ይሆናሉ።

- በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ታጣቂ ቡድኖች ንግግር / ድርድር አንቀበልም ማለታቸው እራሳቸውን ነው የሚጎዳቸው። በአማራ ያሉ በርካታ ሰዎች " የቆሙለት ዓላማ ፍትሃዊ ነው " የሚል እምነት/አላቸው ይህንኑ መከራከሪያቸውን ከግጭት ይልቅ በውይይት ማቅረብ አለባቸው።

- በአማራ ክልል ውጊያዎች የሚቀጥሉ ከሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች እንዳለው በውጤቱ የሚሰቃዩት ሰላማዊ ሰዎች ናቸው።  

- ህወሓት በኀይል ወሰን ለማስመለስ ከሚደረግ እንቅስቃሴ መቆጠብ አለበት።

- የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ኃይሎች በድርድር ተስፋ ሳይቆርጡ መተማመን ለመገንባት የሰላም ውይይትን ሊቀጥሉ ይገባል።

- ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በውስጣዊ ግጭቶች እየታመሰች ትገኛለች።

- የኢትዮጵያ መንግስት የአገሪቱን ችግሮች በኀይል ለመፍታት ከሚያደርገው ጥረት መቆጠብ አለበት። በእስር ላይ የሚገኙ ቁልፍ የፖለቲካ ሰዎችን መፍታቱ ጠቃሚ ነው፤ ያን ተፈጻሚ ማድረግ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የፖለቲካ ውይይት ሊያግዝ ይችላል።

- ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ስምምነት ሊፈጸም ይገባል።

- ሁሉም የታጠቁ ተዋናዮች፣ በመላ አገሪቱ አዲስ የሕዝብ መፈናቀልን ጨምሮ ለሰዎች ስቃይ ምክንያት ከመሆን መገታት አለባቸው።

- የታጣቁ ኃይሎች ት/ቤቶችን፣ ጤና ተቋማትንና የውኃ መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ማድረግ ማቆም አለባቸው። የተሟላና ያልተገደበ ሰብአዊ አቅርቦት ሊኖር ይገባል። ይህም ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ማድረግን ይጨምራል።

- ግጭት የኢትዮጵያውያንን ሥቃይ ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የለውም። ውይይት ትኩረት ሊደረግበት ይገባል።

- ምንም እንኳን ፍጹም ሊሆን ባይችልም፣ ሁሉም ወገኖች የአገራዊ ምክክሩን ዕድል ሊጠቀሙበት ይገባል።

#USEmbassyAddisAbaba
#VOA
#EthiopiaInsider

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Big5Ethiopia

ቢግ ፋይቭ ኮንስትራክት ኢትዮጵያ አውደ ርዕይ ያካተተው የሲፒዲ ነጥብን የሚያስገኘው መድረክ ስድስት የሙያ ዘርፎችን የያዘ ነው።

እነዚህም ቴክኖሎጂ፣ የፕሮጀክት አስተዳደር፣ አርክቴክቸርና ንድፍ፣ ዘላቂነት(ሰስተነብሊቲ)፣ ምህንድስና እና መሠረተ ልማት ናችው።

ሁሉም ውይይቶች በየራሳቸው ብቁ ባለሙያዎች የሚመሩ ሲሆን፣ ፋይዳ ያላቸው እይታዎችንና አመለካከቶችን ያጋራሉ።

የውሃ አቅርቦት መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች፣ ሞጁላር ግንባታ በዲጅታል ንድፍ ልምምድ ውስጥ፣ የመገኛ ቦታ(geospatial) ቴክኖሎጂና ቢም እንዲሁም አርክቴክቸር በከተማ ቅየሳ ውስጥ ያለው ሚና፣ ከሚዳሰሱ ርዕሶች መካከል ይገኛሉ።

በነጻ ለመጎብኘትና ለመታደም አሁኑኑ ይመዝገቡ፡- https://bit.ly/3UsrL5I

የሁነቱን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ፡-https://t.me/big5ethiopia
#DStvEthiopia

💥 አንድም ጎል ፣ አንድም ደቂቃ እንዳያመልጣችሁ!

👉 ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ ፣ ሁሉንም ጨዋታ በላቀ ጥራት ይመልከቱ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ ወይም *9299# ይደውሉ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... ወንዶች በትምህርት ሰአት ሁሉ የቀን ስራ በመስራት ርሀባቸውን ለማስታገስ በጥረት ላይ ሲሆኑ ሴቶችም ላልተገባ ችግር ተጋልጠዉ መማር አልቻሉም " - የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን ማህበር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር አደረኩት ባለው ማጣራት በክልሉ ውስጥ ባሉት የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች ለመማር የተመደቡ ዕጩ መምህራን ሁሉም በሚባል መልኩ  ትምህርታቸውን በፋይናንስ እጥረት በአግባቡ እየተማሩ…
" ችግሩ በሚባለዉ ደረጃ የተጋነነ ባይሆንም ጊዜያዊ እርምጃ ለመዉሰድ እንቅስቃሴ ጀምሬያለሁ " - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ

ከሰሞኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባሉ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች ለመማር የተመደቡ ዕጩ መምህራን ሁሉም በሚባል መልኩ ትምህርታቸዉን በፋይናንስ እጥረት እየተማሩ አለመሆኑን የደቡብ ኢትዬጵያ ክልል መምህራን ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል።

ወንዶች ትምህርት መማር ሲገባቸው የቀን ስራ እየሰሩ እንደሆነና ሴቶችም ላልተፈለገ ችግር መጋለጣቸውን ጠቁሞ ነበር።

ተማሪዎቹ በ2015 ዓ/ም ወደ ኮሌጆች ሲገቡ ከመንግስት የሚሰጣቸዉ 450 ብር በቂ እንዳልሆነ እየታወቀ ቢጀመርም እስካሁን አለመስተካከሉንና ለዚህም በተከታታይ ደብዳቤ መጠየቁን ማህበሩ መግለጹ አይዘነጋም።

ጉዳዩን በተመለከተ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስተያየቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥቷል።

የቢሮው ምክትል ሀላፊ ዶ/ር ታምራት ይገዙ ፤ " ጉዳዩ በተባለዉ ልክ የተጋነነ ባይሆንም የተወሰነ ችግር መኖሩን አውቀን እየሰራንበት ነው " ብለዋል።

" ለችግሩ የአጭር ጊዜ መፍትሄ ለመስጠት እንቅስቃሴ ጀምረናል " ያሉት ሀላፊው " አሁን ላይ ተማሪዎቹ ያለባቸዉን የቤት ኪራይ ችግር ለማቅለል ከዲላ እና ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር መነጋገር ጀምረናል " ብለዋል።

ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር ጥሩ መግባባት ላይ መደረሱን የገለጹት ዶ/ር ታምራት ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋርም ሂደቱ ጥሩ መሆኑን አመልክተዋል።

" በቋሚነት ችግሩን ለማስተካከል እየሰራን ነው። ምናልባትም ለሚቀጥለዉ አመት ሲመጡ የሚከፈላቸዉ ገንዘብም ይጨምራል ብዬ አስባለሁ " ሲሉ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Ethiopia

" አምባሳደሩ ንግግራቸው ሀገሪቷን እንዴት መምራት እንዳለብን ያልተጠየቀ ምክር ለመመምከር የሞከረ ነው " - መንግሥት

የኢትዮጵያ መንግሥት በአሜሪካ አምባሳደር የተንጸባረቀው ሀሳብ " ሀሰተኛ እና ተቀባይነት የሌለው ነው " ብሎታል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ትላንት አሜሪካ ስለ ኢትዮጵያ ያላትን ፖሊሲ በንግግር ማሰማታቸው ይታወሳል።

ይህን በተመለከተ ዛሬ የኢትዮጵያ መንግሥት በውጭ ጉዳይ በኩል መግለጫ አውጥቷል።

በዚህም የአምባሳደሩ ንግግር " በተረጋገጠ መረጃ ላይ ያልተመሰረተ ነው " ብሎታል።

" በምርጫ ወደ ስልጣን የመጣን መንግስት እንጥላለን በሚል የሚንቀሳቀሱ፣ ንጹሃንን ከሚያግቱና ከሚያሸብሩ አካላት ጋር መንግስትን መጥቀሳቸውም ተገቢ አይደለም " ብሏል።

ንግግራቸው " የኢትዮጵያ መንግስት ሀገሪቷን እንዴት መምራት እንዳለበት ያልተጠየቀ ምክር ለመመምከር የሞከረ ነው " በማለት ገልጾታል።

" ከሁለቱ ሀገራት ታሪካዊና ወዳጅነት ላይ ከተመሰረተው ግንኙነት የተቃረነ ነው " ሲልም አክሏል።

መንግሥት በመግለጫው ላይ ፤ " የተፈጸመው ዲፕለማሲያዊ ስህተት ነው " ያለ ሲሆን በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመስራት የተፈጠረውን ስህተት እንዲታረም እንደሚደርግ ገልጿል።

ኢትዮጵያ የሰላምና የጸጥታ ጉዳዮችን ጨምሮ ከአሜሪካ ጋር ለመስራት ያላትን ዝግጁነትም ገልጿል።

@tikvahethiopia
" ፖሊስ ከተማሪዋ ህልፈተ ህይወት ጋር በተያያዘ ምርመራ እያደረገ ነው " - አሶሳ ዩኒቨርሲቲ

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የጂኦግራፊ ትምህርት ክፍል የ4ኛ ዓመት ተማሪ የነበረችው ተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ህይወቷ አልፏል።

ዩኒቨርሲቲው የተማሪዋን ሞት 'ድንገተኛ ህልፈት'  በማለት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ የሀዘን መልዕክት አሰራጭቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪዋ ' #በጩቤ_ተወግታ ህይወቷ እንዳለፈ ' የሚገልፁ መረጃዎችን ተመልክቷል። ይህን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲውን አነጋግሯል።

በጉዳዩ ላይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አንድ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አመራር፤ " ፖሊስ ከተማሪዋ ህልፈት ጋር በተያያዘ የጠረጠረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያደረገ ይገኛል " ብለዋል።

" በዩኒቨርሲቲው ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ የተሰራጨው መረጃ ጉዳዩ ገና በፖሊስ የተያዘ በመሆኑን ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

ዩኒቨርሲቲው የተማሪዋን አስክሬን ወደቤተሰቦቿ አሸኛኘት ማድረጉንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

Via @tikvahuniversity
" የ18 ወራት የዱቲ ክፍያ አልተከፈለንም " - የዲላ ዙሪያ ወረዳ ጤና ባለሙያዎች

" መሠረታዊ ችግሩ የበጀት ችግር ነው፤ የካሽ እጥረት ነው ያለው " - የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ

በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ በ6 ጤና ጣቢያዎች የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች የ18 ወራት የዱቲ ክፍያ እንዳልተከፈላቸው፣ እንዲከፈላቸው ቢጠይቁም መፍትሄ እንዳላገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ጤና ባለሙያዎቹ በሰጡት ቃል፣ " እንዲከፈለን ጠይቀን ነበር። ‘#ገንዘብ የለንም እንከፍላለን’ እያሉ ነው የተበጀተ በጀት እያለ ገንዘቡን ለሌላ ጉዳይ እየተጠቀሙ ያቆዩት " ብለዋል።

- ጪጩ
- አንድዳ
- ስሶታ
- ወቸማ
- ኡዶ
- ቱምትቻ በተሰኙ የወረዳው 6 ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች ከ01/06/2015 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 01/09/2016 ዓ/ም ለ18 ወራት የዱቲ ክፍያ አልተከፈለም ነው ያሉት።

ያልተከፈላቸውን ገንዘብ መጠን ሲገልጹም አንዷ ቅሬታ አቅራቢ፣ " የእኔ ከ80,000 ብር በላይ ነው። ከእኔ በላይ ደመወዝ እርከን ላላቸው ደግሞ ይጨምራል። የአንድ ሰው ከዚህ በላይ ሲሆን፣ የ6ቱ ጤና ተቋም ብዙ ገንዘብ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ የጠየቅናቸው የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዱዓለም ማሞ፣ " ጉዳዩ በእርግጥ ያለ ነው። መሠረታዊ ችግሩ የበጀት ችግር ነው፤ የካሽ እጥረት ነው ያለው። ያን ለመፍታት በጋራ እየሰራን ነው " ብለዋል።

ባለሙያዎቹ፣ 'የተበጀተ በጀት አለ ግን ለሌላ ጥቅም እያዋሉት ነው ያዘገዩብን' ላሉት ቅሬታ በሰጡት ምላሽ ኃላፊው፣ " እንደዛ አይደለም። በጀቱ ተይዟል እውነት ነው። ነገር ግን የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንጂ ወረዳውም ለመክፈል ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ አይደለም " ሲሉ ተናግረዋል።

የዞኑ የብልጽግና ጽ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አይደፈር ሽፈራው በበኩላቸው ፤ ችግሩ የጥሬ ገንዘብ እጥረት መሆኑን ገልጸው፣ ለ3 ዓመታት የዱቲ ክፍያ 6.4 ሚሊዮን ብር እንደተበጀተ፣ ገንዘቡን ለማፈላግለግ እየተሰራ እንደሆነና ዱቲ የሚከፈላቸው የባለሙያዎች ብዛት መረጃም እየተሰበሰበ መሆኑን አስረድተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ገንዘብ ማስተላለፍ ሲፈልጉ ከእሁድ እስከ እሁድ ለ24 ሰዓት ክፍት በሆነው የቨርቹዋል ባንክ ማዕከሎቻችን ይጠቀሙ።

#virtualbanking #bankinginethiopia #banksinethiopia #ITM #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
የ ZTE ስልኮች ከልዩ ስጦታ ጋር!

ዘመናዊ የ ZTE ስማርት ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ በመግዛት የዩትዩብ ጥቅልን ጨምሮ ወርሃዊ ዳታ ከድምጽ ጥቅል ጋር በስጦታ ያግኙ!

በአቅራቢያዎ በሚገኙ የአገልግሎት ማዕከሎቻችን እንዲሁም የአዲስ አበባ ደንበኞቻችን በቴሌገበያ ድረገጽ ጭምር https://telegebeya.ethiotelecom.et/ ያገኟቸዋል!

የዜድ.ቲ.ኢ 5ጂ ብሌድ ኤ73 እና ዜድ.ቲ.ኢ ብሌድ ቪ40 ፕሮ ሲገዙ እስከ ግንቦት 23 ድረስ የኤርፖድ ስጦታ ያገኛሉ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
° “ ልጄ በሕይወት ስለመኖሯ እርግጠኛ አይደለሁም ” - ልጄ ተጠለፈች ያሉ አባት

° “ የልጅቷን አባት መስለው ቃለ መጠይቅ የሚያደርጉ አሉ ” - የኮሬ ዞን አስተዳዳሪ 

° “ በ2015 ዓ/ም ብቻ 23 ሴቶች ጠለፋና አስገድዶ መድፈር ተፈጽሞባቸዋል ” - የዞኑ ፍትህ ቢሮ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጠለፋና እየተስፋፋ መሆኑን፣ በዚህም ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላክ እንዳልቻሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

አቶ ወንድሙ ወዬሳ የተባሉ የዞኑ ነዋሪ ባለፈው ወር የማርያም የተባለች ልጃቸውን “ ጉልበተኞች ምሽት 3 ሰዓት በራቸውን ሰብረው ጠልፈው ዱልኬ ” ወደሚባል ቦታ እንደወሰዷት፣ ጠላፊዎቹ ከተያዙ በኋላ ከእስር እንደተለቀቁ በማህበራዊ ሚዲያ ሲገልጹ ተስተውለዋል።

“ ልጄ በሕይወት ስለመኖራ እርግጠኛ አይደለሁም ” ያሉት እኝሁ አባት፣ የጠላፊ ቤተሰቦች ይባስ ብለው ሽምግልና እንደላኩ፣ በዚህም እኝሁ አባት ለጸጥታ አካላት አሳውቀው ቢያሳስሯቸውም እንደተለቀቁ ፣ የጠላፊ ቤተሰቦችም #ፌዝ እና #ዛቻ እያደረሱባቸው በመሆኑ የዞኑ አካላት ፍትህ እንዲሰጧቸው ጠይቀው ነበር።

ይህች ልጅ በጠላፊዎች እጅ 2 ወር በላይ ሆኗታል።

ከዚህ ባለፈ ደስታ ደመቀ የተባለች ልጃገረድ ተጠልፋ የተወሰደች ሲሆን በጠላፊዎች እጅ ከወር በላይ እንደሆናት ተሰምቷል።

እንደ አጠቃላይ ያለውን የጠለፋን ወንጀል በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸውና ስሜ ባይጠቀስ ያሉ የዞሬ ዞን ፍትህ መምሪያ አካል፣ “#ችግሮቹ አሉ። ጠላፋዎቹ ከትምህርት ቤት መልስም ይፈጸማሉ” ሲሉ አረጋግጠዋል።

“ ለሚስትነት የሚጠለፉ አይመስልም። ጠላፊዎቹ ወደ ሱዳን በኩል ወርቅ አለ በጅማ በኩል የሚጓዙበት ‘በዚያ አካባቢ የሚመጡ ሎሌዎች ናቸው’ ነው የሚባለው። ይህ የሚሆነው ጎርካ ወረዳ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

የየማርያምን ጨምሮ በ2016 ዓ/ም የተፈጸሙትን የጠለፋ ወንጀሎች በተመለከተ ገና መረጃ እያሰባሰቡ መሆኑን ገልጸው፣ “ በ2015 ዓ/ም 23 ሴቶች የጠለፋና አስገድዶ መድፈር ተፈጽሞባቸዋል ” ብለዋል።

ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የኮሬ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ በቀለ በበኩላቸው፣ “ ሚዲያ ላይ የሚባለው መሬት ላይ አለ ወይስ የለም ? የሚለውን በሚባለው ክላስተር ላይ ሂጄ የሃይማኖት አባቶችን፣ አረጋዊያንን ለማማከር ሞክሬአለሁ። አሁን በሚባለው ልክ አይደለም ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ‘ከፓሊስ ጣቢያ ሰው እየተለቀቀ ነው’ የሚለው ነገር ስም ለማጥፋትና ዞኑን ለማጠልሸት እየተደረገ ያለ ነው ” ያሉት አቶ ታረቀኝ፣ “ የልጅቷን አባት መስለው ቃለ መጠይቅ የሚያደርጉ አሉ። ቃለ መጠይቅም ራሱ አርሶ አደር መስሎ የሚሰጥ አለ ” ነው ያሉት።

የኮሬ ዞን ሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተፈራ ቦንደሮ በበኩላቸው፣ ከወረዳው ወደ ዞን የቀረበላቸው ቅሬታ እንደሌለ፣ ጎርካ ወረዳ ለመረጃ ሩቅ በመሆኑ ጉዳዩን እንዳልሰሙ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቢጂአይ #ፐርፐዝብላክ " ገንዘቡንም አልመልስም ሲል በደብዳቤ አሳውቋል " ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ " የመመለስ አለመመለሱ ጉዳይ በቀብድ ውሉ መሰረት የሚታይ ነው " - ቢጂአይ ኢትዮጵያ ስምንት ወራትን የፈጀውና ያለስኬት የተጠናቀቀው የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ሂደት አሁን ላይ ወደ ክስ ሂደት አምርቷል። ገዢ ሆኖ የቀረበው ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ክስ እስከሚመሰርት ድረስ…
#Update

ቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና ፐርፐዝ ብላክ በፍርድ ቤት መር አስማሚ በኩል አለመግባባታቸውን በስምምነት ፈተዋል።
 
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሁለቱ ወገኖች መካከል የተፈፀመውን ስምምነት አፅድቆ ክሱን በመዝጋት እግዱም እንዲነሳ አዟል፡፡
 
በስምምነቱ መሰረት ቢጂአይ-ኢትዮጵያ የተከፈለውን የቀብድ ክፍያ ለፐርፐዝ ብላክ የመለሰ ሲሆን ፐርፐዝ ብላክ በፍርድ ቤት የጀመረው ክስም ተቋረጦ እግዱ ተነስቷል።

@tikvahethiopia