#መቐለ
በሀገር መከላከያ ሰራዊት በቁጥጥር ስር የዋለችው መቐለ ከተማ ምንም እንኳን ህዝቦቿ ወደቀደመ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው ባይመለሱም በአስተማማኝ ሰላም ላይ ትገኛለች።
በሌላ በኩል የህወሓት ቡድን በርካታ ቁጥር ያላቸውን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ጥሎ ሄዷል ፥ የቡድኑ ልዩ ሃይል አባላት ሲጠቀሙበት በነበረ ቅጥር ግቢ ውስጥ በርካታ የጦር መሳሪያዎች በሀገር መከላከያ ተይዘዋል።
ህዝቦቿም ለሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ያላቸውን ክብር እና አድናቆት መግለፃቸውን መከላከያ ሰራዊት ዛሬ አሳውቆናል።
መረጃውን የላከልን በራያ ግንባር የሚገኘው ሃምሳ አለቃ አበበ ሰማኝ ነው።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#መቐለ_ዩኒቨርሲቲ
በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ እና በዘንድሮው ዓመት ለምረቃ የሚበቁ ተማሪዎች ምንም አይነት ችግር ሳይገጥማቸው መቆየታቸውን ተናግረው ሆኖም ግን ለከፍተኛ ርሃብ እና የውሃ ጥም ተዳርገው መቆየታቸውንና በአሁኑ ሰዓት የመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፍ እያደረገላቸው ይገኛል።
በአሁን ሰዓት ተማሪዎቹ ምንም አይነት ምግብ የሚያዘጋጁ ሰራተኞች በቅጥር ግቢው ባለመኖራቸው ምክንያት እየተቸገሩ መሆናቸውን በመግለፅ መንግስት እና የሚመለከታቸው አካላት በጉዳዩ ላይ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸውም በአፅንኦት ጠይቀዋል።

#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,298
• በበሽታው የተያዙ - 430
• ህይወታቸው ያለፈ - 6
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,150
አጠቃላይ 110,984 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,715 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 76,067 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
331 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#Mekelle
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሀይል ዛሬ መቐለ ከተማ መግባቱን አሳወቀ።
ዛሬ መቐለ የገባው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ልዩ ኮማንዶ እና የወንጀል ምርመራ ቡድን ነው።
የፌዴራል ፖሊስ ከ 'ሀገር መከላከያ ሰራዊት' ጋር በመቀናጀት በህግ የሚፈለጉ የህወሓት ተፈላጊ አባላትን ማደን መጀመሩን ገልጿል።
የኮማንዶ ቡድኑ በመቐለ ከተማ በሚያደርጋቸው አሰሳዎች እና የተለያዩ ኦፕሬሽኖች እንዲሁም በወንጀል ምርመራ ቡድኑ የሚገኙ ውጤቶችን በቀጣይ ለህዝቡ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞች ዛሬ ወደ መቐለ መጓዛቸውን ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ (የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ) ለቪኦኤ ተናግረዋል።
በመቐለ ያሉት የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መስጫ እቃዎች ማከማቻ ላይ ጉዳት መድረሱንና ይህም እንደሚጠገን አሳውቀዋል።
ከቴሌ ታውሮች ጋር የሚያገናኙ በርካታ የፋይበር ኬብሎችም ተቆርጠዋል ይህም ይጠገናል ብለዋል ወ/ሪት ፍሬህይወት።
የመቐለ ከተማን ጨምሮ በመላው ትግራይ ክልል የቴሌኮም አገልግሎት ለማስጀመር በመቐለ ያለው (core site) ጉዳት መጠን መለይት አለበት ፤ ጉዳቱ ከፍተኛ ከሆነ አገልግሎቱን ለመመለስ 'ረጅም ጊዜ' ሊወስድ እንደሚችል ተናግረዋል።
በሌላ በኩል #ሽረ አካባቢ ያለ ፋይበር ኦብቲክ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ፤ ጉዳቱ ረጅም ኪሎ ሜትር ስለሆነ ጥገናው እስካሁን #እንዳልተጠናቀቀ ወይዘሪት ፍሬህይወት ለቪኦኤ ራድዮ ጣቢያ ገልፀዋል።

#UPDATE
- በደቡብ ክልል የ2012 የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከታህሳስ 7-9/2013 ዓ/ም በሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች እንዲሰጥ ዛሬ ተወስኗል፡፡
- ጋምቤላ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከታህሳስ 6- 8 / 2013 ዓ/ም ባለው ጊዜ እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ዛሬ አስታውቋል።
- በሐረሪ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከታህሳስ 7-9 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሰጥ በክልሉ ትምህርት ቢሮ ተወስኗል።
* ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በ156 የመፈተኛ ጣቢያዎች 73 ሺህ 45 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መውሰድ ጀምረዋል።

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,522
• በበሽታው የተያዙ - 595
• ህይወታቸው ያለፈ - 9
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,318
አጠቃላይ 111,579 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,724 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 77,385 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
317 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,522
• በበሽታው የተያዙ - 595
• ህይወታቸው ያለፈ - 9
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,318
አጠቃላይ 111,579 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,724 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 77,385 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
317 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦
1. በሽረ ከተማ ዙሪያ በሚገኝ ስፍራ በርካታ የመሳሪያ ተተኳሾች እና ፈንጂ መሳሪያዎች በመከላከያ ሰራዊት አማካኝነት ለመንግስት ገቢ መደረጉን ኢፕድ አስነብቧል።
2. የዕርዳታ ቁሳቁሶችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እየተጓዙ ቢሆንም አሁንም ድረስ በአካባቢው ጦርነት ቀጥሏል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ሮይተርስ አንድ የዕርዳታ ሰራተኛን ጠቅሶ እንደዘገበዉ በመቐለ ከተማ ደቡባዊ እና ምዕራባዊ ክፍል ዛሬም ጦርነት እየተካሄደ ነዉ ሲል በድረገፁ አስነብባል።
3. አቶ ጌታቸው ረዳ አሁንም በትግራይ ክልል ጦርነቱ አልቆመም ፤ የሚቆምም አይደለም፤ አሁንም ቀጥሏል ሲሉ ዛሬ በትግራይ ቴሌቪዥን ወጥተው ተናግረዋል።
አቶ ጌታቸው ፥ "መቐለ ገቡ ማለት መቐለ ተቆጣጠሩ ማለት አይደለም። መቐለ ገብተዋል ፥ መቐለን መቆጣጠር ግን የህዝብን መንፈስና ስለልቦና መግዛት ይጠይቃል" ሲሉ ተደምጠዋል።
4. አቶ ዛጊድ ኣብርሃ (የዴሞክራሲ ማዕከል ግንባታ ሚኒስትር) ለBBC፥ በትግራይ ክልል ጦርነት የሚባል ነገር የለም ፤ ህወሓት ጦርነት ለማድረግ የሚያስችል ወታደራዊ ቁመና ፣ መሳሪያ እንዲሁም የህዝብ ድጋፍ የለውም ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ዛዲግ፥ አሁን ላይ ጥቂት በጣት የሚቆጠሩ በህግ የሚፈለጉ የህወሓት ቡድን አባላትን እየተከታተሉ መያዝ ነው የቀረው ፤ ይሄ ጦርነት አይደለም ፤ በልምምድ አንዳንዴ እንደዚህ አይነት ድምፅ ሊሰማ ይችላል ብለዋል።
5. ሰሞኑን በትግራይ ክልል ኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ለ2 የተለያዩ የውጭ ድርጅቶች ይሰሩ ነበር የተባሉ 4 ኢትዮጵያዊያን መገደላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
አቶ ዛዲግ ኣብርሃ ፥ አሁን ላይ ስለዚህ ጉዳይ መረጃ እንደሌላቸው ገልፀው ፤ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ግን የማንኛውም አይነት ሲቪል ጉዳት ማስወገዱን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
@tikvahethiopia

#TiborNagy
በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር የሆኑት ቲቦር ናጊ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ መሻሻል ቢያሳይም የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳይ ትኩረት ሲለሰጠው ይገባል ብለዋል።
ቲቦር ናጊ ሰብዓዊ እርዳታ በሚመለከት ለBBC የተናገሩት፦
"ግጭቱ ተባብሶ በነበረበት ወቅት አንዳንድ ቁልፍ ቦታዎችን ለመቆጣጠር ፍልሚያ በሚደረግበት ወቅት የግንኙነት መስመሮች ተቋርጠው ነበር ፤ ነገር ግን በአሁን ሰዓት ወሳኝ የሚባለው ፍልሚያ ተጠናቋል።
ግጭቱ ሙሉ በሙሉ ቆሟል ማለት ግን አይደለም ፤ በዚህ ሰዓት ዋነኛው ትኩረት መሆን ያለበት ሰብዓዊ እርዳት እንዴት ወደ አካባቢው ማድረስ ይቻላል የሚለው ነው።
ተመድ እና የኢትዮጵያ መንግስት እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ያልተቋረጠ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸው ትልቅ ነገር ነው።
የዚህም ስምምነት ተግባራዊነት ደግሞ ወሳኝ ነው። እርዳታ ሰጭ ድርጅቶችም ወደ አካባቢው ለመግባት ሁኔታዎች ሁሉ ሊመቻችላቸው ይገባል።"

#FDREDefenseForce
ብ/ጄነራል ተስፋዬ አያሌው በጦርነቱ አብዛኛው የሚዋጋው የህወሓት ኃይል መመታቱን ከፋና ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል።
ወንጀል የሰሩ ፣ ያስተባበሩ ፣ የመሩ ፣ ያሰቡ የህወሓት አመራሮች ተደብቀዋል ብለዋል።
በተጨማሪም የተደበቁ ከሀገር መከላከያ የወጡ ጄነራሎች ፣ ኮሎኔሎች እንዳሉ ገልፀዋል።
ብርጋዴል ጄነራል ተስፋዬ ፥ "አብዛኞቹ ኮሎኔሎች በውጊያው ሞተዋል፣ ተመተዋል፣ የተቀሩ / የተወሰኑ ሊኖሩ ይችላሉ ፤ ከጄኔራሎችም ከሩቅ ሆነው ነው ሲያዋጉ የነበሩም የተወሰኑ የተመቱ አሉ ፤ በቀጣይ የምንይዛቸው የተደበቁም አሉ" ብለዋል።
እየተካሄደ ያለው ዘመቻ የሚጠናቀቀው በህግ የሚፈለጉት የህወሓት ቡድን አባላት ሲያዙ ወይም ሲደመሰሱ ብቻ ነው ሲሉ ተናግረዋል።