TIKVAH-ETHIOPIA
ፊሊፒንስ ውስጥ 9 ዶክተሮች በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው መሞታቸው ተሰምቷል። የሰዎችን ህይወት ለማትረፍ ከፍተኛ ትግል እያደረጉ ያሉት የፊሊፒንስ የጤና ባለሞያዎች በቂ መከላከያ እያገኙ አይደለም ተብሏል። #StayHomeSaveLives @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ ከፊሊፒንስ በDW ፦
- የፊሊፒንስ ሕክምና ማህበር የ9ኙ ሐኪሞቹ ህልፈት የጤና ባለሞያዎች የቫይረሱን መከላከያ ቁሳቁስ እንደማይቀርብላቸው ማሳያ ነው ሲል ወቀሳውን አቅርቧል።
- በዋና ከተማዋ ማኒላ የሚገኙ ሶስት ትልልቅ ሆስፒታሎች በመሙላታቸው በቫይረሱ ታመው የሚመጡ ሰዎችን መቀበል አቁመዋል።
- በመቶዎች የሚቆጠሩ ሐኪሞች ለቫይረሱ ተጋላጭ በመሆናቸው እና በቫይረሱ ሊያዙ ይችላሉ በሚል ጥርጣሬ ለ14 ቀናት መለየታቸውንም ተነግሯል። ይህ ደግሞ ለደሃዋ ፊሊፒንስ በእንቅርት ላይ እንዳይሆንባት አስግቷል።
- በማኒላ ከሆስፒታሎች አቅም በላይ የሆኑትን ታማሚዎች ወደ ሌሎች ሆስፒታሎች ማድረስ ካልተቻለ የሃገሪቱ የሕክምና ስረዓት ውድቀት ሊያጋጥመው ይችላል ተብሏል።
#DW #REUTERS
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia