TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የቱርክ ፕሬዘዳንት የ7 ወር ደሞዛቸውን ለገሱ!

በቱርክ የኮሮና ቫይረስን [ኮቪድ-19] ለመግታት በሚደረገው ጥረት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች እገዛ ለማድረግ ሀገር አቀፍ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። በዚህም ፕሬዘዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን የ7 ወር ደሞዛቸውን ለግሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
10,827 ዜጎቿ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁባት ቱርክ በቫይረሱ ወረርሽኝ በእጅጉ እየተጎዳች ለምትገኘው ጣልያን የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጋለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እናመሰግናለን! Thank You!

በመላው ዓለም ላይ የምትገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት የሆናችሁ እንዲሁም የቤተሰቡ አባል ያልሆናችሁ የጤና ባለሞያዎች እሰራችሁት ላለው ገድል እናመሰግናለን።

በህክምና ቁሳቁስ እጥረት የራሳችሁን፣የቤተሰቦቻችሁን ጤና አደጋ ላይ ጥላችሁ የሰው ህይወት ለማትረፍ እየከፈላችሁት ያለው መስዋእትነት በልባችን ተመዝግቧል። ሁላችንም ከእናተው ጋር ነን!

#RiseUp
.
.
All we need all we need is #hope
And for that we have each other
And for that we have each other
And we will rise
We will rise
We'll rise
We'll rise

#AndraDay

ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
ሰላም እደሩ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንደምን አረፈዳችሁ?

"የኮሮና ቫይረስ በሽታ መከላከያ መንገዶችን በመተግበር እራሳችንንና ማህበረሰባችንን እንጠብቅ!" - ዶ/ር ሊያ ታደሰ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

በ 444 #FightCOVID19 የቲክቫህ ኢትዮጵያ ግሩፑ ውስጥ ከ9,000 በላይ የቤተሰባችን አባላት ተቀላቅላችሁ ለወገናችሁ ድጋፍ እያደረጋችሁ በመሆኑ ከልብ እናመሰግናለን። አሁንም እገዛችሁ አይቋረጥ 444 ከ1 ብር ጀምሮ አስተዋፅኦ አድርጉ፤ አብረን እንቁም!

ውድ ቤተሰቦቻችን መልዕክቶቻችሁን በዚህ ማስቀመጥ ትችላላችሁ፡ https://t.me/joinchat/FCD9AhWFZJX_rX95-4rWNQ

አንድ ላይ ሆነን እንሻገራል!
መልካም ቀን!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሀዋሳ ከተማ የኮሮና ቫይረስን [COVID-19] ለመከላከል በዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ የኬሚካል ርጭት በመከናወነ ላይ ይገኛል። የኬሚካል ርጭቱ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኃላ ይጠናቀቃል።

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

በሶማሌ ክልል መንግስት የተወሰዱ እርምጃዎች፦

1. የክልሉም የፌዴራል ጸጥታ አካላት ከምግብና አስፈላጊ ቁሳቁስ በስተቀር ምንም አይነት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በድንበር አከባቢዎች እንዳይገቡ ማድረግ

2. የትራንስፖርት አገልግሎትን በተመለከተ ከጭነት አቅማቸው 50 በመቶ ቀንሰው ዋጋ ሳይጨመር 12 ሶዎች የሚጫኑ ሚባሶች 6 ሶዎች በመጫንና ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ይችላሉ ተብሏል።

3. የምሽት መዝናኛዎች ፣ ጭፈራ ቤቶች እና ሰው በሚበዛበትና የመዝናኛ ስፍራዎች እንደ DSTV፣ጫት ቤቶችና የመሳሰሉት ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉ ውሳኔ መተላለፉን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል፡፡

4. የክልሉ ህዝብ ከጸጥታ አካላትና ጤና ባለሙያዎች ጎን እንዲቆሙና አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርጉላቸው ጥሪ ቀርበዋል።

5. ጦርታ የወጡ የህክምና ባለሙያዎችና በዘንድሮ በጤና ዘርፍ የሚመረቁ ተማሪዎች ሁሉ የክልሉ ጤና ቢሮ መጥቶ እንዲመዘገቡ ተወስኗል።

(የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዳማ ከተማ የኮሮና ቫይረስን [ኮቪድ-19] ለመከላከል በዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ ተዋህስ መድሃኒት ርጭት ስራ መከናወኑን የአዳማ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HumanRightsWatch

በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ወረርሽኝ ወቅት ይሁነኝ ብሎ ኢንተርኔት ማቋረጥ አሊያም መገደብ ገዳይ ሊሆን ይችላል ሲል ሒዩማን ራይትስ ዎች አስጠነቀቀ። ድርጊቱ በርካታ መብቶችን ይጥሳል ብሏል። እነ ኢትዮጵያ ሕይወት ለማዳን በአፋጣኝ አገልግሎቱን እንዲመልሱ ጠይቋል።

ሒዩማን ራይትስ ዎች እንዳለው ኢትዮጵያ ፣ ባንግላዴሽ ፣ ሕንድ እና ምያንማር የኢንተርኔት ግልጋሎት ያቋረጡ ናቸው። በኢትዮጵያ በወለጋና ጉጂ ዞኖች የተቋረጠው ኢንተርኔት እና ስልክ ሥራ እንዲጀምር የጤና ባለሙያዎችና ፓርቲዎች ጭምር እየጠየቁ እንዳለ ይታወቃል።

https://www.hrw.org/news/2020/03/31/end-internet-shutdowns-manage-covid-19

#EsheteBekele Pic : #BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዩኒቨርሲቲዎች ቀጣይ ሀገራዊ ግዴታ!

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም ትላንት ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዚዳንቶች ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ባደረጉት ውይይት ዩኒቨርስቲዎችን ለኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዎች ለይቶ ማቆያና በቫይረሱ ለተያዙት ማገገሚያ እንዲሆኑ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ገምግመዋል፡፡

ፕሮፌሰር ሂሩት በዩኒቨርስቲዎቹ ጥሩ ዝግጁነት መኖሩን ጠቁመው አሁን ያለውን የዶርሚተሪ አቀማመጥ መቀየር ፤ መፀዳጃ እና መታጠቢያ ቤቶችን በበቂ ሁኔታ ማዘጋጀት እንደሚገባና እንዲሁም የምግብ አቅርቦት በዩኒቨርስቲዎች እንደሚሸፈን ገልጸዋል፡፡

ዩኒቨርስቲዎች ካሉባቸው ወረዳዎች ፣ ዞኖች፣ ከተማዎች እና ክልሎች ጤና ቢሮዎች እንዲሁም ከጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ መስራታቸውን እንዲቀጥሉም አሳስበዋል፡፡

#MoSHE
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ውስጥ በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት ዳግም እንዲጀምር መደረጉን የክልሉ መንግስት ገለፀ።

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ በአካባቢዎቹ የቴሌኮም አገልግሎት ዳግም ወደ ስራ እንዲመለስ የክልሉ መንግስት እና የፌደራል መንግስት በጋራ ሲሰሩት የነበረው ስራ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

ይህንን ተከትሎም ከዛሬ ጀምሮ በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ውስጥ በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት ዳግም አገልፍሎት እንዲጀምር ተወስኗል ብለዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TIGRAY

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የጣሱ በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ!

በትግራይ ማእከላዊ ዞን የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ለመከላከል የተወሰነውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተላልፈው የተገኙ ግለሰቦች በእስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ ተደረገ ።

የትግራይ ማዕከላዊ ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ አቶ እያሱ ተስፋይ እንዳሉት አለአገባብ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉና ገደብ የተጣለባቸው እንቅስቃሴዎች የጣሱ ከ270 በላይ የንግድ ተቋማት እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

በአክሱም ከተማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ክልከላዎችን የተላለፉና ያለአገባብ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ ግለሰቦች በገንዘብ እና እስራት ተቀጥተዋል።

የትግራይ ማእከላዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትናንት ባስዋለው ችሎት በአዋጁ ክልከላ የተደረገባቸውና ያለ አግባብ የዋጋ ጭማሪ አድርገው የተገኙ ግለሰቦች በአንድ አመት እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ ወስኗል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች 25 ደረሱ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የታማሚዎች ሁኔታ፦

- በኮሮና ቫይረስ የተያዙት 2 ግለሰቦች የ30 ዓመትና የ36 ዓመት ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ በተመሳሳይ በረራ ከዱባይ በመጋቢት 15/2012 ዓ/ም ወደ ሀገር የገቡ ሲሆን በአስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ሲሆን የበሽታውን ምልክት ታይቶባቸው በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- 3ኛዋ ታማሚ የ60 ዓመት እድሜ ያላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ መጋቢት 6/2012 ዓ/ም ከፈረንሳይ የተመለሱና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ የበሽታውን ምልክት በማሳየታቸው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆነው በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- ሶስቱም የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።

#DrLiaTadesse #EPHI

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

በድሬዳዋ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ስርጭትን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ግብረኃይል ውሳኔ አስተላልፏል።

ከነገ መጋቢት 23/2012 ጀምሮ የተላለፉ ውሳኔዎች:-

1. ወደ ድሬዳዋ ከተማ የሚገቡም ሆነ የሚወጡ ከፍተኛ እና መለስተኛ ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፓርት አገልግሎት ከነገ መጋቢት 23/2012 ጀምሮ ዝግ ሆኗል።

2. ማንኛውም አይነት የድሬዳዋ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ከባጃጅ እስከ ሚኒባስ ድረስ ከነገ መጋቢት 23 ጀምሮ እስካልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት መስጠት አይችሉም።

3. በየትኛውም የድሬዳዋ አቅጣጫ የሚገኙ የድሬዳዋ መግቢያ በሮች ከነገ ጀምሮ ከእንቅስቃሴ ዝግ ተደርገዋል።

4. የእለት መሰረታዊ ፍጆታ እቃዎችን መሰረት ያደረጉ የገበያ ቦታዎችን ሳይጨምር እንደ ታይዋን ሌሎችም የግብይት ስፍራዎች ከነገ ጀምሮ ዝግ እንዲሆኑ ተወስኗል።

5. ከፍተኛ የሰው ኃይል ያላቸው ፋብሪካዎች እረፍት በመስጠት እና በሽፍት በማሰራት የሰው ኃይል ቁጥር እንዲቀንሱ ተወስኗል።

6. በጅቡቲ መስመር የሚገቡ የተለያዩ ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ነዳጅ እና እህልን ጨምሮ ሌሎች የሎጂስቲክ እንቅስቃሴዎችን ይህ ክልከላ አይመለከትም።

[የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፣ DMMA]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዛሬው እለት የዑለማ ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስ አስመልክቶ የተሰጠ ፈትዋ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ምክር ቤት የኡለማዎች ምክር ቤት የኮሮና ወረርሽኝ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተገለጸ በኋላ መጋቢት 12/2012 ባለ 4 ነጥብ ፈትዋ (ሃማኖታዊ ብይን) መስጠቱ ይታወሳል፡፡

በተሰጠው ብይን አብዛኛው ሙስሊም ህብረተሰብ እየተጠቀመበት እንደነበር የገለጸው ምክር ቤቱ ከበሽታው አስከፊነትና ምክር ቤቱ ካለበት ሀይማታዊና ሃገራዊ ሃላፊነት አኳያ ተጨማሪ ፈትዋ (ሃማኖታዊ ብይን) መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል፡፡

በመሆኑም ምክር ቤቱ በበሽታው የተያዙ ሰዎች እና እድሜያቸው የገፉ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም ሙስሊሞች እቤታቸው ሆነው መስገድ ግዴታ መሆኑን ሃማኖታዊ ብይን ሰጥቷል፡፡

በተጨማሪም ከዛሬ ጀምሮ በሽታው [ኮቪድ-19] በሰው ልጆች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት መቆሙ በጤና ባለሙያዎች እስከሚረጋገጥበት ጊዜ ድረስ በየመስጊዱ የሚደረጉ የጀመአ እና የጁመኣ ሰላቶች እንዲቆሙ መወሰኑን ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ቴሌቪዥን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

ከዛሬ ጀምሮ ወደ አፋር ክልል የሚገባ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ እንደማይኖር የክልሉ መንግሥት አስታውቋል።

ምንጭ፦ የክልሉ መንግሥት ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia